October 11, 2010

ጠቅላይ ቤተ ክህነት በአስተዳደራዊና መዋቅራዊ ማሻሻያ ዋዜማ?

(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 10/2010፤ መስከረም 30/2003 ዓ.ም):- ጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደራዊና መዋቅራዊ ማሻሻያ ሊደረግበት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የደጀ ሰላም ምንጮች አስታወቁ። 

ከትናንት በስቲያ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ ከመስከረም 28/2003 ዓ.ም ጀምሮ ከሥልጣናቸው እንደሚነሡ መዘገባችንን መነሻ ያደረጉት ምንጮቻችን እንዳብራሩት ጉዳዩ ንቡረ ዕዱን የማንሣት ወይም የማዘዋወር ሳይሆን የኃላፊነት ሽግሽግ እንደሚሆን ገልጸዋል። ምንጮቹ የሚሉት ትክክል ከሆነ በቤተ ክህነቱ አስተዳደር ላይ ሁነኛ የአሠራር ለውጥ ይኖራል ተብሎ ይገመታል። ዝርዝሩን በቅርቡ እንደምንመለስበት እናስታውቃለን።

9 comments:

Anonymous said...

i don't expect any change from EOTC leader

Anonymous said...

I don't expect anything new,most of them are lebochi and they just transfer them to another location for onother corruption.

Anonymous said...

ወሬው እውነት ከሆነ ጥሩ ግን ስጋቴ ወሬ ብቻ እንዳይሆነረ ነው??

Anonymous said...

PLEASE LET US PRAY FOR THE EXPECTED REFORM BE REAL. EJIGAYEHU AND OTHERS MAY BE OUT OF GAME FROM OUR BETEKIHNET MEWAKIR. NOW THEY ALONG WITH LIKE BEGASHAW ARE BECOMING UNDERGROUND LEADERS, WITH THE CONCENT OF THE PATRIARK.

ANY WAY WE WILL SEE IT AFTER THE SINODE MEETING.

BUT ALL POPS SHOULD BE COUREGOUS ENOUGH TO DECIDE SUCH A GOOD REFORM ON THE ADMINSTRATIVE SIDE OF BETEKIHNET.

REALLY WHAT MOST OF THE STAFFS THERE NEED IS COLLECTION OF NON EDUCATED PEOPLE, NOT ONLY ACCADAMICALY TRAIINED BUT ALSO THE TRUE "LIKAWENET" IN THE CHURCH.

CHER YASEMANE!

Anonymous said...

MAY THE HELP OF GOD BE WITH UD TO SEE SUCH REFORM IN THE CHURCH.

HODAMOCHEM BOTACHEWENE YEYEZALU!

123... said...

የቤተክርስትያናችን ችግር ዘርፈ ብዙ ነው በተለይ በ አሁኑ ወቅት ቤተክርስቲአን ተወጥራ ያለችበት ፫ ጉዳዮች ያሉ ይመስለኛል አነርሱም :-
፩ኛ የገንዘብ አያያዝ ግልፅነት አለመኖር አና ተጠያቂነት ማጣት
፪ኛ ሙስና፣ መሰረተ አምነት ለመናድ ተቁአማዊ አቅሟን ለመናድ ላይ ታች የሚለው ተሃድሶ አና ዘርፈ ብዙ መዋቅሩ አና
፫ኛ የ አክራሪ አስልምና ተግዳሮት ተጠቃሽ ናቸው ።

አነኝህን ችግሮች ስናይ ዛሬ ቤተክርስትያን የ አስተዳደር መዋቅሯን ማሻሻሏ ቀዳሚ መሆኑን አንመለከታለን ።የ አስተዳደር መዋቅር በ ትክክለኛ የሰው ኃይል መሞላት አና ተቁአማዊ አቅም ማጠናከር ለሙስና በር ይዘጋል። ለ ሙስና በር ከተዘጋ ደግሞ ለ ተሃድሶም ሆነ ለ አክራሪ አስልምና አደጋ በሯ ዝግ ይሆናል ።ሌላው ማወቅ ያለብን ነገር የ ቤተክርስትያናችን ችግር ዘርፈ ብዙ በመሆኑ ደረጃ በደረጃ የሚፈታ አንጂ ባንድ ጊዜ ሁሉንም ነገር መጠበቅ ይከብዳል ''ሮም ባንድ ቀን አልተገነባችም '' የሚለው አባባል ማሰብ ያሻል ። በ አነኝህ ሁሉ ምክንያቶች አንዴ አኔ አስተሳሰብ በአሁኑ ጊዜ የሚደረገውን መዋቅራዊ ለውጥ ከየትም ይነሳ ከየትም ከምር ከሆነ አና ለይምሰል ካልሆነ መደገፍ ከ ቅን የ ቤተክርስቲአን ልጆች የሚጠበቅ ይመስለኛል ።

Anonymous said...

May God help us!

Anonymous said...

ተቋማዊና መዋቅረዊ ለውጥ የመዋቅሩ ኣባለትና መሥራቾችን የግል ልባዊ ለውጥ ይሻል፡፡ የግል ለውጥ የሚመጣው በንስሐ በራስ ላይ መጨከንን ይጠይቃል፡፡ በንስሐ በራስ ላይ ለመጨከን ኃይል የሚገኘው ከእምነትና በእምነቱ ይገኛል ተብሎ የሚታመነውን ፀጋ መቀበል መቻልን ያሳያል፡፡ በዚህ መሠረት በቤተክህነት ለውጥ ይመጣል ብሎ ለማሰብ በመጀመሪያ አባላቱ እምነትን በንግግርና በጽሐፍት ደረጃ ብቻ ሳይሆን በግልና በወል ገንዘብ አድርገዋል፡፡ በእግዚአብሔር ማመንና ለእርሱም መታዘዝ ሊጀምሪ ነው ብሎ መቀበል ያስፈልጋል፡፡ እንደ እኔ ከሆነ ግን ዘረኛ ቡድን በእግዚአብሔር ያምናል ብሎ ለማመን እግዚአብሔርን መሳደብ ስለሚሆንብኝ ምኞቴ ሁሉ መጀመሪያ በእግዚአብሔር እንዲያምኑ፣ ከዚያም እንዲፈሩትና በአምሳሉ የተፈጠረውን ሰው እንዲያፍሩት ብቻነው፡፡ ከዚያ ቀጥሎ ለውጥ ይመጣል፡፡ ካልሆነ ግን ለውጡ የተለመደው ሌብነትን የማራዘም ጨወታ ነው፡፡ እግዚአብሔር እምነት ይስጠን፡፡

123... said...

-----ከ ላይ በ ቤተክህነት ውስጥ ባሉት ሰዎች ላይ መንፈሳዊነት ያስፈልጋል ያለው አስተያየት ሰጭ ትክክል ነው መጀመርያ በ ቤተ ከህነቱ ውስጥ ያሉት ሰዎች ፈሪሃ አግዝያብሔር አንድኖራቸው ያስፈልጋል ።በ ዘረኝነት ተተብትበዋል አና ።
የ ሀገሪቱ አጠቃላይ ሁኔታ ገፅታም በ አዚሁ ውስጥ ይንፀባረቃል ።በ መሆኑም መዋቅር ማስተካከል አንደጊዝያው መፍትሄ አንጂ ለ ዘለቀታውስ ስታሰብማ ዘረኝነትን መሰረት ያረገው የ ክልል አደረጃጀትስ ከ ቤተክርስቲአን አለማቀፋዊ ተልኮ ጋር መች ይሄድና። አንዳንዴ አኮ ቤተክህነት ነው ወይንስ ቤተመንግስት መጀመርያ መጥራት ያለበት? የሚለው ጥያቄ ወሳኝ ሆኖ ፊቴ ይደቀናል ።

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)