November 27, 2010

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን የገንዘብ እና ንብረት ቆጠራ ላይ ጥብቅ መመሪያ ሰጠ


 • ለሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ እና ለሥራ አስኪያጁ ንቡረ እድ  አባ ገብረ ማርያም አቀባበል ተደርጓል፡፡
 • አጥቢያ አብያተ ክርስቲያኑ ለሀገረ ስብከቱ ፈሰስ ማድረግ የሚጠበቅባቸው የ58 ሚሊዮን ብር ዕዳ ያለባቸው ሲሆን ሀገረ ስብከቱ ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ፈሰስ ማድረግ ከሚጠበቅበት የዘመኑ ገቢ የ13 ሚሊዮን ብር ጉድለት ተገኝቶበታል፡፡    
 • ‹‹ምእመናን ተቸግረው በሚሰጡት ገንዘብ መልሰው እንዲያዝኑ ልናደርጋቸው  አይገባም፡፡›› (ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ)
 • ‹‹ለቅጥር፣ ዕድገት እና ዝውውር አማላጅ የመላክ ጉዳይ አይቻለሁ፤ በግልጽ  ማስታወቂያ በሚወጣው መሠረት ከሚፈጸመው በቀር በምልጃ የሚደረግ ነገር  አይኖርም፡፡›› (ንቡረ እድ አባ ገብረ ማርያም)
(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 27/2010፤ ኅዳር 18/2003 ዓ.ም)ትናንት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ጥሪ በተደረገላቸው የአዲስ አበባ ገዳማት እና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ የሰበካ ጉባኤ ጸሐፊዎች፣ ሒሳብ ሹሞች፣ የስብከተ ወንጌል ሐላፊዎች እና የምእመናን ተወካዮች በተገኙበት በጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለሆኑት ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ እና ለሥራ አስኪያጁ ንቡረ እድ አባ ገብረ ማርያም የአቀባበል እና የትውውቅ መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመለሱ

(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 26/2010፤ ኅዳር 17/2003 ዓ.ም)የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት ከኅዳር ስምንት ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ ትምህርት በማቆም እና ከምግብ ቤቱ አገልግሎት በመከልከል ባነሷቸው ችግሮች አፈታት ላይ ስምምነት ተደረሰ፤ ደቀ መዛሙርቱም ከትናንት ኅዳር 18 ቀን 2003 ዓ.ም ምሽት ጀምሮ በኮሌጁ የምግብ ቤት አገልግሎት መጠቀም መጀመራቸው ታውቋል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ከኮሌጁ አስተዳደር እና ቦርድ ጋራ ከስምምነት ላይ እንዲደርሱ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የነገረ መለኮት ምሩቃን ማኅበር እና ደቀ መዛሙርቱ አቤቱታቸውን ካቀረቡላቸው የውጭ አካላት አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ናቸው፡፡

November 24, 2010

መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎቹ አድማቸውን ካላቆሙ ይባረራሉ አለ

 (በምዕራፍ ብርሃኔ፤ የሪፖርተር ጋዜጣ የኖቬምበር 24/2010 እትም):- የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ከህዳር 8 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ የምግብና የትምህርት አድማ የመቱ ከመቶ በላይ የሆኑ ተማሪዎችን (ደቀመዛሙርት) ወደ ትምህርት ገበታቸው የማይመለሱና ከሆነና የኮሌጁን ምግብ የማይመገቡ ከሆነ፣ የኮሌጁን ንብረት አስረክበው ክሊራንስ በማስፈረም የትምህርት ተቋሙን በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ ከትናንት በስቲያ አስታወቀ፡፡

November 20, 2010

ቤትህን አስተካክል


 "ሕዝቤ ሰንፈዋልና አላወቁኝም፤…። 
ማስተዋልም የላቸውም፤ ክፉ ነገርን ለማድረግ ብልሃተኞች ናቸው በጎ ነገርን ማድረግ ግን አያውቁም።" (ኤር.፬፡፳፪)
             
(አብርሃም ሰሎሞን)
በእጅህ ያኖርኩትን የብርሃን ፀዳል መቅረዙን
              ከስፍራው መጥቼ ሳልወስደው፣
ከዝናም በኋላ ደመናት ሳይሸሹ ፀሐይ
          ሳትጨልም ቀኑን ሳልጋርደው፣
ከማሳው ያለውን ፍሬ አልባ ዘርህን ማለዳ
       መጥቼ ከእርሻው ላይ ሳልነቅለው፣
የሰጠሁህን ሀብት ከመዳፍ ከጉያህ በአንድ
 ጀምበር እድሜ አውጥቼ ሳልጥለው፣
እፍ ያልኩበትን ነፍስ ከውስጥህ ለይቼ
          ወደነበረበት ስፍራ ሳልመልሰው፣
አእምሮ አለህና ነቅተህ ተዘጋጅተህ አደራህን
                ፈጽም አስተውል አንተ ሰው።

November 19, 2010

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጁ ደቀ መዛሙርት የምግብ ቤቱ ሐላፊ እንዲነሡላቸው ጠየቁ

(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 19/2010፤ ኅዳር 10/2003 ዓ.ም)የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት በምግብ አቅርቦት ጥራት፣ በጤና አገልግሎት ሽፋን፣ በሥርዐተ ትምህርት ጫና እና የደቀ መዛሙርት መማክርት መቋቋምን አስመልክቶ ለተቋሙ አስተዳደር ያነሷቸው ጥያቄዎች፣ “ወቅታዊ ምላሽ እና ተገቢ ትኩረት አልተሰጣቸውም” በሚል ከትናንት አንሥቶ በካፊቴሪያው ባለመመገብ እና ትምህርት በማቋረጥ የጀመሩትን ተቃውሞ ቀጥለው ውለዋል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ዛሬ ጠዋት የበላይ ሐላፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ እና ሌሎች የኮሌጁ አስተዳደር ሐላፊዎች በተገኙበት በተነሡት ጥያቄዎች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸው ተዘግቧል፡፡

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት ለተቋሙ አስተዳደር የተለያዩ ጥያቄዎችን አቀረቡ


 • ‹‹60 ተማሪዎች ከምግብ ጋራ በተያያዘ የጤና ችግር ገጥሟቸዋል›› ተብሏል፤ 
 • ለኮሌጁ ዲግሪ እና ዲፕሎማ ዕውቅና የማይሰጡ ተቋማት አሉ፤
 • የኮሌጁ ቦርድ እና አስተዳደር ለተማሪዎች መማክርት ም/ቤት መቋቋም ፈቃድ ለመስጠት ተስኖታል፤
 • ደቀ መዛሙርቱ ያቀረቡትን ጥያቄ በመጠቀም “የራሳቸውን ዓላማ ለማስፈጸም የሚሹ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ” እንደሚገባ ተገልጧል፤
(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 16/2010፤ ኅዳር 7/2003 ዓ.ም) የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት ከምግብ ጥራት፣ ከጤና እክል እና ከሚያገኙት የሕክምና ደረጃ፣ ከሥርዐተ ትምህርት ተገቢነት እና ከተማሪዎች መማክርት መቋቋም ጋራ በተያያዘ በኮሌጁ አስተዳደር ‹‹በአስቸኳይ ሊስተካከሉ ይገባሉ›› ባሏቸው ችግሮች ዙሪያ ተቃውሞ አንሥተዋል፡፡

November 17, 2010

የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ቤተ ክህነቱ ላለበት የአሠራር ብልሹነት ማሳያ ሆነ

 • የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር የሀገረ ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ አስጠነቀቀ
(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 16/2010፤ ኅዳር 7/2003 ዓ.ም) የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ለቤተ ክርስቲያኒቱ ልማት መሰናከል እና ለገጽታዋ መበላሸት ዕንቅፋት ሆኖ የሚገኘውን የቤተ ዘመድ አስተዳደር፣ ሙስና እና የሥነ ምግባር ብልሽት በአስቸኳይ እንዲያስተካክል አስጠነቀቀ፡፡ ‹‹ኅብረተሰቡ በሀገረ ስብከቱ ላይ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ምክር ቤቱን እስከ መጠየቅ ደርሷል›› ያለው ጽ/ቤቱ “ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ” እስከ መባል የደረሰው የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት አስተዳደር በአፋጣኝ ይሻሻል ዘንድ የሀገረ ስብከቱ ሠራተኞች የሚፈጥሩት ጫና እና የኅብረተሰቡ ቁጣ እየተጠናከረ መምጣቱን ለሊቀ ጳጳሱ አስረድቷቸዋል፡፡ ችግሮቹ በምክክር የማይፈቱ ከሆነ ለሕዝቡ ምሬት ምላሽ ለመስጠት ጉዳዩ በሕግ አግባብ የሚታይ ይሆናል ብሏል አስተዳደሩ፡፡

November 16, 2010

አ.አ ዩኒቨርሲቲ መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስን ዘከረ

 • የመጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስ ፋውንዴሽን›› እንዲቋቋም ተጠይቋል
 •  ዝክሩ ለቤተ ክህነቱ ነቀፌታ(ተግሣጽ) ሆኖታል
 •  መጋቤ ምስጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ በዝክሩ ላይ ስለ መጋቤ ብሉይ ሰይፈ  አሟሟት የሰጡት እና ቤተ ክህነቱን የተቹበት ቅኔ ታዳሚዎችን አነጋግሯል
 • ዩኒቨርስቲው ዕውቀታቸው ለሀገር እና ለትውልድ የሚተርፉ ሌሎች ሊቃውንትንም አሥሦ የሚዘክርበት ‹‹አጉሊ መነጽር›› እንዲያደርግ ተጠይቋል
(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 16/2010፤ ኅዳር 7/2003 ዓ.ም)የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሊቃውንት ጉባኤ መምሪያ ሐላፊ ለነበሩት እና ነሐሴ አንድ ቀን 2002 ዓ.ም መንሥኤው ባልታወቀ ድንገተኛ ዕረፍት ከዚህ ዓለም በሞት ለተለዩት ለሊቁ መጋቤ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስ የመታሰቢያ መርሐ ግብር አካሄደ፡፡

November 15, 2010

በዱባይ ሻርጃ ለአንድ ወር የሚዘልቅ የስብከተ ወንጌል ጉባኤ ሊካሄድ ነው

 • በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የሊባኖስ እና አካባቢው አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲሜጥሮስ አህጉረ ስብከታቸውን እያወኩ በሚገኙት ሕገወጦች  ላይ ርምጃ እንዲወሰድ ቋሚ ሲኖዶሱን በደብዳቤ ጠይቀዋል፡፡ 
 • ከሕገ ወጦቹ አንዱ የሆነው እና በአገር ውስጥ በስም ማጥፋት ወንጀል ክስ የተመሠረተበት በጋሻው ደሳለኝ ነገ ወደ ሥፍራው ይጓዛል፤
 • "የዱባይ ቅዱስ ሚካኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን"  በሚል ጉባኤ ለማካሄድ የተዘጋጁት አካላት ሕገ ወጥ መሆናቸው ተገልጧል፤
(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 14/2010፤ ኅዳር 5/2003 ዓ.ም)በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የሊባኖስ እና አካባቢው አህጉረ ስብከት ሥር በሚተዳደረው በዱባይ - ሻርጃ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ለአንድ ወር የሚዘልቅ የስብከተ ወንጌል ጉባኤ ተዘጋጀ፡፡ የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳደር የስብከተ ወንጌል ጉባኤውን ለማስተዋወቅ ‹‹ሕዝቤ ሆይ ወደ ቤትህ ግባ›› በሚለው የነቢዩ ኢሳይያስ መሪ ቃል ባወጣው ፖስተር ላይ እንደተገለጸው፣ ጉባኤው የሚካሄደው በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲሜጥሮስ ተባርኮ ወደ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የገባው የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ታቦት ኅዳር 12 ቀን 2003 ዓ.ም ከመንበረ ክብሩ ወጥቶ የሚደረገውን ክብረ በዓል መሠረት አድርጎ ነው፡፡

November 14, 2010

ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ወደ አሜሪካ ሄዱ

ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል
(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 13/2010፤ ኀዳር 4/2003 ዓ.ም)በጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዲን ሆነው የተመደቡት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ዛሬ ኅዳር 4/ 2003 .ም በዲሲና አካባቢው አቆጣጠር ከጠዋቱ 3 ሰዓት (9:00 AM) ዋሽንግተን ዲሲ  መግባታቸው ታወቀ:: ዳላስ ለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የደብረ ምረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ እና ጥቂት ምእመናን በቦታው በመገኘት አቀባበል ተደርጎላቸዋል:: የብፁዕነታቸው ወደ ዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት መሄድ ሀገረ ስብከቱ እውቅና ይኑረው አይኑረው ለጊዜው ባይታወቅም፤ በአቀባበል ሥነ ርዓ ላይ ግን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብሃም አልነበሩም::

November 13, 2010

በሐዋሳ ለብፁዕ አቡነ ገብርኤል ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

 • ከ20 በላይ መኪኖች እና ሰባት ሞተረኞች ጥቁር ውኃ ላይ ተሰልፈው  ተቀብለዋቸዋል፤ ፓትርያርኩ አልተገኙም፡፡
 • ብፁዕነታቸው፣ ‹‹ውበት የሚኖረው በአንድነት ውስጥ በመሆኑ በኅብረት   አንድ ሆነን መገኘት ያስፈልገናል፤›› በማለት መክረዋል፡፡ 
 • ጥቂት ቲፎዞዎች ጥቁር ጨርቅ ሲያውለበልቡ ታይተዋል
 • እነ ያሬድ አደመ የተለቀቁት፣ ‹‹ዐቃቤ ሕግ የምርመራ ሂደቱን ከጊዜ ቀጠሮው  በፊት ማጠናቀቁን ሪፖርት በማቅረቡ የዋስ መብት ተጠብቆላቸው ነው›› ተብሏል፡፡
(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 13/2010፤ ኀዳር 4/2003 ዓ.ም)በጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የሲዳማ፣ አማሮ እና ቡርጂ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው የተመደቡት ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ዛሬ ረፋድ ላይ ሐዋሳ ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ ሊቀ ጳጳሱን ለመቀበል ከሀገረ ስብከቱ፣ ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን እና ከምእመናን ተውጣጥቶ የተቋቋመው 40 አባላት እና ልዩ ልዩ ዘርፎች ባሉት የአቀባበል ኮሚቴ፣ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ከብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል፣ ብፁዕ አቡነ ያሬድ እና ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ጋራ በሐዋሳ ከተማ መግቢያ - ጥቁር ውኃ አምስት ሰዓት ግድም ሲደርሱ በበጎ ፈቃድ በተሰለፉ ከኻያ በላይ መኪኖች እና ሰባት ሞተር ሳይክሎች በማጀብ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

በሐዋሳ ቅ/ገብርኤል ውስጥ ብጥብጥ የፈጠሩት ተፈቱ


(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 12/2010፤ ኀዳር 3/2003 ዓ.ም) እሑድ ጥቅምት 28 ቀን 2003 ዓ.ም በሐዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በተፈጠረው ዐምባጓሮ በሕጋዊ የገዳሙ ሰንበት ት/ቤት አባላት ላይ ከፍተኛ የድብደባ ጉዳት በማድረሳቸው ተከሰው የተያዙት ያሬድ አደመ እና ዓለምነህ ሽጉጤን ጨምሮ 11 ያህል ሰዎች ዛሬ ተፈቱ።

November 12, 2010

To Deje Selam: What Should We do?

To:    dejeselam@gmail.com       
(By Tewahedo)
Peace for All of You in The name Of Jesus Christ the Savior!
I agree and support DSs report about the abuse and disagreements in church but this is not the way to solve the problems of the church. If we want to solve the problems once and for all we need other mechanism. Shall we let DS and other Medias continue on the reporting this chaos’s, frustrations and divisions among Christians?

November 11, 2010

የሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ ሹመት እያነጋገረ ነው


ሊ/ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ
 • ‹‹በቅዱስ ሲኖዶስ ጥፋተኛ የተባለን ሰው ሹመት መስጠት ብቻ  ሳይሆን በሥራ መመደብ ስሕተት ነው፡፡››   (የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ተቃውሞ) 
 • በአስተዳደር እና አቅም ግንባታ መምሪያ ቦታ አዲስ ሹመት ተሰጥቷል
(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 11/2010፤ ኀዳር 2/2003 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን በተመለከተ በቅዱስ ሲኖዶስ የተሠየመው አጣሪ ኮሚቴ ለጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ባቀረበው ሪፖርት እንዲሁም በ29ው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ስብሰባ ላይ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሪፖርት ውስጥ ተካትቶ በቀረበው የቁጥጥር አገልግሎት ሪፖርት ቃለ ዓዋዲውን ተከትሎ ከመሥራት እና መልካም አስተዳደርን ከማስፈን አኳያ በተገኘባቸው ከፍተኛ ግድፈት የተነሣ ከሥራ አስኪያጅነት ሐላፊነታቸው እንዲወገዱ፣ የፈጸሟቸው በደሎች ሁሉ ተጣርቶ በሕግ እንዲጠየቁ የተወሰነባቸው ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ማዕርግ የልማት ጉዳዮች ዘርፍ ሥራ አስኪያጅ ሆነው መሾማቸው ጥያቄዎችን እያስነሣ ይገኛል፤ በቤተ ክርስቲያኒቱ ወቅታዊ ችግሮች ዙሪያ በምእመኑ ዘንድ አንድ አቋም እና ግንዛቤ እየተፈጠረ የመጣበትን አትኩሮት ለማስቀየስ የሚደረግ ጥረት አካል ተደርጎም ተወስዷል፡፡

November 10, 2010

ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ከኦስትርያ መልስ


ርእሰ ዜና
 • ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ በጠቅላይ ቤተ ክህነት የልማት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ተሾሙ፡፡ ቀደም ሲል ሊቀ ማእምራን ፋንታሁንን በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የአስተዳደር እና አቅም ግንባታ መምሪያ ሐላፊነት ለመመደብ በፓትርያርኩ ቀርቦ የነበረው ሐሳብ በዋና ሥራ አስኪያጁ በገጠመው ብርቱ ተቃውሞ ውድቅ እንደተደረገ ተገልጧል፡፡
 • የአስተዳደር እና አቅም ግንባታ መምሪያ ሐላፊ የነበሩት አቶ ደሳለኝ መኰንን ከሐላፊነታቸው በራሳቸው ፈቃድ ለቀዋል፤ ምክንያቱ ‹‹የተሻለ ሥራ እና ደመወዝ በማግኘታቸው ነው›› ተብሏል፡፡ (ዝርዝሩን እንመለስበታን)

በሐዋሳ ቅ/ገብርኤል ውስጥ ብጥብጥ የፈጠሩ ፍርድ ቤት ቀረቡ

 • ያሬድ አደመ እና ዓለምነህ ሽጉጤ አሉበት፤
(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 10/2010፤ ኀዳር 1/2003 ዓ.ም)እሑድ ጥቅምት 28 ቀን 2003 ዓ.ም በሐዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በተፈጠረው ዐምባጓሮ በሕጋዊ የገዳሙ ሰንበት ት/ቤት አባላት ላይ ከፍተኛ የድብደባ ጉዳት ያደረሱት ያሬድ አደመ እና ዓለምነህ ሽጉጤን ጨምሮ 11 ያህል ሰዎች በትናንትናው ዕለት ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ በተጎጂ ቤተሰቦች በተመሠረተው ክስ ፖሊስ ሀገረ ስብከቱን በማወክ እና የክልሉን ሰላም በማደፍረስ ሁከት በፈጠሩት ግለሰቦች ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማሰባሰብ እና ቀሪ ሁከተኞችን ለማደን የጠየቀው ዘጠኝ ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ጥያቄ የፍርድ ቤቱን ይሁንታ አግኝቷል፡፡ ከሁከቱ በኋላ እሑድ ዕለት ረፋድ ላይ ወደ አዲስ አበባ ለመሔድ ሲዘጋጅ የተያዘውን ያሬድ አደመን፤ አባቶችን፣ የሐዋሳ የፍትሕ እና ልማት ኮሚቴ አባላትን እና ማኅበረ ቅዱሳንን በስም እየለየ የሚያክፋፋ የቅስቀሳ ወረቀት ሲበትን በማግስቱ ሰኞ የተያዘውን ዓለምነህ ሽጉጤን ለማስመለቀቅ ጓደኞቻቸው በየአቅጣጫው የሚያደርጉትን ጥረት ቀጥለውበታል፡፡

November 8, 2010

በሐዋሳ ቅ/ገብርኤል ትናንት በተከሰተ ብጥብጥ ጉዳት ደረሰ፤ አዋኪዎቹ በፖሊስ ተይዘዋል

 •  ሁከቱ ሊቀ ጳጳሱ ወደተመደቡበት ሀገረ ስብከት እንዳይመጡ ለማሣቀቅ እና አዲሱ ሥራ አስኪያጅ ችግር መፍታት እንደተሳናቸው ለማሳየት ጀምበር በጠለቀችባቸው በእነ ያሬድ   አደመ የታለመ ነው፤
 • ‹‹በሁከቱ ስለት፣ ዱላ እና ድንጋይ የተጠቀሙት ወሮበሎቹ ባደረሱት ድብደባ ከአምስት ያላነሱ የሰንበት ት/ቤት አባላት እና ፖሊሶች ተጎድተዋል፤ አንዱ ወጣት ጆሮው የተቆረጠ  ሲሆን በጭንቅላቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ሌላው ወጣት ደግሞ ራሱን ስቶ በጉሉኮስ እየተረዳ ይገኛል፡፡›› (የሆስፒታል ምንጮች)
 • ፖሊስ ከያሬድ እና ዓለምነህ ሽጉጤ በተጨማሪ በሁከቱ የተሳተፉ ሰባት ቀንደኛ ግለሰቦችን  በቁጥጥር ሥር አውሏል፤
 • ፓትርያሪኩ፣ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ እና በጋሻው ደሳለኝ ሁከተኞቹን ለማስለቀቅ ጥረት  እያደረጉ ነው፤
 • የሐዋሳ የአገር ሽማግሌዎች ዛሬ የክልሉን ርእሰ መስተዳድር እንደሚያነጋግሩ ይጠበቃል
 •  በመጪው ቅዳሜ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ወደ ሐዋሳ እንደሚመጡ በአዲሱ ሥራ አስኪያጅ ሲነገራቸው ያጉረመረሙት ‹‹የተስፋ ኪዳነ ምሕረት›› አባላት የሊቀ ጳጳሱ ወደ ሀገረ ስብከቱ  መምጣት እንደሚያስከፋቸው በአዎንታ አረጋግጠዋል
 • ‹‹እነያሬድ አደመ ተከልክለው ማንም አራት ጎማ ያመጣው ሁሉ በዚህ መድረክ ላይ አያዝበትም፡፡››

ሐውልቱ እንዲፈርስ ከተወሰነ 10 ቀን አለፈው፤ የብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ‹‹የመታሰቢያ ሐውልት›› ተመረቀ

 •  "ከ30 ምእመናን 26ቱ ሐውልቱ እንዲወገድ የተላለፈውን ውሳኔ እና ሐውልት ማቆም በቀኖና ቤተ ክርስቲያን እንደሚከለከል ያውቃሉ፡፡›› (ካፒታል ጋዜጣ ያሰባሰበው የሕዝብ አስተያየት)
 •   ፓትርያርኩ የሲኖዶሱ ምልአተ ጉባኤ ከወሰነባቸው ቃለ ጉባኤዎች አራቱን እስከ አሁን ለጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ አልመሩም፤
(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 8/2010፤ ጥቅምት 29/ 2003 ዓ.ም) - ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን እና ከሥርዐተ አበው በተፃራሪ እንዲሁም በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ውሳኔ ሳይደገፍ የተተከለው የአቡነ ጳውሎስ ሐውልተ ስምዕ እንዲነሣ እና በየአብያተ ክርስቲያኑ የተሰቀሉት ቢልቦርዶች እንዲሰበሰቡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የሰጠው ትእዛዝ ከዐሥር ቀናት በላይ አስቆጥሯል፡፡

November 7, 2010

No anonymity any more?

(Deje Selam; November 7/2010): We came across wonderful concept posted about our blogging world: the issue of being anonymous while writing and commenting, by a bloger called "Mahlet Zesolomon".

To show a solidarity with our fellow blogger Mahlet, we started our Deje Selamaweyan "to be registered and have names" before commenting and No anonymity any more. Read her article below and also visit her blog and leave your comments there.

November 5, 2010

በጋሻው ደሳለኝ ፍርድ ቤት ቀረበ


 • ‹‹አዎ፣ ተሳድቤያለሁ፤ ወደፊትም እቀጥላለሁ›› (በጋሻው ደሳለኝ
 • 500 ብር ዋስትና አስይዟል፤ ለብይን ለኅዳር 23 ቀን እንዲቀርብ ታዟል
 • ‹‹ኀይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶችህ ዋሹብህ›› (ጥቂት ቲፎዞዎቹ የለበሱት ቲ-ሸርት)
 (ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 5/2010፤ ጥቅምት 26/2003 ዓ.ም)በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የድሬዳዋ ማእከል የስም ማጥፋት ወንጀል ክስ የቀረበበት በጋሻው ደሳለኝ ዛሬ በድሬዳዋ ካውንስል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡ ዛሬ ጠዋት በተሠየመው ችሎት በተከሰሰበት የስም ማጥፋት ወንጀል ጉዳይ የእምነት ክሕደት ቃሉን የተጠየቀው በጋሻው የተከሰሰበትን የንግግር ቃል መናገሩን አምኗል፡፡

Patriarch Paulos Statue and its Catholic origin: A Rejoinder to Dilwenebru's Article

(Addisu Tesfaye):- I read Dilwonberu's article, posted on Deje Selam, which was written with the intent of defending the patriarch Paulos statue. Anyone who reads the article could understand the implicit and explicit message Dilwenberu tried to convey. Explicitly, he has expressed the contempt he has for the Holy Synod for passing the resolution to demolish the statue of patriarch Paulos.

ዋኖቻችሁን አስቡ (ዕብ ፲፫፥ ፯)

ቀሲስ መብራቱ (ከፌስቡክ የተወሰደ)
(ቀሲስ መብራቱ ኪሮስ (ቶሮንቶ : ካናዳ):- ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለዕብራውያን በጻፈው መልእክት በ11ኛው ምዕራፍ አካሄዳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር ያደረጉ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳንን የእምነት ተጋድሎ በአጭሩ ይተርካል። ስለ ሁሉም “እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛል”  ካለ በኋላም እነዚህ ታላላቅ የእምነት ምስክሮች በእምነት መንግሥታትን ድል እንደነሱ፣ የአንበሶችን አፍ እንደዘጉ፣ የእሳትን ኃይል እንዳጠፉ፣ በእስራትና በወኅኒ እንደተፈተኑ እንዲሁም ይህች ዓለም ለእነርሱ ስላልተገባች የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው በዋሻና በምድር ጉድጓድ ውስጥ እንደኖሩ ይነግረናል።

November 4, 2010

ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ ወደ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ቅጽር ግቢ እንዳይገቡ የተጣለባቸው እገዳ እየተከበረ አይደለም

ወ/ሮዋ በሐውልቱ ምረቃ ዕለት ንግግር ሲያደርጉ
 • ወይዘሮዋ ‹‹ሲኖዶሱ በእኛ ገንዘብ ምን አገባው?›› በሚል የምልአተ ጉባኤውን ውሳኔ አፈጻጸም በመቃወም ተግባራዊነቱን የሚያደናቅፍ ቡድን አደራጅተው ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው፤
 • በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ላይ ጠንካራ ትችት የሰነዘሩባቸውን ብፁዓን አባቶች እየደወሉ በመሳደብ እየዛቱባቸው ነው፤
 • ያሬድ አደመ ‹‹በደረቅ ቼክ ማጭበርበር››፣ በጋሻው ደሳለኝ ‹‹በስም ማጥፋት››  ወንጀሎች ተከሰዋል፤
(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 4/2010፤ ጥቅምት 25/2003 ዓ.ም)ጥቅምት 25 ቀን 2003 ዓ.ም፤ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የዋና ሥራ አስኪያጁ ጽ/ቤት የአቡነ ጳውሎስን ‹‹ሐውልተ ስምዕ›› በኻያ ቀናት ውስጥ ከቦታው በማንሣት እና በየአብያተ ክርስቲያኑ የተሰቀሉትን የፓትርያርኩን ቢልቦርዶች በመሰብሰብ በመንበረ ፓትርያርኩ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር ውስጥ እንዲያስቀምጥ ያስተላለፈው ውሳኔ አንድ ሳምንት ያህል ሆኖታል፡፡ ለውሳኔው አፈጻጸም የዋና ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ጽ/ቤት በቁርጠኛነት እየተንቀሳቀሰ ስለመሆኑ ጠርጣሪዎች በርካታ ጥያቄዎችን እያነሡ ይገኛሉ፡፡

ጀርመን ሬዲዮ (DW) & አሜሪካ ድምጽ (VOA) ሪፖርታዥ

November 2, 2010

ለድል ወንበሩ እና ለመሰሎቹ

(አብርሃም ሰሎሞን እንደጻፈው):- መጠነ ሰፊ የሆነ ማብራሪያ ለመስጠት የሞከረው ድል ወንበሩ ስለ ሐውልቱ በተቀኘው የእንግሊዝኛ ቅኔ ኃይለሥላሴን እና ሌሎች ነገሥታትን፣ አቡነ ቴዎፍሎስን እና መንግሥቱ ኃይለማርያምን፣ ከዚያም ወጣ ብሎ የግብፁን ፓትርያርክ አቡነ ሺኖዳን በመጥቀስ በተለያየ ጊዜ የተሠራላቸውን ስዕላትና ሐውልት ካየውም ከሰማውም እንዲሁም ከጉግል ውስጥ ገብቶ ከጎለጎለው ማስረጃ በመነሣት እስኪ መልሱልኝ የሚል ጥያቄ አቅርቧል። እንዲያውም የሚያሳምነኝ ካለ እኔም የይፍረስ ስምምነቱን አስተሳሰብ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ ይለናል። አንዳንዶችም በሰጡት አስተያየት የሰማዕቱን የቅዱስ አቡነ ጴጥሮስን ሐውልት ስንቀበል እንዴት የአቡነ ጳውሎስን ሐውልት ለመቀበል ልባችንን እናከብዳለን?

የአንባብያን አስተያየት


How come what is acceptable to ECC is unacceptable to EOTC?

Dear Deje Selamaweyan,
Here is a Tigrai Online article by a certain Dilwenberu Nega defending the Patriarch Paulos Statue, criticizing the Holy Synod that it decided the demolition of the statue. Taking the identity of the writer and the way he presented the religious agenda, our Church problem might twisted to an unnecessary line beyond the scope of the Church. People who are not related to the Church who created the problem started to make their ideologies Orthodox and travel all the way to Egyptian desert to substantiate their motives.
Deje Selam
 ++++++
By Dilwenberu Nega (Oct. 31 2010)
(Tigrai Online):- Over the last week a confraternity of scare-mongerers were in a state of frenzy, following reports that the gaggle of 'Princes of the Church' who make up EOTC's Governing Body, The Holy Synod, has decided to demolition Patriarch Paulos's monument which stands outside the precinct of the Church of Medehanealem in Bole, as well as, the removal from church compounds of Millennum billboards showing the Patriarch in deep prayer mode.

November 1, 2010

አቡነ ጳውሎስ ‹‹የሐውልት ፍለጋ›› ዑደት ጀምረዋል

 • ትናንት የደብር ቅዱስ ደብረ ጽጌ ማርያም ገዳምን ጎብኝተዋል፤
 • በዚህ ሳምንት ውስጥ ከግብጽ ገዳማት ወደ አንዱ ለማምራት እየተዘጋጁ ነው፤
(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 1/2010፤ ጥቅምት 22/2003 ዓ.ም) ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ትናንት ጥቅምት 21 ቀን 2003 ዓ.ም በዋለው እሑድ ሰንበት በሰሜን ምዕራብ ሸዋ - ሰላሌ ሀገረ ስብከት የምትገኘዋን የደብር ቅዱስ ደብረ ጽጌ ማርያም ገዳምን ጎበኙ፡፡ የሥሪቷ ጥንታዊነት እስከ መካከለኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ ወደኋላ በሚቆጠርላት የደብር ቅዱስ ደብረ ጽጌ ማርያም ገዳም አሁን ቆሞ የሚታየው ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን የተሠራው በኢትዮጵያዊው ቀዳማዊ ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ዘመን በ1952 ዓ.ም ነው፡፡ በገዳሟ ቤተ መቅደስ ውስጥ ያለውን በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ መልክእ የተቀረጸውን ምስል የጎበኙት ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ምስሉ ፎቶ ግራፍ እንዲነሣ ማዘዛቸውን፣ በቃላቸውም ትእዛዝ መሠረት ምስሉ ፎቶ ግራፍ መነሣቱ ተዘግቧል፡፡

ብፁዕ አቡነ ገብርኤል የሐዋሳ ሊቀ ጳጳስ እንዲሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነውን የዝውውር ውሳኔ የሚቃወም አድማ እየተካሄደ ነው

 • አድማውንያስተባበሩት በጋሻው ደሳለኝ እና ምርትነሽ ጥላሁን ናቸው
 • አድማውን በመጠቀም ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ እና በጋሻው ደሳለኝ ሐውልቱ እንዲነሣ ቅዱስ ሲኖዶስ ያስተላለፈው ውሳኔ ተፈጻሚነት እንዳያገኝ የሚጠይቅ የአቤቱታ ፊርማ እያሰባሰቡ ነው
 • የእነ ያሬድ አደመ የዐመፅ ጎራ በተወሰደው አቋም ላይ መከፋፈሉ እየተነገረ ነው
 • መንግሥት የማያባራው የዐመፅ ድራማ እንዲያበቃ ተጠይቋል
 ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 31/2010፤ ጥቅምት 22/2003 ዓ.ም)‹‹የአጣሪ ኮሚቴው ሪፖርት ሳይሰማ ቅዱስ ሲኖዶስ አቡነ ፋኑኤል ከሲዳማ አማሮ እና ቡርጂ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጵጵስና እንዲነሡ እና ብፁዕ አቡነ ገብርኤል እንዲመደቡ የወሰነውን ዝውውር እንቃወማለን”  በሚል ከሐዋሳ፣ ዲላ እና ይርጋዓለም ከተሞች የተውጣጡ ናቸው የተባሉ ተቃዋሚዎች አዲስ አበባ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ደርሰው ተመልሰዋል፡፡

የኅትመት ብዙኀን መገናኛዎች ለሰሞናዊው የቅዱስ ሲኖዶስ እና አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ስብሰባ የሰጡት ሽፋን

(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 31/2010፤ ጥቅምት 21/2003 ዓ.ም)ካጋመስነው የጥቅምት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ጀምሮ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተካሄደው 29ው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ እና ቅዳሜ በተጠናቀቀው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ላይ ያተኮሩ ዘገባዎች በአገር ውስጥ በሥራ ላይ የሚገኙ ጋዜጦች እና መጽሔቶች ግንባር ቀደም ሽፋን እያገኙ ነው፡፡

Abune Paulos should be stopped


 “…The one who stiffens his neck  after numerous rebukes will suddenly be destroyed without remedy…” (Prov 29:1)
 (ደጀ ሰላም፣ Deje Selam)It is undoubted fact that the Ethiopian Orthodox Church is going through a rigorous tribulation. Even though, in its long history, the Church have suffered from both internal and external aggressions; what has been happening at the time of the current Patriarch His Holiness Abune Paulos is completely and absurdly new.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)