October 24, 2010

የቅ/ሲኖዶስ ሁለተኛ ቀን ውሎ


  • አቡነ ሳሙኤልን ከአ.አበባ ለማስነሣት የአ.አ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎችና ፀሐፊዎች ፈረሙት ተብሎ ለአጀንዳነት የቀረበው ደብዳቤ ውድቅ ተደርጓል፤

(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 24/2010፤ ጥቅምት 14/2003 ዓ.ም):- ቅ/ሲኖዶስ ትናንት ቅዳሜ ሁለተኛ ቀን ጉባዔውን ቀጥሎ ዘጠኝ አባላት ባሉት አጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴ ተዘጋጅቶ የቀረበለት የአጀንዳ ዝርዝር ላይ ተወያይቶ አጽድቋል። አጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴው ያቀረባቸው አጀንዳዎች ሙሉ በሙሉ ከመጽደቃቸውም በላይ ቅዱስ ፓትርያርኩ ያቀረቧቸው ሌሎች ሁለት አጀንዳዎችም በተጨማሪ ተይዘዋል። በውይይቱ ወቅት “አዳዲስ ጳጳሳትን ስለመሾም” ቀርቦ የነበረው ሐሳብ ውድቅ የተደረገ ሲሆን አሁን የሚደረገው ሹመት አስፈላጊ አለመሆኑን ምልዓተ ጉባዔው ተስማምቶበታል። “ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ለማሻሻል” የቀረበውም አጀንዳ እንዲሁ ውድቅ ሲደረግ “ባለው ሕግ መቼ ተጠቀምንበት እና ነው አዲስ ሕግ ያስፈለገን?” የሚል ጥያቄ ቀርቦበታል። ለቅ/ሲኖዶሱ “አዲስ የስብሰባ ሥነ ሥርዓትና ሥነ ምግባር ስለማውጣት” በተነሣው ሐሳብ ላይም እንዲህ ዓይነቱ ደንብ በመንፈስ ቅዱስ ለሚመራው ለቅ/ሲኖዶስ ተስማሚ አይደለም በሚል ውድቅ መደረጉን ምንጮቻችን አብራርተዋል።

በቅ/ሲኖዶስ የዛሬ ውሎ ስለ አዲስ አበባ ሀ/ስብከት እና ስለ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ጉዳይ እንዲያጣራ የተሰየመው አጣሪ ኮሚቴ ሪፖርት በንባብ ተሰምቷል። በዋነኝነት ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልን ከሚነሣባቸው ክስ ሁሉ ነጻ ያደረጋቸው ነው የተባለው ይህ ሪፖርት ብፁዕነታቸው በታገዱበት ወቅት ቅሬታቸውን በደብዳቤ ሲገልፁ ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መዋቅር በመዝለል ለመንግሥት አካላት ግልባጭ ማድረጋቸው በአሉታዊነት ተነሥቷል። ሪፖርቱ በጠቅላላው ብፁዕነታቸውን ሲቀርብባቸው ከነበሩት ክሶች በሙሉ ነጻ አድርጓቸዋል ተብሏል። ሪፖርቱ ከቀረበ በኋላ ለውይይት ለሰኞ ተቀጥሯል።

ቅ/ሲኖዶስ ዛሬ እሑድን እረፍት አድርጎ ነገ ሰኞ ስብሰባውን ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል።
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)