October 28, 2010

ርእሰ አንቀጽ፦ የሀ/ስብከት ምደባ አጀንዳ አባቶች የምትለያዩበት/ የምትከፋፈሉበት “የመሪባ ውሃ” እንዳይሆን (ዘጸ. 17)

  • ዘዴው “በጎሽ ቆዳ ተደብቆ ጎሽን መውጋት” የሚለው ያረጀ ዘዴ፤ አባቶችን "በሀ/ስብከት ምደባ ሰበብ" መከፋፈልና እርስበርሳቸው ማጋጨት ነው
(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 27/2010፤ ጥቅምት 17/2003 ዓ.ም):- የሰሞኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ አባቶች የወሰዱት አቋምና በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰኑ ውሳኔዎች የምእመናኑን ልብ በተስፋ የሞላ፣ አንገቱን ቀና እንዲያደርግና በአባቶች ላይ ያሳደረውን ቅሬታ እንዲያነሳ በር የከፈተ ነው። ቅ/ሲኖዶስ አጀንዳዎቹ ላይ በሕቡር ልብ እና በሕቡር ቃል አንድ ሆኖ እየተወያየ መጥቶ ስብሰባውን ለማጠናቀቅ ትንሽ አጀንዳ ፈሪ፣ ምናልባትም የአንድ ቀን ስብሰባ ብቻ ነው የቀረው። ይሁን እንጂ ዛሬ ረቡዕ በነበረው “የጳጳሳት ምደባና ዝውውር” አጀንዳ ውይይት ወቅት የአባቶች አንድነት እንዲፈታ ጥሩ መንገድ የተገኘ ይመስላል። በስብሰባው ወቅት “በአርምሞ” የቆየው አካል በተግባሩ ወቅት “ከንዋመ አርምሞ”ው ነቅቶ በተግባር ውሳኔዎቹን እንዳይቀለብሳቸው እያስፈራን ነው። አበው እንደሚሉት “ዓይጥ ወልዳ ወልዳ …” እንዳይሆን አስግቶናል። ለዚህም የሚከተሉትን ነጥቦች ለማቅረብ ወደድን።

በዛሬው ዕለት በቅዱስ ፓትርያርኩ በቀረበው በጳጳሳት ዝውውርና ምደባ ላይ እንደቀደሙት አጀንዳዎች የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በአንክሮ አጢነው ሊወያዩባቸው ይገባል። በቅዱስ ፓትርያርኩ የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ አንዳንድ ችግሮች ያሉበት እንደሆነ ማስተዋል እንችላለን። ከሀገረ ስብከታቸው ምዕመናን ጋር እጅና ጓንት ሆነው እየሰሩ ያሉ ሊቃነ ጳጳሳት ወደ ሌላ ቦታ ማዘዋወሩ ሰላምን ለማደፍረስ ካልሆነ ሌላ ምንም ፋይዳ የለውም። ለአብነት ያህል በሀገረ ስብከታቸው አመርቂ የሥራ ውጤት እያስመዘገቡ ካሉት ሊቃነ ጳጳሳት መካከል አንዱ የሆኑትን ብፁዕ አቡነ አብርሃምን መጥቀስ ይቻላል። ይህ በቅዱስ ፓትርያርኩ ሳይቀር የታወቀ ነው። በሀገረ ስብከቱ ካሉ  ካህናትና ምእመናን የይነሱልን ጥያቄ ሳይቀርብ የአዋሳ ምእመናን በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ላይ ላቀረቡትና ላሰሙት አቤቱታ አጫፋሪ በማድረግ ከሀገረ ስብከታቸው ምእመናን ጋር በጥሩ መንፈስና በመግባባት እየሠሩ ያሉትን ሊቃነ ጳጳሳት ለማዘዋወር መፈለግ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ይበጃል ከሚል መንፈስ የቀረበ ስላልሆነ ብፁዓን አበው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በጽሙና ልታስቡበት ይገባል።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም
በተለይ የዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከትን ለማጠናከር ብፁዕ አቡነ አብርሃም ከፍተኛ መስዋዕትነት እየከፈሉ በመሆናቸው፣ ሀገረ ስብከቱ በሁለት እግሩ ቆሟል ለማለት ስለሚያስቸግር፣ የራሱ መንበረ ጵጵስና የተገዛ ቢሆንም ዕዳው ገና ተከፍሎ ያላለቀ በመሆኑ፣ የመንበረ ጵጵስናው ቤተ ክርስቲያን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የሌሎችን ቤተ አምልኮ ለተወሰነ ሰዓት በመከራየት አገልግሎት ሲሰጥ በመቆየቱ፣ አሁን በቅርብ ቀን ሊዝ የተደረገው (የተከራየው) ወርሃዊ ክፍያው ከፍተኛ በመሆኑ፤ በአጠቃላይ ሀገረ ስብከቱ በወር ከአስር ሺህ ዶላር በላይ ወጪ ስለሚጠብቀው፤ ይህ ሁሉ ወጪ የሚሸፈነው ደግሞ በምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት (መንበረ ጵጵስና) ቤተ ክርስቲያን አባላት በመሆኑ፣ እነዚህ ምእመናን በብፁዕ አቡነ አብርሃም የሥራ መሪነት በአካባቢው ያለውን ፈተና ተቋቁመው በመንፈሳዊ ትጋት እየሠሩ እያለና ለወደፊት ሀገረ ስብከቱ የራሱ ቤተ ክርስቲያን እንዲኖረው እየተፋጠኑ ባለበት በዚህ ሁኔታ ላይ ሠርተው እያሠሩ ያሉትን አባት ማንሣት የተጀመረውን መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ከማኮላሸት፣ ሀገረ ስብከቱንም ከመግደል ውጪ ምንም ጥቅም አይኖረውም።  

ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል
የብፁዕ አቡነ አብርሃምን ሀ/ስብከት ለአብነት ጠቀስን እንጂ በሌሎቹም ቦታዎች ብዙ ተመሳሳይ ጉዳዮች ይኖራሉ። ለምሳሌ በሥራቸው መልካም እመርታ አሳይተው የነበሩት ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ወደ ሀ/ስብከታቸው የማይመለሱበት ምንም አጥጋቢ ምክንያት አልቀረበም። በደፈናው “ጳጳሳትን የመበወዝ አበዜ” በተለይ ቅዱስነታቸው በዘመነ ፕትርክናቸው ከሚወቀሱበትና ከሥርዓተ አበው ፈቀቅ ለማለታቸው ከሚከሰሱባቸው ጉዳዮች አንዱ መሆኑ ይታወቃል። ወደቀደመው ሥርዓት መመለስ ካለብን ወደፊት ቅ/ሲኖዶሱ ሊያስብባቸው ከሚገቡት ነገሮች አንዱ ይኸው  የሊቃነ ጳጳሳቱና የሀ/ስብከታቸው ጉዳይ ነው። አንድ ሊቀ ጳጳስ ሀ/ስብከቱ እንደ ሕጋዊ ሚስቱ ናት። በየጊዜው ሚስት እየፈቱ ሌላ ማግባት እንደሌለ ሁሉ አባቶችን በየዓመቱ ከሀ/ስብከታቸው እያፋቱ ለሌላ የመዳሩ ዘመን አመጣሽ አሠራር ሕግ ሊበጅለት ይገባል። “ብፁዕ አቡነ እገሌ ዘ…” ምን እንበል? ዛሬ አንዱ ጋር ናቸው፤ ነገ ደግሞ ሌላ። ለስም አጠራርም የማይመች ነው። ለጊዜው ይህንን ሐሳብ በዚህ እንግታ።

ቅ/ሲኖዶሱ ሌላው ሊያስብበት የሚገባው አምና የተጀመረው የሥራ አስፈጻሚው ጉዳይ ነው። ሰሞኑን የተወሰኑት ዕንቍ ዕንቍ ውሳኔዎች ከጥቅም ላይ ካልዋሉ “የወረቀት ላይ ነብር” ከመሆን ያለፈ ፋይዳ አይኖራቸውም። ሥራ አስፈጻሚውን የመሰለ ይህንን ተግባራዊ የሚያደርግ አካል ማቋቋም ካልቻላችሁ ነገሩ ዞሮ ዞሮ “ዓይጥ ወልዳ ወልዳ” ይሆናል።

በመጨረሻ ማንሣት የምንፈልገው ነገር ቅዱስነታቸው ባላቸው ሰፊ የከፋፍለህ ግዛ ዘዴ ቅ/ሲኖዶሱን የሚከፋፍሉበትና አቅም የሚያሳጡበት ዘዴያቸው ይኸው የቦታ ጥያቄ ነው። በዛሬው ውሎ እንኳን 3 ቡድን ተፈጥሯል። አንዱ እኔ ከሀ/ስብከቴ ካልተነሣሁ ምን ቸገረኝ ባይ፤ ሁለተኛው እንደምንም የምፈልገውን ላግኝ ባይ፤ ሦስተኛው በዚህ ተሠላችቶ ጉባዔውን ሳይፈጽም ወደመጣበት ለመመለስ የቸኮለው ናቸው። ይኼ ሁሉ ዞሮ ዞሮ የሚጠቅመው የቅ/ሲኖዶስ መጠናከርን ለማይፈልገው ክፍል ነው። አባቶች አደራችሁን። አስደስታችሁን ስታበቁ በመጨረሻ ጉድ ሆናችሁ፣ ጉድ እንዳትሠሩን፣ ቤተ ክርስቲያንንም ጉድ እንዳትሠሯት። በየሀ/ስብከታችሁ ስትመለሱ የጀግና አቀባበል ሊያደርግላችሁ በልቡ እየተዘጋጀ ያለውን ምእመን አንገት እንዳታስደፉት። ውይይቱ ወደ ጭቅጭቅ ተለውጦ ጉባዔው ሳይታሰር እንዳይበተን፤ ይህ አጀንዳ የመሪባ ውኃ ታሪክ እንዳይሆን (ዘጸ. 17፤ ዘኊ. 20፡24፤ ዘኊ. 27፡14፤ ዘዳ.32፡51 እና ዘዳ. 33፡8)። አደራ!!!!
ቸር ወሬ ያሰማን፤አሜን።

21 comments:

G/Egzabehar said...

Egzabehar yeredan lela men yebalal ye Betkrsetyan Amelak eswe le betw yemsefelgewen yaderg Amen

G/Egzabehar said...

Egzabehar yeredan

Anonymous said...

ማሳሰቢያችኹን አባቶች እንዲሰሟችኹ ምኞቴ ነው። ረ የራሴንም ተማጥኖ አክልበታለኹ። ይህ እንደተጠበቀ ግን፤ አንድ ነገር ግር አለኝ።

"ይህ ሁሉ ወጪ የሚሸፈነው ደግሞ በምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት (መንበረ ጵጵስና) ቤተ ክርስቲያን አባላት በመሆኑ... ለወደፊት ሀገረ ስብከቱ የራሱ ቤተ ክርስቲያን እንዲኖረው..." ምን ማለት ነው?

ዲሲ የሚገኘው ሀገረ-ስብከት ባንድ አጥቢያ ምእመናን ትከሻ ላይ ብቻ ነው ያለው? እንዲያ ከኾነ፤ ሊቀ-ጳጳሱ "በጥሩ መንፈስና በመግባባት እየሠሩ ያሉት" ከዚሁ አጥቢያ ምእመናን ጋራ ብቻ ነው የሚል ትዝብት አይፈጥርምን?

ደግሞስ በመላ አሜሪካ "ኢትዮጵያ እናታችን ያዲሳባው ሲኖዶስ አባታችን" የሚሉትን አብያተ-ክርስቲያን ያላቀፈ ሀገረ-ስብከት በምን ስሌት ሀገረ-ስብከት ሊባል ይችላልና ገና ወደፊት "የራሱ" ቤተ-ክርስቲያን እንዲኖረው ይመኛል? ጥቂት ግራገባኝ። ክሥቱ ሊተ እስኩ።

Anonymous said...

አባቶቻችን አደራ አደራ አደራ:: አደራ በምድር አደራ በሰማይ::

Anonymous said...

I told you guys the meeting creats problem instead of solution. you will see soon. i said nothing will be changed except doing revange.
come on guys be patient do n't go to judgement. you know abba Pauls and Meles, if someone is popular the people , they don't like that person to perform his job in the same place for a long period.

Anonymous said...

በስመአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን!
እኔ የዲሲ ሀ/ስብከት ምእመን ስሆን አባታችንን አትንኩብን፣ እኛ አባታችን ይቀየሩልን አላልን፡፡ ሀ/ስብከታቸውን በአግባብ እያቀኑ ላሉት እኝህ ትጉህ አባት በረቱ ጠንክሩ ነው እንጂ ይህ ተገቢ አይመስለኝም፡፡ ከፋፍለህ ግዛ ለመንግስት ካቢኔ እንጂ በእግዚአብሔር ላለን አይደለም። አባቶቻችን ይህንን በሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ እንድታስፈጽሙልን እኛ ምእመን ልጀቻችሁ እንለምናለን፤ እንማልዳለን፡፡
ቴድሮስ (ጥበበ ስላሴ) ከዲሲ

Anonymous said...

Dear Deje Selam

If you say Aba Paulos is divisive (yemikefafil)and does not stick with the truth, and the church's Kenona, why you call him "Bistu e Kidus"? Is this not hypocrite?

Thank you.

tekle stephanos said...

የመንግስት ድርሻ ምን መሆን ኣለበት። ኣሁን ይዞት አየትጉዋዘ ባለው ልማታዊ መንገድ ከማንኛውም ሃገራዊ ተቁዋማት ውስጥ ያሉ ሙሰኞችን በማያዳግም ሁኔታ ለመምታት ኣንድ ጠንካራ ግንባር መፍጠር ግድ ይለዋል። በተለይም ሃይማኖታዊ ተቁሞች ውስጥ ያሉትን ነቀዞች። በሃይማኖት ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ ኣለመግባት ማለት ወንጀል አየተሰራ አያየ ከሩቅ ሆኖ አንዳላየ ማለፍ ማለት ኣይደለም። ይህ ገለልተኝነት ሳይሆን ግድ የለሽለት ነው። መንግስት በመንግስትነቱ ማድረግ ያለአትን ህጋዊ ከለላ ለቤተ-ክርስቲኒቷ መስጠት ኣለበት። ይህን በማድረጉ በቤተ-ክርትያኒቱ የውስጥ ኣገልግሎት ገባ ማለት ኣይደለም። በውስጧ ተሰግስገው አንደ መዥገር ተጣብቀው የህዝብን ደም አየመጠጡ፣ተው የሚላቸውን ሰራተኛ ላይ ያለ ይሌለ የበቀል ዱላቸውን በማሳረፍ በፍርሃት ተሽማቆ አንዲቀመጥ አንደሚያደርጉ አናውቃለን።ይሄ ለመንግስትም ይጠፋዋል ማለት ኣይደለም። አንዚህ ነቀዞች የማይፈልጉትን ሰራተኛ አሱ ፖለቲከኛ ነው አሷ ተቃዋሚ ነች አያሉም መንግስትንና ሰራተኛውን ማቃቃሪያ አኩይ ብልጠትም ኣላቸው። ህዝብ በማናቸውም ሁኔታ ሰላም ከሆነ መንግስትን ከመደገፍ ወደኁላ ኣይልም። ስለዚህም መንግስት ሲኖዶሱ የወስናቸውን ማንኛውንም ውሳኔ አንደ ቤተ ክርስቲያኗ ህልውና ቆጥሮ ኣስፈላጊውን ሃላፊነቱን አንዲወጣ አንጠይቃለን። መንግስት ንቆ ሊያየው የማይችለው ማፍያ በዚህች ጥንታዊት የአምነት ተቁኣም ውስጥ መረቡን ከዘረጋ ኣመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ወንጀሉን ኣስከፊ የሚያደርገው ደግሞ የማፍያው መሪ በምንም መልኩ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጋር ምንም ኣይነት ግንኙነት የሌላት ጋለሞታ ምሆኗ ነው መንግስት የዚህችንም ሴትዮ ንብረት ተቆጣጥሮ በምጥጠይቅበት ወንጀል ሁሉ ኣስፈላጊውን ርምጃ አንዲወሰድባት መደረግ ኣለበት። ቅዱስ ፖትርያርካችን በስጋ በአድሜ የደከሙ ቢሆንም ኣአምሮኣቸው ግን ከተንኮልና ከክፋት የፀዳ ኣይደለም። ለዚህም ለተጨማልቀ ሙስና ማእከሉ አሳቸው ናቸው። ወስብሃት ለእግዚኣብሄር። ቸር ወሬ ያሰማን////.

Anonymous said...

@Anonymous #2...can you NOT add gasoline on the fire..., i think you are missing the whole point. Just to clarify, the focal point of this article is NOT about Misrake Tsehay or any other Church... the whole point here is to indicate what is being done is NOT acceptable, especially in a time where Bitsue Abune Abrham is trying to motivate the lost souls and help us lift our heads up high and testify the truth about the Church Canon and laws that our Fathers left us. This is defiantly not the best decision… to move him and bring somebody else is a slap in the face for the younger motivated generation that is working hard to follow the right path…therefore my Brother/Sister please stay focused on the main point and stop trying to bring the wrong subject at the wrong time... I am not saying you don’t have a valid point, but the timing is wrong. I take this opportunity to ask Deje Selam to write another article and raise the topic Anonymous #2 brought up so people can understand why Misrake Tsehaye Miemenan is mentioned as a primary funder…but for now let’s not loos focus

Anonymous said...

+++
አባቶች አደራችሁን። አስደስታችሁን ስታበቁ በመጨረሻ ጉድ ሆናችሁ፣ ጉድ እንዳትሠሩን፣ ቤተ ክርስቲያንንም ጉድ እንዳትሠሯት። በየሀ/ስብከታችሁ ስትመለሱ የጀግና አቀባበል ሊያደርግላችሁ በልቡ እየተዘጋጀ ያለውን ምእመን አንገት እንዳታስደፉት። ውይይቱ ወደ ጭቅጭቅ ተለውጦ ጉባዔው ሳይታሰር እንዳይበተን፤ ይህ አጀንዳ የመሪባ ውኃ ታሪክ እንዳይሆን (ዘጸ. 17፤ ዘኊ. 20፡24፤ ዘኊ. 27፡14፤ ዘዳ.32፡51 እና ዘዳ. 33፡8)። አደራ!!!!

በአባቶች አጠገብ ያላችሁ ምዕመናን አደራ አለባችሁ ተመካከሩ::

ቸር ወሬ ያሰማን፤አሜን።

tad said...

DS and MK got just two bishops, Abba Abraham and Abba Samuel?What makes these two bishops so special that we have to care for them so differently? May be both of them so dependent on MK for survival? They can't think out of the boxes of MK'S?
DS, "Don't push me to question your honesty and integrity'?

Unknown said...

Dear Tad,

To understand what we mean by that, you should follow our threads of ideas for some time now. We know you are a good Deje Selamawi for quite some time, unless there is another Tad. No problem questioning a media. That is what you should do. But we help whoever is to be helped as long as he is with the Church. We can not talk about MK, unless we believe the conspiracy theory that DS=MK, etc. No time for that kind of stuff.

ene negn said...

Geta Hoy ante melkamun taderg zend yetamenk neh.Fitsamewn asamirew.Amen.

Ze-egzine said...

TAD: I agree with you.

Anonymous said...

ሊላይ ነኝ። አቡነ ጳውሎስን ብቻ በመውቀስ ላይ መጠመድ የለብንም። ወይም አቡነ እገሌ ለኛ አስፈላጊነታቸው ከየትኛውም ጳጳስ በላይ ነው የሚል ጠባብነት ላይ ማትኮር ለቤተክርስቲያን ሰላም እድገት አያመጣም። በአጠቃላይ ጳጳሳት ለተሾሙበትና ለያዙት ስልጣን የሚመጥን ስራና መንፈሳዊ ልማት በየተመደቡበት ቦታ እንዲያመጡ መታገል ይኖርብናል። ሁለትና ሶስት ቦታ ተዘዋውረው መስራት ካቃተቸው በጡረታ ተሰናብተው ቤተክርስቲያን እስከዕለተ ሞታቸው ትሸከማቸው። ወደፊት በሚሾሙት ላይ ስራቸው፣ ምግባራቸው፣መንፈሳዊነታቸው የተመሰከረላቸው ይሆኑ ዘንድ ድምጻችንን አስተባብረን እንጩህ። ድምፃችን እንድ እስከሆነ ድረስ ውጤታማ የማንሆንበት ምክንያት የለም። ለሹመት የሚቀርቡትን ማን ምን እንደሆነ በተናጠል አንዱ ባያውቅ፣ በጋራ ከሆን ግን የሚያውቅ አይጠፋንም። በምናውቀው ላይ በመረጃ መታገል የጋራችን ይሁን። ወደማጠቃለያዬ ስመጣ አቡነ አብርሃም (በግሌ አውቃቸዋለሁ)የአሜሪካ ነዋሪዎቻችን ምስክርነታችሁን መስጠታችሁ ጥሩ ሆኖ ሳለ የማይስማማኝ ነገር ከእኛ ተዛውረው መሄድ የለባችሁም ማለታችሁ ነው። የአዋሳ ህዝብ አቡነ አብርሃምን የመሰለ አባት አያስፈልገውም ማለት ነው? ጠንካራ አባት እየተዘዋወረ የተሾመበትን መንጋ ቢመራ ምን ክፋት አለው? ለእናንተ የደረሰው ልማትና ሰላም በናንተ ክልል ብቻ ታጥሮ መቆየቱ ለምን?ይልቅ አቡነ አብርሃም ያላቸውን ስጦታ እየተዘዋወሩ ያካፍሉ፣ እሳቸውን የመሰሉ እንድመጡልን እንጣር፣ እኔን ብቻ ይድላኝን እንተው። አንዳንዶች ጳጳሳት እኮ ያሉበት ሀገረስብከት ሲመቻቸው ልማትና እድገት ኖረም አልኖረ ዝም ብሎ መቆየትን ይሻሉ። እነዚህኞቹ የገደሉትን ማን ህይወት ይዝራበት? ጥያቄዬ ነው።

ዳዲ said...

አሁንም አባቶች በርቱልን !!!
ውሳኔያቺሁን በጉጉት ነው የምንብቀው::
እግዚአብሔር ይርዳን !
አሜን

Anonymous said...

ዉድ ሲሳይ
እኔ ያለሁት አዉሮፓ ነዉ። አቡነ አብርሃም ወደ እኛ ቢመጡልን ደስታየ ወደር የለዉም። ነገር ግን ዲሲ ቢቆዩ ለቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ ደህንነት ይበጃል ባይ ነኝ። ምክንያት
1. ሰዉ ፖለቲካንና ተዋህዶን እያነካካ ምስቅልቅል ባለበት ቦታ ጊዜዉ ለሚጠይቀዉ የተዋህዶን እዉነተኛ አቋም እያንጸባረቁ ስለሚገኙና በቅዱስ ፓትርያርኩ አዲሱ ሊቀ ጳጳስ ይህንን ለመልመድ ሌላ ዘመን ስለሚፈጅባቸዉ
2.ዲሲ በ ሲኖዶሶች፣ ራስ ገዝ አብያተ ክርስቲያናት...ወዘተ መሰነጣጠቁና ለወደፊቱ የቤተ ክርስቲያን አንድነት አደገኛ ማዕከል መሆኑ፤ ለዚህም በትኩረት የሚሰራ፣ አካባቢዉን የለመደ ትጉህ አባት ስለሚያስፈልግ
- የዲሲ አካባቢ አብዛኛዉ ምዕመን እውነታዉን ከተረዳ ማን ወደ ሲኖዶስ ይሄዳል? ማንስ ከስርአት ለወጣ ራስ ገዝ ንዋዩን ይከሰክሳል?
3. ወጣቱን ማዕከል ያደረገ ስራ በመስራት የጀመሩትን ፈፅመዉ ለፍሬ ቢበቃ የምትጠቀመዉ ተዋህዶ እና ልጆቿ እንጂ ዲሲዎች ብቻ ስላይደሉ
4. ...በመሳሰሉት
እዚያዉ ቢቆዩ እመርጣለሁ። ሰዉ ቁስሉ በበረታበት ቦታ መድሐኒት እንደሚያፈስ ማለት ነዉ።
አምላከ ዳዊት ቤቱን ይገንባ። አሜን።

ዳዲ said...

አሁንም አባቶች በርቱልን !!!
ውሳኔያቺሁን በጉጉት ነው የምንብቀው::
እግዚአብሔር ይርዳን !
አሜን

Anonymous said...

በዚህ መሥመር ሦስተኛ ተራ ላይ ጥያቄ ላነሣኹት "አኖኒም" ምንም ማብራሪያ ሳትሰጡኝ፤ አሥራ-ምናምነኛ ላይ ያለው "ታድ" ላነሣው ነጥብ ወዲያው ከሥሩ ብቅ ብላችኹ መለሳችኹለት። ታዘብዃችኹ።

መርከቤ ንጉሴ/ከአዲስ አበባ/ said...

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ፡፡ አሜን!!
ወገኖቼ በቅድሚያ እኔ ምንም የማላውቅ ሐጥእ ሰው እንደሆንኩ ይታወቅልኘ፡፡ ነገር ግን የምሰማውና የማየው አስተያየት እንድሰጥ አስገድዶኛል፡፡ በውጭ ሃገር የምትኖሩ ኦርቶዶክሳውያን እውነት የኛን ኦርቶዶክሳውያን አንድትና ሕገ-እግዝአብሔር መጠበቅን ትመኛላችሁ? አዎን ካላችሁ ታዲያ ለምን እውነተኛ የሆነ እውነተኛ ያልሆነ ሕጋዊ የሆነ ሲኖዶስ ሕጋዊ ያልሆነ ሲኖዶስ እያላችሁ ለምን መከፋፈልን ትፈጥራላችሁ? እንዳይነኩብን የምትሏቸው አባት ጠንካራ ከሆኑና ብዙ ሥራ የሰሩ ከሆነ ደከም ወዳለው ደግሞ እየተዘዋወሩ አስተዋፅኦ ቢያበረክቱ ምን ክፋት አለው መደገፍ ሲገባችሁ ለምን ወሳኝ እኛ ነን ትላላችሁ? የመንፈስ ቅዱስን ሐሳብ መጋፋት ስለሚሆንባችሁና አባቶቻችን በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው የወሰኑት ውሳኔ ትክከል አይደለም እኛ ከናንተ እናውቃለን በማለት በተለያየ ሲስተም ስሕተት እየሰራችሁ ስለሆነ ይልቅ ለሐይማኖታችን የሚበጀው እንዲመጣና የተወሰነው ተግባራዊ እንዲሆን ሥልጣኑ የአባቶቻችንና የመንፈስ ቅዱስ ሰለሆነ በቀና አስተሳሰብ ለአባቶቻችን ፀጋውን እንዲያበዛላቸውና የጀመሩት በሰላም እንዲጠናቀቅ መፀለይ ይበጀናል፡፡

ቸሩ አምላካችን ለአባቶቻችን ብርታቱን ያድልልን፡፡
መርከቤ ንጉሴ/ከአዲስ አበባ/

Anonymous said...

First let me confese that I used to have a very negative view of you guys, deje selamawiyan. I, as everyone else, used to think, the blog is an extension of hate politiking in the church by MK.

Though I still have my reservations about MK, I would like to say, I am proud of you guys and appologize for my previous misconception.

You guys are doing a FANTASTIC JOB, Holy task that would help our church for long time to come.

here is my question,

It seems that the Pathriarich is the ill of all problems for the church, (kefafleh giza and using all tactics) is expected of an evil not from someone from Holy.

So, why dont the Synod, remove him from his position ????????

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)