October 27, 2010

ቅ/ሲኖዶስ በሕንጻዎች እና ቤቶች አስተዳደር እና በልማት ኮሚሽን ውስጥ የሚፈጸሙ ሕገ ወጥ አሠራሮች እና ምዝበራዎችን በመመርመር ውሳኔዎችን አስተላለፈ

  •  የሕንጻዎች እና ቤቶች አስተዳደር ሥራ አስኪያጅ ከሐላፊነታቸው ተነሡ፤
  • የአስተዳደር ቦርዱ ከቅዱስ ሲኖዶሱ በጽሑፍ ለቀረቡለት ጥያቄዎች የሰጠው ምላሽ ሐሰተኛ እና ከጥያቄው ጋራ የማይገናኝ በመሆኑ ቀደም ሲል የተወረሱ ቤቶች አስመላሽ በመሆን የሠሩት መጋቤ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዘማርያም በድንገት እንዲጠሩ ተደርጓል፡፡
  • "አጥፍተናል፤ እናስተካክላን" (የልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር)፤
  • የተወረሱ ቤቶች እና ሕንጻዎች አስመላሽ ሆነው የሠሩት መጋቤ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዘማርያም "ቤቶቹን እና ሕንጻዎቹን በማስመለሴ ተቆጭቻለሁ፤ አስተዳደሩ ሕግ እና የአሠራር ደንብ የለውም፤ ለሙስና የተጋለጠ ነው፤ ቤቶቹን ለመከራየት በጨረታ ተወዳድረው ካሸነፉት ይልቅ ከበላይ አካል በሚወርደው ትእዛዝ ለዘመድ አዝማድ ከዋጋቸው በታች እና በነጻ የሚከራዩት ይበዛሉ፤ እውነት እንድናገር የሚፈለግ ከሆነ ለሥራዬ ዋስትና ይሰጠኝ" በማለት ለሲኖዶሱ በማስረዳት ተማፅነዋል፡፡
  • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የዘመኑ ገቢ ላይ ከ13 ሚልዮን ብር በላይ ጉድለት እንዳለ በ29ኛው የመንበረ ፓትርያሪክ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ በማጋለጣቸው ‹‹ከሥራ ትባረራለህ፤ ጡረታ ትወጣለህ›› እንደተባሉ ለተናገሩት መጋቤ ካህናት ኀይለሥላሴ ‹‹ዋስትና እንዲሰጡ›› የተጠየቁት ፓትርያርኩ ‹‹በሃይማኖት ላለነው ሁሉ ዋስትናችን እግዚአብሔር ነው፤ መፍራት የለብዎትም፤ ይናገሩ!!›› ብለዋል።
  • በመቐለ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ቅዱስ ፍሬምናጦስ ኮሌጅ እየተካሄደ ባለው የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ ሳቢያ "ቤተ ክርስቲያኒቱን አሳልፈን ልንሰጣት ነው” (ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ያቀረቡት ሪፖርት)
  • ቋሚ ሲኖዶስ በሁሉም ተቋማት ውስጥ ስለ ቀረቡት የሕገ ወጥ አሠራር እና የሙስና ተግባራት ከሚመለከታቸው ሐላፊዎች ጋራ በመመካከር አስፈላጊውን እና ተገቢውን መመሪያ እንዲሰጥ ተወስኗል፤
  • የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በነገው ስብሰባ ይወሰናል ተብሏል፤
  • የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በነገው ዕለት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፤  (ዝርዝር ዜናውን ከቆይታ በኋላ እናቀርባለን)
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)