October 27, 2010

“ሐውልቱ” ምን ይሁን?

(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 27/2010፤ ጥቅምት 17/2003 ዓ.ም):- ቅዱስ ሲኖዶስ በማያሻማ መልኩ ከትምህርተ ተዋሕዶም ሆነ ከ ሥርዓተ አበው ውጪ የሆነው “ሐውልተ ስምዕ” እንዲነሣ ከወሰነ ጀምሮ የተለያዩ ደጀ ሰላማውያን እንዴት እንደሚፈርስ በቀልድ እያዋዛችሁ አስተያየታችሁን ሰጥታችኋል። 

እንግዲህ መፍረሱማ ከሆነ እንዴትና ምን መሆን እንዳለበት ከታሪካችን መጠነኛ አስተያት በመጨመር አጭር ሐሳብ ለማካፈል ወደድን። ሐውልቱ በደህና ቦታ፣ ለምሳሌ ቤተ ክህነቱ ባሠራው ሙዚየም ወይም በሌላ ተገቢ ቦታ አልያም በዚያው በቦሌ መድኃኔ ዓለም “ሙዚየም” (ካላቸው) መቀመጥ አለበት።

አባቶቻችን ቤተ ክርስቲያንን ለ15 ዓመታት ያቃጠላትና ያወደማትን የግራኝን ካባ እና መጎናጸፊያ በመርጡለ ማርያም ገዳም ካስቀመጡ፤ በመረዝ ጋዝ ሕዝባችንን የፈጀውን የጣሊያን ከአየር የሚወረወር ቦንብ በአድዋ  ሥላሴ ካስቀመጡ፤ ይህም ትውልድ ይህንን “ሐውልት” ለመጪው ትውልድ መማሪያ እንዲሆን በተገቢው ቦታ ማስቀመጥ አለበት። 

ስድስት ኪሎ ያለው የማርክስ ሐውልት ላይ ቀለም እንደተደፋው፤ የሌኒን ሐውልት በጭንቅላቱ እንደተገለበጠው፤ ወይም ሩቅ ምሥራቅ የሳዳም ሐውልት መጫወቻ እንደሆነው መደረግ የለበትም። ይህ ታሪካችን ነው። የቅ/ሲኖዶስ ገድል ሲጻፍ አብሮ መጠቀስ ያለበት የአባቶቻችን የመንፈሳዊ አርበኝነት ውጤትም ነውና በሥነ ሥርዓት ይቀመጥ።  
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)