October 29, 2010

የቅ/ሲኖዱስ ምልአተ ጉባኤ ጠንካራ ውይይት በስብከተ ወንጌል አገልግሎት ዙሪያ


የዛሬ የቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ ተጨማሪ አርእስተ ዜና
 •  ያጋጠሙ ችግሮችን ለይቶ ለነገ መፍትሔ የሚያቀርብ አምስት አባላት ያሉት ኮሚቴ አቋቋመ
 • በጋሻው ደሳለኝ፣ ሌሎች ሕገ ወጥ ሰባክያን እና ዘማርያን የሚፈጥራቸው ችግሮች ዋነኛው  ርእሰ ጉዳይ ሆኗል፡፡
 • ብፁዓን አባቶች ፓትርያሪኩን እና ለበጋሻው ደሳለኝ የጥፋት ተግባር ተባባሪ ሆነዋል ያሏቸውን ወገኖች ወቅሰዋል በድርጊታቸውም መማረራቸውን ገልጸዋል፡፡     
 • በሰሞኑ አንገብጋቢ አጀንዳዎች በአመዛኙ አርምሞን መርጠው የቆዩት አቡነ እስጢፋኖስ በጋሻው ደሳለኝ ይቅርታ በመጠየቁ፣ ፓትርያሪኩ በተገኙበት ቆሞ በማስተማሩ አገልግሎቱን እንዲቀጥል እንደተፈቀደለት፣ ከዚህ አኳያ አህጉረ ስብከት እርሱን ማገዳቸው ትርጉም እንደሌለው የተናገሩት ንግግር የብፁዓን አባቶችን ጆሮ አስይዟል፡፡ ሊቀ ጳጳሱ   በጉባኤው ላይ ተሸማቅቀው የሰነበቱበት እና ዛሬ አንደበታቸውን የከፈቱበት ሁኔታ በተለይ የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ የበላይ ሐላፊ በሆኑት ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ክፉኛ አስነቅፏቸዋል - ‹‹እርስዎ የሚደግፉበትን ምክንያት ላውጣው  ወይ?››      
 • ብፁዕ አቡነ ሉቃስ በጋሻው በስሙ ያወጣቸው ጽሑፎች፣ ስብከቶች፣ ግጥም እና  ዜማዎች ተመርምረው እንዲቀርቡ ተወሰነ እንጂ እንዲሰብክ ፈቃድ እንዳልተሰጠው አስታውሰዋል፡፡       
 • ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ፓትርያሪኩ በጋሻው በሐውልት ሥራው ለነበረው ተሳትፎ ፈቅደው በሰጡት የምስክር ወረቀት በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዘንድ ተቀባይነት እንዳለው በማስመስል እየነገደበት መሆኑን፣ የብዙኀን መገናኛዎች መረጃ እየጠቀሱ ስለ እርሱ ብዙ መረጃዎችን እያወጡ፣ ምእመናንም ያንን ይዘው ለእኛ እያቀረቡ እየሞገቱን ሳለ እርስዎ የእግዱን ውሳኔ ተፈጻሚነት በመጣስ እያበለሻሹት ነው በማለት አቡነ ጳውሎስን ተችተዋል፡፡
 • በጋሻው ደሳለኝን ጨምሮ በሌሎች ‹‹ሰባክያን እና ዘማርያን›› በስብከተ ወንጌሉ አገልግሎት ላይ እየተፈጠሩ ያሉ ችግሮችን ለውሳኔ ያመች ዘንድ ለይተው ከመፍትሔ  ሐሳብ ጋራ እንዲያቀርቡ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል፣ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ፣ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል እና ብፁዕ አቡነ ሉቃስ የሚገኙበት ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡  
 • የስብከተ ወንጌሉ ስምሪት፣ የሰባክያነ ወንጌሉ እና ዘማርያኑ አገልግሎት ማእከላዊ  መዋቅሩን ጠብቆ እንዲመራ፣ አገልጋዮቹ በቤተ ክርስቲያኒቱ የአገልግሎት መዋቅሮች  ውስጥ ተወስነው የትምህርት ደረጃቸው እንዲመረመር፣ መሠረታዊ ትምህርቱ የሌላቸው ሥልጠናው እንዲሰጣቸው፣ ከመናፍቃን ጋራ በስውር እና በገሃድ በመመሣጠር በአደባባይ/በዐውደ ምሕረት/ ኑፋቄ ያስተማሩ እና ድፍረት የተናገሩ በአደባባይ ይቅርታ እንዲጠይቁ እና ቀኖና እንዲሰጣቸው የሚያስችል ውሳኔ ይተላለፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
 • የካናዳ ሀገረ ስብከት ለሁለት ተከፍሎ ብፁዕ አቡነ ሙሴ በአንዱ እንዲሾሙ ተወስኗል፤
 • ‹‹የካናዳ ሀገረ ስብከት ሰፊ ብቻ ሳይሆን እስከ አሁን እየተሠራበት በቆየው በጽኑዓን  አባቶች፣ ምእመናን እና ወጣቶች ብርታት ጠንካራ ማእከላዊ አስተዳደር፣ ታዋቂ እና ተጽዕኖ ፈጣሪ አስተዳዳሪዎችን የሚሻ በመሆኑ ለጳጳሳቱ ማረፊያ እንኳን ባልተዘጋጀበት  ሁኔታ ለሁለት እንዲከፈል መወሰኑ በአግባቡ ሊጤን ይገባዋል፡፡›› (ታዛቢዎች)
 • በጀትን አስመልክቶ በተደረገው ውይይት በወር ብር 50,000 ለመንበረ ፓትርያሪኩ ቴሌፎን  አገልግሎት እና የጽሕፈት መሣሪያዎች ወጪ፤ በወር ብር 5,000 ለስብከተ ወንጌል ወጪ   መመደቡ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ በ29ው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ስብሰባ ላይ የመምሪያው ሐላፊ ባቀረቡት የሒሳብ ሪፖርት በዘመኑ ከወጪ ቀሪ 480.00 ብር ብቻ በካዝና እንደሚገኝ፣ የበጀት እና የሰው ኀይል እጥረት ዋነኛ ችግሩ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
 • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ከነገሌ ቦረና ወደ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ወሊሶ ተዛውረዋል፤ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል በተጨማሪ ደርበው ይይዛሉ፤
 • የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በነገው ዕለት እንደሚጠናቀቅ እና ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡      
ዝርዝር ዜናዎቹን እንደረሰልን ለማቅረብ እንሞክራለን። ተከታተሉን፡፤ አስተያየታቸውን መስጠታችሁን ቀጥሉ!!!!
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)