October 25, 2010

የሐዋሳ ምእመናን የደረሰውን በደል በማስረጃ አቀረቡ፤ አጣሪው ተልዕኮውን ፈጽሞ ተመልሷል

(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 25/2010፤ ጥቅምት 15/2003 ዓ.ም):- የሐዋሳ ምእመናን የደረሰውን  በደልና ጥፋት የሚያሳይ ባለ 73 ገጽ የጽሑፍ ማስረጃ እና 6 የድምጽ እና የምስል (Audio and Video) ችግሩን ለማጣራት ወደ ቦታው ላቀናው ልዑክ አቀረቡ። አቤቱታ አቅራቢዎቹ ያቀረቡት ማስረጃ በደምሳሳው ሲታይ በሀ/ስብከቱ እና በልዩ ልዩ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ተፈጽሟል የሚሉትን የገንዘብ ምዝበራ የሚያሳይ፣ በየዐውደ ምሕረቱ ስለተፈፀሙ አባቶችን የማዋረድና የማንኳሰስ ተግባራት፤ ስለተፈፀሙ የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ጥሰቶች ወዘተ የሚያትት ነው።


የአጣሪ ኮሚቴው አባላት  ዝርዝሩን ከሰሙ በኋላ “እንዲህ ዓይነት ነገር ገጥሞን አያውቅም፤ ለመናገር የከበደ፣ የሚያሳፍር” መሆኑን ተናግረዋል ተብሏል። ጉዳዩን ለመከታተል የገቡ የክልሉ የአስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ደግሞ “የሰማነው ነገር የከበደ ያስቸገረ ነገር ነው። የተወሳሰበ ወንጀል ነው የተፈፀመው” ማለታቸው ተሰምቷል።

በወቅቱ የተከሳሾቹ ቡድን አባል ዲ/ን ያሬድ አደመ በቀረበባቸው ማስረጃዎች ከመደንገጡ የተነሣ “ቤተ ክህነቱን እናውቀዋለን። እንዲህ ማስረጃ ማጠናቀር አይችልበትም። እንዲህ የሚያደርገው ማ/ቅዱሳን ነው። ዐውደ ምሕረቱን ማንም አይከለክለኝም። ነገ እቆምበታለሁ” ሲል ተሰምቷል።

18 comments:

ጂግሳ said...

በለስዋን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል፡፡ የታገሱት ሁሉ የአግዚብሔርን ድንቅ ስራ ያዩታል፡፡ አሁንም በትዕግስት መጠበቅን እመርጣለሁ፡፡ እግዚአብሄር ለቤቱ ቀናተኛ ነው፡፡ ወንጌሉስ እስመ ቅንዓተ ቤተከ በላኣኒ አይደል ያለው፡፡

Anonymous said...

Oh God,Glory to you,I think now we are in a good track!

Anonymous said...

tehadisowoch mahibere kidusann endet endemitelut!yhin yalkubet miknayat ato yared yhin yaregew mahibere kidusan new lemin ylal? yetehadisowochin gawad ymiberebir hulem mahiberu new ende? mahiberekidusanin yemitala tehadisoo weym benesu yetemola yewah new!yh premiss endet new?

Unknown said...

Be ergetem ewnet tedebeka atekerem
ke dilla eske hawasa yetederegew gife ena mizebera ye tegefu abatoch enba wodko aykerem abatochachen ewnetun aytew ewneten endeferdu endeastekaklu yadergelen amen.

Anonymous said...

yasafiral, Feyel wedi kizimzim wediya

Welete Maryam said...

ለሁሉም ጊዜ አለው አይደ ያለው ጠቢቡ ሰለሞን...

desa said...

goodjob dejeselam! bertu

Anonymous said...

Dear Mahibere Kidusans
Where are u in Hawassa. Your name is stated so much in hawassa. You should say some thing... Any way we are having a chance to evaluate u.

Dirsha said...

Our mother is in danjer. The presence of the Mafiya group is showing us such a result otherwise it could have been solved early.I fear the result may not be complet b/c the mafiyas have a big branch and they are realy supported by the patriaric( cause for every multifacited problems of our church). So let's pray and play important roles in this critical time. Especialy those who are near to the government please tell the real situation and make them to do the write measure b/c it is the government who is playing pivotal role in the dicision of our fathers interfering by opposing the national low.Amilake Israel Yitebiken

Anonymous said...

Lehulum endeyesiraw yikefelewal.

zikere said...

egeziabhere lhezibu yemibjewene yameta

Anonymous said...

ጉዳዩን ረጋ ብሎ ማየት ያስፈልጋል ፡፡ እኔ ሁለት አይነት ስጋ አለኝ
1. በትክክል ተፈጽሞ ከሆነ የፈጸሙት ሰዎች ተሃድሶዎች አሊያም መናፍቃን ወይም የአህዛብ ወገን የሆኑ ነገርግን የቤተክርስቲያን ልጅ የሚመስሉ ተኩላዎች ናቸው፡፡
2. ህዝቡን ባልሆነ መንገድ እንቀሳቅሰውና መረጃ አጠናቅረው የቤተክርስቲያንን አባቶች ከህዝቡ ለማጣላትና ቤተክርስቲያኗን ለማፍረስ ሚጣደፉ ሰዎች እንዳይሆኑ እፈራለሁ፡፡ ነገር ግን ማህበረ ቅዱሳን በወቅቱ እግዚአብሄር ያስነሳው የቤተክርስቲያን ጠበቃ እንጂ ሌላ እንዳልሆነ የማይካድ ሃቅ ነውና የራስን ችግር ማህበረ ቅዱሳን ላይ መጣል ተገቢ አይደለም፡፡

Anonymous said...

እኔ እኮ በጣም የሚገርመኝ ....በሆነ ባልሆነው ሁሉ "ማኅበረ ቅዱሳን" ነው መጠምጠሚያቸው!??....... የፈረደበት ምስኪን:: አባላቱ ግን ታድለው?!! ከዚህ ሁሉ መከራ በኋላ እውነት አርነት /ነጻ/ ሲያደርጋቸው ማየት እፈልጋለሁ የምር:: ....እውነት ማለት ደግሞ እግዚአብሔር ነውና::

ድሬያ መደአ said...

ምን አለበት ማ/ቅዱሳን አርፎ ቢቀመጥ አታወጡትም እንጂ የናንተን ጉድ እንጽፍ ነበር አቤት እግዚኦ !!!

yemelaku bariya said...

ያሬድ ጥፋቱን እንዳመነ ነገር ግን እንዳልተጸጸተ የሚንቀሳቀሰውም በዓላማ እንደሆነ የራሱ ንግግር መረጃ ነው:: "ይህን ቤተ ክህነቱ ሊያቀነባብረው አይችልም ማኅበረ ቅዱሳን ነው" ይህ አባባል ስራውን ምንያህልበረቀቀ ሁኔታ እየሰራ እንደሆነና በዙሪያው ያሉሰዎች በማይረዱትመልክ እየተንቀሳቀሰ እንደነበርና ይህን ሊደርሱበት የሚችሉትን በሱ ግምት ኮንኗል፣ ድርጊቱን ግንአላስተባበለም:: ከመድረኩ ማንም አያወርደኝም ያለው ትቢተኝነቱን እና የጀመረውን ተልኮ ሳይፈጽም ላለመቅረት ጥረት እያደረገ እንደሆነ ያስረዳል:: የሱ ግምት ይህ ይሁን እንጂ እሱን የከሰሰው የአዋሳና አካባቢው ምእመናን እንጂ ማ/ቅ አይደለም የቀረበው መረጃ ራሱ የፖተለከውን እንጂ ሌላ አይደለም መከላከያውም ሚስጥሬን ለምን አወቁብኝ እንጂ አላደረኩትም ወይንም ተጸጽቶ አጥፍቻለሁ አይደለም:: ምንአይነት ትቢት ነው:: ማንን ቢተማመን ይሆን:: አይ ክህደት:: የባህሪ አባቱ (አባ ) መላኩን የተሳጣቸውን ተልኮ ያልተወጡ ደካማ እና ለአደራ የማይበቁ በመሆናቸው የተሰጣቸውን አስኬማ መልሶ ለአስኬማው የሚበቃ አባት እስኪገኝ መቀበል ነው:: ደግሞ ይህንን ፖለቲካ አድርገውት በሃገራቸው አሜሪካ እንዳያምሱን ሁለመናቸውን ማለትም ከቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸውን ማንሳት ያስፈልጋል:: የሳቸው ምኞት በሊሞ መንሸራሸር ነው አሁን ግን የዲሲ ሚካኤል ምዕመናን ሳቸውን በሊሞ የሚንደላቅቋቸው መስሏቸው ከሆነ ያ የለም ከአሁን በፊትም ያከብሯቸው የነበረው የቤተ ክርስቲያን ወገን መስለዋቸው ነው:: አሁን ያ ተለውጧል ማንነታቸውን እና የማንን ተልዕኮ ለማስፈጸም እየተንቀሳቀሱ እንደሆን ራሳቸው አረጋግጠውልናል:: ነገር ግን ራሳቸው የሊሞ ሹፌር ሁነው እያንሸራሸሩ መንሸራሸር ይችላሉ::

yemelaku bariya said...

ያሬድንና ማኅበረ ቅዱሳንን የተለያዩ መሆናቸውን እኮ እናውቀዋለን:: እነሱ አስራታቸውን ከፍለው በነጻ አገልግለው ከዛ በተጨማሪ አውጥተው የአብነት መምህራንን ረድተው ገዳማትን ደግፈው ነው እነ ያሬድና ግብረ አበሮቻቸው ቤተ ክርስቲያንን ( with out investment, they collect a return) የሃብታቸው ምንጭ አድርገው በምትኩ አብነቱ ጠፍቶ በነሱ ንግግር አውደ ምህረቱ እንዲሞላ ገዳማቱ ተዘግተው የነሱ ትምህርት እና ክህደት በአዳራሽ እንዲሆን ነው:: ይህእንግዲህ አንዱ የሚያለያያቸው ነው:: ያሬድና መሰሎችህ ልታውቁት የሚገባው ስለ ቤተ ክርስቲያን አንዲነት፣ ህልውና፣ እና እንዲሁም ስለተዋህዶ እምነት የቆመ ሁሉ ማህበረ ቅዱሳን ነው:: ይህደግሞ እነ አባታችን አትናቲዎስ ዘእስክንድሪያን ሁሉ ያካትታል:: እርግጥ በተረፈ አርዮሳውያን ዘንድ ተዋህዶዎች አይወደዱም:: ድሮውንስ ብርሃን ከጨለማ ፣ በጎነት በክፋት ፣ እምነት በክህደት ፣ ለጋስነት በንፉግነት ዘንድ ፈጽሞ አይዎደዱም::

Anonymous said...

ዉድ ደጀ ሰላም
የቅዱሳን አምላክ ይርዳን እንጂ በያሬድ እና በአባ ፋኑኤል ላይ ያደረዉ ሰይጣን በቀላሉ የሚወጣ አይደለም
የሲኖዶስ አባላት ትክክለኛ ዉሳኔ እንዲወስኑ ፀሎት ያስፈልጋል
ነገር ግን ላለፉት 2 ቀናት አዉደ ምህረታችን በመከበሩ በጣም ደስ ብሎናል እ\ር ይመስገን
ከአሁን በሁዋላ አዉደ ምህረታችን የመናፍቃን መፈንጫ አትሆንም
ቢሞክሩ ግን አንገታቸዉን አንቀን ነው የምናወርዳቸዉ

Anonymous said...

hawasan yatseda amlak betekihinetin yiffewisilin

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)