October 25, 2010

የቅ/ሲኖዶስ አጀንዳዎች


(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 24/2010፤ ጥቅምት 14/2003 ዓ.ም):- “በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 ድንጋጌ መሠረት ከጥቅምት 12 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ” በመካሔድ ላይ የሚገኘው የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በብፁዕ አቡነ ናትናኤል ሊቀ መንበርነትና በብፁዕ አቡነ ሉቃስ ፀሐፊነት የተወከለው 9 አባላት ያሉት ኮሚቴ አጀንዳዎች ማዘጋጀቱን፣ በዚያም ላይ ሌሎች አጀንዳዎች እንደተጨመሩበት መዘገባችን ይታወሳል። ለመረዳት እንዲያስችለን አጀንዳዎቹን እንደሚከተለው እናቀርባለን።
 1. የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ቃለ ምዕዳን፤
 2. የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን በተመለከተ አጣሪ ኮሚቴው ያቀረበውን ጽሑፍ ማድመጥና መወሰን፤
 3. ስለ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ችግር በቅዱስ ሲኖዶስ በተሰየሙት በሊቃነ ጳጳሳት ተጠንቶ የቀረበውን ጥናት ማዳመጥን መወሰን፤
 4. ሀገረ ስብከት ለሌላቸውና ዝውውር ለጠየቁ ሊቃነ ጳጳሳት ተነጋግሮ መወሰን፤
 5. ማዕከሉን ባልጠበቀ መንገድ ከቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ውጪ በተሠሩና በሚሠሩ ጉዳዮች ላይ ተነጋግሮ መወሰን፤
 6. የኪራይ ቤቶችን አስተዳደር ችግር በተመለከተ ተወያይቶ መወሰን፤
 7. የልማት ኮሚሽንን ችግር በተመለከተ ተነጋግሮ መወሰን፤
 8. ስለ አብነት ት/ቤቶች እና ስብከተ ወንጌል ተነጋግሮ መወሰን፤
 9. የትምህርት ተቅዋማትን ሁኔታ በተመለከተ ተነጋግሮ መወሰን፤
 10. ከቅድሰት ሀገር ኢየሩሳሌም የሚቀርበውን ጉዳይ ተወያይቶ መወሰን፤
 11. በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት መኖሪያ ቤት ጄኔሬተር እንዲገባ ተወያይቶ መወሰን፤
 12. ከየአህጉረ ስብከቱ በጽሑፍ የሚቀርቡ ችግሮችን መስማት፤
 13. የሰበካ ጉባዔ ዓመታዊ ሪፖርትን ተወያይቶ ማጽደቅ፤
 14. የደመወዝ እስኬል ማስተካከልን ተነጋግሮ ስለመወሰን፤
 15. ዓመታዊ በጀትን ተነጋግሮ ስለመወሰን፤
 16. የቋሚ ሲኖዶስ አባላት በመመሪያው መሠረት ምርጫ ተወያይቶ መወሰን ናቸው።

የአጀንዳ አዘጋጅ ኮሚቴው አባላት ብፁዕ አቡነ ናትናኤል (ሊቀ መንበር)፣ ብፁዕ አቡነ ማትያስ፣ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል፣ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ፣ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ፣ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ፣ ብፁዕ አቡነሚካኤል፣ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ እና ብፁዕ አቡነ ሉቃስ (ጸሐፊ) ናቸው።
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)