November 13, 2010

በሐዋሳ ቅ/ገብርኤል ውስጥ ብጥብጥ የፈጠሩት ተፈቱ


(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 12/2010፤ ኀዳር 3/2003 ዓ.ም) እሑድ ጥቅምት 28 ቀን 2003 ዓ.ም በሐዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በተፈጠረው ዐምባጓሮ በሕጋዊ የገዳሙ ሰንበት ት/ቤት አባላት ላይ ከፍተኛ የድብደባ ጉዳት በማድረሳቸው ተከሰው የተያዙት ያሬድ አደመ እና ዓለምነህ ሽጉጤን ጨምሮ 11 ያህል ሰዎች ዛሬ ተፈቱ።

በተጎጂ ቤተሰቦች በተመሠረተው ክስ ፖሊስ ሀገረ ስብከቱን በማወክ እና የክልሉን ሰላም በማደፍረስ ሁከት በፈጠሩት ግለሰቦች ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማሰባሰብ እና ቀሪ ሁከተኞችን ለማደን የጠየቀው ዘጠኝ ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ጥያቄ የፍርድ ቤቱን ይሁንታ አግኝቶ ነበር፡፡ ከሁከቱ በኋላ እሑድ ዕለት ረፋድ ላይ ወደ አዲስ አበባ ለመሔድ ሲዘጋጅ የተያዘውን ያሬድ አደመን፤ አባቶችን፣ የሐዋሳ የፍትሕ እና ልማት ኮሚቴ አባላትን እና ማኅበረ ቅዱሳንን በስም እየለየ የሚያክፋፋ የቅስቀሳ ወረቀት ሲበትን በማግስቱ ሰኞ የተያዘውን ዓለምነህ ሽጉጤን ጨምሮ በእስር ላኢ የነበሩት እነዚህ ሰዎች በምን ሁኔታ እንደተፈታ የታወቀ ነገር ባይኖርም ምናልባት ነገ ወደ ሐዋሳ ጉዞ ከሚአደርጉት ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር የተገናኘ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል። ቅዱስነታቸው “ባይሆን ዋስ እሆናለሁ” ማለታቸው ይታወሳል።

ነገሩን ግር የሚያደርገው የሰዎቹ መፈታት ሳይሆን የተፈቱበት አግባብ ነው ያሉ ምንጮች እንደጠቆሙት ፖሊስ ቀነ ቀጠሮ ጠይቆ ፍርድ ቤትም በፈደበት በዚህ ጊዜ በአቋራጭ መፈታታቸው የሕግ አካሄዱን ጥያቄ ምልክት ላይ ጥሎታል። የሕግ የበላይነቱ ወዴት ደረሰ? የፍርድ ቤቱስ ቀነ ቀጠሮ? ሰዎቹ ዛሬ እንደተፈቱ ወደ ቅ/ገብርኤል ገዳም ስብከተ ወንጌል አዳራሽ በመሔድ “ምሕላ ካላደረግን” በሚል መጠነኛ ግርግር መፍጠራቸውም ተሰምቷል።

11 comments:

Orthodoxawi said...

Egzio Meharene Kirstos Egzio!
Meharene Kirstos Egzio!
Meharene Kirstos Egzio!
Meharene Kirstos!

Egzio Meharene Kirstos Be Ente Mariam!
Meharene Kirstos Be Ente Mariam!
Meharene Kirstos Be Ente Mariam!
Mahrene Kistos!!!

wesetu yetekatel sew said...

<> ይሄ ነዉ አይደል የኢህአዲግ ፍላጎት እንደ ድመት ፍቅር እንድንበላላ

truth said...

I don't have much knowledge how Ethiopia's courts system work.Based on my little knowledge how US justice system work and what I read from DS so far,I can guess that the defendant accused of initiating or participating in violence. I don't think these charges prevent them from release in bills. Let's not make minor issue political.

ብዕሩ ዘአትላንታ said...

ከብዕሩ ዘአትላንታ
ማህበረ ቅዱሳንን የሚጠሉ እነ ማን ናቸዉ?
ግልጽ ደብዳቤ ሀይማኖትና ተዋህዶ ለገባቸዉ ለአንድቷ ቤተ ክርስቲያን ልጆች። ለመሆኑ የእነ ያሬድ አደመ፣የዲ.ን በጋሻዉ ፣ የሌሎችም መሰል የድቡሽት ላይ ሊቆች...ባገኙበት መድረክ ሁሉ ማግሳታቸዉ ዓላማቸዉ ምን እንደሆነ መገንዘብ አያዳግትም። የሚደንቀዉ ግን የማህበሩ ልጆች ዝምታ ነዉ። በጨዋ ቤት ፍቅርና ሙያ በልብ ነዉና ከዓላማችሁ ሊገታ የሚቅበዘበዘዉን አዉሬ በመለየታችሁ ኮራሁባችሁ። በርቱ የጥቂት የአባ ጳዉሎስ ቅልቦች ድስኩር የትም አይደርስም። በጋሻዉን እንደ ዝና ሚደሰኩረዉን የዉጭ ጉዞ አባ ጳዉሎስ ተማጽኖ እንዲሳካለት ምኞቴ ብርቱ ነዉ። በአካል እንዳገኘዉ ፈልጌ ነዉ። ተርቦቹን! ለተዋህዶ ሃይማኖታቸዉየሚማስኑትን የቁርጥ ቀን ልጆች እንዳሳየዉ ። ብዕሩ ዘአትላንታ

የድር-ትዝብት said...

ይድረስ ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኣማኝ ወገኖቼ፥ ድቅድቅ ባለው ጨለማ በዋጠው መንገዳችን ውስጥ ግን ደግሞ በሩቅ የሚታየኝ ብርሃን ኣለ። ተስፋን የሰነቀ ብርሃን። ምን ይዞ ሊመጣ እንደሚችል የመተንበይ ፀጋ ባይኖረኝም ያ ብርሃን ግን ትንሳኤን ኣርግዟል። በዚህ ወቅት በመዋዕለ ስጋ ለምንቀሳቀሰው ኣማኞቿ የተዋህዶ እምነት በሞትና በህይወት መካከል ቆማ፣ ሞቷን የሚሹ ሲስቁ ትንሳኤዋን ለምንናፍቅ ደግሞ በመቃብር ውስጥ(በቅዳሜ ስዑር) ውስጥ የምትገኝና የትንሳኤዋን ሰንበት እየጠበቅን አንደምንገኝ ነው ለእኔ የሚገባኝ። ቅድስት ሃገር ኢትዮጵያ፤ እግዚኣብሄር ትእዛዙን ጠብቀን በቃሉ ብንመራ የዘላለም ህይወትን የምናገኝበትንና ዓለም ሊድንበት የሚችለውን ፅላተ ህጉን በምድሪቷ ኣኑሯል። በዚህም ምክንያት እኛ አንደ ኣህዛብ ልንኖር ኣልተፈቀደልንም። የያዝነውን ህግ ልንመራበት ህጉ ግድ ይለናል። የቤተ ክርስቲያናችን ቀኖናዋ እና ዶግማዋ ቤተ ክርስቲያኗን ብቻ ሳይሆን ምድሪቱንም ማስተዳደር ይችላል።መሆንም ያለበት ይሄው ነው። ሃይማኖታችን እምነታችን ብቻ ኣይደለም ሃገራችንም እስትንፋሳችንም ደማችንም ነው እንጅ። ህዝባችን ሃይማኖቱን መኖር ኣለበት። ርሃብ፣ቸነፈር፣ችጋር እና በሽታ አንዲጠፋ በሃይማኖት መኖር ኣለብን። በልመናና በድህነት ልንኮራ ኣንችልም። ቤተ-ክርስቲያናችን ሃብታም ነች። በየትኛውም ኣለም ያሉ ቤተ-ኣህዛቦቹም ሆኑ ቤተ-ኣምልኮዎች ገንዘብ የሚሰበስቡት ከኣባላቶቻቸው እንጂ ከመንግስት ኣይደለም። የምዕራቡ ዓለም ቤተ-ኣምልኮዎች ዛሬ ዛሬ ለናይት ክለብ እና ለግሮሰሪነት አየተሸጡ ያሉት በፓስተሮቻቸው ስግብግብነት አና በራሳቸው ፍላጎት አየተረጎሙ የሚያስተምሩትን መጽሓፍ ቅዱስ አንኩኣን መኖር ባለመቻላቸው የሚነዱትን መኪና የሚያስገነቡት ህንጻ ከቢሊየነሮቹ ነጋዴዎቹ ተርታ ተሰልፈው ቁጭ ብለዋል።ይህን ስራቸውን ሚድያው እያወገዘው ይገኛል። በየመድረኩም ላይ የሚያሳዩትን የፈጠራና የሃሰት ፈውስ ዛሬ ዛሬ አውቅ በሆኑ ሚድያዎች መሳለቂያ መሆን ከጀመረ ሰነባብተዋል። ይህንን ታዲያ የኛም ሰባክያን ማለት የራሳችን ጉዶች ሳይቀሩ ኮርጀዋታል። ቤተ-ክርስቲያንን በየ ጉራንጉሩ ውስጥ ከመክፈት ኣንስቶ በየ ኣዳራሹ ህዝብን አየሰበሰቡ አናስተምርህ ማለት፤ ከዛም ገንዘብ ለእዚህ ገዳም ማሰሪያ ነው እባካችሁ ጣልጣል ኣድርጋችሁ ሂዱ ይህና ይህን በመሳሰለው ወንጀል አራሳችንን ተብትብን ኣስረን በሌላ ላይ ጣት መቀሰር እኛን ነፃ ሊያወጣን ኣይችልም። ኣንዳንዴ ከመሪ ተመሪ ተሽሎ ይገኛል ኣባቶች ብለን ላይ ተቀምጠው ስለ ቅድስናቸው ይምንዘምርላቸው ሰዎቻችን ሁሉን ማለቴ ኣይደለም ኣንዳንዶቹ ምንነታቸውን አና ማንነታቸውን ኣፋችንን ሞልተን ለመናገር በአጅጉ አንቸገራለን። በኢትዮጵያ የሃገረ ስብከት ጳጳስ የሆነ ኣባት ኣሜሪካ ሲመጣ ሃገረ ስብከቱን ዞር ብሎ ሳያይ የሚሄድበት ምክንያት ሌላ ምክንያት ከሌለ በስተቀር፤ ከምድር በታች ያለ ምንም ምክንያት ሊሰጠው ኣይችልም።ለነገሩ የለበሱት ልብሰ ተክህኖ ኢትዮጵያዊ ፓስፖርታቸው ደግሞ ሌላ ነው። እሷነቷን ንቀው ዜግነታቸውን ለሽጡባት ሃገር ህዝብ ጳጳስ መሆን ለኔ በጣም ቢያሳዝነኝም ለነሱ ግን ኣንድ ዓላማ ኣላቸውና በሁለት ኣለም የሚኖሩ ተንሳፋፊዎች ናቸው። ይቀጥላል.....

awudemihiret said...

ለዛች ሃገርም ሆነ ቤተክርስትያን እግዚአብሄር ብቻ ይሁናቸው እንጂ ሁለቱም መሪዎች ሳይሆኑ አጥፊዋች ናቸው።

Sam for Nairobi said...

Do not expect any thing from the Government agents but God. Our God always gives lesson in this way to make his people return to him. By any means all are his creatures. In the church history, the enemies of the church were always lived shorter and the way how they lost was tragical. Awwasians, pray for them. your blood will bring peace soon. Let The God of John the chrysostomos always be with you.

Anonymous said...

አንድ ሀሳብ አለኝ
ለመንደርደሪያ ያህል ግን ከመናፋቃን በኩል በደረጃ እየመጡ ያሉትን መፈታተኖች ላስታውስ ድሮ ድሮ በየቤታቸው መኖራቸውን ለማሳወቅ በር ዘግቶ በመጮህ በማልቀስ ጎረቤት መረበሽ ነበር ከዛ መንደር ውስጥ ድንኳን ተክሎ መንደር ማወክ...ከዛ የሆኑ ሰባት ጥቅሶቻቸውን ይዘው አስፋልት ላይ ሰውን አላስኬድ ማለት ወጣቱ በልጦ ሲገኝና ጥቅስን በጥቅስ ሲያፋጥጣቸው በነቦንኬ እና ዘመቻ ፊሊጶስ አይነት ሽብር ይዘው መጡ ከዛም የእኛኑ ሰባኪዎች በተሃድሶነት አስነሱብን ሚስኪን ህዝባችንን እርስ በእርሱ አባሉት ምዕራባውያንን ይዞ ወደገሀነም እየገባ ያለ የክህደት አስተሳሰብ፣ የምዕራቡን አለም ከመንፈሳዊነት ያራቆተ ጥቅም ላይ ተኮር ፍልስፍናዊ የመጽሀፍ ቅዱስ መሳይ ትምህርት ሊነዙ ተጉ ቤተክርስቲያኗን ለመቀየር የራሳችንን ሰዎች አስነስተው ሰላማችንን አሳጡን አውደምህረቱን የትንቅንቅ አደረጉት እምነት፣ ስርአት፣ ትምህርት፣ ውብ ዝማሬ፣ ሊቃውንት፣ ዘማሪያን፣ ትሁት አማኝ ህዝብ....እያለን ምንም እንደሌለን ያለ ጥቅም ኩርምት ብለን ነገ ምን ይዛልን ትመጣለች እያልን አስፈሪዋን ቀን እንጠብቃለን። ዛሬ አንድ ነገር ካላደረግን ኩርምት ብለን ነገን ብንጠብቃት የትጉዎቹ የክፉዎቹ የስራቸውን ውጤት ይዛልን ትመጣለች እንጂ ለእኛ የሚሆን ምንም አናገኝም። የእግዚአብሔር ቀን እስክትመጣ።
እኔ እንደሚሰማኝ በተለይ እዚህ በውጪው አለም ያለን ኦርቶዶክሳውያን እየቆጨን ያለን ሰዎች ላስቸኳይ ጊዜ አይነት ድምፃችንን ለማሰማት መደራጀት ያለብን
ይመስለኛል በዚህ የአዋሳ ህዝብ አርአያ ሊሆነን ይችላል የሚቆረቆሩ አባቶች ዲያቆናት መምህራን ዘማርያን ምእመናን ሞልተውናል እና ያለንን ሁሉ አስተባብረን በርከት ብሎ አዲስ አበባ እስከመሄድ ድረስ በተደራጀ መልክ ድምፃችንን ማሰማት አለብን ከግለሰብ ተነስቶ በቡድን ሲል አልፎ አናታችን ላይ የወጣው ድፍረት እኛ ዝም በማለታችን ነው መንገድ ላይ ተራ ጥቅስ በመጥቀስ የተጀመረ ማዋከብ አልፎ ሲኖዶስ ገብቶ አባቶቻችን በሀይማኖታችንንና በስርአታችን መሰረት ቤተክርስቲያናችንን እንዳይመሩ ማወክ ደረጃ የደረሰው በእኛ ህብረት ማጣት ነው ወደዳችሁም ጠላችሁማ ጥረታቸው በእጃችን ላይ የያዝነውን ጥሬ ለመበተን ነው። እናም መልእክቴ እንደራጅና የሲኖዶሱ አቅም የሚመለስበትን ሁኔታ እንፍጠር፣ ለአባቶቻችንን የሚታይ የሚጨበጥ ፍርሀታቸውን የሚያስለቅቅ መከታ እንሁናቸው፣ ሲኖዶሱ የወሰናቸው ውሳኔዎች ተግባራዊ እንዲሆኑ በማንኛው መንገድ እንጠይቅ። የተዋህዶ ልጅ ነኝ ከአሜሪካ

wordofa said...

gizew dersewal

Anonymous said...

ደጄ ሰላሞች

እናንተ እዉነቱን የሚነግራችሁን ለምን ትሳደባላችሁ የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አለዉ
የመወያያ ብሎግ እስከሆነ ድረስ ለምን መስማት የምትፈልጉትን ከንቱ ዉዳሴ ብቻ በብሎጋችሁ
ታወጣላችሁ አናንተና መሰሎቻችሁ የምትፅፉትን ሁሉ እናነባለን እዉነተኛ ለቤተክርስቲያን
የምታስቡ ከሆነ እዉነቱን አዉጥቶ የሚፅፈዉን ፅሁፍ ሌላዉ አንብቦ እንዳያገናዝብ ነዉ
የምንልከዉን ፅሁፍ የማታወጡት ይገርማል

እውነቱ እዉነት ሀሰቱ ሀሰት መሆኑኮ አይቀርም እግዚአብሔር ልቦናችሁን ያብራላችሁ
የማይገለጥ የተሰወረ - የለምና የተደበቀዉ እዉነት በክርስቶስ ብርሃን ይገለፃል--

Unknown said...

bedejeselam fikir selam ewnet neber dro
ahun gin neger wushet bicha hone benante dejeselam
egziabher kelay hono min yil yihon?

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)