October 27, 2010

አባቶቻችን፤ እናመሰግናለን። ውሳኔው ይተገበር ዘንድ እንጠብቃለን

(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 26/2010፤ ጥቅምት 16/2003 ዓ.ም):- በሰሞኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ ብፁዓን አባቶቻችን ያሳያችሁት መንፈሳዊ አርበኝነት እና ለጉባዔያችሁ የሚገባ እና የሚስማማ ውይይት ብዙ ደጀ ሰላማውያን እንዳሉት “እንድንኮራባችሁ፣ ከቀቢፀ ተስፋ እንድንወጣ” አድርጎናል። አሁን አንድ ትልቅ እርምጃ ተራምዳችኋል። ቀጥሎ የምንጠብቀው ነገር ውሳኔያችሁ በተግባር እንዲተረጎም ማድረጉ ላይ ነው። ለዘወትሩ እንደተለመደው “ቤተ ክህነት የአጀንዳ እና የውሳኔ ችግር” የለባትም። ችግሯ የውሳኔ እና የውሳኔ አፈጻጸም ነው። አሁን በምልዓተ ጉባዔችሁ “ያረመሙ” ሁሉ ቆይተው እናንተ ወደየሀገረ ስብከታችሁ ከተመለሳችሁ በኋላ ካጎነበሱበት ቀና ቀና ብለው “ጨዋታው ፈረሰ ዳቦ ተቆረሰ” እንደሚሉት ሕጻናት እንዳያደርጉት ጥንቃቄ ይፈልጋል። ከስብሰባው መበተን በፊት የውሳኔያችሁን አፈጻጸም የሚከታተል ክፍል ማቆማችሁን እርግጠኛ ሁኑ። ሁላችንም በጉጉት እየጠበቅናችሁ ነው። በርቱልን። ቸር ወሬ ያሰማን፤ አሜን
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)