October 23, 2010

አጣሪ ኮሚቴው ወደ ሐዋሳ ተጉዟል


(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 22/2010፤ ጥቅምት 12/2003 ዓ.ም):- የሐዋሳውን ችግር ለመፍታት ቃል በተገባው መሠረት አጣሪ ኮሚቴው ዛሬ ሐዋሳ ከተማ ገብቷል። በ12 የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች እንዲሁም በሚኒ ባሶች እና የቤት መኪናዎች ተጭኖ የመጣው ቁጥሩ ከ700 በላይ የሚሆን የሐዋሳ እና አካባቢው ሕዝበ ክርስቲያን በብዙ ደጅ ጥናት መልስ ሊያገኝበት ያልቻለውን የአቡነ ፋኑኤልን ጉዳይ ለአንዴም ለመጨረሻውም ለማከናወን ወደ አዲስ አበባ መምጣቱን መዘገባችን ይታወሳል። በተደጋጋሚ ስንዘግብ እንደቆየነው ምእመናኑ ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ ይህ ለ4ኛ ጊዜያቸው መሆኑ ነው። ነገር ግን ጠቅላይ ቤተ ክህነቱም ሆነ ቅዱስነታቸው ችግሩን ሳይፈቱ ይልቁንም ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በድንዳኔያቸው እንዲቀጥሉበት የበለጠ ዕድል ሲሰጣቸው ቆይተዋል። ሊቀ ጳጳሱ እንዲያገለግሉት የተሾሙለትን ሕዝበ በማስመረራቸው እየገፉ ከመሔዳቸውም ባሻገር ለሕዝቡ ያላቸውን ንቀት በአደባባይ ሳይቀር ማሳየታቸውን ቀጥለዋል። የሐዋሳ ምእመን በድጋሚ የመጣው ጉዳዩ መስመር ስቶ ወደ አላስፈላጊ መንገድ ከመግባቱ በፊት የመጨረሻ አቤቱታቸውን ለማሰማት ነበር።
 
ቅዱስነታቸውም “ነገ ጠዋት (ማለት ዛሬ አርብ) ወደ ሐዋሳ አጣሪ ኮሚቴው ይላካል” ያሉ ሲሆን ይኸው የአጣሪ ኮሚቴ ወደ ሐዋሳ የመሔድ ጉዳይ ከንግግር ባለፈ እስካሁን ተግባራዊ ሳይሆን መቆየቱን ሐዋሳውያኑ አስታውሰዋል። “ቅዱስ አባታችን፤ እውነተኛ አባት ይስጡን” ያለው የሐዋሳ ምእመን ችግሩን በዚሁ መፍታት ካልተቻለ “ከእንግዲህ ድጋሚ አንመጣም፤ በሰላም ይለያዩን (ከአቡኑ ጋር)፤ አሁን እርሶ ችግሩን መፍታት ስላልቻሉ መነጋገር የምንፈልገው ከቅ/ሲኖዶስ ጋር ነው” ማለቱም ተሰምቷል።  በመጨረሻም አጣሪውን ኮሚቴ ዛሬ አርብ ለመላክ በመስማማት ውይይቱ የተፈፀመ ሲሆን ሕዝበ ክርስቲያኑም ወደ ሐዋሳ በሰላም ተመልሷል። እንደተባለውም ኮሚቴው ዛሬ ወደ ሐዋሳ ለመንቀሳቀስ ችሏል።
7 comments:

selamawi said...

በስመ ስላሴ አሃዱ አምላክ አሜን

እኔ እምለው አቡነ ፋኑኤል አዋሳን የሚወዱት ከሆነ ለምን ህዝቡን በመልካም አያስተዳድሩትም ህዝቡ ከጠላቸው ማንን ሊመሩ ነው እዚያ የተቀመጡት በጣም ያሳዝናል ከሲኖዶስ አባላት በኩል የሚሰነዘረው ሃሳብ አቡነ ፋኑኤል አዋሳ እንዲቆዩ የፓትርያርኩ ፍላጎት ነው ይመስለኛል የገቡላቸውን ቃል ላለማፍረስ እየታገሉላቸው ነው አሜሪካንን ጥለው ሲሄዱ አዋሳን ነው ተስፋ አድርገው የሄዱት እሳቸው የወደዱት አዋሳ ላንጋኖን ነው ህዝቡ ደግሞ አልወደዳቸውም እንዴት ይሁን ከ700 ህዝብ በላይ ከአዋሳ አዲስ አበባ ድረስ ተጉዞ መጥቶ ተቃውሞውን ማሰማቱ ምን ያህል ቢበደል ነው ደግሞስ ህዝቡ አልፈልግም ካለ አጣሪ ኮሚቴ ለምን አስፈለገ ? እንደኔ እንደኔ አቡነ ፋኑኤል የአዋሳ ነገር አክትሞለታል ወደ ባህር ዳር ደግሞ ቢሞክሩ የተሻለ ይመስለኛል

Anonymous said...

+ + +

Dear Selamawi,

Why you wish Abune Fanuel to come and try in Bahir Dar, do you think he have a place in bahir dar? is it not enough that he disappoint our brother's and sister's in Awassa. But i would prefer for him to try the country he is proud of (usa)?

fkre said...

እንደ እኛ መጥፎ ይወድልናል ሰላማዊት ባይሆን ወደ ድሬዳዋ ወደ እናታቸው ይሂዱ እንጅ መቸም ምን አሰቀያሚ ቢሆን ልጅ አይጣል በሀርዳርማ የነ አቡነ ቶማስ አቡነ ሰላማን እነ አቡነ በርናባስ የሰሩበት ነው እኮ

Abetu said...

Abetu eskemeche zim tilenaleh???????????????????????????????????/

Dan said...

የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 5

1 ሕዝቡንም አይቶ ወደ ተራራ ወጣ፤ በተቀመጠም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀረቡ፤
2 አፉንም ከፍቶ አስተማራቸው እንዲህም አለ።
.
.
13 እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም።
14 እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም።
15 መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል።
16 መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።
17 እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም።
18 እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም፥ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ።
19 እንግዲህ ከነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ ታናሽ ይባላል፤ የሚያደርግ ግን የሚያስተምርም ማንም ቢሆን እርሱ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ ይባላል።
20 እላችኋለሁና። ጽድቃችሁ ከጻፎችና ከፈሪሳውያን ጽድቅ ካልበለጠ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም።

እንግዲህ የማንን ትምህርት ትእዛዝ እንከተል?
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ወይስ የሌሎችን?

ቅ.ዮሐንስ አፈወርቅ ይህን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የተራራው ስብከት እየጠቀሰ ሲያስተምር " ሌሎች ሕይውታቸው ኑሯቸው ክርስቲያናዊ ሳይሆን የማይጣፍጥ አልጫ ቢሆን ሐዋርያት (ዲያቆናት ቀሳውስት ጳጳሳት) ክርስቶስን በመምሰል ወንጌላዊ ህይወት እየኖሩና እያስተማሩ የሌሎችን ሕይወት ከአልጫነት ወደ ጣፋጭነት (ጨው የማይጣፍጥን ወደ ጣፍጭነት እንደሚለውጠው) ይለውጠዋል::

በሐዋርያዊነት ሥራ የተሰማሩ(ዲያቆናት ቀሳውስት ጳጳሳት) ሥራቸው ሕይወታቸ የማይጣፍጥ ሆኖ ሲገኝ በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም።

እነዚህ ጨው ያልሆኑ ሁሉ ከቦታ ወደ ቦታ ቢቀያይሯቸ በሙስና ላይ ሙስና corruption (ሙስና በገንዘብ ብቻ አይደልም) ሙስና ማለት ውድቀት ጥፋት ማለት ይምስለኛል::
በሥርዓተ ቅዳሴ/የምስጋና ቅዳሴ ከቅዱስ ባስልዮስ ጸሎት "እግዚአብሔር ዐብይ ዘለዓለም ዘለሐኮ ለሰብ እንበለ ሙስና:: ለዘለዓለም ታላቅ የሆንክ እግዚአብሔር ሰውን ያለ ጥፋት ያለ ድክመት የፈጠርክ" ይላል::

የማይጣፍጥ መራራ ሥራ ያላቸው ከውሽኝጝተን አዋሳ ከአዋሳ ወደሌላ ቦታ ማቀያየር ድንጋዩን ጨው ነው ግዙ ብሎ ለማታለል መሞከር ነው::

እንግዲህ ቅ. ሲኖዶሱ የሚለውን እንሰማለን::

ሌሎቹም አባቶች "መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል። መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።"

ጨው ነን ብለው የሙያምኑ የመረረውን የሚያሳዝነውን ድርጊት ሁሉ በቅድስና ሕይውታቸው ኑሯቸው ምሳሌነት በትምህርታቸው በአባት ግሳጼ ይጣፍጡ::
በግልጽ ይናገሩ ብርሃናቸው እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ

ትምህርታቸው የአባት ግሳጼአቸው በሁሉ ዘንድ ይሰማ።
ለምሳሌ
"ከሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት መካከል አንዱ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የቅዱስ ፓትርያርኩን ጽሑፍ በመቃወም እንደገሰጿቸው ታውቋል።"

"ጥቅምት አራት ቀን ለመወያየት የተቀመጡት አባቶች በቅዱስነታቸው ላይ ያላቸውን ቅሬታ የገለፁ ሲሆን በተለይም ብፁዕ አቡነ ገብርኤል “በጽኑዕ አገዛዝ ውስጥ ነን ያለነው፤ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን እየተጣሰ መሆኑን ለማረጋገጥ ቦሌ መድኃኔ ዓለም ሒዱና ሐውልቱን ተመልከቱ” ማለታቸው ተሰምቷል። ሌሎቹም አባቶች “ተደብድበን ሳለን መንግሥት ፍትሕ አልሰጠንም” እንዳሉ የተጠቆመ ሲሆን ለዚህ አስተያየት የግል ሐሳባቸውን ከሽማግሌዎቹ አንዱ “መንኮሰ ሞተ አይደለም ወይ? እንኳን መደብደብ ሰማዕትነትስ ብትቀበሉ (ብትሰየፉስ?)?” ሲሉ በመመለስ አባቶች ያላቸውን ከፍ ያለ ኃላፊነት አስታውሰዋቸዋል። " ከደ.ሰ. ሪታርት

ሌሎቻችሁም ትምህርታችሁ የአባት ግሳጼአችሁ በሁሉ ዘንድ ይሰማ።
በዚህም ሁሉም ያው ናቸው ብለን ከማዘን ይጠብቀን::

Anonymous said...

Wittiness,
Oh, friends Why Dire,USA,or Bahirdar?!! No one can imagine how this man and his two fellows( Dn.Yared and Melake Tsehay)buried us alive. I don't think they are Orthodox. I haven't seen such a devilish father in my life. So, since they have no place in paradise, I think it is better to to send him to Addis where he built a ground + Villa that worth 5 Million.

Mamush said...

People please don't undermine fathers. Please keep your sprite. "ATISALEKUBACHEW"

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)