October 22, 2010

የሐዋሳ ምእመናን ለ4ኛ ጊዜ ለአቤቱታ ወደ አዲስ አበባ መጡ


(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 22/2010፤ ጥቅምት 12/2003 ዓ.ም):- የቅ/ሲኖዶስ ጉባዔ ትናንት ሐሙስ በጸሎተ ምሕላ ከመጀመሩ አስቀድሞ ከአዋሳ የመጡ ከ700 ያላነሱ ሰዎች ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ከትሞ ውሏል። በ12 የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች እንዲሁም በሚኒ ባሶች እና የቤት መኪናዎች ተጭኖ የመጣው የሐዋሳው ሕዝበ ክርስቲያን በብዙ ደጅ ጥናት መልስ ሊያገኝበት ያልቻለውን የአቡነ ፋኑኤልን ጉዳይ ለአንዴም ለመጨረሻውም ለማከናወን ነበር ዓላማው። በተደጋጋሚ ስንዘግብ እንደቆየነው ምእመናኑ ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ ይህ ለ4ኛ ጊዜያቸው መሆኑ ነው። ነገር ግን ጠቅላይ ቤተ ክህነቱም ሆነ ቅዱስነታቸው ችግሩን ሳይፈቱ ይልቁንም ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በድንዳኔያቸው እንዲቀጥሉበት የበለጠ ዕድል ሲሰጣቸው ቆይተዋል። ሊቀ ጳጳሱ እንዲያገለግሉት የተሾሙለትን ሕዝበ በማስመረራቸው እየገፉ ከመሔዳቸውም ባሻገር ለሕዝቡ ያላቸውን ንቀት በአደባባይ ሳይቀር ማሳየታቸውን ቀጥለዋል። የሐዋሳ ምእመን በድጋሚ የመጣው ጉዳዩ መስመር ስቶ ወደ አላስፈላጊ መንገድ ከመግባቱ በፊት የመጨረሻ አቤቱታቸውን ለማሰማት ነበር።

አብዛኛውን ምእመን በቅ/ማርያም እንዲቆይ ከተደረገ በኋላ በተወካዮቹ አማካይነት ከቅዱስነታቸው ጋር ለመገናኘት የቻለ ሲሆን በወቅቱም ሊቃነ ጳጳሳቱ አቡነ ሚካኤል፣ ሳዊሮስ፣ ዲሜጥሮስ፣ ኢሳይያስና ፊሊጶስ በተገኙበት ከቅዱስነታቸው ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጓል። ቅዱስነታቸውም “ነገ ጠዋት (ማለት ዛሬ አርብ) ወደ ሐዋሳ አጣሪ ኮሚቴው ይላካል” ያሉ ሲሆን ይኸው የአጣሪ ኮሚቴ ወደ ሐዋሳ የመሔድ ጉዳይ ከንግግር ባለፈ እስካሁን ተግባራዊ ሳይሆን መቆየቱን ሐዋሳውያኑ አስታውሰዋል። “ቅዱስ አባታችን፤ እውነተኛ አባት ይስጡን” ያለው የሐዋሳ ምእመን ችግሩን በዚሁ መፍታት ካልተቻለ “ከእንግዲህ ድጋሚ አንመጣም፤ በሰላም ይለያዩን (ከአቡኑ ጋር)፤ አሁን እርሶ ችግሩን መፍታት ስላልቻሉ መነጋገር የምንፈልገው ከቅ/ሲኖዶስ ጋር ነው” ማለቱም ተሰምቷል።  በመጨረሻም አጣሪውን ኮሚቴ ዛሬ አርብ ለመላክ በመስማማት ውይይቱ የተፈፀመ ሲሆን ሕዝበ ክርስቲያኑም ወደ ሐዋሳ በሰላም ተመልሷል። እንደተባለው ኮሚቴው ዛሬ ወደ ሐዋሳ ይሒድ አይሒድ ዘግይቶ የሚታይ ይሆናል።9 comments:

Unknown said...

ዝምአልልም ዘልደታ
ለመሆኑ አባቶቻችን በዚህ ዘመን ጠቦቶቼን ግልገሎቼን በጎቼን ጠብቁ አሰማሩ የሚለውን መመሪያ አስትቶ በትኑ አንከራቱ ያለቸው ማን ይሆን ወጎኖቻችን የመጡበት ጊዜ ያወጡት ገንዘብ ምን ያህል መንፈሳዊ ቱርፋት ባበረከተ ነበር፡፡እረ እባካችሁ ለአባቶቻችን በጎ የሆነ በተለየይ በአሁ
ኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ውሳኔ ይወስኑ ዘንድ አጥብቀን እንጸልይ፡፡

Anonymous said...

በአባቶች ወንበር የተቀመጡ አረመኔዎች ዋው……………..?

ሀይለ ገብርኤል said...

ሰላም ለኵልነ
በነገራችን ላይ ትላንት የመጣዉ የሐዋሳ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ከዲላ ና ከሐዋሳ ዙሪያ ጭምር ነዉ። እኔ በወቅቱ ቦታዉ ተገኝቼ ነበር። የቅዱስ ፓትርያርኩ የመጀመርያ ምላሽ ያሳዝን ነበር።
በአባቶችና ወንድሞች "270 ኪ.ሜ አቋርጠን ነዉ የመጣነዉ፤ 'አጣሪዉ ኮሚቴ በሁለት ቀን ዉስጥ ይላካል' ተብሎ እኛ ግን
ሁለት ሳምንት ታገስን፥ አልመጣም።" ተብሎ
አቤቱታ ሲቀርብ ፤ በፓትርያርኩ "ከኢትዮያ አልወጣችሁም እኮ!!የመጣችሁት አዲስ አበባ ነዉ....፤ የአጣሪዉ መዘግየት ግን ለእኔም ግልጽ አይደለም ።"ተብሎ ነበር የተመለሰዉ።
ከቅርብ ሰዎች በሰማኋቸዉ መረጃዎች፥ አባቶች ፥ጥፋተኛ መሆናቸዉ ተረጋግጦ ከሚነሱ በፈቃደኝነት አልተመቸኝም ብለዉ እንዲነሱ አቡነ ፋኑኤልን እንዳግባቡ፤ እሳቸዉም
ሀሳቡን ተቀብለዉ ወደ ሐዋሳ ይሄዳሉ እዚያም
ለግብረ አበሮቻቸዉ /የታወቁት/ ይናገራሉ።
"you made a BIG mistake!",said the
bussinessman. ሀሳብ ተቀየረ!!
እነ ያሬድ አደመ/እዉነትም ያሬድ አድሟል!/
በመኪና ሰዉ ጭነዉ ፥አበል ከፍለዉ ይመጣሉ
ሲባልም ሰምቻለሁ። እሱማ ምን ያድርግ!!
የሞት ሽረት ሆኖበት ነዉ። እሳቸዉ ከሌሉ በደቡብ ክልል ማን ያስፈነጥዘዋል? የዲላም ሕዝብ ተቃዉሟል።
መድሃኔ አለም ለአጣሪዎቹ እዉነትን
የሚመሰክሩበት ልቦና ይስጣቸዉ።አሜን።

fkre said...

አባቶች ለምን ዝም አላችሁ ልጆቻችሁ እንድህ ስንሆን ? እኔ ግን ጨነቀኝ ከዚህ በኃላ አባት ሚለውን ሳስብ ይደክመኛል ከዚህ በላይ ወደየት ለማደግ ነው የምፈሩት? ለምን አምባ ገነኖችነ አትቃወሙም? የኢትዮጵያ ኅዝብ ለናንተ ሳይሆን ይቀራል?

Anonymous said...

እስከ አሁን ዝም ያለ እግዚአብሔር ጅራፉን ያነሣ ዕለት አቤት መንጋውን እንዲጠብቁ ያኔ አደራ የተባሉ እንደ አዋሳው ጳጳስ ዓይነት ሆዳሞች መሬት ስትጠባቸው ማየት እንዴት ያስጨንቃል?

እግዚአብሔር በዐይነ ምሕረቱ ይመልከተን፡፡

Anonymous said...

አግዚአብሔር ቤተ ክርስትያናችንን ይጠበቅ ።

indo said...

indis
በየቤቴክርስትያኑ እየተደረገ ያለው ነገር ከቀን ወደ ቀን እየባሰ፣ልዪነት እየሰፋ፣ዐዉዴምህረቱ የእ/ር ቃል የምነገርበት መሆኑ ቀርቶ ዕድሉን ያገኙ ሁሉ የዛቻ፣የፉከራ እና የበላይነታቸውን የምያሰሙበት እየሆነ መምጣቱ ከመታወቅም አልፎ ምዕመኑ" ምነው ዛቻው ቀርቶብን በሠላም የማንንም ዘለፋና ትችት መስማት ቀርቶብን ፀሎተንን ብቻ እያደረስን ብንሄድ ምን አለበት" ማለት ከጀመሬ ሰንበትበት ብሏል፡፡በጣም የሚያሳዝነው በአሁኑ ዘመን በሀይማኖታዊ ጉዳይ ይቅርና በማናቸውም ማህበራዊ ሥፍራዎች መከባበር፣መደማመጥ ህግን ማክበርና መስከበር በተለመደበት ወቅት ቤቴክርስትያናችን ግን ይህን ድርጊት የሚቃወሙ ይመስል በየዐወዴምህረቱ ድራማ እየሰሩ ይኖራሉ፡፡ መምህራ ነን ተብየዎችም በየበዓላቱና ምዕመናን በምሰባሰቡበት ጊዜ ሁሉ በየቤቴክርስትያኑ ስም የገንዘብ ማሰባሰብ ድርጊታቸውን ቀጥሏል እዝህ ጋር መታሰብ ያለበት ነገር ለምን ሰበሰቡ አይደለም የቤቴክርስትያንቱ ችግር ምን እንደሆን ስለምያውቅም ነው ህዝቡ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል የቻለውን ሁሉ የምያደርገው፡፡ ግን ምን ያደርጋል ገንዘቡ የግለሰቦች መበልፀጊያ ከመሆንም አልፎ በአሁኑ ሰዓት ከታችኛው የአገልግሎት ዕርከን እስከ ላይኛው የሀይማኖት መርዎች ነን ባዮች ጭምር በዝህ ዓይነት ጨዋታ ውስጥ ገብተው ቤቴክርስትያንቱን እያመሱ ይገኛል፡፡ አንድ በጣም የምገርመኝ ነገር ደግሞ "ከኛ ምጠበቀው መድረክ ላይ መገኘት ነው የምናገርና የምያስተምር እ/ር ነው በምል ንግግር ሰበብ ማክራፎን በጨበጡ ቁጥር ስሳደቡና ስዘልፉ ለምያሰተውል ሰው እንደ እ/ር እንድህም ይላል ወይስ የግለሰቦቹ ስመት ነው ያስብላል፡፡ለማንኛውም እንደእኔ አመለካከት ምዕመኑ ማሰብ ያለበት በ ማንኛም የአገልግሎት መስክ ወደ ቤቴክርስታያንቱ ዐውደ ምህረት ብቅ የምሉትን ግለሰቦች በማስተወልና በንቃት መከታተል ወሳኝ ነው ምክንያቱም በዝህ ሁነታ የምታመን አንድም አገልጋይ ይኖራል ብሎ ማሰብ ስለምከብድ መማለተቴ ነው፡፡

DEREJE THE AWASSA said...

dear dejeselams
God bless Our Church
Now(9:00pm) or 3:00 local time, at night the Committee leading by Abune Gorgorios is arived at awassa.tommorow we will have discussion. pleas those of you read this message pray for the church and us.
Tewahido forever

Anonymous said...

+++
ለቅዱስ ሲኖዶስ

"የሐዋርያት ሥራ 20:28 በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።"

ረዴኤተ እግዚአብሔር አይለየን:: አሜን

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)