October 7, 2010

«የአበባ ወር» ወርኀ ጽጌ

(ማ/ቅዱሳን ድረ ገጽ):- በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ከመስከረም 26 ቀን እስከ ኅዳር 6 ቀን ያለው ጊዜ ወርኀ ጽጌ ይባላል፡፡ ይህ ወቅት ምድር በአበቦች ቀለምና መዓዛ የምታጌጥበት በመሆኑ «የአበባ ወር» ወርኀ ጽጌ ተብሏል፡፡

አበባ የፍሬ እናት ነው፡፡ አበባን ያየ ሰው ሕይወቱ በተስፋ ትሞላለች፡፡ መልካሙ ፍሬ ከአበባው ይገኛልና፡፡ እመቤታችንም የተባረከ ፍሬ መድኃኒተ ዓለም ኢየሱስ ክርሰቶስን ያስገኘች አማናዊቷ አበባ ናት፡፡ የአዳም ተስፋ መፈጸሙን፣ የነቢያት ትንቢት መድረሱን ያበሰረችን የድኅነት ምልክት እርሷ ናት፡፡ «ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል» እንዳለ ነቢየ ልዑል ኢሳይያስ (ኢሳ 7÷14)፡፡
የአበቦች መፍካት የጥጋብ ዘመን መምጣጡን ያበስራል፡፡ ወርኃ ክረምት ዘር ገና በምድር ላይ ስለሆነ ጎተራው ይሟጠጣል፡፡ መሶቡ ድንግጥ ይላል፡፡ የክረምቱ ጊዜ በጎመንና በቅጠላ ቅጠሉ በጥራጥሬው ጭምር ይወጣል፡፡ ከአዲሱ ዘመን መባቻ ጀምሮ ግን «የጎመን ምንቸት ውጣ የገንፎ ምንቸት ግባ» በሚለው ባሕላዊ አገላለጽ የአዲስ እህል ሽታ ይሰማል፡፡ የእሸት ጊዜ ይታያል፡፡ ይህ ጊዜ ምድር በሥነ ጽጌያት ( በአበቦች ኅብር) አጊጣ፣ ሰማይ በከዋክብት አሽብርቆ የሚታይበት፣ የጠራ ውኃ ከወንዞችና ጅረቶች የሚፈስበት፣ ንፁሕ አየር የሚነፍስበት፣ አዕዋፍ ከተሰደዱበት እየተመለሱ የሚዘምሩበት፣ እንስሳትና አራዊት ለምለሙን ሳር እየነጩ ጥሩውን ወሃ እየተጎነጩ የሚፈነድቁበት ጊዜ ስለሆነ ለፍጥረት ደስ ይላል (መኃልይ 2÷13)፡፡

          «የዘንድሮን ክረምት ወጣናት በመላ
          አንድ ቀን ሰናድር አንድ ቀን ስንበላ
          እኛስ ይችን ክረምት ወጣናት በመላ
          በኩርማን እንጀራ ጎመን ተጠቅልላ»
እንደሚባለው ክረምት ያለችውን አብቃቅቶ የሚከረምበት ጊዜ ነው፡፡ አበቦች በጋራ በሽንተሩ ሲፈነዱ ማሳውና ጓሮው ሲያብብ ግን የጥጋቡ የእህሉ ወቅት መምጣቱን ይናገራሉ፡፡

የድኅነት ምግብ የጽድቅ ውኃ አጥቶ በሲዖል በረሃ በጽድቅ ረሃብ ለተንገላታው የአዳም ዘር ነፍስ በእግዚአብሔር ቸርነት በጌታችን ሥጋና ደም በጸጋ መንፈስ ቅዱስ የምትጠግብበት ዘመን መድረሱን ያበሠረችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት፡፡ ዛሬም ቢሆን የተስፋ መቁረጥና የጭንቀት፣ የደዌ ሥጋና የደዌ ነፍስ ረሃብ ለወደቀባቸው እመቤታችን የመዳን ተስፋቸው ናት፡፡ በዚህም የተነሳ ቅዱሳን አበው እመቤታችንን በአበባ መስለው ምስጢር ከምሳሌ በማስተባበር ስደቷን በወርኃ ጽጌ ያስቡታል፡

ይህ የእመቤታችን መታሰቢያ ወር በቤተክርስቲያናችን የሚከበረው በሚከተለው ሁኔታ ነው፡፡
       1ኛ. በማኅሌት
       2ኛ. በቅዳሴ
       3ኛ. በዝክር

ማኅሌት
ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት፣ በአምላካችን ቤት በአደባባዮች የምትቆሙ እናንተ የእግዚአብሔር ባርያዎች ሁላችሁ በሌሊት እጃችሁን አንሱ፣ እግዚአብሔርንም ባርኩ (መዝ 133÷1-2) በማለት እንደተናገረው አባቶቻችን ከቅዳሜ ማታ እስከ እሑድ ጠዋት እንዲሁም በክብረ በዓላት እጆቻቸውን ለጭብጨባና ለሽብሸባ አንስተው፣ በከበሮና በጸናጽል እየወረቡ፣ በመቋሚያ እየዘመሙ፣ ያለ ድካምና መሰልቸት ሲዘምሩ ያድራሉ፡፡ ምዕመናንም እንቅልፍ ሳያታልላቸው፣ ድካም ሳይበግራቸው ከአባቶቻቸው ጋር በቤተክርስቲያን በመገኘት በዕልልታ በዝማሬ እያጀቡ ያድራሉ፡፡ በዚህ ወቅት የሚቀርበው ዝማሬ ሦስት ወገን ነው፡፡

1. ከቅዱስ ያሬድ ድጓ

ቤተክርስቲያናችንን በዓለም አቀፍ ደረጃ ካሳወቋት ሊቃውንተ ቤተክርሰቲያን መካከል አንዱና ዋነኛው ቅዱስ ያሬድ ነው፡፡ የቅዱስ ያሬድ ዜማ ከአርያም የተገኘ በመሆኑ ጊዜ የማይሽረው ዘመን የማይለውጠው የቅድስት ቤተክርስቲያን አንጡራ ሀብት ነው፡፡

ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ዓመቱን ክረምት፣ መጸው፣ ሐጋይ ፀደይ ብሎ በመከፋፈል በየዘመኑ የሚዘመረውን መዝሙር አዘጋጅቷል፡፡ በወርኃ ጽጌም ቅዱስ ያሬድ የምድሪቱን በአበባ መሸለም፣ በቡቃያ ማማር፣ የክረምቱን የጭቃና የድጥ ወቅት ማለፍ በተመለከተ እግዚአብሔርን ካመሰገነበት ድርሰቱ እየተውጣጣ ይዘመራል፡፡ በተለይ በወርኀ ጽጌ፡፡

2. ማኅሌተ ጽጌ

ይህ መዝሙር የእመቤታችንን ታሪክ ከጽንሰቷ እስከ ልደቷ፣ ክብሯን፣ ንጽህናዋን፣ በሄሮድስ ምክንያት የደረሰባትን ስደትና መከራ የበረሀውን ጉዞ እያነሳ የሚያመሰግን ታሪካዊ ይዘት ያለው ድርሰት ነው፡፡

ማኅሌተ ጽጌን የደረሱት አባ ጽጌ ብርሃን የተባሉ ሊቅ መሆናቸው ይነገረል፡፡ ዘመኑም በ14ኛው ክፍለ ዘመን ነው፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስ የምሁርን ሕዝብ አስተምረው ወደ ይፋት በማምራት ወንጌልን በመስበክ ላይ እያሉ «ክርስቶስ ተወለደ፣ ሞተ፣ ተነሣ እያሉ እንዴት ያስተምራሉ;» በማለት አንድ አይሁዳዊ ሊቅ ጠየቃቸው፡፡ እርሳቸውም በትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 11 ቁጥር አንድ ላያ የጻፈውን የነቢዩን ቃል («ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል፣ ከሥሩም ቄጥቋጦ ያፈራል» የሚለውን) ጠቅሰው ስላብራሩለት በትምህርታቸው አምኖ ተጠምቆ ለመመንኮስ በቅቷል፡፡ ስሙንም ጽጌ ብርሃን በማለት ሰይመውታል፡፡

አባ ጽጌ ብርሃን ምሁረ ኦሪት ስለነበረ አብሯቸው እየተዘዋወረ ሀዲስን ከብሉይ አስማምቶ ከተማረ በኋላ እንደ መዝሙረ ዳዊት 150 አድርጎ ማኅሌተ ጽጌን ከአማካሪው ከወረ ኢለኀው ተወላጅ ከአባ ገብረማርያም ዘደብረ ሐንታ ጋር በመሆን አዘጋጀው፡፡ ድርሰቱም ቤት እየመታ በአምስት በአምስት ስንኝ እየተከፈለ ነው፡፡

በዚህ ጊዜም ጾም የጌታንና የእመቤታችንን ስደትና መንገላታት በማሰብ ስለ ፍቅራቸው ባሕታውያን፣ መነኮሳትና አንዳንድ ምዕመናን በፈቃዳቸው ይጾማሉ፡፡

3. ሰቆቃወ ድንግል

«ሰቆቃ» ማለት ለቅሶ ዋይታ ማለት ነው፡፡ እመቤታች «ልጄን ይገድሉብኛል ብላ የሄሮድስ ወታደሮች ሲከተሏት፣ የዮሴፍ ልጅ ዮሳዕ የቤተልሔምን ሕጻናት እልቂት ሲነግራት፣ ጥጦስና ዳክርስ የተባሉ ከግብጽ ወደ እስራኤል በሚወስደው መንገድ በጋዛ በር የሚዘርፉ ሽፍቶች ሲያጋጥሟት ያለቀሰችውንና በተወደደ ልጇ ላይ የወረደውን መሪር እንባ በማስታወስ የሚዘመር ነው፡፡ ይህም መዝሙር በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በደብረ ወርቅ ቤተክርስቲያን የድጓ መምህር በነበሩት በመምህር አርከ ሥሉስ እንደተደረሰ ይነገራል፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
http://mahiberekidusan.org/Default.aspx?tabid=88&ctl=Details&mid=371&ItemID=57

6 comments:

Rama said...

Please refer MK Web and help us to read
http://www.eotcmk.org/site/images/stories/jornal.JPG
የጥናትና ምርምር ማዕከሉ የመጀመሪያ የጥናት መጽሔቱን (journal) ያስመርቃል።
በተ/ሥላሴ ጸጋ ኪሮስ
የማኅበረ ቅዱሳን ጥናትና ምርምር ማዕከል “የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጥናት መጽሔት(Journal of Ethiopian Church Studies)” በሚል ስያሜ የመጀመሪያ የጥናት መጽሔቱን መስከረም 29 ቀን 2003 ዓ.ም ያስመርቃል።
መጽሔቱ በባለሙያዎች ታይቶና ተገምግሞ እንዲሁም ሳይንሳዊ የምርምር ዘዴን ተከትሎ በዓመት አንድ ጊዜ የሚወጣ ሲሆን፤ የአሁኑ ዕትም በሦስት ቋንቋዎች የቀረቡ ስምንት የጥናት ጽሑፎችን ይዟል። ከነዚህም ውስጥ ሦስቱ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጁ ሲሆን አምስቱ በአማርኛ ቋንቋ ቀርበዋል።

በአማርኛ የተዘጋጁት ጸሑፎች በአርኪዎሎጂ ቁፋሮ ስለተገኘው የ6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የሕንፃ ቤተክርስቲያን ፍርስራሽና ኪነ ሕንጻዊ ፋይዳው፣ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ከግብፅ ቤተክርስቲያን ጥገኝነት ተላቃ በራሷ ፓትርያርክ ለመመራት ስለበቃችበት የረጅም ጊዜ ትግል፣ በዓለም የቅርስ መዝገብነት ስለተመዘገቡት ነገር ግን ብዙም ስለማይታወቁት የሥነ ጽሑፍ ቅርሶቻችን፣ ስለቤተክርስቲያን ንብረቶችና ይዞታዎች የሕግ ጥበቃና ልመናን ለማስቀረት በ1911 ዓ.ም በአንድ የቤተክርስቲያኒቱ ሊቅ የተጠቆሙ መፍትሔዎችን አስመልክቶ የቀረቡ ሐሳቦች ናቸው፡፡

በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተጻፉት ደግሞ በቅዱስ ላሊበላ ቤተ ማርያም ውስጥ የሚገኙ ሥዕለ እንስሳ ከመጽሐፍ ቅዱስና ከሥነ ጥንት ጥናት /አርኪዎሎጂ/ ጋር ያላቸው አንድምታ፣ ስለ እንጦጦ ማርያም ሙዚየም አጠቃላይ ዳሰሳ እና በአባ ገሪማ ገዳም የሚገኝ በዘመነ አክሱም የተጻፈ መጽሐፈ ወንጌል የሚሉ ናቸው፡፡

በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ የቤተ ክርስቲያን አባቶች፣ ከጥናትና ምርምር ሥራ ጋር ግንኙነት ያላቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተወካዮችና ታዋቂ የምርምር ሰዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Rama said...

Please refer MK Web and help us to read
http://www.eotcmk.org/site/images/stories/jornal.JPG
የጥናትና ምርምር ማዕከሉ የመጀመሪያ የጥናት መጽሔቱን (journal) ያስመርቃል።
በተ/ሥላሴ ጸጋ ኪሮስ
የማኅበረ ቅዱሳን ጥናትና ምርምር ማዕከል “የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጥናት መጽሔት(Journal of Ethiopian Church Studies)” በሚል ስያሜ የመጀመሪያ የጥናት መጽሔቱን መስከረም 29 ቀን 2003 ዓ.ም ያስመርቃል።
መጽሔቱ በባለሙያዎች ታይቶና ተገምግሞ እንዲሁም ሳይንሳዊ የምርምር ዘዴን ተከትሎ በዓመት አንድ ....

ዘቢለን ጊዮርጊስ said...

ሰላም ለእናተ ይሁን ወርኅ ጽጌ የጻፋችሁት መልካም ነው ወቅቱን የጠበቀ ስለሆነ ነገር ግን የምሰጠው አስተያየት አለኝ የእመቤታችንን የስደት መጽሀፍ የደረሱት አባ ጽጌ አብርሀም ናቸው ይላል የጻፋችሁት ላይ እኔ ደግሞ የተማርኩት አባ ጽጌ ድንግል ተብየነው እንዲያውም ገዳማቸው በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በግምት ከደሴ 250ኪ.ሜ ይገኛል የኔ ጥያቄ የትኛው ነው ትክክል?

Selome said...

Qale hiwoten yasemalen Amen !!!


YE EMEBETACHEN FEKERA BEREKETA AYLEYEN Amen .

Anonymous said...

ከድንግል ማርያም በረከት ረድኤት ያሳትፈን

Anonymous said...

Dejeselam mahlete tgane yederesut aba tega brehane sayhonu aba tega dengle nachew yetarem mekonnen

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)