October 14, 2010

"የሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች" ደራሲ፣ ዘሪሁን ሙላቱ በእስራት እና በገንዘብ ተቀጣ

(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 14/2010፤ ጥቅምት 4/2003 ዓ.ም):- ‹የሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች›› ጽሑፍ በወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ፣ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ እና በጋሻው ደሳለኝ የስም ማጥፋት ወንጀል ክስ የቀረበበት ሊቀ ትጉሃን ዘሪሁን ሙላቱ በአንድ ዓመት ከስምንት ወር እስራት እና በ2000 ብር እንዲቀጣ የፌዴራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ወሰነ፡፡ 

ዛሬ ጥቅምት አራት ቀን 2003 ዓ.ም ፍርድ ቤቱ በሰጠው የቅጣት ውሳኔ ዘሪሁን ሙላቱ ራሱን ሆነ ብሎ ለመጥፎ ሥራ በማነሣሣት የግል ተበዳዮችን ሰብእና አጸያፊ እና አሠቃቂ በሆነ መልኩ በማዋረዱ፣ ይህም የግል ተበዳዮች በሚመሯቸው የሃይማኖት ሰዎች ዘንድ ተአማኒነት እንዳይኖራቸው የተደረገ ሤራ በመሆኑ የአንድ ዓመት ከሦስት ወራት፤
በተለያዩ የስልክ ቁጥሮች እየደወለ በማስፈራራት ከግል ተበዳዮች ገንዘብ በመጠየቁ የአምስት ወራት በአጠቃላይ የአንድ ዓመት ከስምንት ወራት እስራት እና የ2000 ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡ የግራ ቀኙ ይግባኝ የመጠየቅ መብት የተጠበቀ ነው ያሉት ዳኛው ፖሊስ ተከሳሹ እጁ ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ ታሳቢ በሚሆን መልኩ ቅጣቱን እንዲያስፈጽም በማዘዝ ፋይሉን ወደ መዝገብ ቤት ተመላሽ አድርገዋል፡፡ ዘሪሁን ሙላቱ በተላለፈበት ውሳኔ ላይ ይግባኝ እንደሚጠይቅ ከቅርብ ወዳጆቹ የተገኘው መረጃ ለመረዳት ተችሏል፡፡

የሐውልቱ ስር ቁማርተኞች”ን ማንበብ ከፈለጉ ...

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 18/2010)፦ የፓትርያርኩና የማፊያው ቡድን “ስውር ፀሐፊ” (Ghost Writer) ዘሪሁን ሙላቱ ስለ ፓትርያርኩ ሐውልትና ተያያዥ ጉዳዮች  ባለ 50 ገጽ መጽሐፍ ማውጣቱን፤ እነ በጋሻው ደሳለኝና ኤልዛቤል የምትባለው ወ/ሮ እጅጋየሁ እንደተጠቀሱበት፤ ዲያቆን ሲባል ቆይቶ በቅርቡ ሊቀ ትጉሃን የሚል የማዕረግ ስም የደረበው Ghost Writer ዘሪሁን ሙላቱ ጊዜውን በቶሎ በማጥናት እና የፓትርያርኩ ሐውልት ብዙ ተቃውሞ እንደበዛበት ሲመለከት፣ የሐውልቱ ተቃዋሚዎች ያሉትን በመሰብሰብና መጽሐፍ አድርጎ በማሳተም ሲያሳዝነው የሰነበተውን ምእመን አሁን ደግሞ ገንዘቡን ሊበላው ይህንን ፓምፍሌት (መጽሐፍ ለማለት ይከብዳል) ማሳተሙን በተከታታይ መዘገባችን ይታወሳል። መጽሐፉን ማንበብ ለፍርድ ይመቻልና እነሆ እንዲህ አዘጋጅተነዋል። ለማንበብ ይህንን (አስነብበኝ) ይጫኑ።

 


8 comments:

Anonymous said...

If the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church had had its own court and judges, the accusers also would have been incarcerated for many years. If Abune Paulos had accused Begashaw when he had defamed the arch bishops and patriarch as well as the orthodox people, Begashaw would have been in the prison.

Anonymous said...

የሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች የተባለውን መጽሐፍ አላየሁትም ነበርና አሁን ስላስነበባችሁኝ አመሰግናለሁ። አጻጻፉ ምህረት የለሽ መሆኑ መንፈሳዊነት ቢጎድለውም በውስጡ የተጻፉት መረጃዎች እውነት ከሆኑ እግዚኦታ ያስፈልጋል እላለሁ። ገመናቸው በዚህ መጽሐፍ ከወጣው ጥቂት ሰዎች ባሻገር በቤተክርስቲያን ዙሪያ ያላችሁት ሙሉ በሙሉ ቁማርተኞች መስላችሁ ታያችሁኝ።

አቤቱ ማረን ይቅር በለን! ስለእናትህ ብለህ ከጥፋት አድነን!!

አሜን።

awudemihret said...

አንቺም ክፉ ነበርሽ ክፉ አዘዘብሽ፤እንደ ገና ዳቦ እሳት ነደደብሽ፡፡የስራህን አግኝተሃል፡፡ገና የእግዚአብ
ሄር ይቀርሃል፡፡

Unknown said...

“የሊቀ ትጉሃን” የሚለዉ ሹመት የኣንድ ክንፍ ማፍያዉን ዘሪሁንን የሰጠስ ማን ይሆን? እስራቱ እና መቀጮዉ እነ ማፍያዉ በጋሻዉ ወደፊት ይካፈሉታል ተብሎ ካልሆነ ያነሰ ይመስለኛል! ወይስ እነሱ በቆፎሩት ጉድጓድ መግባት እንዳለ ኣዉቀዉ በጉቦ እንዲቀነስ አድርገዉት ይሆን ?!
ለማንኛዉም እዉነተኛ እርምት ኣግኝተህ የምእመናን ልቦና ሳታቆስል ቤተክርስትያንህን በቅንነት ለማገልገል ልቦናህ እንዲታደስ ኣምላክ ያዘጋጀልህ ቅጣት ይሆናል እና በፀጋ ተቀበለዉ
ከኣሁን በፊት የሰራሃቸዉን ጥፋቶች ኣባቶችን እና ምእመናንን ይቅርታ በመጠየቅ ከህሊና እስርነት ነፃ ብትወጣ ይሻላል።

Anonymous said...

እንደ እኔ እንደኔ ማንም ሰው ቤተ ክርስቲያንን ሲበድል መጋለጥ አለበት ብየ አምናለሁ ።እነዚህም የተጋለጡ ሰዎች በቤተ ክርስቲያን ላይ ምን ያህል በደል እያደረሱ እንዳሉ ጉዳያቸውን ለማስፈጸም በአዲስ አበባው ሀገረ ስብከት አካባቢ ደጅ እየጠኑ ያሉትን ካህናት መጠየቁ ብቻ በቂ ነው።
ጸሐፊውን ሊያስተቸው የሚችለው
1ኛ. ከተቆርቁአሪነት ተነስቶ የጻፈው አይመስልም። ምክንያቱም ከ እነዚህ ሰዎች ጋር ለብዙ ጊዜ አብሮ ሲሠራ ነበር።
2ኛ. አቀራረቡ በጣም የተጋነነ እና አንዳንዴም ለማመን የሚያስቸግሩ ነገሮችን መጨመሩ ነው።
3ኛ.በሀውልት ሥራው ላይ ግልህ ሚና ሲጫወት በነበረው ሊቀ ካህናት ጌታቸው ዲኒ ላይ ምንም የጻፈው ነገር ባለመኖሩ።አድልወ ያለበት አጻጻፍ ይመስላል። ለነገሩማ ደጀ ሰላምም እንደምታዳላ መታዘብ ችለናል።

Tamiru said...

እግዚአብሔር ሥራውን የሚሰራበት ጊዜ አለው፡፡

አምና በአቡነ ሳሙኤል ሲፅፍ ኤልዛቤል ደግፋው ነበር አሁን በራሷ ጻፈባት “ቦ ጊዜ ለኩሉ”
ምንም እንኳን የተጠቀመው ቃላት አስነዋሪ ቢሆንም ትንሽም ቢሆን ያቀዘቅዛቸዋል፡፡
አሁንም የቀሩት የቤተክርስቲያን ጡት ነካሾች እግዚአብሔር ያጋልጣቸው፡፡
ቢዘገይም የእጃቸው ማግኘታቸው አይቀርም፡፡

Dan said...

መተየቅ ወይም ማመቅ የምፈልገው ከተጻፈው ውስጥ የቱ ሀሰት ና ስም ማጥፋት ነው
ከተጻፈው ውስጥ የቱ አሉባልታ ሳይሆን በእርግጥ የተፈጸመ ነው ብሎ ያጣራ ማስረጃ ያቀረበ አለ ወይ

ሌላው ጥያቄ እነዛ የጳጳሳቱን በር እስከ መስበር በሕይውታቸው አደጋ
ለማድረስ የቃጡ ወንጀለኞች ምነው እንዲህ በአጣዳፊ ለፍርድ አልቀረቡም
ስም ማጥፋት ነው ውይስ በሕይወት አደጋ ለማድረስ ሙከራ ና ንብረት ጉዳት
ማድረስ ከፍተኛው ወንጀል

Orthodoxawi said...

ቁናው ቁናዬ ነው ትንሽ ዙሩ በዛ
ሰው በድዬ ነበር እኔም እንደዋዛ

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)