October 26, 2010

ሰበር ዜና፦ ቅዱስ ሲኖዶስ የአቡነ ጳውሎስ ‹‹ሐውልተ ስምዕ›› እንዲፈርስ ወሰነ

ዝርዝር ዜናው እንደደረሰልን እናቀርባለን፤ ተከታተሉን!!!!!
  •  በየአጥቢያ አብያተ ክርስቲያኑ የተሰቀለው የአቡነ ጳውሎስ ፖስተርም እንዲነሣ ተወስኗል፤
  • በቅርቡ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መዋቅሮች የተሾሙት ሐላፊዎች የቅጥር ሁኔታ  ተመርምሮ በሚቀጥልበት እና በሚቋረጥበት ሁኔታ ላይ ውሳኔ የሚሰጥበትን አግባብ አስቀምጧል፤
  • ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ ወደ ቅጽረ መንበረ ፓትርያርኩ እንዳይገቡ ታግደዋል!!
  • አቡነ ጳውሎስ በሐውልቱ ሥራ ላይ ‹‹አልተሳሳትኩም››፤ ‹‹እኔ አላውቅም›› የሚሉ  እርስ በርሳቸው የሚጋጩ እና ግራ የሚያጋቡ አቋሞችን አንጸባርቀዋል፤ በሌሎቹም  ውሳኔዎች ላይ አርምሞን መርጠዋል፡፡ ብዙዎች ሁኔታውን ‹የውዥንብር እና የጸጥታ ዲፕሎማሲ› ብለውታል፡፡
  • ‹‹ውሳኔው የቅዱስ ሲኖዶሱን ግብራዊ ህልውና የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔዎቹ ተፈጻሚ መሆናቸውን ስብሰባው ሳይፈጸም ማረጋገጥ አልያም ከጽ/ቤቱ ጋራ በመሆን ውሳኔውን የሚያስፈጽም አካል መሠየም አለበት፡፡›› (የምእመናን አስተያየት)
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 26/2010፤ ጥቅምት 16/2003 ዓ.ም):- ‹‹ኦ አምላኬ፣ የአባቶቻችንን አንድነት አጽና፤ ምእመናን ሆይ፣ እባካችሁ በርትተን እንጸልይ›› ይላል ከትናንቱ  የዜና ዘገባ በኋላ ለደጀ ሰላም በድምፅ እና በጽሑፍ የደረሰ የደጀ ሰላማውያን አስተያየት፡፡

ተማኅፅኖው እና ጸሎቱ ሥራውን መሥራቱ ደግሞ ከመንበረ ፓትርያርኩ የቅዱስ ሲኖዶስ መሰብሰቢያ አዳራሽ ዛሬ ቀትር ላይ በምሥራች መልክ ተሰምቷል - ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬው ከሰዓት በፊት የስብሰባው ውሎው ከሆነው ጊዜ ጀምሮ በአገር ውስጥ እና በውጭ በሚገኙ የኅትመት እና ኤሌክትሮኒክስ ብዙኀን መገናኛዎች፣ ደጀ ሰላምን በመሳሰሉ የጡመራ መድረኮች (ብሎጎች)፣ ብፁዓን አባቶች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እና ሰባክያነ ወንጌል በቆሙባቸው ዐውደ ምሕረቶች እና ዐውደ ትምህርቶች፣ የመንግሥት ሹማምንት፣ የአገር ሽማግሌዎች እና የራሳቸው የፓትርያርኩ ቤተ ዘመዶች ሳይቀሩ ሲያዝኑበት፣ ሲመክሩበት፣ ሲገሥጹበት እና ሲያወግዙት የቆዩት የአቡነ ጳውሎስ ‹‹ሐውልተ ስምዕ›› እንዲፈርስ፣ በሥዕለ ገጻቸው አምሳል ቢያንስ በዐሥር የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እና ሌሎችም አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን የተሰቀሉት ፖስተሮች በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ ትምህርተ ሐዋርያት እና ቀኖና ቤተ ክርስቲያን እንዳይፋለስ ለመጠበቅ ባለበት መንፈሳዊ ግዴታ እና በሕገ ቤተ ክርስቲያን በተሰጠው የማይገሰስ ሥልጣን በዛሬዋ ዕለት እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆኖ ወስኗልና!! ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ፡፡ አሜን፡፡

+++++++++++++++++ ደጀ ሰላም ስለ ሐውልቱ ከዘገበችው በጥቂቱ ለማስታወሻ +++++++++++++++
(ደጀ ሰላም፣ ጁላይ 20/2010)፦ ይህ ዝግጅት የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ (ዶይቸ ቨለ) ያዘጋጀው ነው። ሐውልቱን አስመልክቶ ኦርቶዶክሳውያን ምን እንደተሰማቸው መጠነኛ ገለጻ ነው። እንዲህ የሚናገር ቁርጠኛ ሰው አያሳጣን።

ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን

JULY 11, 2010


ሐውልቱ ተመርቋል፣ “ለ500 ዓመት ይጠቅማል፣ አፈር ውስጥ ቢቀበርም አይበላሽም” ተብሏል


(ደጀ ሰላም፣ ጁላይ 11፤ 2010)፦ “የቅዱስ ፓትርያርኩን 18ኛ ዓመት በዓለ ሲመት ምክንያት በማድረግ በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔ ዓለም ቤተ የቆመው ዛሬ ሲመረቅ ሐውልቱን ያሰሩት ሰዎች “ለሚቀጥሉት 500 ዓመታት ያለምንም ችግር ይኖራል” ሲሉ አሞካሽተውታል። በዚሁ ወቅት በተደረገው ገለጻ “ለቅዱስ ፓትርያርኩ ይህ የሚገባቸው ነገር ነው” ተብሏል። የአሰሪ ኮሚቴውን መግለጫ ያነበቡት “ባለ ሽጉጡ ሊቀ ካህናት” ጌታቸው ዶኒ “ቅዱስነታቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያላቸው” መሆናቸውን በመግለጽ የሐውልቱን መመረቅ አብስሯል። ሐውልቱ ምን ያህል እንዳወጣ ባይገለጽም ይህንን የሁለት ቀን ዝግጅት ስፖንሰር ያደረገው የነዲ/ን በጋሻው ደሳለኝ ማኅበር ከ100 ሺህ ብር በላይ ማውጣቱን ራሱ በጋሻው በንግግሩ ገልጿል። 
በዚህ የሁለት ቀን ዝግጅት ከየመድረኩ እንዳያስተምር የተከለከሉት በጋሻውና ጓደኞቹ በ100 ሺህ ብር የማስተማር ፈቃዳቸውን መግዛት ችለዋል ማለት ነው። በሌላ በኩል ግን የቅ/ሲኖዶሱን ውሳኔ ለማስፈጸም የሞከሩት የአዋሳ ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በጋሻውን እንዳያስተምር ከከለከሉ በኋላ በቅ/ትርያርኩ ትዕዛዝ፣ በአቡነ ገሪማ ፊርማ ከሥራቸው ተባረዋል። ይቺ ናት ቤተ ክህነት!!! ምን ችግር አለ፣ ዋናው መቶ ሺህ ብሩ ነው። ዲ/ን በጋሻው አሁን ሐውልት አቆመላቸው፣ ቀጥሎ ደግሞ ጽላት ይቀረጽላቸው ሳይለን ይቀራል? ዞሮ ዞሮ የቻይናዎቹ ተረት እንዴት ገላጭ ነው? “ለገንዘብ ብሎ ስለ እግዚአብሔር የሚሰብክ ሰው የበለጠ ገንዘብ ከተሰጠው ለሰይጣንም ይሰብካል” (የቻይናዎች አባባል)
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን
++++++++++++

JULY 16, 2010


ሁለት ጽሑፎች ስለ ሐውልቱ ጉዳይ:- ባሮክ እና ገብር ሔር እንደጻፉት

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 16/2010)፦  ትናንት እንደዘገብነው፣ "ስውሩ ፀሐፊ" ዘሪሁን ሙላቱ ያዘጋጀውና በፓትርያርኩ “የተባረከው” ጽሑፍ በሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ ስም "ነጋድራስ ጋዜጣ" ላይ ታትሞ ወጥቷል። ይህ ኢ-ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ይሁንታ መውጣቱ እጅግ አሳዛኝ እና ዘመነ-ንስጥሮስን የሚያስታውስ ነው። አምስተኛው ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ሞት ሥልጣናቸውን እስኪነጥቃቸው ድረስ ሳይወገዙ ቢቆዩም እንኳን ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ጥሩ ቅን አባት ሲሰጠን ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የጣሱ ፓትርያርክ ናቸውና እንኳን በሕይወት እያሉ ከሞቱም በኋላ ቢሆን ስማቸውና ተግባራቸው ሊወገዝ ይገባዋል። 
የእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን የኑፋቄ ትምህርት ሲያስተምር የነበረውን አርጌንስ ከሞተ ከ300 ዓመት በኋላ እርሱንም የጻፋቸውን ስፍር ቁጥር የሌላቸውን መጻሕፍቱንም ማውገዟ ትምህርት ሊሆነን ይገባል። አቡነ ጳውሎስም አሁን የሚያወግዛቸው ሲኖዶስ ባናገኝ እንኳን ለዚህ ሥራቸው ከሞቱም በኋላ ውግዘቱ አይቀርላቸውም፤ ንስሐ እስካልገቡበትድረስ። ለጊዜው ግን ይህንን ካቶሊካዊ ሥራቸውን የሚሞግቱ ሁለት ጽሑፎችን ከዚህ በታች ተመልክቱ። አትማችሁ ላላነበቡ አድርሱ፤ ለታሪክም አስቀምጡት።

ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜንየሐውልቱ ሥር «ቁማርተኞች»


(ባሮክ ዘሣልሳይ ሽሕ)

ሐምሌ አራት ቀን 2002 ዓ.ም በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስተያን ደጃፍ ዐጸድ ላይ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ «የምስክርነት» ሐውልት ቆሟል፡፡ ሐውልቱ ከመቆሙ በፊትም ሆነ ከቆመ በኋላ ሁለት ተቃራኒ ሐሳቦች እየተንጸባረቁ ናቸው፡፡ የመጀሪያው እና በአሠሪ ኮሚቴዎቹና በዙሪያቸው ካሉ ጥቂት ግለሰቦች የተደመጠው ሐሳብ፣ «ሐውልት ማቆም የቤተ ክርስቲያኗ ሥርዐት ነው» የሚል ነው፡፡ የዚህ ተፃራሪ የሆነውና አብዛኛውን ሕዝበ ክርስቲያንና የቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና የመንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀመዛሙርት ያካተተው ሁለተኛው ሐሳብ ደግሞ፣ «ሐውልት ማቆም በቤተ ክርስቲያኗ ሕግ፣ ቀኖና ሥርዐት የተወገዘ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የሌለው ነው» የሚለው ነው፡፡

ከዚህ አንጻር ለሕዝበ ክርስቲያኑ እውነታውን ከመግለጽ አኳያ መጽሐፍ ቅዱስ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ እና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ውሳኔ እንዲሁም በጥቅሉ የቤተ ክርስቲያኗ አስተምህሮ እና ሊቃውንት ምን ይላሉ? የሚለውን በጥንቃቄ መመርመር ለሁሉም ማለፊያ በመሆኑ የሚከተሉት ትንታኔዎች ቀርበዋል፡፡

1.    ጥንተ ሐውልተ

መስከረም 1987 ዓ.ም በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ልዩ ትእዛዝ፣ በብፁዕ አቡነ መቃርዮስ በወቅቱ የትግራይ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሰብሳቢነት፤ በመልአከ ሰላም ዳኛቸው ካሣሁን፣ በሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ በመጋቤ ምስጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ፣ በመጋቤ ብሉይ ሠይፈ ሥላሴ ዮሐንስ አዘጋጅነት፣ «ሃይማኖት የለየንን መቃብር አንድ አያደርገንም» በሚል ርእስ የተዘጋጀው መጽሐፍ ስለ ሐውልት ምንነት እና አጀማመር ሲያስረዳ እንደሚከተለው ይላል፡፡


ሐውልት አንድ ወጥ የሆነ ክብነት ወይም ማእዘንነት ያለው፤ ከድንጊያ ተጠርቦ፣ ከኖራ እና አሸዋ፣ ከሲሚንቶ እና ከተፈጨ ደንጊያ ተሠርቶ ለመታሰቢያ የሚተከል፣ እንደ ዐምድ /እንደ ምሰሶ/ የሚቆም መዘክር ነው፡፡ ሐውልት- የሚያመለክተው በአንድ ዘመን በአንድ ቦታ ላይ የተፈጸመን ድርጊት ስለሆነ ከብዙ የድንጋይ ቁልል /ጉር/ ሊሠራ ይችላል፡፡ በቀድሞ ጊዜ ሐውልት የሚቆመው በጦር ሜዳ ወድቀው ለሚቀሩ ጀግኖች፤ በስደትና በሽሽት ጊዜ በጉዞ ላይ በሚደርስ ድንገተኛ ሞት፣ ከቤተሰብ ተለይተው በመንገድ ዳር ለሚቀበሩ ወገኖች መታሰቢያ ነበር፡፡» /ገጽ-32/


በዚህ ምክንያት ሐውልት የመቆሙም ጥቅም «ይኽ መቃብር የእገሌ ወይም የእገሊት መቃብር» ነው ተብሎ ለመታወቂያና ለመታሰቢያ ነው እንጂ መንግስተ ሰማያት የሚያወርስ፣ ሰማያዊ ጥቅምን የሚያስገኝ አይደለም፡፡ በዚህ መልኩ እና ዐውድ /Context/ ለሙታን ሐውልት ማቆም በያዕቆብ ወልደ ይስሐቅ ዘመን የተጀመረ ልማድ መሆኑን ቅዱስ መጽሐፍ ሲገልጥ፣ «ወአቀመ ያዕቆብ ሐውልተ ላዕለ መቃብረ ራሄል፤ ወይእቲ ተሰምየት ሐውልተ ራሄል፤ ያዕቆብ በራሄል መቃብር ላይ ሐውልትን አቆመ፤ እስከ ዛሬም የራሄል ሐውልት ተብሎ ተሰየመ፤» በማለት ነው፡፡ /ዘፍ. 35.20/


እንግዲህ ከዚህ የሙታን ጥንተ ሐውልት ታሪክ መረዳት እንደሚቻለው አንድ ወጥ የሆነ የቆመ ድንጊያ /ትክል/ ምልክት እንጂ ዛሬ በዘመናችን የአቡነ ጳውሎስን የ«ምስክርነት ሐውልት» ጨምሮ/ በተለያየ ቅርጽና መልክ እንደሚሠራው ያለ ጥርብ ድንጋይና የእምነ በረድ፤ የአሸዋና ሲሚንቶ፣ የኖራና የጠጠር ክምር አይደለም፡፡ ያዕቆብም ለራሔል የመታሰቢያ ሐውልት ያቆመበት ምክንያት ወደሀገሯ ሳትገባ በድንገት በመንገድ ዳር አርፋ ከወገኖቿ ጋራ ለመቀበር ዕድል ሳታገኝ በመቅረቷ ለመታሰቢያ ነው፡፡ በመስከረም 1987 ዓ.ም በቅዱስ ፓትርያርኩ ልዩ ትእዛዝ የተዘጋጀውም መጽሐፍ ይኽ የራሄል የመታሰቢያ ሐውልት አሁን በዘመናችን ከሚቆሙት ሐውልቶች በእጅጉ መለየቱን ሲገልጽ፣ «... አሠራሩም ሆነ አፈጻጸሙ በዘመናችን እንደሚታየው ያለ ሁኔታ አልነበረም፤ ሊሆንም አይገባም፡፡» ይላል፡፡ /ገጽ. 34/


ስለዚህ ከዚህ መረዳት የሚቻለው የሐውልትን ታሪካዊ ዕድገት እንጂ ሥርዐተ አበው እና ሕገ ሃይማኖት ኾኖ መሥራቱን እና መደንገጉን አይደለም፡፡ ግን ልማድ ነው፡፡ ከገድለ ቅዱሳን እንደምንረዳው፤ እንኳን በሕይወት ያሉ ይቅርና ሃይማኖታቸውን ጠብቀው፣ ሥነ ምግባራቸውን አሳምረው በሞት ዕረፍት የተለዩን ደጋግ አባቶችና እናቶች በመካነ መቃብራቸው ተአምራት እየተደረገ እንኳን ምልክት /ትክል ድንጋይ/ ይቆማል እንጂ ሐውልት አይሠራም፡፡ የቀደሙት ክርስቲያኖች አባቶቻችን የሙታንን መታሰቢያ አስመልክቶ በመካነ መቃብር ላይ የሚያደርጓቸው ምልክቶች ልዩ ልዩ ዐጸዶችን /ዛባቸነ/  መትከል ነው፡፡ /ገጽ 36/

ከዚህ ጋር በተያያዘም የሚነሣው ሌላ ነጥብ «የሐውልት ምረቃ» ነው፡፡ እንኳን በሕይወት ያለ ሰው ሐውልት ይቅርና ከዚህ ዓለም በሞት ለተለየ ሰው ሐውልት አቆሞ ማስመረቅ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ያልተፈቀደ መሆኑን የቤተ ክርስቲያኗ አቋም የተገለጸበት ይኸው በቅዱስነታቸው ልዩ ትእዛዝ የተዘጋጀው መጽሐፍ ያስረዳል፤ እንዲህ በማለት፡- «የሐውልት ምረቃ» የሚባለው ከቤተ ክርስቲያን ያልተሰጠ እንግዳ ልማድና ከመንፈሳዊ ሥርዐት ውጭ የሚፈጸም ነው፡፡ ለሞቱ ሰዎች ለሥጋቸው ትንሣኤን፣ ለነፍሳቸው በጎ ዕረፍት ስጥ ለማለት ለምሕረትና ለይቅርታ በመካነ መቃብር ላይ ጸሎት ይደረጋል፡፡ በሐውልት ዙሪያ ሕዝብ ሰብስቦ ሐውልቱን ግምጃ አልብሶ ጸሎተ አኰቴት ማድረስ ግን በቀኖና ቤተ ክርስቲያን የታዘዘም የተፈቀደም አይደለም፡፡» /ገጽ-37/


2.   የሐውልት ክልከላ ምክንያት

ከጥንት ጀምሮ እንደሚታወቀውም ሆነ በባዛንታይ በ787 ዓ.ም በተወሰነው ውሳኔ መሠረት ቤተ ክርስቲያን የቅብ ወይም የጭረት ሥዕልን እንጂ ቅርጽን ወይም ሐውልትን አትጠቀምም፡፡ በሮማውያምኑ ዘንድ ቢኾን የጣዖት አምልኮ ከጥንቱ በተወረሰ ልማድ ካልሆነ በቀር በቤተ ክርስቲያን ትውፊት ቅርጽ /ሐውልት/ ማቆም የተፈቀደ አይደለም፡፡ በቤተ ክርስቲያን ትምህርት፣ ታሪክና ትውፊት ሐውልት ሳይሆን ሥዕል የተፈቀደ፣ የተለመደና ሥርዐታዊ ነው፡፡ ይኽም አምስት ነገርን መሠረት በማድረግ ነው፡፡

2.1 መጽሐፍ ቅዱስ

እግዚአብሔር አምላክ ለሙሴ ከሰጣቸው ዐሥርቱ ትእዛዛት አንዱ «በላይ በሰማይ በታችም በምድር ካለው፤ ከምድርም በታች በውሃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ የተቀረጸውን ምስል ለአንተ አታድርግ፤ የሚለው ነው፡፡ /ዘጸ. 20.4-5/ በዚህ መሠረት የተቀረጸ ምሳሌ /ሐውልት/ ቁጥሩ ከአምልኰ ባዕድ ስለሆነ ቤተ ክርስቲያን ትቃወማለች፡፡

2.2 የታሪክ መዛግብት እና መረጃዎች ምስክርነትቀደምት የቤተ ክርስቲያን አበውና የታሪክ ጸሐፊዎች በቤተ ክርስቲያን ሥዕል እንጂ ሐውልት የተፈቀደ መሆኑን አልገለጹም፤ አላስተማሩም፡፡ አውሳብዮስ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ መጽሐፉ፣ «ታላላቅ ሥዕላትን አይቻለሁ፤ የመድኃኔ ዓለም፣ የቅዱስ ጴጥሮስና የቅዱስ ጳውሎስ ሥዕላት እስከ ዘመናችን ድረስ አሉ፡፡» አለ እንጂ ሐውልትን አልጠቀሰም፡፡ /Eusabius, History of the church, Book III, page 20/


በቤዛንታይን መንግሥት የቅዱሳት ሥዕላት ክርክር በተካሄደ ጊዜ ቅዱሳት ሥዕላትን በተመለከተ ሦስት መጻሕፍትን የጻፈው ታላቁ ሊቅ ዮሐንስ ዘደማስቆ፣ «ሥዕል በቤተ ክርስቲያን ሁለት ዐይነት ጥቅም አለው፡፡ ከእነዚህም አንዱ በዋሻ እንደነበሩት ክርስቲያኖች ተአምራት ነክ የቅዱሳት መጻሕፍትን ታሪክ ማነበብ ለማይችሉ ሰዎች ለማስረዳት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሃይማኖቱን ሳይፈራ፣ ሳያፍር መስክሮ በሰማዕትነት የሞተ ወይም ስለ ዓለም እና ስለራሱ በመጸለይ መላ ሕይወቱን ከፍትወታት፣ ከእኩያት፣ ከአጋንንት ጋር በመጋደል ያሳለፈውን ሰማዕት ወይም ጻድቅ በሥዕል ለመዘከር፣ በሥዕሉም አማካይነት እያንዳንዱ ምእመን ለሥዕሉ ባለቤት ክብርና ፍቅር ለመግለጥ ነው፤» በማለት ጻፈ እንጂ ሐውልትን አልጠቀሰም፡፡ /አባ ጎርጎርዮስ፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣ ገጽ 99/ ከዚህ ሊቅ በተጨማሪም እነጎርጎርዮስ ዘዐቢይ እና ባስልዮስ ዘቂሣርያ በየድርሳኖቻቸው ስለቅዱሳት ሥዕላት አስፈላጊነት እንጂ ስለ ሐውልት ተከላ እና ምረቃ አልጻፉም፡፡


2.3 የኦሪየንታል አብያተ ክርስቲያን ትውፊት /Oriental Church tradition/

የነገረ እግዚአብሔር ሊቃውንት ስለምዕራብና ምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት ሲያስተምሩ «East is Iconic, west is pictorial» /ምሥራቅ ሥዕላዊ፣ ምዕራብ ባለ ምስል ናቸው/ ይላሉ፡፡ የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት ሥዕል ሲሉ ሦስት ማእዘናዊ /three dimensional/  የሆነውን ሐውልትን በመተው ወካይ ትርጉማዊ እውነታን የሚያስፍረውን ሥዕልን ይጠቀማሉ፡፡ /Coptic Encyclopedia Vol. 4 -1276/


በዚህም መሠረት በምሥራቃውያን ትውፊት ሥዕል ሊታይ ወይም ሊዳሰስ የሚችል ቅርጽ የሌለው ሁለት ማእዘናዊ /two-dimensional/ የሆነ በቀለም የሚሠራ ነው፡፡ በኢትዮጵያ፣ በግብጽ፣ በሶርያም ሆነ በአርመን ገዳማት ቅዱሳት ሥዕላት እንጂ ሐውልቶች አይገኙም፡፡ ሌላው ቀርቶ መለካውያን ኦርቶዶክሶችም /Chalcedonian/ Byzantine Orthodox Churches/ በሥርዐታቸው ሐውልትን አይጠቀሙም፡፡ /2ኛው የኒቂያ ጉባኤ ውሳኔ 787 ዓ. ም/

2.4 የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት ምስክርነት

በቤተ ክርስቲያናችን የተጻፉ መጻሕፍት ሥዕል እንጂ ሐውልት የቤተ ክርስቲያን መሆኑን አይገልጹም፤ እንዲያውም ይከለክላሉ፡፡ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ «የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ» በተባለው የታወቀ መጽሐፋቸው፣ «በምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት ትውፊት መሠረት ሥዕል የሚሣለው በቀለም ነው፡፡ ላቲኖች ግን ቅርጽን /ሐውልትን/ ይጠቀማሉ፡፡» በማለት ገልጠዋል፡፡ /ገጽ 114/ ይኽም የሚያመላክተን ትውፊታችን የቀለም ሥዕል እንጂ የቅርጽ ሐውልት ያለመሆኑንን ነው፡፡


በ1970 ዓ.ም የታተመው «The Ethiopian Orthodox Church» የተሰኘው የአእምሮ ወንድማገኘሁ መጽሐፍም፣ «ኦርቶዶክሳውያን የሚያከብሩት ዝርግ /flat/፣ ሁለት ማእዘናዊ /two dimension/ ቅዱሳት ሥዕላትን ነው፡፡ ለሦስት ማእዘናዊ ሐውልት /Statue/ አይጸልዩም፡፡ ምክንያቱም ዕውናዊ ጠባይ ሰላለውና በራሱም ጣዖትን ማክበር ስለሆነ ነው፡፡» ይላል፡፡ /ገጽ 91/


«የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት፣ ሥርዐተ አምልኮና የውጭ ግንኙነት» በሚል ርእስ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳተመው መጽሐፍም ቅዱሳት ሥዕላት በቤተ ክርስቲያን ስላላቸው ክብር ይዘረዝራል እንጂ «ሐውልት የቤተ ክርስቲያን ትውፊት ነው» ብሎ አልጠቀሰም፡፡ /ገጽ-95/


«ሃይማኖት የለየንን መቃብር አንድ አያደርገንም» በሚል ርእስ በ1987 ዓ.ም የተዘጋጀው መጽሐፍም፣ «የክርስቲያኖች ሐውልት ቤተ ክርስቲያን ናት፤ አማንያን በአርባ በሰማኒያ ቀን እየተጠመቁ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማሕፀነ ዮርዳኖስ በመወለድ ከሥላሴ ልጅነትን ይቀበሉባታል፡፡ ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ በሚለዩበትም ጊዜ የዕረፍት ቦታቸው ናት፡፡ ቤተ ክርስቲያን የጸሎት የመሥዋዕት ቦታ ከመሆኗም በላይ በተስፋ ትንሣኤ የሚታረፍባት ስለሆነች ሲያዩት ደስ በሚያሰኝ፣ ሲመላለሱበት ኅሊናን በሚስብ ንጽሕና መጠበቅ ይኖርባታል እንጂ የሐውልት መከማቻ ልትሆን አይገባም፡፡ ሐውልት... ትንሣኤን ስለሚያስረሳ አፍአዊ ምልክት /ከንቱ መታለያ/ ነው፡፡ ... ልምዱም የመጣው ከሌሎች እንጂ ከአባቶቻችን የመጣ ባህልና ትውፊት ስላልሆነ እንዳይቀጥል የሚደረግበት መንገድ መፈለግ ይኖርበታል፡፡» በማለት አስፍሯል፡፡ /ገጽ፣ 35 እና 38/

2.5 የቤተ ክርስቲያን ጸሎት ምስክርነት /Liturgical witness/

የቤተ ክርስቲያን ትምህርትና ሥርዐተ አምልኰ ከሚገለጽባቸው መንገዶች አንዱ ሥርዐተ ጸሎት ነው፡፡ በዚህ ውስጥም ዶግማዋ፣ ታሪኳና ሥርዐቷ ተካትቶ ይገኛል፡፡

ቅዱሳት ሥዕላት ቤተ ክርስቲያናዊ ሥርዐትና ትውፊት በመሆኑ «መልክእ ሥዕል» የተሰኘ ጸሎት አለው፡፡ «መልክአ ሐውልት» ግን የለም፡፡ ይኽንንም መልክአ ሥዕል ሲገልጽ «ሰላም ለሥዕልኪ እንተ ሠዓላ በእዱ፣ ሉቃስ ጠቢቡ እም አርባዕቱ /ወንጌላውያን/ አሐዱ፤ ቅድመ ሥዕልኪ እሰግድ ወለሥዕለ ወልድኪ እገኒ፤ ማርያም ድንግል ማርያም እመ አዶኒ» በማለት ነው፡፡ /መልክአ ሥዕል/

በመቅድመ ተኣምረ ማርያምም «ለሥዕሏ ያልሰገደ ስም አጠራሩ ይጥፋ» ይላል እንጂ “ለሐውልቷ ያልሰገደ” አይልም፡፡ እነዚህ ሁሉ የቤተ ክርስቲያን ጸሎት ክፍሎች የሥዕልን ሥርዐታዊነትና ትውፊታዊነት እንጂ የሐውልትን ኦርቶዶክሳዊነት አይመሰክሩም፡፡

እንግዲህ ከላይ በቅደም ተከተል የጠቀስናቸውን ማስረጃዎች «የሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች» እንደሚሉት ሳይሆን ቅዱሳት ሥዕላት እንጂ ሐውልት ኦርቶዶክሳዊ አለመሆኑንን የሚያመለክቱ ናቸው፡፡ ለጊዜያዊ ስምና ዝና እንዲሁም ለገንዘብ ተብሎ እውነተኛውን የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አጣምሞ ማቅረብ በእግዚአብሔርም በታሪክም፣ በሕግም ከማስጠየቁም በላይ በቅዱስነታቸው ክብርና ስም በመቆመር ለሃይማኖታችን መዘባበቻን ለምእመናንም ኀፍረትን ማትረፍ ነው፡፡

ለሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን ተፃራሪ የኾነው የዚህ ሕገ ወጥ ድርጊት ፊታውራሪዎች፣ አባሪ እና ተባባሪዎች የፓትርያርኩን 18ኛ ዓመት በዓለ ሢመት ምክንያት በማድረግ በተቋቋመ ኮሚቴ ሽፋን የሚንቀሳቀሱ ናቸው፡፡ እንደ እውነቱ ከኾነ በየዓመቱ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ለሢመተ ፕትርክና በተመረጡበት ቀን የሚከበረው ይህ በዓል ለታሪካዊቷ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የነጻነት በዓል ነው፤ ከኮፕት ቤተ ክርስቲያን ሞግዚትነት ተላቃ ከራስዋ አበው መነኮሳት እና ሊቃውንት በተመረጡ አባቶች ለመመራት የበቃችበት ነውና፡፡ ይኹንና በዘንድሮው በዓለ ሢመት ዝግጅት ስም የፓትርያርኩን የ«ምስክርነት ሐውልት» በማን አለብኝነት እና ግልጽነት በጎደለው የጥቅም ትስስር ሠርተው ያስመረቁት ግለሰቦች የቤተ ክርስቲያኒቱን የነጻነት በዓል በባዕዳን ትምህርት እና ልማድ በመለወጥ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ የሽፍትነት እና የቁማርተኝነት ተግባር በመፈጸም የግል እና የቡድን ጥቅማቸውን እያዳበሩ ከመኾናቸውም በላይ ከሌሎች ቤተ እምነቶች የቅልውጥ ድርጊቶችን በመውሰድ ጥንታዊትና ስንዱ እመቤት በኾነችው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የባርነት መንፈስ ለማስፈን እየማሰኑ ይገኛሉ፡፡

ከፓትርያርኩ ሽልማት ኮሚቴ አባላት አንዳንዶቹ የቤተ ክርስቲያኒቱን ቆብ እና ቀሚስ ለብሰው፣ መስቀል ጨብጠው ሲያበቁ ከፕሮቴስታንት አብያተ እምነት ለአንዱ ክፍል ማደራቸውን በጻፉት ደብዳቤያቸው ያረጋገጡ፣ በረከት ሞልቶ ከተረፋት እናት ቤተ ክርስቲያን ይልቅ የሌሎችን ገፈራ ለመቀላወጥ በደጃቸው የተለጎሙ፣ በሄዱበት ሁሉ የቤተ ክርስቲያኒቱን ፍሬ በልተው እና አራቁተው እብስ የሚሉ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹም በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ውስጥ አንዳችም በይፋ የታወቀ ሥልጣን እና ተግባር ሳይኖራቸው፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ በሠራቻቸው የኪራይ ቤቶች በነጻ እየኖሩ፣ ቅዱስ ፓትርያርኩን ያሻቸውን በማስወሰን ግፈኛ ኤልዛቤላዊ ተግባር የሚፈጽሙ፣ ሐውልተ ስም አቁመው መስዋእተ እርያ የሚያቀርቡ ናቸው፡፡

አንዳንዶቹም በቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የሚሰጠው ነገረ መለኮት የብረት ቆሎ ሲኾንባቸው በፕሮቴስታንት «ሐሊበ - ቃል» ተዘርተው የበቀሉ፣ ተኮትኩተው ያደጉ፣ ኦርቶዶክሳዊ ሥርዐትን እና ካህናትን የሚነቅፉ እና የሚዘልፉ፣ ፕሮቴስታንታዊ ፓስተሮችን የሚያሞጋግሱ እና በፕሮቴስታንታዊ ዘይቤዎች የተጠመዱ፣ ትላንት «የመስቀሉ ሥር ቁማርተኞች» ብለው በተናገሩበት አንደበታቸው ዛሬ የተለወጡ ኹኔታዎች በሌሉበት የውዳሴ ከንቱ ዶፍ የሚያወርዱ፣ የእኛ ያልሆነ እንግዳ ልማድ አስርገው ኢየሩሳሌም ዘሞዐብ ሊያደርጉን የሚርመሰመሱ ክልኤ ባሕርይ ናቸው፡፡ ሌሎቹም ከድመት ጠጉር ልመው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሰርገው የገቡ እና በጭንቅ የተገኘን የቤተ ክርስቲያን ንዋይ እርም የበሉ ናቸው፡፡ ሌሎቹም ቀደም ሲል ፓትርያርኩን ሲዘልፉ የነበሩትን ተፃርረው ለ«ስድብ አፋቸው» ምላሽ የሰነዘሩ፣ ዛሬ ግን እነዚያኑ ዘላፊዎች ሕገ ወጥ በኾነ እና በአፈሳ በተገኘ ሹመታቸው እየጠሩ የሚያወድሱ፣ የብር ቀፈታቸውን ለሚሞላቸው ሁሉ የጥፋት ብዕራቸውን የሚመዙ ምንደኞች እና ቅጥረኞች /Ghost writers/ ናቸው፡፡ እንግዲያስ ያላወቀ ይወቃቸው፤ ያወቀም ይጠንቀቃችው። እግዚኦ ቦኡ አሕዛብ ውስተ ርስትከ፣ ወአርኰሱ ጽርሐ መቅደሰከ፣ ወረሰይዋ ለኢየሩሳሌም ከመ ልገተ ዐቃቤ ቀምሕ፡፡


   +++++


ምስል ማቆም የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ባህል ነውን?
(ገብር ሔር ዘመ/መንግሥት)

“ጌታቸው ዶኒ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሕጋዊ ወኪል” በሚል ስም የወጣውን በሐሰት የተሞላ መጣጥፍ ባነበብኩ ጌዜ “ጠላቶችሽ ሁሉ አፋቸውን አላቀቁብሽ እያፍዋጩና ጥርሳቸውን እያፋጩ ውጠናታል ተስፋ ያደረግናት ቀን ይህች ኛት አግኝተናታል አይተናታልም ይላሉ” በማለት ነቢየ እግዚአብሔር ኤርምያስ ስለ ኢየሩሳሌም የተናገረው ኃይለ ቃል ነበር ትዝ ያለኝ (ሰቆ.ኤር.216)፡፡


በሊቃውንት ተሞልታ የነበረችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እነሆ እነዚያ ትንታግ የሆኑ ሊቃውንቶችዋ አልቀው በላይዋ ላይ ወልደ ዶኒን የመሰሉ አራሙቻዎች በቅለውባታል እንኩዋን ሊቀ ካህናት የሚለውን የቤተ ክርስቲያኒቱን ታላቅ የማዕረግ ስም የያዘ ቀርቶ ጨዋ የሚባለው ተራው ምዕመን አሳምሮ የሚያውቀውን የቤተ ክርስቲያኒቱን እምነትና ሥርዓት በማን አለብኝነት ግዚያችን ዛሬ ነው የቤተ ክርስቲያኒቱ ጠበቆች እነ አለቃ አያሌው አረፍተ ዘመን ገትቱዋቸዋል የቤተ ክርስቲያኒቱን ቁንጮም ተቆጣጥረነዋል በማለት ዓለም ያወቀው ፀሐይ የሞቀው የካቶሊክ ና የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከሚለያዩበት አንዱ የሆነውን ምስልን ቀርጾ በቤተ ክርስቲያን ማቆምና ለጸሎትና ለሥርዓተአምልኮ መጠቀምን ኦርቶዶክሳዊ ሥርኣት አስመስለው ለመሾም ለመሸለም ብለው በቤተ ክርስቲያኒቱ ቅጽር  አቁመዋል፡፡ያቆሙት የፓትርያርኩ ምስል የቤተ ክርስቲያኒቱን እምነትና ሥርዓት የማይፈቅደው መሆኑን የሚያውቁ የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች በመቃወማቸውም ይህን የምእመናኑን ተቃውሞ ለማስቆም አስበው ድርጊቱን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ለማስመሰል ያልተጻፈውን እንደተጻፈ በማስመሰል ልክ በጥንቆላ ተግባሩ እንደሚያጭበርብረው ሁሉ አሁንም ምዕመኑን በመጽሐፍ ቅዱስ ያልተጻፈን እንደተጻፈ በማድረግ ለማደናገር የሞከረበት ትብታቡ እውነተኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆችን ከእምነታቸው ጋት ያህል ፈቀቅ እንደማያደርጋቸው እምነቴ ቢሆንም ይህ መሳቲና ግብር አበሮቹ የቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ ያልሆነውን እንደሆነ አድርገው በቤተ ክርስቲያኒቱም ውክልናሳይኖራቸው ያላቸው አስመስለው እያቀረቡ ያሉትን የቅሰታ ተግባር በዝምታ ማለፍ የቤተ ክርስቲያን ልጅነቴ ስለማይፈቅድልኝ ይህን ጦማር ልጽፍ ተገድጃለሁ፡፡በቀይ ቀለም የቀለመው ጌታቸው ዶኔ ከተበተበው ትብታብ የተወሰደ መሆኑን ለአንባብያን ማሳወቅ እወዳለሁ፡-

ዳሩ ግን የቅዱስ ፓትርያርኩ ሐውልት መተከል ከቤተ-ክርስቲያን ሥርዓትና ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አንጻር ተቀባይነት ያለውና ፈጣሪ ያዘዘው መሆኑን ቅዱሳት መጻሕፍት በአንድነት የሚመሰክሩት ነው:: ለእመቤታችን ድንግል ማርያያ ስዕል ፊት ድንግል ማርያምን ያከብራል ይጸልያል ይማጸናል አበው ሊቃነ ጳጳሳት በድንግል ማርያም መልክ ያስቀረጹትን በአንገታቸው ያጠለቁትንም የምስል ውጤት (አይከን) ይስማል ይሳለማል::  የስዕልና የምስል መንፈሳዊ አገልግሎቶች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሰፊው ይታወቃል:: የመስቀል አይነቶች ሁሉ መጠናቸውና ይዘታቸው ይለያይ እንጂ ሁሉም የተቀረጹ የቅርጻ ቅርጽ ውጤቶችና የምስል ዓይነቶች ናቸው::

የትኛው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሥርዓት መጽሐፍ ነው ምስልን ለጸሎት ለስርዓተ አምልኮ እንድንጠቀም የሚያስተምረው?በኦርቶዶክስ ካባ ተሰውራችሁ ወደ ቤተ ክርስቲያኒቱ የገባችሁ ካቶሊካውያን ከሆናችሁ ያስኬዳችሁዋል ታጣቂው ካህንና የሥራ ባልደረቦቹ እያተቱልን ያሉት ለቅሰጣ ስለገቡባት ቤተ ክርስቲያን እምነትና ስርዓት ሳይሆን ስለሚያምኑበት የካቶሊክ እምነት ነው፡፡ ታላቁ ሊቅ አለቃ አያሌው የጸሎታቸው በረከት ትድረሰንና አቡነ ጳውሎስን የካቶሊክ እምነት አራማጅ ናቸው በማለት አዘውትረው ይከስዋቸው የነበረው በይሆናል ሳይሆን  በእውነት እንደሆነ በእናንተ በሎሌዎቻቸው አማካይነት የቤተ ክርስቲያንዋ ጠበቃዎች አልቀዋል አሁን ቤተ ክርስቲያንዋ ባድማ ሆናለች በሚል እሳቤ የቤተክርስቲያኒቱን እምነትና ሥርዓት ካቶሊካዊ የማድርግ ተልዕኮአቸውን በአደባባይ እየፈጸሙ ያሉበት ይህ ድርጊታቸው ያረጋግጣል፡፡

በዚሁ አንጻር የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስም ሐውልት የሚያሳየው አንድ የስልጣኔ ጮራ እንዳለ ያመላክተናል:: ይህም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን አስተዳደርን ዘመናዊ ለማድረግ በምትሄደው መንገድና አስተዳደራዊ ሥራዎቻቸው ሁሉ ኮምፒተራይዝድ መሆነቸው የሥልጣኔው ተቀዳሚም ተከታይም መሆናቸውን ያመለክተናል::

በዚሁ አንጻር የቅዱስ ፓትርያርኩን ሐውልት ብናየው ቅዱስ ጳትርያርኩ ገና ብላቴና ሳሉ ለዚህ ቅዱስ መንበርና ኃላፊነት ሲጠሩ የገቡት ቃል በዚህ የዓለምና ዓለማዊ ጥበብና አካሄድ የሞቱ ለጽድቅ ግን ሕያው የሆኑ አካሄዳቸውን ከፈጣሪ ጋር ያደረጉ በመሆናቸው:: የቆመው ሐውልታቸው መታሰቢያነቱ ለሞቱለት የጽድቅና የድንግልና ህይወት ብሎም ለተጠሩለት የፕትርክና አገልግሎት መሆኑ ቅቡል የሆነ ቀኖናዊ ትንታኔ ነው::

ይህ የለበጣ አነጋገር መሆኑ መቼም ከፓትርያርኩ ይሰወራል ብዬ አላምንም አባብ ለእባብ ይተያያል ካብ ለካብ ነው፡፡ምክንያቱም የቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ከግዜ ግዜ እየባሰበት ሙስና የሰፈነበት ኮምፒውተራይዝድ ሊሆን ቀርቶ ስለ ኮምፒውተር ምንነት አስፈላጊነት ገና እየተወተወተ ያለ መሆኑን ውስጥ አዋቂ ሁሉ የሚያውቀው ነው፡፡ ጌታቸው ዶኔም ሆነ የሥራ ባልደረቦቹ እነ በጋሻው የጥቅም ሰዎች በመሆናቸው አይደለም የነቁ የበቁ ቅዱስ ማለት ውዳሴ ከንቱ እንዳይሆንባቸው ነው እንጂ እርሳቸው እኮ ከኪሩቤል የበለጠ ክንፍ አላቸው ከማለት ወደኋላ የማይሉ ይህን ድርጊታቸውን የቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶች ካልተቃወሙ ነገ “ሰው በሕይወት ሳለ ነው እንጂ ማመስገንና ክብሩን መግለጽ ከሞተ በኋላ ምን ጥቅም አለው ብለዋል ቅዱስነታቸው” በማለት ኑ ለቅዱስ አባታችን በሕይወት ሳሉ ጽላት እናስቀርጽላቸው ቤተ ክርስቲያንም በስማቸው እንትከልላቸው ባይሉ ታዘቡኝ፡፡ መቼም አንድ ግዜ ኅሊናው በጥቅም የታወረ ሰው የሚሠራውንም የሚናገረውንም አያውቀውም፡፡

ሀ. የእሥራኤል ሁሉ አባት ያዕቆብ ገና በህይወት ሳለ ሐውልቱን አቁሟል::


ያዕቆብ እግዚአብሔር በሕልሙ ተገልጾለት ከነግገረውና ከባረከው በኋላ ሥሙን ቀይሮለታል:: እሥራኤል ብሎ ጠርቶታል ያዕቆብም ሕልሙን ባየበት ሥፍራ ተንተርሶት የነበረውን ደንጊያ መሠረት ባለማድረግ የምስክርነት ሐውልት አስቀምጧል:: (ዘፍ 28÷18' 31÷45-54)

ያዕቆብ በሕይወት ሳለ ሐውልቱን አቁJል የሚል ከውሸትም ያለፈ ነጭ ውሸት ማስቀመጥህ መጽሐፍ ቅዱስን ገልጦ የሚያይ የለም ብለህ ይሆን? ያንተንና የመሰሎችህን የርክሰት ስራ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ለማስመሰል አበው ያላለፉበትን የትዕቢት ራስን የማምለክ ሕይወት እንደፈጸሙት አድርጎ ማቅረብ የርክሰት ተግባር ነው፡፡ለነገሩ ዋሽቶ መኖርን የሕይወትህ ዕጣ ክፍል ካደረግህ ካንተ የእወነት ፍሬን መጠበቅ ጌታ ከኩርንችት በለስ አይለቀምም እንዳለው ነው፡፡

ክርስቶስ በከበረ ደሙ ፈሳሽነት የገዛችሁ ምዕመናን ሆይ የዚህን መሳቲ አጭበርባሪነት የጠቀሳቸውን ጥቆሶች አንብባችሁ ማንነቱን ትረዱ ዘንድ እተወዋለሁ፡፡

አባታችን ያእቆብ ግን ለምሥክርነት የሚሆን ድንጋይ ሃውልት አድርጎ ማቆሙ ከመገለጹ ውጭ የራሱን ምስል ሐውልት አድርጎ አቆመ የሚል ከቶ በዘፍጥረትም ሆነ በሌላው የመጸሐፍ ቅዱስ ክፍል አልሰፈረም ዘፍ.31፤45፡፡

በፍኖተ ሎዛም ተንተርሶት የነበረውን ድንጋይ ወስዶ ሐውልት አድርጎ አቆመው ይላል እንጂ የረሱን ምስል ቀርጾ አቆመ የሚል ከቶም አልተጻፈም፡፡ዘፍ.28፤18፡፡

“የሚያናውጡአችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንዶች አሉ”ገላ.1፤7፡፡እንደተባለው ጌታቸው ዶኒና ባልደረቦቹ የመጸሐፍ ቅዱስን ቃል ለገዛ ጥቅማቸው ሲሉ እንዴት እያጣመሙ እንደሚጠቅሱ ከራሳቸው ጽሁፍ ተገንዝበናል፡፡

 በቅዱስ መጽሀፍ ሐውልት ለምልክትነት፣ ለምስክርነትና ለመታወቂያነት ተጠቅሱዋል፡፡በእኛም ሆነ በሌላው ዓለም በሞቱት ምዕመናን መቃብር ላይ ሐውልተ እብን ይቆማል ይህም በያዕቆብ የተጀመረ እንደሆነ ይነገራል ያዕቆብ ለሚሽቱ ለራሄል በመቃብርዋ ላይ ሐውልት እንዳቆመ በመጽሀፍ ተጽፉአል፡፡ዘፍ.35፤20፡፡ጠቀሜታው ይህ የእገሌ መቃብር ነው ተብሎ ለመታወቂያና ለመታሰቢያ እንጂ ሰማያዊ ጥቅምን ያስገኛል ተብሎ አይደለም፡፡ዳሩ ግን በአሁን ዘመን በኢትዮጵያ በአንዳንዳንድ ሙታን መቃብር ላይ እንደሚሰሩት ያለ ጌታ እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን የነቢያትን መቃብር ስለምትሠሩ የጻድቀንንም መቃብር ስለምታስጌጡ ወዮላችሁ (ማቴ 23÷29) እንዳለ ያለ የቅንጦት ሳይሆን ለምልክትነት ያህል የሚቆም ነው፡፡

በመሠረቱ በሐውልት፣ በምስልና በሥዕል መካከል ትልቅ ልዩነት መኖሩን መገንዘብ ያሻል አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ በሚለው መጽሐፋቸው ላይ የሦስቱን ትርጉም በሚከተለው መልክ ገልጸውታል፡-

ሐውልት፤በቁሙ ትክል ድንጊያ እንደ ዐምድ እንደ ምሶሶ የቆመ ክብነት ምእዙንነት ያለው ለመታሰቢያ የሚተከል የሚነደቀ ወይም ከኖራ ካሸዋ ከስሚንቶ ከድንጊያ ዱቄት ቀላቅለው ደባልቀው እያፈሰሱ የሚሠሩት ፍስ ደንጊያ፡፡(ኪዳነ ወልድ ገጽ436)

ምስል፤በቁሙ ጣዖት መታሰቢያ ግልፎ ቅርጽ ተመሳሳይ መልክ ያለው የነገር ምሳሌ(ኪዳነ ወልድ ገጽ 613)

ሥዕል፤በቁሙ መልክ የመልክ ጥላ አምሳል ንድፍ ቢጋር በውሃ በመጽሔት በጥልፍ በስፌት ወይም በቀለም በወረቀት ገዝፎ ተጥፎ ከጽቡር ከእብን ከዕፅ ከማዕድን ታንጦ ተቀርጦ ተሸልሞ አጊጦ የሚታይ የሚዳሰስ ነገር(ኪዳነ ወልድ ገጽ 673)

ከላይ በተገለጸው መሰረት ምስል ማቆምና ሐውልት ማቆም የተለያዪ ናቸው። ቤተ ክርስቲያናችን ለጸሎት፣ ለትምህርትና ለሥርዓተ አምልኮ ደግሞ ሥዕላትን ትጠቀማለች፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንደ ሌሎቹ አኃት አብያተ ክርስቲያናት ምስልን (three dimensional) የሆነን ቅርጽ ለሥርዓተ አምልኮ አትጠቀምም። በቤተ ክርስቲያን ቅጽርም እንዲቆም አትፈቅድም። ይህ አስተምህሮ ኦርቶዶክሳውያን ከካቶሊካውያን የሚለዩበት አንዱ መለያ ነው፡፡

ባለ ሽጉጡ ሊቀ ካሕናትና እነዲያቆን በጋሻው በፓትርያርኩ አይዙአችሁ ባይነት በቤተ ክርስቲያቱ ላይ እያነገሱ ያሉት የካቶሊክን ባህል ነው፡፡ 

የሚከተለውን ዓይን ያወጣ የጌታቸው ዶኔን ውሸት ትመለከቱ ዘንድ እጋብዛችሁዋለሁ፦       

ሐ. ከሙሴ ቀጥሎ የእሥረኤልን ሕዝብ ይመራ የነበረው ኢያሱ 12ቱን የእሥራኤል መሪዎች ጠርቶ ገና በሕይወት እያሉ ሐውልት በስማቸውና በቅርጻቸው አቁሞላቸዋል ኢያሱ ይህንን ያደረገበት ምክንያት እግዚአብሔር ጠላቶቹን መትቶለት የዮርዳኖስን ባህር እንደመሬት እየረገጡት በመሻገራቸው ይህ የፈጣሪ እርዳታ ለምስክርነት ይሆን ዘንድ የመሪዎቹን ሐውልት በቦታው ላይ ማለትም በዮርዳኖስ ባሕር ዳርቻ በስማቸውና በቅርጻቸው አቁሞላቸዋል:: (ኢያሱ 4÷1-9)

መ. የኢያሱ የምስክርነት ሐውልት (ኢያሱ 24÷26) ይህ ብልሁ የእስራኤል መሪ ኢያሱ አገልግሎቱን የሕጉንና የአስተዳደር ሥርዐቱን ለሕዝቡ ሊሰጥና ከሕዝቡ ጋር ቃል ኪዳን ሲያደርግ እርሱ ገና በሕይወት እያለ በራሱ ስምና ምስል ሐውልት አሠርቶ በእግዚአብሔር ቤት ደጅ ለምስክርነት አቁሞታል::

 የእንጀራ ከፋቻችሁን የአቡነ ጳውሎስን ምስል ለማቆም ኢያሱ ያላቆመውን ምስሉንና የመሪዎቹን ምስል ሐውልት አድርጎ አቆመ ብላችሁ መዋሸት ምን ይባላል? 

ስለሆነም ይህንን የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያንና ትምህርትን መሠረት በማድረግ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ጋር ሕብረት ያላቸው አሐት አብያተ ክርስቲያነት ግብፅ ሕንድ አርመንና ሶርያ የሃይማኖት መሪያቸውን መልክ በሰውነታቸው በመነቀስ በመቀለምና በመወቀር ብሎም ገና በሕይወታቸው እያሉ ሐውልታቸውን በማቆም በታሪክ ቀዳሚዎች ናቸው::
 እስቲ የየትኛቸው አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ምስል ነው በሕይወት ሳሉ በቤተ ክርስቲያናቸው ተቀርጾ የቆመላቸው? የአንዳቸውን ስም ሊጠቅሱልን እንኳን አልቻሉም ከላይ በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተጻፈ በማስመሰል ሊያታልሉ እንደሞከሩት ያለ ነጭ ውሸት በመሆኑ ነው፡፡ከእነዚህ አብያተ ክርስቲያናት ግን የአንዳቸውም መሪ በህይወት ሳሉ ምሳላቸውን እንዳቆሙ ከጌታቸው ዶኒ በስተቀር ቆመላቸው የተባሉትም ጭምር አንዳች የሚያውቅ ሰው የለም፡፡ 

37 comments:

Mahlet (እሚ) said...

I could not be happier than this thank you thank you DEJE SELAM.Indeed peace is starting to restore.

EgeziAbeHer yemesgen
EgeziAbeHer yemesgen
EgeziAbeHer yemesgen

ሰናይ said...

ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ።

awudemihiret said...

ይትባረክ እግዚአብሄር አምላኮሙ ለአበዊነ ዘገብረ አቢየ ወመንክረ።

Anonymous said...

egziabher yimesigen... I wish the way dejeselam presents the news could have had a different tone..... it sounded as always..... as if HH is not cooperating at all..... as if he has no potential of correcting his faults unless forced etc.... this approach sounds familiar... hmmm.. not spiritually constructive though..

Anonymous said...

If this decision stands, one down for EOC.

Anonymous said...

ደጀ ሰላሞች የምን መርዶ ነው የምታሰሙን? አምስት መቶ ዓመታት ሳይፈርስ ይቆያል የተባለለትን የቅዱስነታቸውን ሐውልት ሊያፈርሱብን ነው? ባይሆን አምስት ወር እንኳን ይሙላው እንጂ !!!! ቂቂቂቂቀ….ደግሞስ ወይዘሮዋ ጳጳስ ሁለተኛ ወደ ቅፅረ ቤተክህነት እንዳትገባ መከልከል ምን የሚሉት ነው? አንዳንዶች እርሷን ፍለጋ እንዲንከራተቱ ነው ወይስ መንበረ ጵጵስናውን ወደ እርሷቤት ለማዛወር? እስኪ እድሜ ከጨመረልን ገና ብዙ እንሰማለን !

Anonymous said...

GOD IS GREAT
ባካችሁ በርትተን እንጸልይ
ኦ አምላኬ፣ የአባቶቻችንን አንድነት አጽና፤ ምእመናን ሆይ፣ እባካችሁ በርትተን እንጸልይ
ምእመናን ሆይ፣ እባካችሁ በርትተን እንጸልይ.
ምእመናን ሆይ፣ እባካችሁ በርትተን እንጸልይ.
ምእመናን ሆይ፣ እባካችሁ በርትተን እንጸልይ.
ምእመናን ሆይ፣ እባካችሁ በርትተን እንጸልይ.
Ehete micheal

123... said...

በ አጅ የሚዳሰሰው ሀውልቱ መፍረሱ ጥሩ ነው ግን በ አካል ቆሞ የማይታዩት ሐውልቶች ሲፈርሱ ነው ትልቁ ደስታ መሆን ያለበት
አነርሱም የ ዘረኝነት ሃውልት፣
የ ፍቅረ ንዋይ ሃውልት፣
የተዝረከረከ አሰራር ሃውልት፣
የ ጉቦኝነት ሃውልት፣
ግልፅ አሰራር የማጣት ሃውልት፣
በጎችን አለመጠበቅ ሃውልት፣
ሃውልት ሃውልት አለን ብዙ የሚፈርስ ገና ነው።

Anonymous said...

Demissie
O! our Loard I thank you what did with our spritual fathers. Our Lady Holy Virgin Mary please helps our fathers to make the right decision for our mother churches.

God may bless EOC and Ethiopia

123... said...

አዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ደሞ ለማፍረሻ ብሎ ብዙ ብር አንዳይወጣ አሁድ ለ ቅዳሴ ስንመጣ አናፈርሰዋለን!!!

kebede.com said...

ሁሉን በጊዜው የሚስራ እግዚኣብሔር ይመስገን። ኣባቶቼ እግዚኣብሔር የማስፈጸሚያውን ሃይል ይስtachehu. ውሳኔው ይፈጸም!!

እግዚኣብሔር ይመስገን

kebede.com said...

ሁሉን በጊዜው የሚስራ እግዚኣብሔር ይመስገን። ኣባቶቼ እግዚኣብሔር የማስፈጸሚያውን ሃይል ይስtachehu. ውሳኔው ይፈጸም!!

እግዚኣብሔር ይመስገን

Unknown said...

" ለአምላካችንና ለአባታችንም እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን። " ፊል4:20

Anonymous said...

+++
ልዑል እግዚአብሔር ሆይ የቤተክርስቲያንን ትንሳኤ አሳየን:: ምእመናን ሆይ፣ በርትተን እንጸልይ:: አባቶችም በርቱ::

ረድኤት እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን:: አሜን::

SendekAlama said...

+++
አንቺ ቤተ ክርስቲያን ሆይ ትንሣኤሽን ልናይ ይሆን? ትንሣኤሽ የእኛ ትንሣኤ ነውና እውነት ያርገው ! ያጽናው!

ዘሚካኤል said...

የእርሱ ሰአት ሲደርስ ሁሉም ይፈጸማል:: እኛ እንትጋና እንጸልይ። ስላሴ ስራቸውን አይዘነጉም። ቤቱን ይጠብቃል። ተመስገን።

Anonymous said...

ሐውልቱ ለብዙ ሰወች መሰናክል ሆኗልና ከቦታው መነሳት አለበት
የሚለው የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የሚያስደስት ዛሬም አባቶች በችኮላ ሳይሆን ረጋ ባለ መንፈስ እንደሚሰሩ ያሳያል። አባቶች እስከ ዛሬ ለወቀስናችሁ ወቀሳ በአባትነት መንፋሳችሁ ይቀር ትሉን ዘንድ ራሳችንን ዝቅ አድርገን ይቅርታ እንጠይቃለን።
የዘንድሮ ውሳኔያችሁ ለቡ በሃዘን የተሰበረውንና ለማያምኑ መላገጫ የሆነውን ከርስቲያኑን ሕዝብ በሥራችሁ ፈውሳችሁታልና ለአባቶቻችን ኃይልን የሰጠ ለእናንተም ኃይልን ያድላችሁ በርቱልን።

አሁን ወሰናችሁ ማለት ተፈጸመ ማለት ነው ለማለት ያስቸግራል እስከዛሬ ያልወሰናችሁት ምን አለ አፈጻጸም ላይ ግን ችግር ብዙ ጊዜ ይታያል። ይህም < የካህን ስብሰባው አዘቅት ማሰሪያው አሽክት> የሚለው በእናንተ እንዳይደርስ ከአዲስ አበባ ሳትወጡ ሁላችሁም ባላችሁብት ኃውልቱን አስነሱት። አለበለዚያ ውሳኔያችሁ ሁሉ ከእንደዚህ በፊቱ የውሃ ሽታ እንዳይሆን ያስፈራል።

Anonymous said...

ይትባረክ እግዚአብሄር አምላኮሙ ለአበዊነ ዘገብረ አቢየ ወመንክረ።የአባቶቻቸን አምላክ እግዚአብሄር ይባረክ ይመስገን
የቤ/ክ አምላክ ፍጻሜውን
አሳምረው::እልልልልልልልልልልልልልል...........................................................................................................................................

Anonymous said...

+++
Glory be to God, the Almighty. Then, if our fathers are becoming so strong, what an excuse will I have to distance myself from Him?...This is a lesson to me who has forgotten to do his assignment with due to such excuses...

Anonymous said...

This is really a great job of our Holy Father Almighty GOD! Thank you God that performs this things. Now I am realizing that God is with us. Dear fathers of Holy synod this is what a true orthosdox christains longed for long.Now this is time for God to do His work. Bless you all! Eeeellllleeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeeee!

Tesfa said...

ዚናውን ሳነብ እንባየን መቆጣጠር አቃተኝ እውነት ነው ወይስ ምንድን ነው የማነበው እያልኩኝ አለቅስሁ:: አምላክ ሆይ እባክህ እውነት አድርገው እያልኩ አለቀስኩ:: ቅዱሱን የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በሰላም አስፈጽመህ ውሳኔውቹንም በተግባር እንዲውሉ አድርገህ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላምን ለምዕምናን አንድነትን ሰጠህ አሳየን:: እኛም እንደልጅነታችን ለቤተ ክርስቲያን የሚጠቅም ስራ ለመስራት አብቃን:: ይሄን በጎ እና ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሚጠቅም ዘና እንድንሰማ ስላደረግህ እናመሰግንሃልን::

raguel orto said...

የቤተክርስቲያን፡አምልክ፡በእውነት፡ምስጋና፡ይገባዋል፡፡እመቤቴ፡ምስጋና፡ይድረስሽ፡፡

raguel orto said...

የቤተክርስቲያን፡አምልክ፡በእውነት፡ምስጋና፡ይገባዋል፡፡እመቤቴ፡ምስጋና፡ይድረስሽ፡፡

Anonymous said...

እዚአብሔር አምላክ የተመሰገነ ይሁን::

የሲኖዶሱን ውሳኔ እንዲፈፀም መላ አበጅተው ማለፍ አለባቸው አባቶች::

Anonymous said...

do not rash for judgement everybody, we will see. you think ethiopian orthodox church synod back home has power to do this decision? i don't think for me it looks like theory . Tomorrow , you willl see everything is the same.Nothing , Nada. the same abba you saw yesterday, you will see it tomorrow.

Anonymous said...

እኔ ገርሞኝ ነው የሚጽፍላችሁ ያለሁ

ዛሬ ቀን ጓደኛዬ ደጀ ሰላምን አንብብ ብሎ ጋብዞኝ እውነት ከሆነ እንደ ነገረ መለኮት ባለ ቤትነት ሳይሰማኝ አልቀረም
አንድ አባት ፃዲቅ ነው ተብሎ በስሙ ቤተ ክርስቲያን እንዲሰራለት፣ ታቦት እንዲቀረጽለት፣ መንፈሳዊ መዘክር እንዲደረግለት ከተፈለገ ከሕልፈተ ሥጋው በሗላ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የሰውዬውን ሥራን ከ “ሀ” እስከ “ፖ” ተጠንቶ ሲጸድቅ ብቻ ነው። ስለዚህ እውነት እነዚህ ሐወልቱን በማቆም የተሰለፉ እነ” እገሌ ወ ወይዘሮ” የተጠቀሱት ሰዎች በየዋህነት ከሆነ ንስሀ ገብተው ይቅርታ ለፈጣሪ ይቅርታ ለወገን ቢጠይቁ የሚመጎስ መንፈሳዊ ባህል ነው ባይ ነኝ። ቅዱስነታቸውም ጥላ ወድቆባቸው ነው እንጂ በዚህ መንጋ አይገኙም ነበር ። አሁንም ደግሜ ላሰምርበት የሚፈልገው የተጻፈውን ሁሉ ‘የሰው እጅ’ የሌለበት ንጹሕ ከሆነ ብቻ ነው። ለማንኛውም ለዚሁ ፈተና መብቃታቸው ራሱ ቀላል ትምህረት ስላልሆነ እኛም የቆምን መስሎን እንዳንወድቅ ይህ አሉታዊ ስራን መማርያ አድርገን መጠንቀቁ አይከፋም።
የቤተ ክርስቲያን ባለ ቤት ከስሕተት ይጠብቀን!

Anonymous said...

ከአባ ጳውሎስ የተጠራቀመ ሸርና ተንኮሎች መካከል የሚጠቀሱት ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኖ ጉባዔውን ሲያጠናቅቅና ወደየመጡበት ሊቃነጳጳሳት ሲመለሱ የውሳኔዎቹን አፈጻጸም ማዘግየት፤ አለመፈረም፤ የውሳኔውን መንፈስ የሚሸረሽር ደብዳቤ ማብረር፤ አዲስ የተቃውሞ ሃሳብ ማንሳት፤ እያወቁ መርሳት፤ ችላ ማለትና በግልጽ መጋፋት ወ ዘ ተ...እያየናቸው የቆየናቸው ጠባያቸው ነው። ድፍረት የታየበትንና ለቤተክርስቲያን የሚበጀውን የወሰነውን የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ወስኖ በመለያየት ብቻ ከፍጻሜ ይደርሳል ማለት ደክሞ መና በመሆን ወደቀደመው ለቅሶና ሃዘን እንዳይመልሰን ትልቅ ፍርሃት አለኝ። ሰውዬው የመንግስት ወዳጅ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ሲወሰን አንቀላፍተው ሲበተን የሚነቁ ፈላስፋ ናቸውና እጅግ፣ እጅግ የአፈጻጸም ጥንቃቄ ከወዲሁ መላ ሊባልበት ይገባል ባይ ነኝ። ሊላይ ነኝ

Anonymous said...

Nisebiho legziyabhare.

Be meman fit endetmereke be meman fit yifres.

Anonymous said...

WOW!!!!!!!

Anonymous said...

ቅዱስ ሲኖዶስ በእውነትም መንፈስ ቅዱስ የሚመራው ነው በአሁኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ መሰረታዊ የሆኑ ውሳኔውች እየተወሰኑ ነው አምላክ አባቶቻችን ያፅናልን ፡፡ ነገር ግን አንድ የምፈራው ነገር አለኝ እነዚህ ሰዎች በእግዚያብሄር ፊት ስህተት ሲፈፅሙ ያለፈሩ ያልተመለሱ አሁን ውሳኔውን በፀጋ ይቀበላሉ ብየ አለምንም የቤተክርሲቲያንም ፈተና እንድህ በቀላሉ ዋጋ ሳያሰከፍል የፈታል ብየ አልጠብቅም እግዚያብሄር በፆሎት እንድንበረታ ይርዳን፡፡ወንድሞቻችንን የጣለች ሀጢያት ነገ እኛንም እንዳትጥለን አምላክ ይጠብቀን፡፡

Anonymous said...

I like the decision. But it was better if they demolished the erected secular monument at their heart. It was already spiritually demolished before they erect it. I am happy if they remove it from our church compound and installed it somewh...ere in the city as decoration rather than demolishing it totally. It will be used to remember how the existing era Holly Fathers act in the name of God for our next generation.

Any Cynodos member who has such kind of self fame will have to go to the parliament even if they get space to erect such kind of stone for their name or they will have go to bush with gun to get such autocrat power

Dani, I consider how your article on "SEW BEKUMU..." has had an impact on their internal selfish monuments. It was sharp from secular point of view (politically) and spiritual sides to make this action. Keep it up Dn. Daneal.

T/D said...

This is realy the work of the Holy Spirit. Glory to The Father, and of The Son, and of the Holy Spirit Amen.

However, I couldn't beleive this unless I see it demolished. Why don't we campaign to move it from now on before the Sinodos adjornes the meeting once and for all until next year.


I will say that H.H. will really deserve the monument if this decision is implemented while he is alive. So instead of demolishing it, it should be moved to some place and later when the right time comes it will be back , hope by then it will not be against the Dogma of the church.

Cher were yasemachihu!

Dirsha said...

ዚናውን ሳነብ እንባየን መቆጣጠር አቃተኝ እውነት ነው ወይስ ምንድን ነው የማነበው እያልኩኝ አለቅስሁ:: አምላክ ሆይ እባክህ እውነት አድርገው እያልኩ አለቀስኩ:: ቅዱሱን የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በሰላም አስፈጽመህ ውሳኔውቹንም በተግባር እንዲውሉ አድርገህ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላምን ለምዕምናን አንድነትን ሰጠህ አሳየን:: እኛም እንደልጅነታችን ለቤተ ክርስቲያን የሚጠቅም ስራ ለመስራት አብቃን:: ይሄን በጎ እና ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሚጠቅም ዘና እንድንሰማ ስላደረግህ እናመሰግንሃልን::

Tilahun Z Awassa said...

ኧይ በጋሻው!
ኧይ በጋሻው! “ድምፅ ብቻ”


“ሐውልቱ ለ500 ዓመት ይጠቅማል፣ አፈር ውስጥ ቢቀበርም አይበላሽም”

እንኳን ለ500 ዓመት አንድ ዓመትም አልቆመም::

Anonymous said...

እንስራ ለካህን ኑሮ ምሳሌ ነው።
እንስራ ከእግዚአብሔር ብቻ ለሚገኝ ዉሃ ማምጫ ነው ፣ካህናትም ከእግዚአሔር ለሚገኘው ስልጣንና እውቀት መምጫ ናቸው ።
እንስራ የዘወትር መመላለስና ከአለት ጋር መጋጨት ስላለበት ተጠንቅቀው ካልጠበቁት መሰበርም ከሌላው ሸክላ ሁሉ በእንስራ ይፀናበታል፣
ካህናትም ከጥሩውና ከብርቱው እግዚአብሔር ዘንድ መቅረብ ስላለባቸው ካልተጠነቀቁ መቀሰፍ መቀጣት ይፀናባቸዋል ።
እነዚህም ተጠንቅቀው ለፈጣሪያቸው ብቻ አገልጋይ ቢሆኑ ባለትልቅ ፅድቅ ይሆናሉ ፣ለፍትወታቸው ሲሉ አገልግሎታቸዉን ለስጋዊ ጌቶች ቢያደርጉ ግን እንደ እንስራው ከንቱ ይሆናሉ።
( ልዑል ራስ ካሳ ኃይሉ " ፍኖተ አአምሮ " ገፅ ፪፻ ፸፯ )

Anonymous said...

ሓውለቱ ለማፍረስ ኮሚቴ እያቋቋመ ነው አሉ የአዋሳው ሐሳዌ መሲህ

አባል መሆን የምትፈልጉ ተመዝገቡ
ለደማሚት መግዣ የሚሆንም አዋጡ በአንድ ጊዜ አመድ ለማድረግ ሐውልቱ፡፡

Anonymous said...

GOD REALY HAS TIME TO DO EVERY THING.
I CAN'T EXPRESS MY FEELING !!!
THANKS TO HIM.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)