October 22, 2010

የቅዱስ ሲኖዶስ የዛሬ ውሎ


(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 22/2010፤ ጥቅምት 12/2003 ዓ.ም):- የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በዛሬ ውሎው አጀንዳዎችን በመቅረጽ እና ዋና ዋና መነጋገሪያ ነጥቦች ሲያወጣ ውሏል። በቅዱስ ፓትርያርኩ በጽሑፍ በተዘጋጀ ንግግር የተጀመረው ይህ ጉባኤ ቅዱስነታቸው በሥራ አስፈጻሚ ጉባኤው እና በብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ላይ ያላቸውን ቅሬታ ያካተቱበትን ጽሑፍ አድምጧል። ከሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት መካከል አንዱ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የቅዱስ ፓትርያርኩን ጽሑፍ በመቃወም እንደገሰጿቸው ታውቋል።
Bridge of Hope in Mekelle
ከቅዱስ ፓትርያርኩ የመግቢያ ንግግር በኋላ “አጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴ” ወደ መሰየም ተኪዷል። ቅዱስነታቸው በንግግራቸው መካከል የጠቆሟቸውን ሦስት ጉዳዮች ማለትም “ሕገ ቤተ ክርስቲያን ስለማሻሻል፤ አዲስ አበባ ሀ/ስብከትን በአራት ስለመከፋፈል እና አዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ስለመሾም” የሚለውን ጨምሮ ከዚህ በፊት የዘገብንባቸው አጀንዳዎች ላይ ውይይት አድርጓል። “አርቃቂ ኮሚቴው” በጠቅላላው 16 መወያያ አጀንዳዎችን አዘጋጅቶ በከሰዓት በኋላ ውሎው የአጀንዳዎችን ዝርዝር ለምልዓተ ጉባዔው አቅርቧል። ቀደም ብለን ከዘገብንባቸው አጀንዳዎች በተጨማሪ በብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ጉዳይ፣ በአበው እርቀ ሰላም እና ውይይት ጉዳይ ዙሪያ እንዲሁም መቐለ ሚገኘው የከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ በአሜሪካ ከሚገኘው “ብሪጅ ኦፍ ሆፕ” (Bridge of Hope) ከሚባል ድርጅት ጋር ስላለው ግንኙነት እና በኮሌጁ ይደረጋል ስለሚባለው ኢ-ኦርቶዶክሳዊ የተሐድሶ እንቅስቃሴ ጉዳይ ውይይት ለማድረግ በአጀንዳነት ይዟል ተብሏል። በዚሁ አጋጣሚም ቅዱስነታቸው ያቀረቧቸው የአጀንዳ መነሻዎች በአርቃቂ ኮሚቴው “አስፈላጊና ወቅታዊ ያልሆነ” በሚል ውድቅ ተደርጓል። ኮሚቴው ከሰዓት በኋላ የደረሰበትን ውሳኔ በንባብ ለምልዓተ ጉባዔው አሰምቷል። የአጀንዳውን ዝረዝር ሐሳብ በወረቀት አባዝቶ ለማሰራጨት “በመብራት መጥፋት ምክንያት” ለማድረግ አለመቻሉን ኮሚቴው ተናግሯል። ቤተ ክህነቱ “መብራት ሲጠፋ ወዲያው የሚነሣ ጄኔሬተር” እንዳለው የሚታወቅ ሲሆን የመብራቱ መጥፋት ስብሰባውን ማቋረጡን አንዳንዶች አይቀበሉትም። ቅ/ሲኖዶሱ በዚሁ አጀንዳውን በማጽደቅ ውይይቱን ለነገ በማሳደር የዛሬ ስብሰባውን አጠናቋል።
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)