October 29, 2010

የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ተግባራዊነትና ሊገጥሙት የሚችሉት ፈተናዎች


(ከወልደ መንክር):- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ቅዱስ ሲኖዶስ በርካታ አሳሳቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጎ ውሳኔ በማስተላለፍ ላይ ይገኛል ። ይህ ጉባኤ ዛሬ ጥቅምት 19 ወይም ነገ  ጥቅምት 20 2003 ዓ. ም ሊጠናቀቅ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል። በቦሌ የተተከለውን  የአቡነ ጳውሎስን ሐውልት በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ ውይይት አድርጎ ውሳኔ ማስተላለፉ በተለያየ ቦታ የሚገኙ በቤተ ክርስቲያን ልጆች ዘንድ ከፍተኛ  ደስታ ፈጥሯል ። የቅዱስ ሲኖዶስ የስብሰባ አካሄድ ከዚህ በፊት ከነበረው ሁኔታ አንጻር ሰፊ ትንታኔ ሊሰጥበት ቢችልም ለአሁኑ ግን "የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ተግባራዊ  የሚሆነው እንዴት ነው፣ ከዚህ በፊት ከነበረው ተሞክሮ አንጻር ምን ልንጠብቅ ይገባናል፣ የምእመናንና የካህናትስ ሱታፌ በዚህ ወሳኝ ወቅት ምን መሆን አለበት?" የሚለውን መመልከት ተገቢ ነው።

ቅዱስ ሲኖዶስ  በቦሌ የተተከለው የአቡነ ጳውሎስ ሐውልት እና በ15 በማያንሱ አብያተ ክርስቲያናት የተተከለው  ፎቶግራፋቸው እንዲነሣ ወስኗል። አፈጻጸሙ ግን  በጉባኤ እንደተወሰነው ቀላል አይደለም። ከዚህ በፊት በነበራቸው ተሞክሮ እና የገነነውን የፓትርያርኩ የበላይነት ለጊዜው ማሸነፍ ችለው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት  ደፍረው መናገራቸውና በአንድ አቋም መወሰናቸው ጉባኤው  እየጠነከረ መምራቱን አሳይቷል።  ሐውልቱን ለማፍረስ የተደረሰውን ውሳኔ ምን ችግር ሊገጥመው እንደሚችልና የእኛ ድርሻ ምን መምሰል እንዳለበት በቅደም ተከተል ለመመልከት እንሞክር። 

1ኛ. የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ በቃለ ጉባኤው በትክክል መቀመጡ፤
በቅዱስ ሲኖዶስ  የቃለ ጉባኤ አቀማመጥ ታሪክ መመልከት እንደሚቻለው በስብሰባ የተለያዩ  ጉዳዮች ውይይት ከተደረገ በኋላ ቃለ ጉባኤ እንዲያዘጋጁ በተመረጡ ሰዎች ይዘጋጅና ይቀርባል። ረቂቁ ሀሳብ ለጉባኤው ከመነበቡ በፊት ፓትርያርኩ  በተደጋጋሚ ቀረቤታ ባላቸው ሰዎች አቅራቢነት  በግል ተነቦላቸው  የቃላት ምርጫ እና የማይፈለጉ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎችን  ለማደብዘዝ ተሞክሮ  ከሚፈጸም ይልቅ ወደማይፈጸምበት ወይም ወደሚዘገይበት ደረጃ  ለማድረስ  ከፍተኛ ሙከራ ይደረጋል። በጉባኤውም ከተነበበ በኋላ አንዳንድ ቃላት ተጨምረው እንዲፈርሙ ይቀርብላቸዋል። ብዙ ጊዜ   የሚፈርሙት በግል እየመጣላቸው እንጂ በጋራ በተነበበላቸው በአንድ ላይ ስላልሆነ ፓትርያርኩ እስከ መጨረሻው ደቂቃ ሳይደክሙ በመሥራት የሚፈልጉትን ሁሉ በአንድም ሆነ በሌላ ለማካተት እድል ያገኛሉ።

ቅ/ፓትርያርኩ በየቤ/ኑ ካሰቀሏቸው ግዙፍ ሥዕሎች አንዱ
ከዚህ በፊት በቤተ ክርስቲያኒቱ የአስተዳደር በደል ደረሰ ተብሎ አቡነ ጳውሎስን ተጠያቂ የሚያደርጉ ከ5 የማያንሱ ጊዜያት በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ  ከዚህ በፊት ተወስነው ነበር። ነገር ግን ከላይ በጠቀስነው  ስልት ተረስተው እንዲቀሩ ተደርጓል። ለምሳሌ  በቤተ ክርስቲያኒቱ እየተፈጸመ ያለውን የአስተዳደር በደል እንዲመረምርና መፍትሔ እንዲፈልግ  ተቋቁሞ የነበረው አጣሪ ኮሚቴ ሥራውን ሳያከናውን ግራ በሚያጋባ መልኩ እስከ አሁን ተበትኖ የቀረው በሲኖዶሱ በተያዘው ቃለ ጉባኤ ላይ በፓትርያርኩ  የተቀመጠው የደበዘዘ የውሳኔ ሀሳብ አቀማመጥ ነው። በወቅቱ በነበረው የውሳኔ ሀሳብ አሻሚ እና ግልጽነት የጎደለው በመሆኑ ከተመረጠበት ዓላማ ውጭ ሲንቀሳቀስ ተገኝቷል ብለው ለማገድ ችለዋል።

በሌላው  በሁለተኛ ደረጃ በምሳሌት የምናነሣው  ከዚህ በፊት ቅዱስ ሲኖዶስ  በአቡነ ጳውሎስ አቅራቢነት የቤተ ክርስቲያን ዓላማ የሌላቸው ከመናፍቃን ጋር ግንኙነት ያላቸው ወደ ሲኖዶስ በማቅረብ ተቀባይነት እንዲያገኝ ለማድረግ በተደጋጋሚ ይሞክራሉ ታዲያ ይህንን ጉዳይ ቅዱስ ሲኖዶስ ተመልክቶ ቤተ ክርስቲያን  የማኅበራት መብዛት ሳይሆን የሚመሠረቱበት ዓላማ ነው መጠናት ያለበት ብሎ በአቡነ ጳውሎስ የቀረበው ማኅበር ጉዳይ “ተጠንቶ ይቅረብ” ብሎ ሲወስን በቃለ ጉባኤ አያያዝ ግን  በፓትርያርኩና ቀራቢዎቻቸው ተመክሮበት “በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ያሉ ማኅበራት ሁሉ እንዲጠኑ” በሚል ቃለ ጉባኤውን አስቀምጠው አባቶችን በማስፈረማቸው ማኅበረ ቅዱሳንንም እንደገና መጠናት አለበት የማለት ጥያቄ ለማቅረብና ግራ ለማጋባት ተሞክሮ ነበር። ይህ በቀላል ምሳሌ የቀረበው ቃለ ጉባኤ ለአቡነ ጳውሎስ ትልቅ ትኩረት የሚሰጡበትና የሚፈልጉትን ጉዳይ ለማጣመም የሚሞክሩበት መሣሪያ ነው። የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ካላቸው የዋህነት እና የአቡነ ጳውሎስ ቀራቢዎች ደግሞ ካላቸው ግራ የማጋባት ስልት ቃለ ጉባኤ አባቶቻችን ሲፈርሙ በጋራ ተነቦላቸው በመጨረሻው በተስተካከለው ቃለ ጉባኤ  ላይ በጉባኤ ተነቦ ቢሆን እላለሁ።

2ኛ. የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ በፓትርያርኩ ደብዳቤ  ወይም በቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊ መተላለፉን በተመለከተ፤
የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ሲጠናቀቅ የጉባኤው አባላት  የተወሰነውን ጉዳይ ተከታትለው የማስፈጸም ኃላፊነት ለጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ  ሰጥተው ነው የሚሄዱት። ከዚህም የተነሳ በብዙ ነገር ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁን ተጠያቂ የማድረግ ሁኔታ፤ ውሳኔውን ካስፈጸሙ ጠንካራ አባት ካላስፈጸሙ ደግሞ የፓትርያርኩ ተባባሪ አድርጎ የመመልከት ልምድ ይታያል ።
የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔን ተግባራዊ ለመድረግ ግን በቃላት ብቻ በመናገር የሚከናወን አይደለም ብዙ መስዋእትነት የሚጠይቅ ጉዳይ ነው ።  ይህንንም ለመረዳት የውሳኔውን አፈጻጻም አስተዳደራዊ አካሄድ መመልከት ተገቢ ነው ። ብዙ ጊዜ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ሲጠናቀቅ አጠቃላይ የተፈረመበት ቃለ ጉባኤ በፓትርያርኩ  ፈቃድ፣  በፓትርያርኩ ፊርማ ወይም በሲኖዶሱ ጸሐፊ ፊርማ፣  የቅዱስ ሲኖዶስ መዝገብ ቤትን ጣጣ አልፎ መውጣት ይጠበቅበታል። እስካሁን ባለው ተሞክሮ  የሲኖዶሱ መዝገብ ቤት ያለ አቡነ ጳውሎስ ፈቃድ አንድም ነገር እንዲወጣ አያደርግም። አቡነ ጳውሎስ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረውታል ማለት ይቻላል። የሲኖዶሱ ጸሐፊ ለአቡነ ጳውሎስ እንደ ተራ ጸሐፊ ነው የሚታዩት። ስለዚህ  ጸሐፊውም የሚጠብቁት  በፓትርያርኩ የሚታዘዙትን መፈጸም ነው። 

ይህንን  ማድረግ ካልቻሉ ግን በአቡነ ጳውሎስና በቀራቢዎቻቸው ሰው የማይመለከትላቸውን/የማይገነዘብላቸውን መከራ ይቀበላሉ። ይህም ስሜትን በሚጎዳ መልኩ በመስደብ፣ በመናቅ፣ በሰው ፊት ሳይቀር በማመናጨቅ፣ በማስፈራራት ተጽእኖ ማሳደር ይጀምራሉ። ይህንን አልፎ ቃለ ጉባኤው  ተላለፍ ከተባለ የሚፈጀው ቀን ቀላል አይደለም ። የሲኖዶስ መዝገብ ቤትን የተቆጣጠሩት አቡነ ጳውሎስ በመሆናቸው የሲኖዶሱ ጸሐፊ የሲኖዶሱን ማኀተም እንዳያገኙ ይደረጋሉ ። “አሁን የአቡነ ጳውሎስን ሐውልት ይፍረስ ተብሎ የተዘጋጀው ቃለ ጉባኤ ይህንን ሂደት የሚያልፈው እንዴት ነው?”  የሚለው ቀላል አይደለም። ከተሞክሮ አንድ ምሳሌ ማንሣት ይቻላል። ከዚህ ቀደም ቅዱስ ሲኖዶስ ያቋቋመውና በአቡነ ጳውሎስ የፈረሰው የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግር የሚያጠናና የውሳኔ ሀሳብ የሚያቀርብ በአቡነ ጢሞቴዎስ ሰብሳቢነት ይመራ የነበረው የሊቃነ ጳጳሳት ኮሚቴ ለምን አቅም ሳይኖረው እንደቀረ መመልከት ግብዛቤ ይሰጣል። ይህንን ኮሚቴ ተግባሩን እንዲያቆምና በኋላም እንዲታገድ ያደረጉት አቡነ ጳውሎስ  የቤተክርስቲያኒቱን ቅዱስ ሲኖዶስ መዝገብ ቤት በመቆጣጠር ነው። የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ተግባራዊ የማድረግ እና የመከታተል ኃላፊነት ያለባቸው የሲኖዶሱ ጸሐፊ ኮሚቴው ተግባሩን ኢንዲያከናውን የሚችሉትን ለማድረግ  ሞክረው ነበር  በወቅቱ የነበሩት ጸሐፊ ጠንካራ ስለነበሩ ከመንግስትና ከሌሎች አካላት ጋር ስለተፈጠረው  ችግር  ይጻጻፉ የነበሩት ደብዳቤ ማኀተም እና የመዝገብ ቤት ቁጥር በሌለው ነበር።

በኢትዮጵያ የአስተዳደር ልምድ ማኀተምና የመዝገብ ቤት ቁጥር የሌለውን ደብዳቤ ሕጋዊ ደብዳቤ ነው ብሎ የሚቀበለው ማን ነው? ይህ ሁሉ የሆነው አቡነ ጳውሎስ የመዝገብ ቤቱን ማኀተም በመያዛቸው የተነሣ ነበር። አሁንም ቢሆን የቅዱስ ሲኖዶስ መዝገብ ቤት ከአቡነ ጳውሎስ ቁጥጥር ነጻ ካላወጣው አባላቱም ወደ ሀገረ ስብከታቸው ሳይሄዱ ውሳኔው ተግባራዊ እንዲሆን የሚያዘው የተፈረመበት ደብዳቤ እንዲወጣ ካላደረጉና ሐውልቱን በማፍረሱ ሂደት የመንግሥት ጸጥታ አስከባሪ አካላት ለምሳሌ “ፌዴራል ፖሊስ” እገዛ እንዲያደርጉላቸው የሲኖዶሱ ጸሐፊ ወይም ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ  የሲኖዶሱ ጉባኤ ሳይበተን በደብዳቤ ካላሳወቁ በቀር ተግባራዊነቱ የተወሳሰበ ነው።

ቅዱስ  ሲኖዶስ በተሰበሰበ ጊዜ ሁሉ ለቤተ ክርስቲያን የሚጠቅሙ ውሳኔዎችን ቢያስተላልፍም በዚህ አስተዳደራዊ አካሄድ  ማነቆ ምክንያት  አብዛኛው ውሳኔ ተግባራዊ አይሆንም። ስለዚህ “የአቡነ ጳውሎስ ሐውልት ይፍረስ የሚለውን የሚያስፈጽመው ማን ነው?” የሚለው አስተዳደራዊ አካሄዱ ውስብስብ ያደርገዋል። ባለኝ ግንዛቤ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የቃለ ጉባኤውን ኮፒ ይዘው በደብዳቤ ከሲኖዶስ ጽ/ቤት ሳይመራላቸው ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መመሪያ ይሰጣሉ ብየ አልጠብቅም። የተለመደው አካሄድ የሲኖዶሱን ውሳኔ ተግባራዊ  እንዲሆን ከቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ወይም ከፓትርያርኩ በደብዳቤ እንዲደርሳቸው ይጠብቃሉና።

3ኛ. በቋሚ ሲኖዶስ ደረጃ ሊታዩ የሚችሉ አማራጮች፤
ቃለ ጉባኤው እስከሚፈረም ድረስ አቡነ ጳውሎስ የከበዳቸው ውሳኔ ተግባራዊ እንዳይሆን ቀዳዳ በማስቀመጡ ላይም ተግተው ይሰራሉ። ለምሳሌ የውሳኔው  አፈጻጸም በቋሚ ሲኖዶስ እንዲታይ መንገድ ማመቻቸት አንዱ አካሄድ ሊሆን ይቻላል። እስካሁን ባለው አካሄድ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ተግባራዊ እንዳይደረግ ከተቻለም  ውሳኔውን  የሚሽር ውሳኔ በመወሰን ቤተ ክርስቲያኒቱን ከማልማት ይልቅ የማጥፋት ሥራ  አቡነ ጳውሎስ የሚሰሩት  በቋሚ ሲኖዶስ  አማካኝነት ነው። አቡነ ጳውሎስ ሕገ ቤተ ክርስቲያን ካስቀመጠው መመሪያ ውጭ የሚፈልጉትን ውሳኔ እንዲሁም ገንዘብ እስከዛሬ በማውጣት ቤተ ክርስቲያኒቱን አዳክመዋል። የሐውልቱ ይፍረስ ውሳኔ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ለውይይት እንዲቀርብ ካደረጉት የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም እንዳይፈጸም ወይም እንዲጓተት ማድረግ የለመዱት ጥበብ ነው።   ስለዚህ በእኔ አመለካከት ሐውልቱን የማፍረሱ ጉዳይ አቡነ ጳውሎስ በሕይወት እያሉ እንዳይፈጸም  የሞት ሽረት ትግል ማድረጋቸው የማይቀር ነው። በእኔ አስተያየት ሐውልቱ የሚፈርሰው አቡነ ጳውሎስ በሕመም ተይዘው አልጋ ላኢ ከዋሉ እና በመናገር ትእዛዝ ማስተላለፍ የማይችሉ ከሆነ ወይም በሞት ከተለዩ ወይም እውነተኛ ንስሐ ከገቡ ብቻ ነው። አሁን ባሉት በምናውቃቸው አቡነ ጳውሎስ ማንነት ግን የሚችሉትን ሁሉ ይዘው፣ ወይም አባቶችን በጥቅም ተወዳጅተው ዝም በማሰኘት ወይም በየአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በጥቅም የተሳሰሩት ታማኞቻቸው ጋር በመሆን ከቃላት ያለፈ ተግባር እንዳይፈጸም ማድረጋቸው የማይቀር ይመስለኛል። 

ስለዚህ  የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔን  በተለይም ሐውልቱ ይፍረስ የሚለውን ተግባራዊ ለማድረግ  የአቡነ ጳውሎስን ተቃውሞ፤ የአስተዳደራዊ ማነቆውንና ከጠቅላይ ቤተክህነት ጀምሮ እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን  ያሉትን የአቡነ ጳውሎስ የጥቅም ተባባሪዎች እንዲሆም በአቡነ ጳውሎስ በጥቅም የተገዙት ከመንግሥት የተባረሩ የቀድሞ የደህንነት አባላት እና አሁን አቡነ ጳውሎስን በመደገፍ የሚቆሙትን አንዳንድ የመንግስት ባለሥልጣናትን ድጋፍ ማለፍ ይጠይቃል ።

ይህንን በመገንዘብ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ተግባራዊ ይሆን ዘንድ አለማቀፋዊ  ሕብረት የሚያስፈልግ እና በሀገር ውስጥ የሚገኙ ካህናትና ምእመናንም የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በመደገፍ “ተግባራዊ ይደረግ” የሚል የድጋፍ እንቅስቃሴ፣ ከተቻለ ሰላማዊ  የድጋፍ እንቅስቃሴ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም የሚወጡ የሕትመት ውጤቶችም ይህንን ውሳኔ በማስተጋባት ታሪካዊ ድርሻቸውን መወጣት አለባቸው ።
የእግዚአብሔር  ቸርነት አይለየን።

11 comments:

Anonymous said...

we are very unfortunate to have such kind of Pope.

EHETE MICHEAL said...

እግዚአብሔር ሆይ ሁሉን ልታደርግ ይቻልሀልና እርዳን እርዳን እርዳን፣እስከመቼ ልጆችህ ተሳቀን አዝነን እንኖራለን ጌታ ሆይ አንተ ሁሉን አዘጋጅ ፣ እስካሁን ያለውን ያልታሰበ የሲኖዶስ ውሳኔ ይተገበር ዘንድ ያንተን ቅዱስ ፍቃድ እንሻለን
EHETE MICHAL

soliyana said...

Dear dege selamoch hulachinenim yasaseben guday afetsatsemu endet yehonal yemilew new ergit new Abune Paulos yemadakem limed selalachew yehinenu limedachewun endemitekmubet ena weyzerowa Jerusalem huna AJENDAW lay endayfermu hawultum ayfersem ged yelwotem bemalet be telephone sitagebabachew ena kene tizaze aywetum bebalet setnager bejoroachen yesemanew neger neger new erswam bebisechet yemetachibetn yegel sera satfetsim new gubayew ke meftsemuena lefirma kemkirebu befit teneseta wede A.A yetmelsechew selzh enante endalachut le miliate gubayew rekiku tenebo ezaw lay mefermu yeshalal bichal bichal Haweltu eskifers deress wesanew endetelalfe shefino makoyet yemil hasab new yalegn lehulum Amilake Kidusan yerdan esti.

Anonymous said...

Yejimarem yefitsamem balebet Amilakachin Egziabher fitsamewn yasamirew zende metsely new kegna yemitebkew.

Anonymous said...

OH my God meche new fetenachen yemiyalekew?

but my question is do you mean that those newly appointed bishops to differenet dioceses have to wait this paper? i don't know exactly but i think no so if the new appointment is implemented with out waiting the minutes by what logic is they need to wait the minutes to demolish the statue.

Azekeri Dengil
Azekeri Dengil
Azeketi Dengil

Anonymous said...

+++

መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 29:11 ልጆቼ ሆይ፥ በፊቱ ትቆሙና ታገለግሉት ዘንድ፥ አገልጋዮቹም ትሆኑ ዘንድ፥ ታጥኑለትም ዘንድ እግዚአብሔር መርጦአችኋልና ቸል አትበሉ።

ምዕመናን እና ሰንበት ት/ቤት ተማሪች ለንግስ ሲሄዱ ቢያፈርሱት ሲኖዶስ ወስኖአል:: ደጋፊዎች ምንም ሌያደርጉ አይችሉም::

እግዚአብሔር ሆይ ሁሉን ልታደርግ ይቻልሀልና እርዳን:: አሜን

DEREJE THE AWASSA said...

ይድረስ ለደጀሰላሞች
ይች መልክት ለአዲስአበባ ምዕመናንና ምዕመናት ትሁንልኝ።
የአዋሳ ክርስቲያን ፋኑኤልን ያህል የሰው ሃውልት ሲያፍርስ እናንተ የድንጋይ ክምር መናድ ተሳናችሁ?
እግዚአብሔር ይርዳችሁ።

Anonymous said...

Oh Lord,what kind og news is that brothers?Let God bless you.This is what every Orthodox religion followers ecpecting.Let's seethe end result.
Deje selam Gosh bertu bertu.Let God be with you.

Anonymous said...

Why too much worries? Just designate a powerful explosive device and convert this Diety to ash. It is that simple! No need to speculate many ways to implement.
God is always good, our ORTHODOX TEWAHIDO WILL SHINE FROM EAST TO WEST and from NORTH TO SOUTH. Abetu Fetari hoy Miheretih fetina le hagerachin ena hizbochua tidres.

Anonymous said...

እኔ ዬምለዉ - ሀዉልቱን ማፍረስ ቀላል ነዉ
እንዴት በሉኝ - ትቂት የተዋህዶ ልጆች ሆነን ከሌሊቱ በ9 ስአት ወጥተን የሀውልቱን እጅ ወይም አፍንጫውን እንስበረው
ከዚያ ሀውልቱ ሲታይ ይበልጡኑ አስቀያሚ ይሆናል
ያኔ በሙሉ እንዲፈርስ አባ ጳዉሎስ ፈቃድ ይሰጣሉ
መቸም እንደገና አድሱት አይሉ

Anonymous said...

Engesdi Auen Yemtykew EGZIABHREN New Ortodox Haymnoit Endnateu Sedte Endtweta Ayflgem Patryalkuen Andbtachwen Yezgalen Weyem, Kezi Alem Be Selam Yasnbtachew Amen!

Ye Sinodyosen Sira Besleam Yasftmlen Amen!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)