November 5, 2010

በጋሻው ደሳለኝ ፍርድ ቤት ቀረበ


  • ‹‹አዎ፣ ተሳድቤያለሁ፤ ወደፊትም እቀጥላለሁ›› (በጋሻው ደሳለኝ
  • 500 ብር ዋስትና አስይዟል፤ ለብይን ለኅዳር 23 ቀን እንዲቀርብ ታዟል
  • ‹‹ኀይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶችህ ዋሹብህ›› (ጥቂት ቲፎዞዎቹ የለበሱት ቲ-ሸርት)
 (ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 5/2010፤ ጥቅምት 26/2003 ዓ.ም)በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የድሬዳዋ ማእከል የስም ማጥፋት ወንጀል ክስ የቀረበበት በጋሻው ደሳለኝ ዛሬ በድሬዳዋ ካውንስል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡ ዛሬ ጠዋት በተሠየመው ችሎት በተከሰሰበት የስም ማጥፋት ወንጀል ጉዳይ የእምነት ክሕደት ቃሉን የተጠየቀው በጋሻው የተከሰሰበትን የንግግር ቃል መናገሩን አምኗል፡፡ በድምፅ የተቀረጸውን የንግግሩን ቅጂ ለፍርድ ቤቱ ያቀረበው በጋሻው፣ “ማኅበሩን እንደ ድርጅት ሳይሆን በማኅበረ ቅዱሳን ሽፋን የሚነግዱትን ነው የተሳደብኩት፤ በዚህ ደግሞ ወደፊትም አቀጥላለሁ፤ አላቆምም” በማለት ለችሎቱ ማስረዳቱ ተዘግቧል፡፡

በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ በተ ክህነት የዋና ሥራ አስኪያጁ ጽ/ቤት፣ በስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ከአገልግሎት የታገደው በጋሻው ደሳለኝ መንገሻ እግዱን በመተላለፍ ሚያዝያ 19 ቀን 2002 ዓ.ም በድሬዳዋ ሳባ ደብረ ኀይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ‹‹ንጉሥ በዙፋኑ አለ›› በሚል ርእስ ባሰማው ንግግር ብዙዎች በሚዲያ ‹ቢዘምቱበትም› እርሱን በዐውደ ምሕረት ከመቆም የከለከለው እንደሌለ ርእሱን ለራሱ ተርጉሞ ስለ ራሱ ከመናገር ያላፈረው ተከሳሹ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ በጸደቀለት መተዳደሪያ ደንብ በቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ውስጥ ተደራጅቶ መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ እና ልማታዊ አገልግሎት እንዲሰጥ የተፈቀደለትን ማኅበረ ቅዱሳንን፣ “የወንድሞችን ደም ያፈሰሰ፣ አባቶችን በጋዜጣው ያዋረደ፣ ዘራፊ እና ሌባ” እንደ ሆነ ባልተገራ አንደበቱ መወንጀሉ ይታወሳል፡፡

ዐቃቤ ሕግ ክሱን የሚያስረዱለትን ሦስት የሰው ምስክሮች እና የቪሲዲ ማስረጃዎች ያቀረበ ሲሆን ከሦስቱ ሰዎች ሁለቱ በሰጡት የምስክርነት ቃል ተከሳሹ በተጠቀሰው ወቅት የተባለውን ውንጀላ ሲናገር መስማታቸውን አስረድተዋል፤ የቀረበው የቪሲዲ ማስረጃም ይህንኑ የሚያረጋግጥ መሆኑ ተገልጧል፡፡ ተከሳሹ የፈጸመውን የስም ማጥፋት ወንጀል በማመኑ፣ ይህም በዐቃቤ ሕግ በቀረበበት የሰው እና የሰነድ ማስረጃ በመረጋገጡ ብይን ለመስጠት ለኅዳር 23 ቀን 2003 ዓ.ም የቀጠረ ሲሆን በፖሊስ ተይዞ እንዲቀርብ የታዘዘው በጋሻውም የ500 ብር ዋስትና እንዲያሲዝ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡ “ወደ ውጭ አገር ስለምሄድ የብይኑ ቀጠሮ ቀን ይጠርልኝ” ብሏል በጋሻው ስለ ቀጣዩ ጊዜ ቀጠሮ ለችሎቱ አቅርቦት በነበረው ጥያቄ፡፡

እስከ ቀትር 6፡30 ድረስ በቆየው የፍርድ ቤቱ ውሎ ዐሥር ያህል የተከሳሹ ቲፎዞዎች፣ “ኀይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶችህ ዋሹብህ” የሚል ጥቅስ የሰፈረበት ቲ-ሸርት ለብሰው በዙሪያው ታይተዋል፡፡ ከቲፎዞዎቹ አንዳንዶቹ ማኅበረ ቅዱሳን በወንጌል እንደተጻፈው፣ “ከመክሰስ ለምን አይመክረውም ነበር” የሚል አስተያየት ሲሰጡ ተደምጧል፡፡ እነርሱ ይህን ይበሉ እንጂ ስም አጥፊው በጋሻው “በመሳደቤ እቀጥላለሁ” ከማለቱም በላይ ዐቃቤ ሕግ ካቀረባቸው ሦስት ምስክሮች ሁለቱ የሰጡት ብቻ እንደሚበቃ በተናገረበት ወቅት፣ “ውሸቱን እንዳይደግምለት ነው” በማለት በችሎቱ ፊት በድፍረት መናገሩ ልበ ደንዳናነቱንና ላለመታረም ያለውን ዝንባሌ የሚያሳይ ተደርጎ ተወስዷል፡፡ በሌላ በኩል ለበጋሻው ጥብቅና የቆሙለት የልምድ ነገረ ፈጅ ከዚህ ቀደም በአካባቢው የነበረውን የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ ለማጋለጥ በተጋደሉት ኦርቶዶክሳውያን አባቶች እና ወንድሞች ላይ የክስ ቻርጅ በማርቀቅ እና ‹በማማከር› የታወቁ መሆናቸው ሲታይ ተከሳሹ የቆመበትን ሰበካ ግልጽ ያደርገዋል ይላሉ ታዛቢዎች፡፡ በቅርቡ በእምነት ኑፋቄያቸው እና በሥነ ምግባር ብልሽታቸው የተነሣ ከድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅነት የተባረሩት ግለሰብም ሌላው የበጋሻው አጃቢ ነበሩ፡፡

በተያያዘ ዜና ‹‹መርከብ›› በሚል ስያሜ ባቋቋመው ‹ጋዜጣ› በማኅበረ ቅዱሳን የድሬዳዋ ማእከል ሰብሳቢ የሆኑትን የዲያቆን ድንበሩ ሰጠን ስም አላግባብ የሚያጠፋ ውንጀላ ያተመው ቀንደኛው የተሐድሶ ኑፋቄ አቀንቃኝ መሪጌታ ጽጌ ስጦታው ባለፈው ዓመት ቀርቦበት በነበረው አሳማኝ ማስረጃ የዘገባውን እውነተኛነት ሊያስረዳ/ክሱን ሊከላከል/ ባለመቻሉ፣ የሰባት ወር እስራት እና 2000 ብር ከተቀጣ በኋላ በቅጣቱ ተመጣጣኝነት ላይ ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው ይግባኝ ተከሳሹ በተጨማሪ ዐሥራ አንድ ወራት እስራት እና በተጨማሪ 16,000 ብር(በድምሩ ብር 18,000) የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍል እንደተወሰነበት ለመረዳት ተችሏል፡፡

76 comments:

Anonymous said...

wat the hell is going on? i think THE DAY IS COMING! Every one wt r u looking at?!! PRAY;PRAY;PRAY;PRAY......

የዲላወርቅ said...

አይ በጋሻው ምድራዊ ዳኛ ለምን የቤተክርስትያን አምላክ ይፋረድህ ይዘገያል እንጇ ሌብነትክ ገሐድ ይወጣል

Anonymous said...

+++
አይ በጋሻው ያልታደልክ ከስራህ ማለት ከተዋህዶ ልጅነትህ ዲቃላ መሆንህ ያየለብህ መጨረሻህን መድሃኔአለም ያሳምረው

Anonymous said...

oh poor begashaw... weta wetana ende shenbeqo tenkebalele ende mukecha....

Anonymous said...

"ሐይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶችህ ዋሹብህ።" ምን ማለት ነዉ? ይሄ ጥቅስ ለክብር አምላክ ለመድሐኒአለም የተነገረ አይደለምን? እናስ ሰዎች በራባቸዉ እንዴት የጌታን በምድራዊ ህግ እንኳን ፊት ቀርቦ የአንደበት ንጽህና ለጎደለዉ፣ አንደበቱ ላልተገራ ለአንድ ዘላፊ ሰባኬ ድፍረት የሚጠቀስ? ሰዉ እኮ በዝና ማማ ላይ ከወጣ ድካሙን መርሳት ይጀምራል። እባካችሁ ጸልዩለት፤ መንፈሰ ድፈረቱ ቢለቀዉ !!! ደጋፊዎችስ ለምን ነዉ፣ በድፍን የምትደግፉ? ሰዉስ ለምን የመመለክ ዝንባሌ ሲያሳይ ተዉ አይባልም? ተመልከቱ ለጌታ የተነገሩ "ትናንሽ ጥቅሶች"ን ለራሳቸዉ መጠቀም ተለማምደዉ ራሳቸዉን ወደ "ክርስቶስነት" ሹመት ካወጡ ሰዎች መካከል አስቀያሚዉን... የበጋሻዉስ መንገድ ወደዚህ አይመራዉምን? ወንድሜ ልብ ይስጥህ... http://abcnews.go.com/Nightline/video/son-god-10894617

WEGEN said...

ZENDOW AFUN EYEKEETE NEW.YE IGZIABHER MELEAK BEKIRBU ANGETUN YIKORTEWAL.PLZZ DONT CALL THIS STUPID ORTODOXAWI,BECAUSE HE NEVER BEEN.
TEBEITNA KURAT YEMOLUT ANAT
SEYFNNA GORADE YEMETUT ANGET
AYIGELAGRLUM ENDIH BEKELALU
KEMERET LAY WEDKEW SAYNKEBALELU

hilena said...

egziabher ahunim lebochin kebetekiristian, aremochin ke azmerachin indinekil intseliy. isu yewededewn yadirg.

Anonymous said...

Aye deje selamche degmo foto ezhe letefcheuolete er teuo atasarerune semu enqane sensa /senebebe yandedale degmo foto teu ged yelacheuome melkame yeseruten enqane foto alsayacheuome mechem ke abatu ke aba pauolse ayense belcheu neu leneye gen altemchgeme yesuna yeweyzerowa foto bezhe bayeuota melkame neu yekidusane amelake yetebkacheu

EHETE MICHEAL said...

ቤተክርሰቲያን መብት እንዳላት ማሳየት ትክክለኛ ነገር ነው፧ ሰዎች ዝም ብለው እየተሳደቡና እየተዛለፉ የሚኖሩበት ህግ የለም፧ የድሬደዋ ማእከል ማህበረ ቅዱሳን ያደረጃችሁት ነገር ትክክለኛ ነው፧ በስጋ መተማመን ፣እራስን ከፍ ከፍ በማድረግ በማን አለብኝነት ቤተክርስቲያንን የሚያውኩ ሰዎችን ለማስታገስ የሚገባውን ነገር ማድጋችሁ ይበል ያሰኛል፧ በዚህ አጋጣሚ በስመ ትህትና መብትን የሚጋፉ ሰዎች ትክክለኛ ፍርድ ከእግዚአብሔር ፣የስገወን ደግሞ ከስጋዊ ዳኛ ምግኘት አለባቸው፧ እንዲህ ልባቸውን ያደነደነውን ነገር ፈጣሪ ይወቀው፧ ሁላችን ስለዚህ የትዕቢት መንፈስ በፀሎታችን እናስባቸው፧ እህተ ሚካኤል

DEREJE THE AWASSA said...

ደጀሰላሞች እግዚአብሔር ይስጥልን
በእውነት በጋሻው የወንጌል ሰው ቢሆን <> የሚለውን ባሰበ ነበር።
ለነገሩ ቅዱሳንን በየመድረኩ ሲሳደብ በየካሴቱ ሲዘልፍ የኖረ መናፍቅ አንድን ማህበር እሳደባለሁ ቢል ምኑ ይገርማል?
ማኅበረ ቅዱሳንን የሚሳደብ የቤተክርስቲያን ጠላት ብቻ ነዉ።
እግዚአብሔር ቤቱን ከተሃድሶአውያን ያፅዳ።

ledet said...

Ato Begashaw esti sebeket legabezeh
'

Yekedemewune Fikerhene Tetehalina....
yemilewune yebefitu Deacon Begashaw yesebekewune
ledettewahido@yahoo.com

Anonymous said...

I am not a fan of Begashaw; I even don't know him in person. Don't know whetehr he is a good or bad guy. However, I know that Mahibere Kidusan has made terrible mistakes a number of times. I don't think his accusation is unwarranted. Even if I appreciate some of the good works MK may have done overall, I am always disappointed when I see them attacking and bleeding people whom they consider as threats to their domination of the church. Whomever they hate, they accuse as Pente or Tehadso. We have lost a number souls to satan or menafikan because of their bull-headed and evil-spirited appraoch to solving differences. I remember, at one point, they accused Bishop MelkeTsedek as pente just to please Patriach Paulos. That is not only childish, but alos satanic. How is MK different from the Meles regime in terms of their approach to dealing with their opponents? Please grow up MK... Continue to do your good work, but clean youself from evils. Also, need to solve problems with other brethren though dialogue and our tradtional shimgilina instead of going to worldy court...

Anonymous said...

D/N Begashaw,
Why all this, you have been a son of this church, you were nothing few years ago now you got fame all over Ethiopia plus you have enough wealth to do any thing you wish to just because of this Tewahido Church. None of your "Menafikan" group raise you to where you are to this day. We have seen you raise from the ash to where you are, however you are the one throwing all kind of speires towards this mother chruch why???? Do you think you can get away with this? you have done so many distruction and people just not responding to your act, because you were possesed by our greatest enemy Sathan, but now enough is enough no more distruction we know now who you are very well, what direction you are trying to take our mother church. That is not going to happen you like it or you hate it that won't happen as long us we are alive we are also son's of Tewahido church, we will not allow you to take us to the main hall of "Menafikan" you can leave us once again or our protector whom you do not believe will give you what you deserve soon.
1) You can go ahead and sell your agly face to your Menafikan not to our people.
2) Go ahead and teach your belive to your friends and followers (Menafikan)
3) Step aside from our church adminstration once and for all.
4) All the statue you errect with your girl friend w/r (...) you can put in errect it once again in to your place and worship it if you like it.
5) You can not talk about MK on your mounth, they have done a list of things for
Thank you for your understanding and sign out.
Son's of Tewahido.
God bless our church.

Anonymous said...

ማኔ ቴቄል ፋሬስ

Anonymous said...

D/N Begashaw,
Why all this, you have been a son of this church, you were nothing few years ago now you got fame all over Ethiopia plus you have enough wealth to do any thing you wish to just because of this Tewahido Church. None of your "Menafikan" group raise you to where you are to this day. We have seen you raise from the ash to where you are, however you are the one throwing all kind of speires towards this mother chruch why???? Do you think you can get away with this? you have done so many distruction and people just not responding to your act, because you were possesed by our greatest enemy Sathan, but now enough is enough no more distruction we know now who you are very well, what direction you are trying to take our mother church. That is not going to happen you like it or you hate it that won't happen as long us we are alive we are also son's of Tewahido church, we will not allow you to take us to the main hall of "Menafikan" you can leave us once again or our protector whom you do not believe will give you what you deserve soon.
1) You can go ahead and sell your agly face to your Menafikan not to our people.
2) Go ahead and teach your belive to your friends and followers (Menafikan)
3) Step aside from our church adminstration once and for all.
4) All the statue you errect with your girl friend w/r (...) you can put in errect it once again in to your place and worship it if you like it.
5) You can not talk about MK on your mounth, they have done a list of things for
Thank you for your understanding and sign out.
Son's of Tewahido.
God bless our church.

Anonymous said...

D/N Begashaw,
Why all this, you have been a son of this church, you were nothing few years ago now you got fame all over Ethiopia plus you have enough wealth to do any thing you wish to just because of this Tewahido Church. None of your "Menafikan" group raise you to where you are to this day. We have seen you raise from the ash to where you are, however you are the one throwing all kind of speires towards this mother chruch why???? Do you think you can get away with this? you have done so many distruction and people just not responding to your act, because you were possesed by our greatest enemy Sathan, but now enough is enough no more distruction we know now who you are very well, what direction you are trying to take our mother church. That is not going to happen you like it or you hate it that won't happen as long us we are alive we are also son's of Tewahido church, we will not allow you to take us to the main hall of "Menafikan" you can leave us once again or our protector whom you do not believe will give you what you deserve soon.
1) You can go ahead and sell your agly face to your Menafikan not to our people.
2) Go ahead and teach your belive to your friends and followers (Menafikan)
3) Step aside from our church adminstration once and for all.
4) All the statue you errect with your girl friend w/r (...) you can put in errect it once again in to your place and worship it if you like it.
5) You can not talk about MK on your mounth, they have done a list of things for
Thank you for your understanding and sign out.
Son's of Tewahido.
God bless our church.

unity said...

የጥቅሱን አጠቃቀም ለግዚው እንተዉና .....‹‹አዎ፣ ተሳድቤያለሁ፤ ወደፊትም እቀጥላለሁ›› የሚለው

1. ከአንድ ክርስትያን ነጝ ባይ ሰው (ሰባኪ) ይጠበቃል ወይ?
2. በሃግሪቱ ውስጥ ህግ የለም ወይ?

ይህ የኢትይጵያን ህዝብ እና መንግስት መናቅ ነው።

Anonymous said...

This is a true preacher, who speakes the truth. Mahbere Kidusan are attakers. If they believe in God they do not go to court. What they hell they are.

Anonymous said...

ይሄንን ጨዋ መክሰስ በራሱ ትንሽ መሆን ነው። ንቀው ቢተውት ይሻል ነበር። ንቆ መተውን የመሰለ ነገር የለም።

Anonymous said...

ማህበረ ቅዱሳን! አይ ስም! ሲይጣን የብርሃን መልአክ መስሎ ይመጣል የተባለው ለዚህ ነው። ይህ ሰወ በላ ማህበር መልካም ስም የያዘ ግብሩ ግን የሰይጣን የሆነ ማህበር ነው። የሚገርመው በውስጡ አንድም አስተዋይ አባል ያለም አይመስልም። በመተታቸው ሁሉንም አውረውታል መሰል። ይህ የበግ ለምድ ለብሶ በቤተ ክርስቲያን ያለ ትኩላ (ጅብ ይሻላል መሰል) ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰላቸውን ክቡር የቤተ ክርስቲያን ልጆች በስጋዊ የጥላቻ መንፈስ ከአገልግሎታቸው ለማደናቀፍ የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። በጋሻው ያለው በሙሉ ትክክል ነው። አዎ ማህበረ ቅዱሳን ሰወ በላ ነው። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንደ ማህበረ ቅዱሳን ያለ ስም አጥፊ ሰውን ከቤተ ክርስቲያን ለመለየት ወደሁዋላ የማይል ድርጅት አይቼ አላውቅም። አዎ ማህበረ ቅዱሳን ሌባ ነው። በቤተ ክርስቲያን ስር ነኝ እያለ ለቤተ ክርስቲያን አባቶች የማይታዘዝና ሰዎች ለቤተ ክርስቲያን አስራት መክፈል ሲገባቸው የሰዎችን አስራት እየሰበሰበ ወደራሱ ኪስ የሚያስገባ ነው። አዎ ይህ ቤተ ክርስቲያን የቤተ ክርስቲያናችን ነቀርሳ ነው። የወንጌልም ጸር ነው።

Anonymous said...

"...ማህበረ ቅዱሳን! አይ ስም! ሲይጣን ..." can you please name at lest one practical example, or you dont know the church and what it means to serve the church?. As to Mahebere Kidusan,let those "Gedamatenna Adbarat" speak!,let those who know it in deed ,not from reading, speak!. But it's not surprising if some one who think he knows from hearing those who think they knew it or from readingor hearsay say the type of comments you just gave...guess u r one of them. Don't be laughed at bro/Sis!

May God help you to see the truth!

Anonymous said...

በጋሻው <>ይላል ጠቢቡ ሰለሞን ፤እባክህን ያለህበትን ሁኔታ አስተካክል።

selamawi said...

በስመ ስላሴ አሃዱ አምላክ አሜን

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋራ ይሁን እኔ ለራሴ አሜን ብያለሁ የናንተን አላቅም በዚህ ዘመን ብዙዎች ሰላምን አይፈልጓትም ለምን ይሆን? ,,, ከክፉ ሽሽ መልካምንም አድርግ ሰላምን እሻ ተከተላትም። መዝ 34፥14
ለምን ይሆን ቅዱስ ዳዊት ይህንን ምክር ሊመክረን የፈለገው ለማንኝኛውም ወደ ሃሳቤ ልሂድ ፊት አውራሪ በጋሻው የአቡነ ጳውሎስ ባለሙሉ ስልጣን ፊታዉራሪ ስርዓት ተበላሸ ቀኖና ፈረሰ ፍርድ ተጓደለ እያሉ የሚጮሁ የቤተክርስቲያን ልጆችን ሊያድን ሙሉ ስልጣን የተቀበለ ልክ እንደ ሃማ ,,,,, እንደ አንበሳ እያገሳ የሚውጠውን የሚፈልግ ጅብ የሚባል አውሬ ነው የጅብ ጸባይ ደግሞ እንደምታውቁት የራሱንም ጓደኛ አንድ ቀን አወዳደቁን አይቶ ይበላዋል ,, እስቲ አስቡት ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይላል

ስለዚህ ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ ሲናገር። ኢየሱስ የተረገመ ነው የሚል እንደሌለ፥ በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር። ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ።
1ኛ ቆሮ 12፥3 እውነት የነበጋሻው መንፈስ የመንፈስ ቅዱስ ነው ትላላችሁ ? አሁን ስለነሱ አላማና እቅድ ለመረዳት ነጋሪ ያስፈልገናል?ይህን ማወቅ የተሳነው ካለ አይኑም ልቡም የታወረ ነው ስለዚህ እባካችሁ አስተያየት ስንሰጥ ቢያንስ ህሊናችንን እንፍራው አንድ ቀን ከሳሽ ይሆነናል ቅዱሳን ስለፍቅር አንገታቸውን ለሰይፍ የሰጡባት እውነተኛይቱ ቅድስት ቤተክርስቲያን መድረክ ላይ አፉን ስድብ ሞልቶ ቆሞ እየተሳደበ እንዲህ አይነቱን ተግባር የሚፈጽምን ሰው መደገፍ ከዲያቢሎስ ሰራዊት ወገን መቆጠር ነው ልብ ይስጠን

awudemihiret said...

ወገን -ግጥሙን በአማርኛ ቢጽፉት እንዴት ያምራል።በአማርኛ ለመጻፍ የሚቀጥለውን ሊንክ ይጠቀሙ።
http://freetyping.geezedit.com/

ደጀሰላማውያን- እግዚአብሄር ይባርካችሁ።በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ ያለው ዳዊት በእናንተ
እየተፈጸመ ነው።እግዚአብሄር ብርታቱንና ጥንካሬውን ከናንተ አያርቅባችሁ።ለእውነተኞች ተስፋ ለቀማኞችና
ስውር ተኩላዎች መድምሰሻ ናሽሁ።በዚሁ ጽኑ ታስቀናላችሁ።

Anonymous said...

esti hulachu faraji atihunu rasu amlaki yifardi 'yhi madrak masadadbiya lmin hone' bagashwn lzhi yabaqachw betekiristiyan nech 'lkibirim lwirdatim' ywisti asrarwa qadmo yiqana yalziya bizu chigir ale anisadadbi

Anonymous said...

Everything I have been hearing these days about Begashaw is so appalling and indelible. Some five years ago (when I was back in Ethiopia) I was an instructor of English language in some institutions of foreign language in Addis Ababa. So, he was one of my students whilst he was attending at the Trinity Theology college. He was so quiet and discipline perosn amongs his peers. I had a very close and valuable friendship with him and his friends, especially outside class time, we used to discuss and share most important things in life, in particular how to live real christian life. But,now unfortunately, what really makes me seethe or angry at begashaw is not only how he is such damn ignorant and peremptory person who deliverately is wrecking his sanctity, but also how he has nobody to revile and remonstrate him to veer him from where he has been going blindly. It's so sad to have him at this very critical time that our Church is encountering.
May God root him out with that moron so called ejigayehu from our mother church.

Anonymous said...

Why!!!why are you spiliting the Holy church,what is your problem Brather if you are thinking for the church why don't you follow the rules and regulations of the church.our holy book says "FOLLOW YOUR FATHERS IN THEIR FAITH ,WHO TOLD YOU THE WORDS OF GOD.

Hanna said...

ከላይ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን የጻፍክው ሰው የአይጥ ምስክር ድንቢጥ ይላል ያገሬ ሰው፡፡ ምስክርነት መስጠት ካለብን በትክክል ብንመሰክር ምን ነበረበት፡፡ እውነቱን ይግለጽልህ ፈጣሪ፡፡

john said...

begashaw what are you doing u now what u are doing now are u cristian or just u are .....
dont do like this no one didn't do like this even "ahezab" we are cristian i think u put ur self up equal to the "abune pawlos" if u are cristian put ur self from there down to the ground no one is following u
why u always bleme every one above u there is a problem with u try to improve your problem come down begashaw ok
dont use words that didnt expect from u ok !!!!!!

Anonymous said...

እሺ በጋሻው ማስተማር ትተህ ታላቁን የአዋሳ ቅ/ገብርኤልን ያሳነፁትን አባቶች ስትሰድብ አመሸህ፡፡ አልፎ ተርፎም ሰሞኑ የተፈጠረውን ይአዋሳውን ችግር አስታከህ ከዛ ከሌባው ያሬድ ጋር እዚህ መጥተህ ሰዎችን ከዲላና ከይርጋለም አሰባሰበህ ለማሳመጽና እርስ በርስ ደም ለማፋሰስ ስትሸርብ ከረምክ፡፡ በእውነት በጣም አሳፋሪ ሰው መሆንህን ባሁኑ ሰኣት ከማንም በላይ እኛ የአዋሳ ህዝበ ክርስቲያኖች ተረድተናል፡፡ በጣም እንወድህ የነበርነው የአዋሳ ክርስቲያኖች የውስጥህ ምንፍቅናና ፍቅረ ንዋይ ገሃድ ሲወጣብህ ጠላንህ፡፡ በዚያ ላይ እኮ ያኔ አንተ ባለህ ተሰሚነት ያንንም ይህንንም ሃይ እያልክ የእውነተኛሰባኪ ተግባር መከወን ትችል ነበር፡፡ ለካስ ውጪህ እንጂ ውስጥህ ሰባኪ አልነበረም ኖሯል!
በቃ አሁን ሁሉም ነገርህ ስለተነቃበት እስካሁን በዘረፍከው ብር ሌላ ቢዝነስ ብትሞክር ይሻልሀል፡፡
ደግሞም በየመድረኩ ላይ ስለራስህ ትልቅነትና ስለማህበረ ቅዱሳን ክፉነት አታውራ፡፡ እርግጠኛ ሆኜ የምነግርህ ነገር ቢኖር ማህበረ ቅዱሳን ወጣቱን ካንተ ስፖንሰሮች(መናፍቃን)ጠብቆ በየትምህርት ቤቱና በየመስሪያ ቤቱ በቃለ እግዚአብሄር አንጾ እያነፀ ያለ የቤተክርስቲያናችን የጀርባ አጥንት ነው፡፡ አንተስ ምን ሰራህ?
ተሳድቤያለሁ፡ አሁንም ገና እሳደባለሁ ነበር ያልከው? አሳፋሪና ወራዳ ነህ፡ አሁን ይብቃህ፡፡ እግዚአብሄርም የውስጥህን አይቶ አብቅቶልሃል፡፡
ደግሞም አቡነ ጳውሎስ የሃውልቱን የስራ ልምድ ይጻፉልህና ኮንትራክተር ሁን!ቂቂቂቂቂቂ....
የፃፍኩት ነኝ
ከኣዋሳ እኔና ጓደኞቼ ወገባችንን ታጥቀን ስንከራከርልህ ነበር፡ አሁን ግን በተለይም ባለፈው ክረምት በአዋሳ ከተማ ቤተክርስቲያንን መሆን የለበትም ብለህ ከመሰልህ ያሬድ አደመ ጋር ሆነህ የመናፍቃን፡ ሙስሊሞችና የፖለቲካ ስብሰባዎችና ጫጫታዎች በብዛት በሚስየናገድበት የአዋሳው አደባባይ ላይ ጉባኤ ማዘጋጀትህ ሳያንስ ይሁን ብለን ቃለ እግዚአብሄር ጠምቶን መጥተን ነበር፡፡ ይሁንና

Anonymous said...

Thank you Dire Dawa MK Center. The center did the right measure. The government is also support this idea. Begashaw main aim is to miss Dire Dawa. The arrogant Begashaw should be stand in court and he must get the right judge for his bad deed. He is ant-orthodox and vagabond. He has not any Christian ethics but his mouth is only Christian

ዳዲ said...

እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅ !!!

Anonymous said...

በአንድ ወቅት በጋሻው ንግግር እንዲያደርግ በተጋበዘበት ስብሰባ ተገኝቼ ነበር። እንዲህ ብሎ ሲናገር ሰማሁት ፣ ማንም የእግዚአብሔርን በልቶ ማኔ ቴቄል ፋሬስ ሳይባልበት አይቀርም...

Anonymous said...

one thing that makes me so sad is when things which are nonsense get popularize and become an issue of discussion. It is so simple for everybody who has right mind to compare the doings of Mk and Begashaw (just uncomparable) so no need to make him apoint of discussion he dosen't even worth this place

Anonymous said...

ደጀ ሰላሞች ሁሉን አድርጉ፤ ግን ከአክብሮት ከትህትና ጋር ቢኾን ጥሩ ነው....። "በጋሻው ደሳለኝ ፍርድ ቤት ቀረበ" የሚል ርእሰ ዜና የሆነ የሚደብር ነገር አለው። እባካችሁ ብዙ መሔድ እየቻላችሁ በትንንሽ ጉዳዮች ተጠምዳችሁ እንዳትቀሩ ፤አሁን መኖሩም መሞቱም ዋጋ ከሌለው ከስምዐ ፅድቅ እባካችሁ ተማሩ። የተዋህዶ ልጆች የምንኮራበት የዜና እና የሀሳብ ማንሸረሸሪያ ድረ ገፅ መኾን ሲችል...እምቧለሌው ከቀጠለ እናንተም በዚያው መንገድ እንዳትሔዱ እፈራለሁ። እስኪ ስለየካው ሚካኤል ብላችሁ!ስንት ዘመን ነው...ስለ ወ/ሮ እንትና እና አቶ ዘሪሁን...እንትና የምናነበው....?..

Anonymous said...

Does this forum support the free exchange of ideas and opinions? Or is it an outlet only to promote MK and attack its critics? Do you have the church or MK deep in your heart? Do you think MK is holy as its name implies? Please let us know in the name of St Mary, whom you claim to love the most. The fact is MK has done more damage than good to EOTC. Who sang the song that says "yeamlak chinkaru ema amist bitcha neber, yeantema Giorgis ejig girum neger." Does MK even know the differences between the sufferings of Christ Jesus and those of St George? What heresy can we talk about more than this? Creating turmoil in the church, attacking brothers/sisters/ fathers etc... are other problems. Please respond now in the name of our most loved Mother and Queen Mary...

Anonymous said...

አይ በጋሻው አሱ አኮ አነጋገሩ ሁሉ ይገልጥበት ነበር የተዋህዶ ልጅ አንዳልሆነ አርሱ ያልባረከው ፩ ካሴት አንዳይሸጥ፤ የጥንቱ አዘማመር ማለት የሥላሴን የአመቤታችን የቅ\ሚካዓል የቅ /ገብርዓል የተክለ ሃይማኖት የገብረ መንፈስ ቅዱስ አረ የቅዱሳን የሰማዕታት ሥም የሚያነሳ ከገበያው ውጪ አንዲሆን ፕሮጀክት አስቀርጾ መጥቶ ያው አንደምንሰማው ለስሙ ብቻ ስለ አመቤታችን አንድ ጣል አንዲያደርጉ አንዳይነቃበት ለዛውም ተራ ግጥም |ጌታ ፣ ውዴ ፣ናፍቆቴ ፣ ትዝ አልከኝ፣ ዘምር ዘምር አለኝ,,,,| በሚሉ ካሴቶች ምድርን በምስጋና ሞላናት አለን ፣ታድያማ የማይገለጽ የተሰወረ የለማ፦አስቲ ዘማርያንም የሆንም ዝም ብለን አንደ ጠፍ ከብት አንመራ በውነት ምን አየሰራሁ ነው ብለን ራሳችንን አንይ፤ ቤተከርስቲያንን አንወቃት,,,

Anonymous said...

woy gude yemenesemaw negere yegermal

Anonymous said...

gude new lala mene elalhu

Unknown said...

He must be liable for what he did wrong…. He has got experienced for being rude in Awassa and no one asking him for… I guess the time is coming to be asked… we had preached and protected by words of GOD but not by someone who pretends having a fear of GOD…. We don’t need such a preacher who always faces logorrhea and gives fruitless words….

Anonymous said...

28ኛው Anonymous ምነው ስምዐ ፅድቅን ኮነንሃት የታድስህ መሰለኝ

Anonymous said...

Ebakcheu sela embetye mareyam belacheu ye w/ro ejegayeune tel.n.telfon kouter yemyawke ebkacheu ega semten ayten zeme senle esacheu alarefoume ebakcheu kawekcheu safuolge plssss

GUD-FELA ZE MINNESOTA said...

BE YOURSELF.

Are you, Begashaw, still continiuing to be stubborn in this issue? You were protected and encircled by the good Tewahedo people; however, you missed the opportunity of being known by them. Now you have been supporting tehadso, which are on the wrong way and position. Money and simple fame led you to follow the devil's path, as you don't know that it is miscalculation. You were done when you failed to give reverence for the Tewahedo Church and began opposing Our Mother Virgin Mary. You were not built up by the spirit of tehadeso until you deny the power of Tewahedo Church. Always there is a chance to come back to the right track as long as you need to do it willingly. Confess to our Tewahedo Church to become a good child of the Church and expose your followers and their fruitless deeds. Protestants are always Protestants. Don't be the victim of their trash moral and earthly benefit. You are totally misled unless you turn your face to be with your first and best religion. No one would be against you if you were the right person to preach Ethiopian Orthodox Tewahedo Church's dogma, doctrine, tradition, and cannon. When we read your book, YE-MESKELU SIR KUMARTEGNOCH, we thought that you were the right person who stood supporting our Church. You challenged the work of the Patriarch, and at the same time you seemed to be the follower of Jesus Christ; however, you were found again gambling under the statue of Abune Paulos. Don't show us your double face strategy in religion. Be yourself. Don't ever be outwitted and beguiled by the words and vain praise of tehadiso and Protestants. Take our insulting as a good advice, as we have been striving to bring you back where you were. Our insulting is much better than Protestants money and futile approach. They are misled and they will mislead others.

Anonymous said...

le 28th Anonymous d/n Begashawu firdbet qerebe siletebale betam kebedeh tadiya Genet qerebe indiluhi tifeligaleh ? midirawiwu sirahi yemejemeriya evaluation be midirawi firdibet silemiwesen ayigremih lelayingawu qeterowu genanewu ina.

"Harka kennani luka fudhatu"
MN irraa.

Anonymous said...

ጥያቄ አለኝ፦
በማህበረ ቅዱሳን የሚናደድ ማነው ወይም የሚጠላቸው ማነው? እኔ እስከማውቀው ድረስ ባላቸው የቤተክርስቲያን ፍቅር፣ እምነታችን እና ስርአታችን እንዳለ ለትውልድ ይተላለፍ፣ እምነታችን ይስፋፋ፣ ገዳማት ይረዱ፣ የቤተክርስቲያናችን መሰረቶች፣ የሊቃውንት ማፍሪያ የሆኑት የአብነት ት/ቤቶች ይረዱ፣ ሊቃውንት አባቶች ይደገፉ ሀገራችን አዎን የክርስትና ደሴት ቅድስት ሃገር ነች፣ በማለታቸው በዘመኑ እውቀት ልክ በተጠናና በተደራጀ ሁኔታ ትውልዱን እንደንብ ሰራዊት በማንቀሳቀስ እንዲተም አድርገው ለቤተክርስቲያን ጠበቃ ስላደረጉት የበሸቁ 1.እንደመሰላቸው ትንሽ ቢገፏት የምትወድቅ መስሏቸው የነበሩ ተሀድሶአዊ መሰሪ አላማቸውን ለማስረፅ የሚንቀሳቀሱ 2.አህዛባዊ አላማቸው የከሸፈባቸው 3.የጭቃ ውስጥ እሾክ ሆነው ቀሚሶቻቸውን አንዠርገው አላማቸው ሆድ መሙላት ብቻ የሆኑ ውስጥ ውስጧን የሚቦጠቡጧት ሆዳሞች እና 4.ቀን ያለፈባቸው ተስፋ የቆረጡ ለውድቀታቸው ማካካሻ ያጡ መሰረተ ቢስ ፖለቲከኞች(ጥሩነቱ እነዚህኞቹ ሞተው ሲያልቁ ነገራቸውም አብሮ ይሞታል ምን አልባት 10 አመት ቢወራጩ ነው ያኔ ወይ ነርሲንግ ሆም ወይ ደሞ አዲዎስ) ጎላ ብለው የሚታዩኝ ሲሆኑ ሌሎችም ይኖሩ ይሆናል ወገኖቼ ለቤተክርስቲያን የሚቆረቆርን ሰው ስርአታችን እምነታችን ይጠበቅ ያለን ሰው ሁሉ ከመጥላታችን በፊት እራሳችንን እላይ ከተጠቀሱት ክፍሎች ውስጥ መኖር አለመኖራችንን እንገምግም ባንዱ ወይም በሌሎቹ ክፍል ውስጥ ካለንበት ጥፋቱ የማህበረ ቅዱሳን ሳይሆን የኛው መሆኑን አውቀን ሚናችንን እንለይ ለቤተክርስስቲያን ተቆርቋሪ የሆነው ትውልድ እንደሆነ የበጋ ወራት ሰደድ እሳት ነው። አየኸው አይደል ለጥምቀት ከቤትክርስቲያን እስከጥምቀተ ባህር ድረስ አስፋልት ጠርጎ ቄጠማ ጎዝጉዞ ቀይ ምንጣፍ አንጥፎ እንደዳዊት በእግዚአብሔር የክብር መገለጫ ፊት ለእግዚአብሔር እየዘለለ ሲዘምር። አይ ሞኞ። ይልቅ ንቃና አብረህ/ሽ/ አመስግን/ኚ/ እኔ የቤተክርስቲያኔ ተቆርቋሪ ነኝ እናንተስ ከላይ ከዘረዘርኳቸው ውስጥ አሉበት ወይስ የቤተክርስቲያን ኖት? የተዋህዶ ልጅ ነኝ።

Anonymous said...

I am truly sorry for being our Church has created the so called preacher like Begashaw. He has superficial and rude personality. He is shaped and fashioned by protestant doctrine. He is assumed himself a big Christian and preacher. But he does not know about Christianity and the mission of the church. His main is to collect money from church like Judah and sell the church to others. We need to pray day and night our Heavenly Father to uncover his mask.

Anonymous said...

YOU MEHABIR SATAN YOU UGLY AND STUPID DONOT BLAME AND ACCUSE FATHERS, PREACHERS LEAVE ALONE. PLEASE YOU ARE JUST ELEMENTARY. WONGEL ANEBEBU.

Anonymous said...

You post when some people insult you to appear democratic, but you dump comments that appear to be critical. I posted a number of decent, but critical, comments, but you blocked them. You are simply cheating yourself, but you will be judged and treated the way you are doing it. Not from me - God will do it in his own ways. thank you!

Tamiru Z hawassa said...

አይ በጋሻው “የሳሮኔ ፅጌረዳ ፤ የኔ ጌታ፤ አበባዬ፤ሆዴ፤ ውዴ” እያልክ ብዙ የዋሃን አታለሃል፡፡
ብዙ የቤተክርስቲያን ሊቃውንት ዘልፈሃል፤ተሳድበሃል የብዙዎች ኦርቶዶክሳውያን ልብ አቁስለሃል፡፡
እኔ እንደ ማ/ቅዱሳኖች ባትሰድበኝም፤ በምታስተምረው ት/ት (የተሳሳተ ት/ት)፤ የቤ/ክ ስርዐት ባልጠበቀ ትምህርትህ አዘንኩብህ፡፡
ብዙ ህዝብ እንዳዘነብህ ነው፤ ቤ/ክን አድምተሃታል፤ እግዚአብሔርን በድለሃል ፡፡
ብዙ ፍርድ አለብህ፡፡
ተመለስ ይበቃሃል ትዕቢት እንደሆነ የግብር አባትህም ከውርደት የጣለው ነው የትም አያደርስህም፡፡
አንተና ተላላኪዎችህ(እነ ያሬድ…) በድፍረት በአውደምህረት ላይ “ከፈለግን የጌድዮን ሰራዊት ያህል ማሰለፍ እንችላለን፡፡”
ስትሉ እንዳልነበረ፤
አጣሪዎች ሀዋሳ ሲመጡ የገጠማችሁ ብታስታውሱ በቂ ይመስለኛል፡፡
የኔ ቢጤዎችን መፈክር እስከማስያዝ የደረሳችሁ ከጎናችሁ ምንም ሰው እንደሌለ ማወቅ ይገባችሁ ነበር፡፡ ይህም ትዕቢት ነው ሌላ ምን እንለዋለን፡፡
አቡነ ፋኑኤል ስለ ተረዱ አይደል “ያሬድ ሸወድከኝ ሰው ሁሉ ከኛ ነው ብለህ ከየኔ ቢጤዎች እና ከምልምል ቴኳንዶዎች ብቻ አስቀረኸኝ” ያሉህ ያሬድዬ (ደረቅ ቼክ አጭበርባሪዬ፤ የፆም አሮስቶዬ፤…)
በጋሻው! ብታምንም ባታምንም ህዝቡ ተከትሎህ የነበረው፤
 በትምህርትህ እንዳልልህ ትምህርትህ የኑፋቄ ነው፡፡
 በእውቀትህ እንዳልልህ 2ኛ አመትህ ላይ በስነ ምግባርህ እና F በማብዛትህ ተባረሃል፡፡
 በድምጽህ ጎርናናነትም አይደለም፡፡
ስለዚህ ከህዝቡ ጎን የቆምክ መስለህ (አላማህ ምን እንደሆነ ባይታወቅም) የቤተክርስቲያንን የመጨረሻው የስልጣን ባለቤት(ከመንፈስ ቅዱስ ቀጥሎ ማለቴ ነው፡፡) የሆነውን የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ የሚጋፉትን ቅዱስ ፓትርያርኩን ስለተቃወምክ ብቻ ነው፡፡
አሁን ደግሞ የሀውልቱ ስር ቁማርተኛ ሆነሃል፡፡
ህዝቡም እርቆሃል፡፡ ንስሃ ግባ ተመለስ ካልሆነም አታስጨንቀን ይለይልህ አላማሀ ንገረን፡፡
የቀድሞ ደጋፊህ አሁን ግብርህ ቤ/ክ የሚጎዳ ስለሆነ (ቤተክርስቲያን የሚነካብኝ ስለማልወድ ነው) የምቃወምህ

ታምሩ ከ አዋሳ

Tamiru Z hawassa said...

አይ በጋሻው “የሳሮኔ ፅጌረዳ ፤ የኔ ጌታ፤ አበባዬ፤ሆዴ፤ ውዴ” እያልክ ብዙ የዋሃን አታለሃል፡፡
ብዙ የቤተክርስቲያን ሊቃውንት ዘልፈሃል፤ተሳድበሃል የብዙዎች ኦርቶዶክሳውያን ልብ አቁስለሃል፡፡
እኔ እንደ ማ/ቅዱሳኖች ባትሰድበኝም፤ በምታስተምረው ት/ት (የተሳሳተ ት/ት)፤ የቤ/ክ ስርዐት ባልጠበቀ ትምህርትህ አዘንኩብህ፡፡
ብዙ ህዝብ እንዳዘነብህ ነው፤ ቤ/ክን አድምተሃታል፤ እግዚአብሔርን በድለሃል ፡፡
ብዙ ፍርድ አለብህ፡፡
ተመለስ ይበቃሃል ትዕቢት እንደሆነ የግብር አባትህም ከውርደት የጣለው ነው የትም አያደርስህም፡፡
አንተና ተላላኪዎችህ(እነ ያሬድ…) በድፍረት በአውደምህረት ላይ “ከፈለግን የጌድዮን ሰራዊት ያህል ማሰለፍ እንችላለን፡፡”
ስትሉ እንዳልነበረ፤
አጣሪዎች ሀዋሳ ሲመጡ የገጠማችሁ ብታስታውሱ በቂ ይመስለኛል፡፡
የኔ ቢጤዎችን መፈክር እስከማስያዝ የደረሳችሁ ከጎናችሁ ምንም ሰው እንደሌለ ማወቅ ይገባችሁ ነበር፡፡ ይህም ትዕቢት ነው ሌላ ምን እንለዋለን፡፡
አቡነ ፋኑኤል ስለ ተረዱ አይደል “ያሬድ ሸወድከኝ ሰው ሁሉ ከኛ ነው ብለህ ከየኔ ቢጤዎች እና ከምልምል ቴኳንዶዎች ብቻ አስቀረኸኝ” ያሉህ ያሬድዬ (ደረቅ ቼክ አጭበርባሪዬ፤ የፆም አሮስቶዬ፤…)
በጋሻው! ብታምንም ባታምንም ህዝቡ ተከትሎህ የነበረው፤
 በትምህርትህ እንዳልልህ ትምህርትህ የኑፋቄ ነው፡፡
 በእውቀትህ እንዳልልህ 2ኛ አመትህ ላይ በስነ ምግባርህ እና F በማብዛትህ ተባረሃል፡፡
 በድምጽህ ጎርናናነትም አይደለም፡፡
ስለዚህ ከህዝቡ ጎን የቆምክ መስለህ (አላማህ ምን እንደሆነ ባይታወቅም) የቤተክርስቲያንን የመጨረሻው የስልጣን ባለቤት(ከመንፈስ ቅዱስ ቀጥሎ ማለቴ ነው፡፡) የሆነውን የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ የሚጋፉትን ቅዱስ ፓትርያርኩን ስለተቃወምክ ብቻ ነው፡፡
አሁን ደግሞ የሀውልቱ ስር ቁማርተኛ ሆነሃል፡፡
ህዝቡም እርቆሃል፡፡ ንስሃ ግባ ተመለስ ካልሆነም አታስጨንቀን ይለይልህ አላማሀ ንገረን፡፡
የቀድሞ ደጋፊህ አሁን ግብርህ ቤ/ክ የሚጎዳ ስለሆነ (ቤተክርስቲያን የሚነካብኝ ስለማልወድ ነው) የምቃወምህ

ታምሩ ከ አዋሳ

aragaw ewnetu said...

Begashaw is against MK because he has anti-ORTHODOX stand. We know most of his followers in Dire Dawa. They strictly tehadsoes. Their names and activities will be post to this blog.

Unknown said...

Mahibere Kidusan ‘ziq bilo berere’, as He stands in the court with Begashaw (Shola) and his fans (Yeshola degafiwoch).

dani said...

አይ በጋሻው ቁጥር 11 የኑፋቄ ትህምርትን በመልቀቅ ምዕመኑን ለመበዝበዝ መነሳትህ በጣም ያሳዝናል፡፡ግን ምን ይባላል ልቦና ይስጥህ፡፡

Henok Demeke said...

ይህ እኮ ለዬት ያለ ነገር ነው ጥጋብ ይባላል፧ በጣም አዋራጅ ከአምላክ በቀላሉ የምያርቅ ነው፧ እባክህ ወንድሜ በጋሻው ደሳለኝ በአፍህ እየወጣ ነውና ተጠንቀቅ፨

fkre said...

እንድህ ነው አንግድህ ያስተማራቸው እሱን እንድያመልኩና እሱን እንድሰብኩ ነው ለጌታ የተባለውን ለበጋሻው ሲጠቀሙ ቅር አላላቸውም አቤት ትምህርተ ክርስትና ደስይላል እባካችሁ አሜሪካ ማስፈራሪያ ናት ? እንደሱ አይነት ጨዋ የሚኖርባት መስሎት ነው ናስቲ እናየዋለን የባጃጅ ሹፌር የለ እዚኅ የምጻሽፈራራበት ብዙ ሀይል አለኝ እያልክ መደንፋት አችል ውነትም ሾላ ነኅ እባክኅ

fkre said...

እንድህ ነው አንግድህ ያስተማራቸው እሱን እንድያመልኩና እሱን እንድሰብኩ ነው ለጌታ የተባለውን ለበጋሻው ሲጠቀሙ ቅር አላላቸውም አቤት ትምህርተ ክርስትና ደስይላል እባካችሁ አሜሪካ ማስፈራሪያ ናት ? እንደሱ አይነት ጨዋ የሚኖርባት መስሎት ነው ናስቲ እናየዋለን የባጃጅ ሹፌር የለ እዚኅ የምጻሽፈራራበት ብዙ ሀይል አለኝ እያልክ መደንፋት አችል ውነትም ሾላ ነኅ እባክኅ

fkre said...

እንድህ ነው አንግድህ ያስተማራቸው እሱን እንድያመልኩና እሱን እንድሰብኩ ነው ለጌታ የተባለውን ለበጋሻው ሲጠቀሙ ቅር አላላቸውም አቤት ትምህርተ ክርስትና ደስይላል እባካችሁ አሜሪካ ማስፈራሪያ ናት ? እንደሱ አይነት ጨዋ የሚኖርባት መስሎት ነው ናስቲ እናየዋለን የባጃጅ ሹፌር የለ እዚኅ የምጻሽፈራራበት ብዙ ሀይል አለኝ እያልክ መደንፋት አችል ውነትም ሾላ ነኅ እባክኅn

ቢኒ said...

እኔ ማህበረ ቅዱሳን የጠመደውን ካላጠፋ እንደማያቆም አውቃለሁ ሁሉም አንድ አይነት ናቸው ከውስጡ ደግሞ መልካም ስነ ምግባር ያላቸው አሉ ለምን ከፉዎቹን እንደማይመክሯቸው አይገባኝም እኔ ለምሳሌ ድንበሩን አውቀዋለሁ ቅን ቤተ ክርስቲያንን መርዳት ብቻ ነው አላማው ሌሎች ደግሞ አሉ ያለ እነሱ አዋቂ ያለ የማይመስላቸው ታድያ ለምን እነድንበሩ እነዚህን አታስታግሶቸውም መቸም ድንበሩ በጋሻው ጸጋው የበዛለት መሆኑን አንተም ታውቃለህ የሁላችን ህይዎት የተለወጠው በሱ ነው ስለዚህ ፍርድ ቤት ባይቆም ምን ይመስልሀል?መቸም ማንበብህ አይቀርም እና አስተያየት ብሰጠኝ ?
ቢንያም ነኝ ከለገ

ቢኒ said...

እኔ ማህበረ ቅዱሳን የጠመደውን ካላጠፋ እንደማያቆም አውቃለሁ ሁሉም አንድ አይነት ናቸው ከውስጡ ደግሞ መልካም ስነ ምግባር ያላቸው አሉ ለምን ከፉዎቹን እንደማይመክሯቸው አይገባኝም እኔ ለምሳሌ ድንበሩን አውቀዋለሁ ቅን ቤተ ክርስቲያንን መርዳት ብቻ ነው አላማው ሌሎች ደግሞ አሉ ያለ እነሱ አዋቂ ያለ የማይመስላቸው ታድያ ለምን እነድንበሩ እነዚህን አታስታግሶቸውም መቸም ድንበሩ በጋሻው ጸጋው የበዛለት መሆኑን አንተም ታውቃለህ የሁላችን ህይዎት የተለወጠው በሱ ነው ስለዚህ ፍርድ ቤት ባይቆም ምን ይመስልሀል?መቸም ማንበብህ አይቀርም እና አስተያየት ብሰጠኝ ?
ቢንያም ነኝ ከለገ

biniyam said...

biniyam said
ደጀሰላሞች እግዚአብሔር ይስጥልን
በእውነት በጋሻው የወንጌል ሰው ቢሆን <> የሚለውን ባሰበ ነበር።
ለነገሩ ቅዱሳንን በየመድረኩ ሲሳደብ በየካሴቱ ሲዘልፍ የኖረ መናፍቅ አንድን ማህበር እሳደባለሁ ቢል ምኑ ይገርማል?
ማኅበረ ቅዱሳንን የሚሳደብ የቤተክርስቲያን ጠላት ብቻ ነዉ።
እግዚአብሔር ቤቱን ከተሃድሶአውያን ያፅዳ።አይ በጋሻው ምድራዊ ዳኛ ለምን የቤተክርስትያን አምላክ ይፋረድህ ይዘገያል እንጇ ሌብነትክ ገሐድ ይወጣልአይ በጋሻው ምድራዊ ዳኛ ለምን የቤተክርስትያን አምላክ ይፋረድህ ይዘገያል እንጇ ሌብነትክ ገሐድ ይወጣል

bp said...

አይ በጋሻው ልቦና ይስጥህ!!
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!!

Yared said...

ሰይጣን በቅዱስ ጴጥሮስ ላይ አድሮ ጌታሆይ አይሁንብህ ሲለው ሂድ አንተ ሰይጣን አለው እንጅ እሽ ብሎ ያቀረበለትን ሀሳብ አልተቀበለም አሁንም ድንበሩ አስተያየቱን ይስጥ ግን በውዳሴ ከንቱ ተጥሎ አንተ የምትለውን ሃሳብ ሊያራምድ ይችላል አንተም የመከፋፈል እቅድ ይዘህ ይመስለኛል ሆኖም ግን ድንበሩ የፈለገውን አስተያየት ይስጥ ጉዳዩ ግን የሱ ብቻ አይደለም ወድሜ ቢኒ የሁሉም ክርስቲያን እንጅ ለሁሉም እኔም የሚለውን ለመስማት ጓጉቻለሁ እጠብቃለሁ የቢን እቅድ ግን ልንነቃበት ይገባል
ያሬደ

Anonymous said...

ወንድሜ ቢንያም ዘለገ አንተ እንዳልከው ያንተን ጥሩ ህይዎት ወደ መጥፎ የለወጠው በጋሻው ይሆናል ግን የድንበሩን ህይዎት ሊለውጥ አይችልም ምክንያቱም በጋሻውን ሊፈጥሩ የሚችሉ መምህራን አስተምረውታልና አንተ የምትለው በጋሻው ቢያስተምረው ክህደት እንጅ አንተ እንደምትለው ቅን ባልሆነ ነበር ምክንያቱም በጋሻው የሚያስተምረው መሰረታዊ 3 ነገሮችን ነው እነሱም ገንዘብ መውደድን ስደብንና ትልቁ ምንፍቅናን ነው ወዳጀ ስለዚህ ድንበሩን እሱ አላስተማረውም አያስተምረውም

ቢኒ said...

ወንድሜ 51ኛ ላይ አስተያየት አንተን መች ጠየኩ እራሱን እንጅ እናንተ እማ መች ቅን ሀሳብ አላችሁና ደጀሰላሞችስ ብትሆኑ የተጠየቀው ሰው ካልሆነ ለምን ታጣላችሁ እኔ የተሻለ የምለውን ጠየኩኝ እንጅ ለማንኛውም አሁንም መልሱን አንጠብቃለን !!
ቢኒ ከለገ

mebrud said...

ቢኒ ዘለገ
ይቺ አፍ እንዳገኘ መጥቀስ እነ በጌ ነው ያስተማሩሽ
"ጸጋው የበዛለት" ነውኮ ያልከን፡፡
የምን ጸጋ ወዳጄ?የስድብ ጸጋ ነው፡፡
ቅዱስነታቸውን መሳደብ ያስተማረንን ነው?
የሐውልት ስራውን ነው?
ኸረ ጎበዝ ዝም ብለን በቃሉ ከምንጫወት እንደዘይቤያችን ጣጣ የለበትም አቦ ማለትኮ እንችላለን፡፡
ይኼ ደርሶ መናፍቅ ይመስል(ነገሩ መናፍቅነት ነው) የሚጠቀሱ ጥቅሶች እንዴት እንደሚያቃጥሉኝ አትጠይቁኝ፡፡
"ጸጋው በዝቶለት"፣ምድርን ከድኖ፤የጌዲዮን ሰራዊት አሰልፎ፡ሀይሉ ብዙ ሆኖ፡ ጠላቶቹ በዝተውበት፡ የወንጌል እንቅፋት ሆነውበት፡ ምን ቀረ
ባህር ከፍሎ፡ሞቶ ተሰቅሎ፡በሦስተኛው ቀን...፡፡
እንዴ ምንድነው ነገሩ
ይሄ ሰው ቅዱስ ጳውሎስ ነው ክርስቶስ፡፡
አሁን ደግሞ ቢታሰር በዝማሬው ሰንሰለት ተበጣጥሶ ሊባል ይችላል፡፡
ይቺ ናት እንግዲህ የነበጋሻው ወንጌል ውጤት፡፡
የትህትና ሀገሯ ወዴት ነው?
አባቶቼ ማሩኝ በትህትና የሰበካችሁት የክርስቶስ ወንጌል ናፈቀኝ፡፡

Ehte maryam said...

ante endet yaleh defar neh dinberun begashawu astemarewu tlaleh bini lege tew enji wedaje endet yihonal degmo besu atmtubn ebakachihu esu altesasakem endalkew bete krstiyann magelgel bchia new srawu ende Begashaw awenabaji ayidelem yedurye hYwet lewachi ante tawkaleh
Ehte maryam

Anonymous said...

ለአሳዳጅም አሳዳጅ አለዉ፡፡ ማቆች በሰፈራችሁት ቁና እየተሰፈራችሁ ነዉ፡፡ ንጹሐንን አባቶች እዳሳደዳችሁ እናንተም እጣዉ ደረሳችሁ፡፡ እሰይ

Anonymous said...

begasahwen yemetesadebu sewoche zem belu!! menem yemetakute nger yelem ena . Ma tefategna ma tekekel endehone behuwala yeleyal. Mehaber kedusan ke semachew jemero eras wedade ena defar nachew enesune belo maheber dedusan!! lezi new erotew kese lay yehedute

ye pente misakiya bayhonu teru new yelk. Yebetachewen Gude ezaw yeyazut! Enesu ahune tebeleten sew kegna yelke begashawen lemen weded belew new !! Geta erasu yefered ma tekekel endhone demo aykerm!! Metaweku Maheber kedusan gen maferiya nachu!!!! Asedabiwochi. Ke kedusan yemayetebek kelit !!

Anonymous said...

well, it's my 1st time when am visiting this web n i learn a lot of things esp. what's going on in our religion. hence, i prefer to mind my own business b/c God have his own time n place to show us what needs to be done n in which way we should follow his rules to him or anyone else, so we all his children must pray from our heart to give us forgiveness n his blessing..there r things coming in front of us so "ቃሉ ይፈጸም ዘንድ ግድ ነውና አውጣን ማለት ብቻ ነው!!!!"

Anonymous said...

Oh! Dear Begashaw, How are You today. You are so foolish that you would rather preach the Holy Gospel forcefully than being a minister called upon with grace.

Your thoughts,words,styles all are attributed to those of Pharisees. I couldn't find even a single fruit of life from you preaching so your are stubborn who dare to appear a minister by force.

May The Lord give you a mind for seeing internally.

Anonymous said...

ድንበሩን ቅን ትላለህ ዋናው መሰሪ የክፋት መፍለቂው ማን ሆኖ ካልክስ ሌሎቹ ናቸው ደጋግ እሱ እንኳን ይችን አመት አያልፋትም እኔ ሰው ይገርመኛል ደግ ሰው አታውቁም ማለት ነው አባቶችን ስም የሚያጠፋው እሱ እንደሆነ እኔ መረጃው አለኝ የራሳቸው አባላቶችም በይፋ የሚያወሩት ነው አንተ ቅን አልከው አየ ቅን እስኪ ዋጋውን በቶሎ ያሳየን

Anonymous said...

tezeker egzio kememerate nihne
wesebse kemesair mewaelihu
wekemetsige gedam kemahu yferihe
abetu bemengistihi asben!

Anonymous said...

ጤና ይስትልኝ ህዝበ ክርስቲያኖች በእውነቱ የሁላችሁንም አስተያየት አንብቤዋለው ለቤተክርሰቲያናችን ያላቹን ቅናት ደስ ሚል ነው ነገር ግን አንድ ማስተዋል ያለብን ነገር አለ በመሰረቱ ወንድም በጋሻው ያረገው ነገር አግባብ ባይሆንም እኛ ግን ነገሮችን ማየት ያለብን ነንደ ይማኖት ሰውና እንደ ቅዱስ ቃሉ መሆን አለበት ሆኖም ሰው ነንና ምናየው እንደሰው ነውና እስቲ እንደቅዱስ ቃሉ እንይ
“መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 16፡7 እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን፦ ፊቱን የቁመቱንም ዘለግታ አትይ ሰው እንዲያይ እግዚአብሔር አያይምና ናቅሁት ሰው ፊትን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል አለው።”
ይላል በውነት ወንድማችን በኛ ፊት ትፋተኛ ነድሆነ በቅዱሱ አምላካችን ፊት ትፋተኛ ይሆን፣ ይህ ቃል ሲፃፍ በሌላ አንድምታ ቢሆንም ሃሳቤን ግን ያገኛቹት ይመስለኛል
“ኦሪት ዘፍጥረት20፡3 መቅደሴን ያረክስ ዘንድ፥ የተቀደሰውንም ስሜን ያጐሰቍል ዘንድ ዘሩን ለሞሎክ ሰጥቶአልና እኔ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከብዳለሁ፥ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ።”
ቃሉ እንደዚ ካለ ዘንዳ የቅዱስ እግዚአብሔር ቤትና ምእመን ያረከሰ የሚቀጣው ፍርድ ቤት ሳይሆን እራሱ ቅዱስ እግዚአብሔር ነው
“መጽሐፈ ሳሙኤልቀዳማዊ2:10 ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ይደቅቃሉ በሰማይም ያንጐደጕድባቸዋል እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል ለንጉሡም ኃይል ይሰጣል የመሲሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።”
ስለዚ ትፋተኛ ከሆነ ቅዱሱ እግዚአብሔር እራሱ ይቀጣዋል እንጂ በዚች አለም ስረአት አይደለም ጌታችን በቅዱስ ቃሉ “በየዮሐንስ ወንጌል2:19 ኢየሱስም መልሶ፦ ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፥ በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ አላቸው።” ብሎ የተናገረው ለምን ይመስላችሃል ቤተ መቅደስ ውሰት የአለም ስረአት ስለገባ አይደለም
ሌላው ማንሳት ምፈልገው ነጥብ ደግሞ “የዮሐንስ ወንጌል 8:11እርስዋም፦ ጌታ ሆይ፥ አንድ ስንኳ አለች። ኢየሱስም፦ እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ አላት።” ከዚ ካል የምንማረው እኛ ከሰነው እንኳ ቢሆን አምላካችን በነፃ ሊያሰናብተው ይችላል ይህን ሁሉ ስፅፍ ግን ለወንድማችን ጥብቅና እየቆምኩ ሳይሆን እንደ ክርሰቲያን ማየት ያለብንን ነጥብ ለማንሳት ነው አሁንም ቢሆን ፍርዱን ለፃድቁና ለቅዱስ እግዚአብሔር እየተውኩ ነው ቸሩ መድሃኒአለም ለተከሳሹ ወንድማችንና ለሁላችን ቅን ልቦና ይስጠን ቤተክርሰቲያናችንና ሀገራችንን ይባርክ ጨረስኩ

debela said...

ወይ በጋሻው በሞሰብ እንጀራ በልተህ በልተህ ስትጠግብ መርዝ ተፍተህ ሰውን በበሽታ ልትገድል?

Anonymous said...

እኛ ግን አንድ ያልተረዳነው ነገር አለ ሰለምን ሰዎች እውነት ሲነገሩ እውነታውን ማመን ይከብደናል እኔ እንደሚመስለኝ ዲያቆን በጋሻው ወጣቱን የቀየረ መምህር ነው በያጠፋ እንኳን ቀርበን ልንነገረው እንጂ እንዲህ ልንለው አይገባም ደግሞም ትክከለኛ ነግር የተናገረ ይመስለኛል እባካቸሁ ቢቻል ቢቻል ሰለፍቅር ያስተማርን ክርስቶስን በለን በፍቅር ሁሉን ነገር ለማሸነፍ እንሞክር እግዚያብሄር ከኛ ጋር ይሁን ፡፡

muluken tekleyohanes said...

begashaw ebakeh atabetabten god yeserahn yesteh

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)