November 1, 2010

የኅትመት ብዙኀን መገናኛዎች ለሰሞናዊው የቅዱስ ሲኖዶስ እና አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ስብሰባ የሰጡት ሽፋን

(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 31/2010፤ ጥቅምት 21/2003 ዓ.ም)ካጋመስነው የጥቅምት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ጀምሮ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተካሄደው 29ው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ እና ቅዳሜ በተጠናቀቀው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ላይ ያተኮሩ ዘገባዎች በአገር ውስጥ በሥራ ላይ የሚገኙ ጋዜጦች እና መጽሔቶች ግንባር ቀደም ሽፋን እያገኙ ነው፡፡

በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ርእሰ አበው (ፓትርያርክ) ከመሆናቸው ባላነሰ በአወዛጋቢ እና እንግዳ ነገረ ሥራቸው የተነሣ የዜና ሰዎች እና የምልአተ ሕዝቡ ትኩረት (Celebrity) የሆኑት የአቡነ ጳውሎስ ሐውልተ ስምዕ  እንዲፈርስ፣ ከሚሌኒየሙ በዓል አከባበር ጀምሮ በየአብያተ ክርስቲያኑ የተሰቀሉት ፖስተሮቻቸው እንዲነሡ፣ እርሳቸውን ተገን በማድረግ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አስተዳደር ውስጥ አድራጊ ፈጣሪ በመሆን የግል ጥቅማቸውን እያሳደዱ የሚገኙት ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ ወደ መንበረ ፓትርያርኩ ቅጽር ትውር እንዳይሉ መታገዳቸው፤ አቡነ ፋኑኤል ከተባባሪዎቻቸው ጋራ በፈጸሟቸው እና በማስረጃ በተረጋገጠው አሳፋሪ ተግባሮቻቸው ከነበሩበት ሀገረ ስብከት መነሣታቸው፤ ከቅዱስ ሲኖዶስ ማእከላዊ አሠራር እና ውሳኔ ውጭ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ውስጥ የሚካሄዱት ሹም ሽሮች፤ ከአንድ ዓመት በላይ በእንጥልጥል የቆየው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩትና በተደረገው ማጣራት በፓትርያርኩ ከሚወነጀሉባቸው ተግባራት ነጻ መሆናቸው የተረጋገጠላቸው የብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ጉዳይ እንዲሁም በሀገረ ስብከቱ ውስጥ ከተንሰራፋው ምዝበራ እና የመልካም አስተዳደር ችግር ጋራ በተያያዘ ሥራ አስኪያጁ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ከሐላፊነታቸው መወገዳቸው የብዙዎችን ኅትመቶች የዜና ሐተታ ገጾች ቀልብ ስቦ ሰንብቷል፡፡

አውራምባ ታይምስ በተሰኘው ሳምንታዊ ጋዜጣ ‹‹የአቤቶ ወግ›› በሚለው ዓምድ ሥር በፖሊቲካ ስላቅ ጽሑፎቹ የሚታወቀው አቤ ቶኪቻው ዛሬ፣ ጥቅምት 20 ቀን 2003 ዓ.ም ‹‹የሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች›› ቁማራቸውን ተበሉ? በሚል ርእስ ያስነበበው ተሣልቆ የብዙዎችን ቀልብ ስቦ ውሏል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ከመቼውም ጊዜ በተለየ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ችግሮች ዙሪያ በመወያየት ‹‹ድንቅ፣ ታሪካዊ፣ ሁለንተናዊ እና ወሳኝ›› መፍትሔዎችን ማስቀመጡን የዘገቡት ደግሞ ሳምንታዊዎቹ ሪፖርተር፣ ነጋድራስ፣ ፍትሕ፣ አዲስ አድማስ እና ዳጉ ጋዜጦች እንዲሁም ሐምራዊ እና ዕንt መጽሔቶች ናቸው፡፡

የኅትመት ውጤቶቹን ለማግኘት ዕድሉ ለሌላችሁ አንባብያን ዘገባዎቹን ለመመልከት ትችሉ ዘንድ በሚከተለው መንገድ አያይዘን አቅርበንላችኋል፡፡ ትከታተሏቸው ዘንድ እየጋበዝን ለዚህ ተግባር ከኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ በበጎ ፈቃዳቸው ለተባበሩን ደጀ ሰላማውያንን ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርብላቸዋለን፡፡

 ማስታወሻ
የጋዜጦቹንና የመጽሔቶቹን ዘገባዎች ለማቅረብ "ቴክኒካዊ" አቅም ስላነሰን ለጊዜው መለጠፍ አልቻልንም።
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)