October 30, 2010

ሰበር ዜና:- አቡነ ጳውሎስ በቃለ ጉባዔው ላይ አልፈርምም አሉ

አርእስተ ዜና 
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 30/2010፤ ጥቅምት 20/2003 ዓ.ም):-
አቡነ ጳውሎስ ሐውልቱ እንዲፈርስ የታዘዘበትን እና የሁሉም ሊቃነ ጳጳሳት ስምምነት የተገለጸበትን ውሳኔ በያዘው ቃለ ጉባኤ ላይ ‹‹አልፈርምም›› በማለት እና ሲጠየቁም ዝምታን በመምረጥ ቀድሞ ሲገለጽ በቆየው እምቢታቸው ጸንተዋል፡፡
አቡነ ይሥሐቅ
አቡነ ጎርጎርዮስ
  •  ከፓትርያሪኩ ጋራ ሌሎች አራት ሊቃነ ጳጳሳትም በተለያየ ምክንያት የሐውልቱ መፍረስ የተገለጸበትን ቃለ ጉባኤ አልፈረሙም፡፡ ሲኖዶሱ ከ43 ያላነሱ በአገልግሎት ላይ የሚገኙ ጳጳሳት እና ሊቃነ ጳጳሳት በአባልነት ይገኙበታል፡፡
  •  የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የሐውልቱን ማስፈረስ ውሳኔ እንዲያስፈጽሙ በስማቸው ተለይቶ በመግለጫው ላይ መስፈሩን በመቃወም ለመፈረም ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ ብፁዕነታቸው ‹‹ከእኔ ስም ይልቅ ቢሮው ነው መጠቀስ ያለበት›› የሚል አቋም እንዳላቸው ተነግሯል፡፡
  •  አቡነ ይሥሐቅ፣ አቡነ መቃርዮስ እና አቡነ ጎርጎርዮስ (ከዚህ በፊት ሐውልቱን ሲቃወሙ ቆይተዋል) ‹ፓትርያሪኩ ሳይፈርሙ በፊት አንፈርምም› በሚል እና ሌሎች ምክንያቶች ለመፈረም ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡
  •  በሕገ ቤተ ክርስቲያን ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ የስብሰባ ሥነ ሥርዐት አንቀጽ ሁለት ንኡስ አንቀጽ 4/ሀ ሃይማኖትን እና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በሚመለከት ጉዳይ ከጠቅላላው አባላት ከአራት ሦስቱ እጅ በተገኙበት ሲኖዶስ በማድረግ በሙሉ ድምፅ ውሳኔ ማሳለፍ እንደሚገባ ተደንግጓል፡፡
  • በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ አንቀጽ 15 ንኡስ አንቀጽ 1 ፓትርያሪኩ በተሰጠው ሐላፊነት መሠረት ሃይማኖትን እና ቀኖና ቤተ ክርስቲያን የመሠበቅ እና የማስጠበቅ፤ በአንቀጽ 16 ንኡስ አንቀጽ 1 መሠረት ደግሞ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ሃይማኖት የሚያፋልስ፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የማይጠብቅ፣ ቤተ ክርስቲያንን የሚያስነቅፍ ተግባር ፈጽሞ ከተገኘ፣ ታማኝነቱ እና ተቀባይነቱ በካህናት እና ምእመናን ዘንድ ተቀባይነት ያጣ ሆኖ ይህም በትክክል ከተረጋገጠ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ከሥልጣን እንደሚወርድ ተደንግጓል፡፡
  • ፓትርያሪኩ ዛሬ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በተጠራው ጋዜጣዊ ጉባኤ በቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት ስምምነት የተደረሰበትን መግለጫ እንደሚያነቡ ይጠበቃል፡፡ መግለጫውን ለማንበብ ፈቃደኛ ካልሆኑ ብፁዓን አባቶች የወከሉት የሲኖዶሱ አባል እንዲያነቡት ይደረጋል ተብሏል፡፡

22 comments:

Anonymous said...

Ewente yekdusane amelake zem alken beka ayayayayay uuuuuu egziooooooo enase kemalkese beseteker men elalew ye abune paulose adegega mewonacheuone tengeraleu auonese abatuochachen mene yeluo yeuone yeche betekirestyan eta fantawa yehe uone beka wey aba pauoluse amilake masetwaluone yesetacheu chegru berasacheu selmayemru mene yederegal auneme cher were yasemane

Anonymous said...

Ewente yekdusane amelake zem alken beka ayayayayay uuuuuu egziooooooo enase kemalkese beseteker men elalew ye abune paulose adegega mewonacheuone tengeraleu auonese abatuochachen mene yeluo yeuone yeche betekirestyan eta fantawa yehe uone beka wey aba pauoluse amilake masetwaluone yesetacheu chegru berasacheu selmayemru mene yederegal auneme cher were yasemane

li said...

Amlake kidusan becherinetu yirdan enji lela min yibalal. Yebedelachin bizat yechrinet ejun eytefebin yihonin?
Yeamlak cherinet,Yekidusan tselot na yeemebirehan milja kaliredan negeru hulu adero kariya lihon yimeslal.
Cherun yaseman

TESFAMARIAM said...

YEDINGIL LIG GETA IGZIABHER HOY ANTE TAWKALEH!!!

Anonymous said...

Yesemay amlak Egziabher yehizbun hazen sema.
Deje Selam owners please can you post pictures of our bishops along with their name?

Anonymous said...

Egziabher Kezi Alem Yasnbtachew Zend BEnateu Sem Enlminewalen Durey Patriyalke

Anonymous said...

አሁን እንደ ራሔል እንባችንን ወደ እግዚአብሔር የምንረጭበት ጊዜ ነው፡፡ ሁላችንም በአቅማችን ቤተ ክርስቲያንን በደሙ ወደ መሰረታት ወደ ባለቤቱ እናልቅስ፣ ከዚያ እርሱ ፍርዱን ይስጥ!

woldegebriel said...

Eregud newe enante ere mengizie metabene!!! Beka tebite becha newe endie yihechene kideste betekerestiean eymrate yalewe!!! yehie mcheme abatochene, yihechene kideste btkerestian , mela memenun andihume mnfse kidusene mnake newe!!!Ere andie menale bkedusane abatoche endayene hulu menale ahuneme biasechresene!! Ere egzio enbele!! Lhaimanotachene enenea
woldegebriel

Mahlet (እሚ) said...

It is our wish to see the well-ordered meeting to end with an assuring baseline for the implementation of the agreed upon decisions and to see the constituent assembly of our fathers to firmly hold the grounds on the Laws of the Church 'n do the just as required with no loop holes for sabotage. Let the Holy Spirit reside in the midst and give our fathers the will and power to act consequently now 'n days to come.
His holiness Abune Paulos's princtonic mind to complicated for credulous mind of other Arch Bishops.His holiness has the capacity to create a diversion from a small gitch of action and expand the corruptive effect till the Fathers themselves doubt what their stand is inrelative to the rest or even who to trust.

jte said...

Amlakachin hoy Lante Hulu Yichalehalina ahunim yanten dink sira initebkalen!Lijochihin asdessitachew! egna lijochih gulbet yellenim, gulbet(hayl) Yante new!zare netsa awtan! Betihin atsdaw!

solomon said...

ብፁዓን አባቶች ስንደሰት ከርመን በመጨረሻው ሰአት አስደንጋጭ ነገር ሰምተን በጣም አዝነናል፡፡ ግን የራሄልን እንባ ያበሰ እግዚአብሔር እሱ ያውቃል ፡፡ ሁሉም ስል ቤተክርስቲያን ያስብ!!

Addiswork said...

Ye Ethiopia Amlak Ferdun yest, menem yemaysanew amlakachen firdun yest lela men yebalal. Le Hatan yemeta Le Sadqan yeterfal. Be selotachen kegonachhu honen enasbachhualen. Yetenesaw maebel beselam yemeles zend egzabeher yerdan.Amen
Addiswork

Anonymous said...

ለውሳኔው ተፈጻሚነት የመንግሥትን እርዳታ መጠየቅ የሚያስፈልግበት ጊዜ ነው ይህንን ማድረግ ቢቻል:: ከዚህ በተጨማሪ ሕዝብ ይወቀው::

Anonymous said...

+++
ወገኞች የቤተ ክርስቲያን ልጆች የፈራነው ይህን ነበር።
ለመሆኑ ምን ይሆን በዓለም መድረክ እንኳ የማይደረግ ድራማ የሚሰራው?!!!!
ብጹዕ አቡነ ፊልፖስስ የፈሩት ምን ይሆን?!!! በእውነት ላሰራሩ ብለው ነው ወይስ ፍርሃት?!!!
ለማነኛውም በያለንበት ያለው አለመደማመጥ ፥ እኔባይነት፥ አለመግባባት ፥ ፍርሀት፥ ወዘተ በብጹዓን አባቶቸ ዘንድ እንዲህ ገዝፎ መታየቱ ዘመኑ ምን ያህል ክፉ መሆኑን ያሳያል። ይህ ካልሆነ ታዲያ እነረሱ የአንዲት የተዋህዶ አባቶቸ ከሆኑ ከኖናዋ ዶግማዋ አንድ እና በግልጽ የተቀመጠ ነው ይህ ልዩነት ከየት መጣ?!!!
እባከችሁ ብጹአን አባቶች የጀመራቺሁትን ቀኖና ቤተክርስቲያ የማስከበር አደራ ባግባቡ አሰፈጽሙ!
የፓትርያርኩም ነገር በጣም አጠያያቂ እየሆነ ነው!! ለምንድነው እነዲህ ግራ የሚያገቡን?!
እንድ ነገር አድርጉ እንጅ!

ሑላችንንም በተዋህዶ ሀይማኖታችን ያጽናን አምላክ ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅልን።

Anonymous said...

+++

ምዕመናን ሆይ ለቤተክርስቲያን ዘብ ቁሞ ችግሯን የሚፈታ ህጋዊ ኮሚቴ እንደ ሀገር ሽማግሌ የሆኑ ፍትህ እውቅና የሰጣቸው ተቌቁመው እንዲሰሩእና የሲኖዶሱን ዉሳኔ ተመርኩዞ ለህግ አካላት በማቅርብ የሚያስፈጽም ማለት ነው:: አቡኑ ግን ፍልም እየሰሩ ነው ልበል ከአለፉ በኋላ አጃቢዎቻቸው የሚያወጡት?
ቤተክርስቲያን ችላቸው ነው እንጅኮ የቤተክርስቲያን አባት አለመሆናቸው በተግባር ከአሳዩ ቆይተዋል እኮ:: ብጹዓን አባቶች በአሁኑ ታግላችኋል ሃይለኛው ዳቢሎስ በህብረት ጾምን እና ጸሎት የሚወጣው ሁኖ ነውእንጅ:: ግን በርቱ ተስፋ እንዳትቆርጡ ዲያብሎስ ደስይለዋልና ደግሞ ጭፍራዎቹ ሥራቸውን ይቀጥላሉና ተሎ ወደ ሀገረ ስብከታችሁ ሂዱ::
ሁላችንንም በተዋህዶ ሀይማኖታችን ያጽናን አምላክ ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅልን።
አሜን::

የቆዘመው said...

እውነት ነው ለምን ይፈርሙ። ፓትሪያሊኩ በአንድ ራስ ሁለት ምላስ ለምን ይባሉ? ትላንት ሃውልቱን ሲያስመርቁ ከቅዱስ መጽሐፍ ጥቅስ ገልጠው ነው። ልክ ዲያቢሎስ ጌታን ክርስቶስ ሊፈታተን በቀረበ ጌዜ ጥቅስ ጠቅሶ እንዳቀረበው። ስለዚህ ነቅሎ ለሚያፈርሰው ጌታ እንተውለት።

Anonymous said...

እኝህን ሰውዬ የሚመራቸው እርኩስ መንፈስ ነው።ጸበል ቢጠመቁ መልካም ነው።
ሲሾሙ አቡነ ዲያቢሎስ አድርጎ ነው የለቀቃቸው።ከሚሰሩት ስራ መገንዘብ ይቻላል።

Anonymous said...

ወገኖቼ!!!!!

ለምንድነው ጥቃቅን ኢሹ እየፈለግን ነገሮችን አዲs የምናደርጋቸው። ቀኖናው ከፈረሰ ገና 3 ወር እንደሆነው (ከሃውልቱ) በሃላ ነው???? የምናየው።

እንደዚሂህ ያሉ ጥቃቅን ጉዳዮችን ስናባዝት አንኳሩ ጉዳይ እየተረሳ ወያኔም ስራውን እየሰራ የቤት ስራችን (the homework that woyane gave us is now extended fom 100 years from what has been said by Meles and Esayas to 120 years). አገራችን ከወደድን 1/ ሁላችንም ወደ እግዚአብሔር መጸለይ 2/ በየግል አጅንዳችን 10ሩን ከመጨበጥ አንድ ሆነን ለአንዲት ኢትዮጵያ መቆም።

ካለዚያ በትንንሹ ጉዳይ ሁሉ ቡራ ከረዮ የምንለው ሁሉ ወያኔን የሚያስደስተው ፎርሙላ መሆኑን መረዳት ያሻል። አቡነ ጳውሎስን ከወያኔ ለይቶ ማየት ግብዝnነት ነው ።

ሀውልቱ እኮ ከወያኔ ጋር የተያያዘ የታሪክ ምልክት እንዲሆን ነው እንደ አክሱም፤ ላሊበላ፤ ፋሲለደስ ሀውልቶች የወያኔን ታሪክ ከ1000 ኣመት በሃላም እንዲዘክር ነው።

ልዩነቶቻችን ትተን ስለኢትዮጵያ እንጸልይ፤ እንታገል። ካለዚያ ጊዜን በከንቱ ማባከን!!!!

ትንቢተ

Unknown said...

ክርስቲያኖች እኚ ሰዉዬ አሁን ዝም ከትባሉ ነገ ደሞ ፅላት ይቀረፅልኝ ማለታቻዉ አይቀሬ ነዉ! ብቻ እርሱ አንድዬ ይርዳን!!!!

Anonymous said...

አቶ መለስና ወያኔ ስልጣንና ጥቅም ያሰከራቸውና ያሳበዳቸው የዘመናችን ጉደኞችና የጥፋት መልእክተኞች ናቸው፡፡
ስለዚህም ከቻልን ነገሮችን ለመቀየር ያቅማችንን መጣር ካልቻልን ደግሞ ወደፈጣሪ መፀለይ እንጂ ብዙም በነዚህ የዘመናችን ጉደኞችና የታሪክ አተላዎችና አራሙቻዎች ብዙም መገረም የለብንም፡፡አቡነ ጳዎሎስም የሀይማኖት አባት ነኝ ብለው እዚህ ቦታ ላይ ቢቀመጡምና ይህ አይነት ሁኔታ ቢፈጠር ብዙም አይግረመን፡፡ምክንያቱም እሳቸውንም እዚህ ቦታ ላይ ያስቀመጣቸው አቶ መለስና ወያኔ ስለሆኑ፡፡ስለዚህም አቡነ ጳዎሎስ እዚህ ቦታ ላይ ከበፊቱም የተቀመጡት የሀይማኖት ስራ ለመስራት ሳይሆን በዋነኛነት የፖለቲካ ስራ ለመስራት ነው፡፡ስለዚህም መተካካት በሚባለው የወቅቱ አሰራር አቶ መለስ የትግል አጋሮቻቸውን ፈንግለው በሌላ እንደተኩ ሁሉ ይህንንም እንደ አንድ የሀይማኖት ሚኒስቴር ብንወስደው አቶ መለስ አቡነ ጳዎሎስን አንስተው ሌላ ለመተካት ብዙም አይከብዳቸውም ወይንም ይህ ቢሆን ብዙ ሊገርመን አይገባንም፡፡
ስለዚህም ዋነው መረዳትና ማየት ያለብን ትልቁን ምስል ማየት ነው፡፡ትልቁም ምስል የአቶ መለስና ወያኔ ታሪካዊ አመጣጥ ተፈጥሮአዊ ባህሪና ከበስተጀርባ ይዘው የተነሱበት ድብቅ አላማቸውና ፍላጎታቸው ምንድን ነው የሚለው ነው፡፡
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ፡፡

Anonymous said...

አቶ መለስና ወያኔ ስልጣንና ጥቅም ያሰከራቸውና ያሳበዳቸው የዘመናችን ጉደኞችና የጥፋት መልእክተኞች ናቸው፡፡
ስለዚህም ከቻልን ነገሮችን ለመቀየር ያቅማችንን መጣር ካልቻልን ደግሞ ወደፈጣሪ መፀለይ እንጂ ብዙም በነዚህ የዘመናችን ጉደኞችና የታሪክ አተላዎችና አራሙቻዎች ብዙም መገረም የለብንም፡፡አቡነ ጳዎሎስም የሀይማኖት አባት ነኝ ብለው እዚህ ቦታ ላይ ቢቀመጡምና ይህ አይነት ሁኔታ ቢፈጠር ብዙም አይግረመን፡፡ምክንያቱም እሳቸውንም እዚህ ቦታ ላይ ያስቀመጣቸው አቶ መለስና ወያኔ ስለሆኑ፡፡ስለዚህም አቡነ ጳዎሎስ እዚህ ቦታ ላይ ከበፊቱም የተቀመጡት የሀይማኖት ስራ ለመስራት ሳይሆን በዋነኛነት የፖለቲካ ስራ ለመስራት ነው፡፡ስለዚህም መተካካት በሚባለው የወቅቱ አሰራር አቶ መለስ የትግል አጋሮቻቸውን ፈንግለው በሌላ እንደተኩ ሁሉ ይህንንም እንደ አንድ የሀይማኖት ሚኒስቴር ብንወስደው አቶ መለስ አቡነ ጳዎሎስን አንስተው ሌላ ለመተካት ብዙም አይከብዳቸውም ወይንም ይህ ቢሆን ብዙ ሊገርመን አይገባንም፡፡
ስለዚህም ዋነው መረዳትና ማየት ያለብን ትልቁን ምስል ማየት ነው፡፡ትልቁም ምስል የአቶ መለስና ወያኔ ታሪካዊ አመጣጥ ተፈጥሮአዊ ባህሪና ከበስተጀርባ ይዘው የተነሱበት ድብቅ አላማቸውና ፍላጎታቸው ምንድን ነው የሚለው ነው፡፡
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ፡፡

Anonymous said...

Does he really believe in Jesus? I doubt it.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)