September 20, 2010

ቤተ ክህነቱ ያጣው የቤተ ክህነቱ ሰው

(ባሮክ ዘሣልሳይ ሺሕ)
1. መግቢያ
የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ሁለት ነው፡፡ የመጀመሪያው ከጳጳሳቱ ሰብእና አንጻር ቤተክህነቱ ያለበትን ሁኔታ ማሳየት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ምእመኑ የቤተክርስቲያኗን ሐዋርያዊነት እና ርእቱነት ከጳጳሳቱ ተክለ ሰብእና አኳያ እንዳይመዝን በሒደት ማመልከትና ጥርጣሬ ውስጥ እንዳይገባ መርዳት ነው፡፡ በመሆኑም ሕዝበ ክርስቲያኑ በአባቶቹ ላይ ከሚታዩ ጉድለቶች በመነሣት በእምነቷ፣ በትውፊቷ፣ በቀኖናዋና በታሪኳ ርቱእነት እና ሐዋርያነት ላይ ምንም ዓይነት ብዥታ እንዳይፈጠርበት በቅድሚያ አሳስባለሁ፡፡ የቤተክርስቲያኗ ርቱእነት እና ሐዋርያነት የሚለካው በሰዎች ሰብአዊ ጉድለትና ድቀት ሳይሆን ወልድ ዋሕድ በሚለው መሠረተ እምነቷ እና ይኽን መሠረተ እምነት ነቢያት፣ ሐዋርያት ከአስተማሩበት ሥርዓተ ትምህርት አኳያ በመሆኑ ነውና፡፡
2. ሦስቱ ጠባየ ጳጳሳት

ቤተ ክህነቱ በየዘመናቱ ሦስት ዓይነት ጠባየ ጳጳሳትን አስተናግዷል፡፡ የመጀመሪያው እና የአብዛኛዎቹ የሆነው አድርባይነት ነው፡፡ የዚህ ምንጩ ደግሞ በዓላማ ለዓላማ የመላእክትን አስኬማ አለመድፋት ነው፡፡ የመላእክት አስኬማ /ምንኩስና/ ንጽሕናን ይጠይቃል፣ ብዙዎቹ ንጽሕናቸውን አጉድፈዋል፡፡ የመላእከት አስኬማ የዚህን ዓለም ጣዕም ይንቃል፤ ብዙዎቹ ዓለማዊነትን ኑሮ አድርገውታል፡፡ የመላእክት አስኬማ የራሴ የሚለው ዘውግ እና ንብረት የለውም፡፡ ብዙዎቹ ግን የዘውግ ብል የበላቸው፤ የዚህ ዓለም ሀብትና ንብረት ያማለላቸው ናቸው፡፡ ይኽ ደግሞ ጥብዓት የጎደላቸው፤ ትጋሀ ሌሊት የማያውቃቸው፣ የመንኖ ጥሪት መዓዛ የማይሸታቸው አድርባዮች እንዲሆኑ አድርጓቸዋል፡፡ በምስጢር የፈጸምናቸው ስህተቶች ከአሁን አሁን ተደረሶባቸው እንጋለጥ ይሆን በሚል የሚደነብሩ እና የማፍያው ቡድንም ይኽን የጎደፈ ገመናቸውን ለምእመኑ እገልጣለሁ እያለ የሚያስፈራራቸው እና ከፍርሃታቸውም የተነሣ ለዚህ ቡድን ፈቃድ እንዲያድሩ አድርጓቸዋል፡፡

ሁለተኛው እና ቁጥራቸው ቀላል ያልሆኑ ጳጳሳት ጠባይ ደግሞ ቸልተኝነት ነው፡፡ የእነዚዎቹ ቸልተኝነት ከጠባቂነታቸው እና ከስንፍናቸው የሚመጣ ነው፡፡ ምንም እንኳን የመላእክት አስኬማ መለያ የሆነው ቅድስና፣ ዘውግ አለመለየት፣ የዓለምን ፈቃድ ማሸነፍን ገንዘብ ቢያደርጉም የጠባቂነት እና የስንፍና ቅንቅን ወሯቸዋል፡፡ ለቤተክርስቲያን የሚሆነውን ሠርተው ከማለፍ ይልቅ ሌሎች እንዲሠሩ ይፈልጋሉ፡፡ እነርሱ መስዋዕት ከሚከፍሉ በሌሎች መስዋዕትነት የቤተክርስቲያንን ዕድገት ማየት ይፈልጋሉ፡፡ እነርሱ የጎደለውን ከሚያሟሉ፤ የጠመመውን ከሚያቀኑ ሌሎች በሚያሟሉት እና በሚያቀኑት ፍኖት መጓዝን ይመርጣሉ፡፡ እነርሱ ተናግረው ከሚያሳምኑ ይልቅ ሌሎች ተናግረው እንዲያሳምኑላቸው ይፈልጋሉ፡፡ እነርሱ ታሪክ ሠርተው ከማለፍ ይልቅ የተሠሩ ታሪኮችን እያመነዠጉ የታሪክ ግብ ይቅርና ምዕራፍ ሳይኖራቸው ያለፉ፤ የሚያልፉ ሰነፎች ናቸው፡፡ እነርሱ የተጣለባቸውን ሓላፊነት በቆራጥነት ከመወጣት ይልቅ ቅዱስ ፓትርያርኩ «ከተስማሙበት ምን አገባን» የሚሉ፤ ቤተክርስቲያን በሰላም ማጣት፣ በመናፍቃን ሴራ፣ በመልካም አስተዳደር ዕጦት ስትታመስ እየተመለከቱ  እነዚህ ሁሉ ችግሮች በአንድ ጀንበር በፓትርያርኩ ሞት የሚፈታ ይመስል ሞት ናፋቂዎች ሆነዋል፡፡ ይኽ መሆኑ ደግሞ ቤተክህነቱን ብቻ ሳይሆን ቤተ ክርስቲያኒቱን በበላተኞች እንድትወረር፣ ቅሰጣ እንዲደረግባት የራሱን አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

ሦስተኛው ጠባየ ጳጳሳት እና በቤተክህነቱ በጥቂቱም ቢሆን ትላንት የነበረ፤ ዛሬ ግን ያጣው ጴጥሮሳዊነት ነው፡፡ ጴጥሮሳዊነት ሰማዕተ ጽድቅ ዘኢትዮጵያ በሆኑት በብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕትነት ላይ የቆመ ነው፡፡ ይኽ ደግሞ ስለ እውነት በእውነት መሞት ልዩ ግብሩ ነው፡፡ ጴጥሮሳዊነት ከላይ እንደተመለከትነው ሁለቱ ጠባየ ጳጳሳት ሳይሆን  በእግዚአብሔር አምኖ የራስንም ሓላፊነት እየተወጡ ውጤቱን የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ብሎ መቀበል ነው፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም «ኢትዮጵያ ከየት ወዴት)» በሚለው መጽሐፋቸው ስለ ጴጥሮሳዊነት እንዲህ ብለዋል፡፡

«. . .ጴጥሮሳዊነት በመሠረቱ መንፈሳዊነት በመሆኑ የሚመካበትም ኀይል መንፈሳዊ እንጂ አካላዊ ወይም ጠመንጃ አይደለም፡፡ የጴጥሮሳዊነት ዓላማ አስፈላጊ ከሆነ ለእምነቱ፣ ለሀገሩና ለወገኑ ለመሞት እንጂ ለመግደል አይደለም፡፡. . . ለመሞት መዘጋጀትና ለእውነትና ለእምነት መሞት ግን ወኔን ይጠይቃል፡፡ መንፈሳዊ [ጴጥሮሳዊ]ወኔ፡፡» /ገጽ.44/

3. ሦስቱ የጴጥሮሳዊነት ምንጭ

ጴጥሮሳዊነት በመንፈሳዊነት ላይ የቆመ የመላእክት አስኬማ ነጸብራቅ እንደመሆኑ ከሦስት ነገሮች ይመነጫል፡፡

3.1 አደራን ለመጠበቅ ዝግጁ ከመሆን

አደራ ክቡር፣ ውድ፣ ታላቅ ምስጢር ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙሩ የሆነው ጢሞቴዎስን የተሰጠውን አደራ በመጠበቅ ሓላፊነቱንና ግዴታውን መወጣት እንደ ሚገባው ሲገልጽ «እቀብ ማህጸንተከ፤ አደራህን ጠብቅ» በማለት ነው፡፡ 1ኛጢሞ.6 .2፡፡ ጢሞቴዎስ በመምህሩ የተጣለበትን አደራ ለመወጣት የዚህ ዓለም ፈቃድ ሳያሸንፈው ተወጥቷል፡፡ የዓላውያን ነገሥታት ማዋከብ፣ ድብደባ አደራውን እንዳይወጣ አላደረገውም፡፡ የአቡነ ጴጥሮስ የሰማዕትነትም ጉዞ መነሻውም መድረሻውም የእነዚህ አባቶች አርአያ ፍኖት ነው፡፡

ለሀገራቸውና ለወገናቸው እስከ መጨረሻዋ ሰዓት ድረስ እውነቱን ከሐሰት በመለየት ለሕዝባቸው የሰጡት ምስክርነት የተጣለባቸውን አደራ ከመወጣት ነው፡፡ አለቃ ተጠምቀ የተባሉ ቅድስናን ከሊቅነት ጋራ አስተባብረው የያዙ የቅኔ መምህራቸው አንድ ቀን ብፁዕነታቸውን ጠርተው የሚከተለውን የአደራ ቃል ያስተላልፋሉ፡፡ «ኀይለማርያም አንተ ወደፊት ጳጳስ ትሆናለህ፤ በወቅቱም አረመኔ በዚህች ሀገር ይሠለጥናል፡፡ ታዲያ ያኔ አንተ ለነፍስህ ሳትሳቀቅ በሰማዕትነት እለፍ፤ ሰማዕትነት ክፍልህ ነው፡፡ አደራ፡፡» /መርሻ አለኸኝ /ዲያቆን/፣ 1986 ዓ.ም፣ ዜና ጳጳሳት ኢትዮጵያውያን፣ ገጽ.80/

ሐዋርያው ቅዱስ ጢሞቴዎስ የመምህሩን የአደራ ቃል በመያዝ እስከ መጨረሻው እንደጸናው ብፁዕነታቸውም የመምህራቸውን የአደራ ቃል በሰማዕትነት አትመው ጠበቁ፡፡ አንዲትም ቀንና ሰዓት ከሞት ሳይሸሹ እና ሳይደበቁ ለአገራቸው ፣ለቤተ ክርስቲያናቸው እና ለሕዝባቸው ሲሉ ሞትን ተጋፈጡ፡፡ የሰማዕትነትን ጽዋ ተጎነጩ፡፡ የዚህ ምንጩ አደራ ነው፡፡ እኔም የጴጥሮሳዊነት አንዱ ምንጩ አደራን ለመጠበቅ ዝግጁ ከመሆን ይመነጫል የምለው ለዚህ ነው፡፡ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ቤተክርስቲያን በአደራ የሰጠቻቸውን ሓላፊነት ለመወጣት ሕዝበ ክርስቲያኑን በጸሎታቸው እየደገፉ፣ በትምህርታቸው እያበረቱ አስተዳድረዋል፡፡

የጴጥሮስን ሥልጣን የያዙ፣ አስኬማውን የደፉ፣ ካባውን የደረቡ፣ መስቀሉን ከእነ በትረ ሙሴው የጨበጡት «ዘመነኞቹ» ጳጳሳት ከቤተክርስቲያን የተቀበሉትን የእረኝነት የአደራ ቃል በመተው ለቤተክርስቲያን ከሚታገሉላት ይልቅ የሚታገሏት ሆነዋል፡፡ ጵጵስናውን ሲቀበሉ የገቡትን ቃለ አደራ በመዘንጋት በጴጥሮሳዊነት ለአገርና ለወገን ሊቆሙ ይቅርና ክብርን ለአጎናጸፈቻቸው እናት ቤተክርስቲያን የማይሆኑ እርባና ቢስ ሆነዋል፡፡ ፍርሃት ድሩን ሠርቶባቸው ትምእርተ ምንኩስናቸውን ሸፍኖታል፡፡ ሹመታቸው የዖዝያን ሹመት እስኪመስል ድረስ የጽድቅ ፈሪዎች፤ የኃጢአት ደፋሮች አስመስሏቸዋል፡፡

3.2. አባታዊ ሓላፊነትን ከመወጣት

የሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕትነት አባታዊ ሓላፊነታቸውን በቆራጥነት ለመወጣት ካደረጉት ተጋድሎ ይመነጫል፡፡ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሕዝብ ቀስቅሰዋል፤ ራስዎም አምጸዋል፣ ሌሎችንም እንዲያምጹ አድርገዋል በሚል የወንጀል ክስ ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡ ችሎቱ ተሰይሞ ሲቀርቡ ዳኛው «ካህናቱም ሆኑ የቤተክህነት ባለሥልጣናት ጳጳሱ አቡነ ቄርሎስም የጣሊያንን መንግሥት ገዥነት አምነው አሜን ብለው ሲቀበሉ እርስዎ ለምን ዐመፁ) ለምን ብቻዎን አፈንጋጭ ሆኑ)» ሲል ጠየቃቸው፡፡ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በቆራጥነት «አቡነ ቄርሎስ ግብጻዊ ናቸው፤ ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኢትዮጵያውያን የሚገዳቸው ነገር የለም፡፡ እኔ ግን ኢትዮጵየዊ ነኝ፡፡ ሓላፊነትም ያለብኝ የቤተክርስቲያን አባት ነኝ፡፡ ስለዚህ ስለ ሀገሬና ስለ ቤተ ክርስቲያኔ እቆረቆራለሁ፡፡. . . እኔን ለመግደል እንደወሰናችሁ አውቃለሁ፡፡ ስለዚህ በእኔ ላይ የፈለጋችሁትን አድርጉ፡፡ ግን ተከታዮቼን አትንኩ» በማለት ሕያው በሆነ ቃላቸው መለሱ፡፡ ሰማዕተ ጽድቅ በሆነ ደማቸው አተሙ፡፡ አኩሪ በሆነ አባታዊ ሓላፊነታቸው ለአገር፣ ለቤተክርስቲያን፣ ለወገን ሁሉ አለኝታነታቸው አረጋግጠው በሰማዕትነት አለፉ፡፡ / መርሻ አለኸኝ/ዲያቆን/፣ 1996ዓ.ም፣ዜና ጳጳሳት ኢትዮጵያውያን፣ገጽ.77/

ዛሬ ቤተክርስቲያንም ሆነች ቤተክህነቱ ያጣው ጴጥሮሳዊነት ይኽ ነው፡፡ በዘመናችን ያሉ ሊቃነ ጳጳሳት ይኽን የጽድቅ ፍኖት ይዘው መጓዝ ሲሳናቸው አይተናል፡፡ እንደ አቡነ ጴጥሮስ የድህነት ቀንበር ለተጫነው፣ በችጋር አለንጋ ለተገረፈው፣ በሀዘን ለተቆራመደውና ለጎበጠው ሕዝባችን ሊቆረቆሩ ይቅርና አባታዊ ሓላፊነት ለሰጠቻቸው እናት ቤተክርስቲያን ጠበቃ መሆን ሲሳናቸው ተስተውሏል፡፡ ሁሉም በሰማዕተ ጽድቅ አቡነ ጴጥሮስ ዘመን እንደነበሩት ግብዊ ጳጳስ ሆነውባታል፡፡ በእርግጥም እውነት ነው፡፡ አንዳንዶቹ የአሜሪካ እና የካናዳ ዜግነት ኖሯቸው በአሜሪካ እና በካናዳ ከቀኖና ቤተክርስቲያን ውጭ የግላቸው ቤተክርስቲያን የከፈቱ ባዕዳን ናቸው፡፡ እዚው ያሉት በየስድስት ወሩ ከዲያስፖራው ምእመን በተወካዮቻቸው አማካይነት የተሰበሰበውን ገንዘብ ለመተሳሳብ እና የድርሻቸውን ለመውሰድ ወደ አሜሪካ ያመራሉ፡፡ በገንዘቡም ከአንድ አባት የማይጠበቅ ኢ-ሥነምግባራዊና ኢ-ሞራላዊ ድርጊቶችን በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ይፈጽማሉ፡፡ ስለዚህ እንዴት ጴጥሮሳዊ ወኔ ይኖራቸው)

ሌሎቹም የቤተክርስቲያን አባት መሆናቸው እስኪጠፋን ድረስ ሀገረ ስብከታቸውን ትተው አዲስ አበባ በዘመናዊ ቪላ የሚሽሞኖሙኑ፤ እነርሱ በሀገረ ስብከታቸው ተቀምጠው የሚሆነውን ከመሥራት ይልቅ፤ ባለጉዳዮችን በየመኖሪያ ቤታቸው የሚያንከራትቱ፤ እንደ ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ ሕዝባዊ አለኝትነታቸውን ከማረጋገጥ ይልቅ፤ ዘመናዊ ቤት የሠሩበትን፣ ዘመናዊ መኪና የገዙበትን፣ በየሳምንቱ ዶሮ፣ ቅቤ፣ ማር፣ በግ የሚያማርጡበትን ገንዘብ የሰጣቸውን ምእመን «ቤተክርስቲያን ተሳልመህ ከመመለስ ውጭ ምንም አያገባህም» ብለው የሚመጻደቁ ፊውዳሎች ናቸው፡፡ /ነጋድራስ ጋዜጣ፣ሐምሌ 30 ቀን 2002 ዓ.ም፣ቅጽ.07፣ቁጥር 240፣ገጽ.2/

አንዳንዶቹም ከቤተክርስቲያን ልዕልና እና መታፈር ይልቅ ራሳቸውን በአገረ ስብከቶቻቸው ልዑላን በማድረግ የሾሙ፤ የአክሊለ ሦክ ምሳሌ የሆነውን ቆብ ማድረጋቸውን ዘንግተው ዘውድ የደፉ ይመስል በዙርያቸው «እራት አግባዎችን» አደራጅተው ለቤተክርስቲያን የማኅፀን እሾኽ የሆኑ፤ የትኛውም አካል እነርሱን እስካልነካ ድረስ ቤተክርስቲያን ላይ «ቤንዚል አርከፍክፎ፣ ክብሪት ጭሮ እሳት ቢለቅ» አባታዊ መዓዛ የማይታይባቸው፤ ጴጥሮሳዊነት እጅጉን የራቃቸው ሥጋውያን ናቸው፡፡ እናም አንዱ ቤተ ክህነቱ ያጣው የቤ ተክህነት ጴጥሮስ እና ጴጥሮሳዊነት ይኽን ነው፡፡

3.3. ከመንኖ ጥሪት
መንኖ ጥሪት በዚህ ዓለም ያለን ማንኛውም ሀብትና ንብረት ንቆ መተው ነው፡፡ «ማንም ከእናንተ ያለውን ሁሉ የማይተው ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም» እንዲል ሉቃ.14.33፡፡ እንግዲህ የዚህን ዓለም ጣዕም ማጣጣም ያልተወ መንፈሳዊ አባት የክርስቶስ ደቀመዝሙር ሊሆን ይቅርና ጥሩ ክርስቲያንም አይሆንም፡፡ እርሱ ምውት ሕሊና ነውና፡፡ የአቡነ ጴጥሮስ የሰማዕትነት ጥብዓት ምንጩ ይኸው መንኖ ጥሪት ነው፡፡ ፋሺስት ጣሊያን የእርሱ አቋም የራሳቸው አቋም፤ የእርሱ የጭቆና አገዛዝ የእርሳቸው አገዛዝ፣ የእርሱ ተራ ፕሮፓጋንዳ የእርሳቸው እውነት አድርገው እንዲቀበሉ መደለያ /ገንዘብ፣ መኪና በዘመኑ ዘመናዊ የሚባል ቤት/ ልስጦት ሳይላቸው ቀርቶ ነውን) ለሕዝባቸው፣ ለሀገራቸውና ለቤተክርስቲያናቸው ሰማዕት የሆኑት) እርሳቸው ግን መንኖ ጥሪትን ገንዘብ ያደረጉ አባት በመሆናቸው ሌሎቹ የቤተ ክህነቱ ባለሥልጣናት ለፋሺስት ጣሊያን ሲያድሩ መደለያው ሳያንበረክካቸው በመንፈሳዊ ወኔ ሰማዕት ሆነዋል፡፡

የዛሬዎቹ አንዳንድ ጳጳሳት የመንኖ ጥሪትን ሕይወቱን ይቅርና ቃሉን ማወቃቸውን እጠራጠራለሁ፡፡ ዛሬ፣ ዛሬ አንዳንዶቹ ለመኪና ስጦታ፣ ለገንዘብ መደለያ፣ ለውዳሴ ከንቱ ብለው እናት ቤተ ክርስተያንን ዋጋ እያስከፈሏት ይገኛሉ፡፡ ዶግማዋን በላንድ ክሩዘር፣ ቀኖናዋን በG+1,2,3,4 . . . . ቤቶች ለውጠዋል፡፡ ሥርዐተ አበውን አመድ ላይ የወደቀ ሥጋ አድርገዋል፡፡ ወርቅና ብር ለመዘነላቸው አጽራረ ቤተክርስቲያን ሁሉ የሚያድሩ እንዲሁም ጥብቅና የሚቆሙ፣ ጥሩ የፕሮፓጋንዳ መሣሪያ ሆነው የሚያገለግሉ ናቸው፡፡

አንዳንዶቹም የጴጥሮሳዊነት ምንጭ የሆነው መንኖ ጥሪት እጅግ ስለራቃቸው በየገዳማቱ፣ በየአብያተ ክርስቲያናቱ ስም የሚሰበሰበው ገንዘብ የገዳማቱን እና የየአድባራቱን መሠረታዊ ችግር ከሚፈታ ይልቅ እነርሱ ኪስ ሲገባ የሚያስደስታቸው፤ በየሀገረ ስብከቶቻቸው ያሉ ሊቃውንት በችጋር ሲሰደዱ፣ ወንበር ሲያጥፉ እነርሱ ግን መደለያ ያቀረቡላቸውን አጽራረ ቤተ ክርስቲያንን ሲከባከቡ፣ ሽርጉድ ሲያበዙላቸው ይታያል፡፡ ከቤተክርስቲያኗ የአስተዳደር ሕግ እና ሥርዐት ውጭ በየሀገረ ስብከቶቻቸው የእኅት እና የአክስት ልጆቻቸውን የሚቆጥሩ፡፡ እነርሱም በአቅማቸው ቤተሰባዊ አስተዳደርን ያሳፈኑ ናቸው፡፡ ለምን) «ጥጃ ጠባ ሆድ ገባ» ነውና፡፡ ከዚህ እውነታ ተነሥተን እነርሱ በፓትርያሪኩ ላይ ያነሡትን የቤተሰብ አስተዳደራዊ በደልን ስንፈትሽ ሞራላዊ ብቃት እንደሌላቸው ማረጋገጥ እንችላለን፡፡ እነርሱም ቤተሰባዊ አስተዳደር ደዌ የተጣባቸው ናቸው፡፡

ለዚህም ነው፡- እኛ እያለን አጽራረ ቤተክርስቲያን አይነኩም ባዮች የሆኑት፡፡ እነርሱ ለቤተክርስቲያን መከራ ከሚቀበሉ ቤተክርስቲያን መከራ መቀበሏን የፈቀዱት፡፡ እነርሱ ሞት ከሚቀምሱ ሥርዓቷን፣ ዶግማዋን፣ ቀኖናዋን ለሞት የዳረጉት፡፡ በአንድ ጀንበር የበር መሰበር ብትንትናቸው ወጥቶ ቤተ ክርስቲያንን ለማፍያው ቡድን ያስረከቡት፡፡ ከቅዱስ ሲኖዶስ ሉዓላዊ እና ሰማያዊ ሥልጣን መከበር ይልቅ የአባ እገሌ መሻር እና የአባ እገሌ መሾም ጉዳይ ሆኖባቸው በፍቅረ ሢመት /በሥልጣን ጥም/ አብደው በቤተክህነቱም ሆነ በቤተ ክርስቲያኒቱ ማየት የሚገባንን የአስተዳደር ለውጥ እንዳናይ ግርዶሽ ሆኑብን፡፡

እንግዲህ ቤተክህነቱም ያጣው የቤተክህነቱ ሰው ጴጥሮስ እና የእርሱ ተክለ ሰብእና ነው፡፡ የእያንዳንዳችንም ውሳኔ የሚጠይቀው ይኽንን ለመመለስ ዝግጁ መሆን ላይ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችንም ሆነች ቤተክህነቱ ከገቡበት ማጥ ልናወጣቸው የምንችለው በጴጥሮሳዊነት ነው፡፡ አምላከ ጴጥሮስ ባዶዋን ለቀረችው ቤተ ክርስቲያናችን እንዲሁም የሰው ያለህ ለሚለው ቤተክህነት ያጣውን ሰው እስኪመልስለት እርሱ እንደፈቀደው ይሁን ከማለት ባሻግር ሁሉም ስለሁሉም በሁሉም የድርሻውን ይወጣ፡፡

33 comments:

Anonymous said...

ሊላይ ነኝ።ለአሁኑ ብዙም የምለው የለኝም ። እንዲያው ግን «ወላድ በድባብ ትሂድ» እንዲሉ ይህች የብዙዎች ዓናማዎች እናት ቤተክርስቲያን በባሮክ የተባ ብርዕ እኒያን አጋልጠው ለአጋላጭ የሰጡንን ሽፍንፍኖች በየፈርጃቸው አስቀምጦ ውስጠ ልብስ ጠባያቸውን ገላልጦ ስላሳየን አበጀህ!!! ልለው እጅግ ወደድሁ። ወላድ ቤተክርስቲያን በድባብ ትሂድ! גרןק השם ባሮክ ሃሼም(ስሙ ይባረክ)

Anonymous said...

ሊቃውንት ይቺን ሰሙን/ሰሞን "ፍሬ" ይሏታል። በመኾኑም ትናንት አሑድ በቅዳሴ ጌታ ለመንግሥተ-ሰማይ ምሳሌ ያደረገው አንድ መልካም ዘርን በርሻው የዘራ እና የሚጎበኝ ሰው ታሪክ ተነቦልናል። በዚህ የወንጌል ምሳሌ እንደሰማነው ከቡቃያ እስከ ጎምር (ፍጹም ፍሬ) ድረስ ያለው ኺደት መደምደሚያ "ወይፌኑ ማዕፀደ = ማጭድ ይልካል" ነው። መተርጕማኑ "ሞት ሠናይት" ብለውታል።

ታዲያ ከላይ እንዳነበብነው እነዚህን አንዲት ቅንጣት የመንፈስ ፍሬ ሊያሳዩን ያልቻሉ ጉዶች በዚህ አያያዛቸው "ሞት ሠናይት" ሳትኾን አጅሬው ጽሉም ገጹን ሕሡም ራእዩን እያሳየ ወደቤቱ ሊወስዳቸው ዓይኑን አፍጥጦ ጥርሱን አግጥጦ እንደተዘጋጀ ማን በነገረልኝ። እኛን ይተውን፣ ቤተክርስቲያኗንም ይተዋት እና ምናልባት ራሳቸውን እንኳ ይድኑ ዘንድ ቅጽበተ-ፈያታይ ዘየማንን ለማግኘት ቢጸልዩ።

Anonymous said...

Dear Dejeselamiawian,

Thank you very much for your date to date effort. Just I want to you pass me this question for Mahber Kidusan.

MK where are you now at this crucial time? Are you freezed by Abay Teshay and others in last time meeting? Where is the effort to address the current issues of the church on your website, news paper? Where you left the energy to push, negotiate the bishops to go in the right direction?

Ohhhhhhhhhh my God are you living the church alone......

Anonymous said...

Dear Deje Selam,

I am a regular reader of your blog from abroad. This last article of your is well articulated! Medhani alem bereketun yadilih! Egziabher betekirstianachinin yitebiqat!! Thank you very much for your effort!!!

Yeqolo Temari

TEWAHEDO said...

_____________

Message 2, to DEJESELAM, ON September 20, 2010

Excellent article! But who is gonna listen this? I think the Holy Synod needs to be sanctified, because it has already lost its sanctify (holiness) due to the following reasons:

1.The current patriarch (the father of all our fathers) in Addis is void of spirituality and by no means BITSU'E WEKIDUS as his customary title says.

2.Most of the bishops ordained by this patriarch are as spiritually perverted as he is. Some are corrupt, and others are not up to the standard of the life of holiness which is sought by the episcopate they entered either by bribing or by mere loyalty to Abba Paulos.

3. There are a few good archbishops, especially those who were consecrated during the time of Abuna T/Haimanot and Abuna Merqorios. But as these fathers too do not have the courage to tell the truth and stand for the oppressed people (as the Gospel orders them to do in accordance with the Messianic Mission of our Lord Jesus Christ Lk. 4:16-19), they can do nothing for our Mother Church, who is suffering from inside and outside as well. Also as these archbishops are far from the modern education and system, they do not know the political trick into which the Church has long fallen.

4. The whole clerical ordination process in the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church is pathetic. History shows that the Coptic bishops who used to govern the EOTC have contributed a lot for the current lack of pastoral care and commitment of the clergy of the EOTC

SO WHAT IS THE SOLUTION?

1.Let the laity (ME'EMENANA) challenge the Holy Synod for the formulation of ADMINISTRATIVE COUNCIL which consists of both the clergy and the laity (among the committed children of the church).

2. If the Synod does not accept this proposal, the laity can forward their request to the government. Though the current government in Etiopia does not care for the church, at least it can show a concern to the serious query of the laity to avoid any puplic upheaval. After all, Meles Zenawi and his thugs now that if a religious riot arises in Ethiopia they cannot control it at all.

3. If this ADMINISTRATIVE COUNCIL is formulated, it would serve as the back bone of the church. It will start its job by clearing up the mess in the church. Among the duties of this COUNCIL, the following can be mentioned:

A. Auditing the budget of the BETE KIHINET and reforming the nepotistic/ethnic way of administration within the patriarchate and all the concerned dioceses (this is a key to solving all the current problems of our Mother Church).

B. Working with the Holy Synod (of course, under the blessing of the Synod) on administrative issues, and playing a vital role during the selection of new bishops, and even that of a patriarch when need be.

C. Organizing workshops to enhance the quality of the clergies' leadership and pastoral care.

D. Working closely with the two theological seminaries (Holy Trinity and St. Paulos’) in Addis Ababa for the promotion of publications on the churches teachings, and mainly on solving the current mind-boggling and numerous problems of the church.

E. Censuring all the spiritual songs and books that are distributed in the name of the church, and controlling the activities of so called associations (MAHIBERAT) including MAHIBARA KIDUSAN about which time is lacking to write.

Blessings,
TEWAHEDO from

TEWAHEDO said...

cont'd...

selamawi said...

በስመ ስላሴ አሃዱ አምላክ አሜን

መቸም አብዛኞቻችን የቤተክርስቲያናችን ችግሮችና ችግር ፈጣሪ አካላት እነማን እንደሆኑ የገባን ይመስላል እስቲ ወደ መፍትሔው እንሂድ ምን እናድርግ ? ከኛ ምን ይጠበቃል?

Anonymous said...

ቤተ ክህነቱ ያጣው የቤተ ክህነት ሰው በሚለው ርዕስ የቤተ ክርስቲያናችን መሰረታዊ ችግር ከታች ያለ መሆኑን እድገነዘብ
አድርጐኛል። ጳጳሳቱ በቤ/ክ ውስጥ ችግር እንዳለ ቢያምኑም ችግሩ
ን ግን እንዲፈታ የሚጠብቁት ግን ሕዝቡን /መንግስትን/ ነው መንግስት እንኮን በጉዳያቸው እንደማይገባ ግልጡን ቢናገርም የፍርሃት መንፈስ የተጸናወታቸው ስለሆን ጴጥሮሳዊ ድፍረት የላቸው
ም በውጭ አገር ያለው ኢትዮጵያዊ በአብዛኛው አገሩ ለመግባት ሲናፍቅ እነርሱ ግን ብለው ቢጠሩ እንኳን ለመሄድ የማይፈልጉ ቢቻላቸው እንደን አባ መላኩ ሲትዝን ለመሆን ቅድሚያ አሳይለም ለመጠየቅ ዝግጅት በማድረግ ላይ የሚገኙ ለቤተ ክርስቲያን መፍትሔ ያመጣሉ ብሎ መጠበቅ ራስን ማታለል ነው።
የሲኖዶስ ስብሰባ ሲደርስ መናለ የሄ ጥቅምትና ግንቦት ወር ባይደርስ ብሄድ ሊያስቀሩኝ ይችላሉ ብለው የሚጨነቁ ከቤተ ክርስቲያን ይልቅ ላራሳቸው ክብር የቆሙ እንዴት ብለው ለቤተ ክርስቲያን ሊቆረቆሩላት ይችላሉ ይቆረቁሯታል እንጂ። ይህ ፍርሃት ደግሞ የሚመጣው ችግር ስላለባቸው ነው። ቀደም ባለው ጊዜ ለጵጵስና የሚታጩ አባቶች በገዳማዊ ሕየወት የሚታወቁ በቤተ ክርስቲያኒቱ ትምህርት በሚገባ የተውጡ ሀላፊነታቸውንም በሚገባ የተወጡ ነበሩ። ዛሬ መንኮ ሳቱ ሁለ እራሳቸውን ቆሞስ ብለው ሰይመዋል።ለጵጵስናውም ከጋዳም ቀርቶ ምርጫው ከአሜሪካ ሆኖል። መነኩሴው ሁሉ በውጭ አገር የፓትርያርኩና
የመንግስት አውጋዥ ነው ። ለአስኬማው ሲል አራት ኪሎ ላይ ደጀ ጠኚ ነው ። በዶላሩ ያንኮኮል ለገዳማዊያን አባቶች አቤቱታ ለማቅረብ የሚዘጉ ቤቶች ለነዚ ይከፈታል።
ስለዚህ ስለቤተ ክርስቲያን መፍትሔ ይመጣል ብለን ከእነዚህ መጠበቅ ላም አለኝ እንዳይሆን እሰካለሁ። መፍትሔው ያለው በእግዚአብሔር እጅ ነው ወደ እርሱ መጸለይ።

ምስጢረ said...

የቤተክርስቲያናችን ጉዳይ እለት እለት እየባሰበት ነው እንደኔ እምነት እያንዳንዱ ምእመን የራሱን እርምጃ ሊወስድ ይገባዋል ከእያንዳንዱምእመን በሚገኝ ሙዳይ ምጽዋት ነው ቪላ የሚገነቡት መኪና የሚገዙት ሌላም ሌላም ስጦታችን ቤተክርስቲያንን ካልጠቀማት ጉዳዩ እስከሚስተካከል ድረስ ልናቆም ይገባል ብየ አምናለሁ ምናልባትም የዘራፋወቹንም የገንዘብ መጠን እንቀንስ ይሆናል እግዚአብሄር ሲያስተካክለው ደግሞ ሆብለን በቻልነው ሁሉ ቤተ ክርስቲያናችን ያጐደሉባትን እንሞላነን ብየአምናለሁ የገጠር አብያተ ክርስቲያናትን ባለመዘንጋት።

Anonymous said...

This was the article we should have discussed long time ago and find solutions.I have never seen the ememy that attacked Tewhadeon other than ABO Abo mebabal. Many decades passed nothing better happened so far. So let's face the truth like the writer of this article. This is time to tell these people enough!Stop!Yabaten bet yewenbedewch washa atadergauat malet ke hulachin ye betekirstian teqorqwari yetebeqal.How long we keep talking? Now is the time of action. Great job the producer and facilititor of this article. Say goodbye to diplomacy and light up the truth. God won't let pops like these who build their villas, buy cars,collect cashes for the inocenet Christians. We let them snatched us now we are getting the consequences.STOP! STOP! STOP!

Anonymous said...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን።
የተወደዳችሁ የተዋህዶ ልጆች በዚህ ጽሁፍ ከቀረበው መንሻ ሃሳብ እንደምንረዳው ቤተ ክርስትያን ልጆችን አላገነኘችም።
እኛ እያንዳንዳችንም ጣታችን ከመጠቆም በስተቀር ጠብታ አሰተዋጽኦ ለማድረግ እምነት፥ትእግስት፥ፍቅር፥ጽናት፥ቅንጅት እና እውነት አጥተናል። እነዚህን ለማግኘት ደግሞ እውነተኛ የተዋህዶ ልጆች መሆን ይጠይቃል፡፡ እኛ መንፈሳዊነትን ተቀዳጅተን ነው ሌሎችን መንፈሳውያን ይሆኑ ዘንድ ማሰተማር ፥ ማበርታት፥ መገሰጽ እና መውቀስ የምንችለው።
ዛሬ ቤተ ክርስትያንም የቤተ ክርስትያን አምላክ እግዚአብሔርም የሚያርሩብን ሆነናል ሁላችንም፡፡ ዛሬ ስለ ተዋህዶ ፥ ስለ ሐይማኖታችን ምንም እንዳንሰራ አዚም ይዞናል። ችግሮቹ ብዙዎች መፍትሄዎችም ከባድ እና የቁርጥ ቀን ልጅ የሚጠይቁ!!!
የተዋህዶ ምእመናና ምእመናት እንዲሁም ካህናት፥ የአሁኑ የጥቅምት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ሥራ ይሰራ ዘንድ ካሁኑ
በመቀናጀት አንድ ነገር ማድረግ አለባቸው።
1.እሰከ አሁን በተጨባጪ በቤተ ክርስቲያናቺን እየተፈጸሙያ ያሉ ቸግሮች በዝርዝር ቢዘጋጁ ፥ እና ለብዙሃኑ የኢ.ኦ.ተ.ቤ ልጆ ቢተላለፍ፡ ምክንያቱም የኢንተር ኔት ወሬ ብቻ ሆኖ እንዳይቀር!!!!
2.ይህ በቤተ ክርስቲያን ላይ እየተፈጸመ ያለ ችግር (ሥርዓትየለሽነት፥ሙስና፥አደርባይነት፥ቸልተኝነት፥የቀኖና ጥሰት፥ አርአያ ክህነት እና ምንኩስና ማጣት፥ ወ.ዘ.ተ) በአስቸኳይ ይስተካከል ዘንድ ለፓትርያረኩ ፥ለጳጳሳቱ እና ለሊቃውንት ጉባኤ በጽሁፍ ቢቀርብ ግላባጩም ለመንግሥት ቢደርስ፥
3.በሓገር ውስጥ እና በውጭ ያሉ የተዋህዶ ልጆች በራሳቸው አነሳሽነት ከየአድባራቱ ለሶስት ቀን ሳይወጡ ምህላ እና ጾም ቢያደርጉ እና የቤተ ክርሰቲያን አባቶች ራሳቸውን እና ቤተ ክህነቱን ያጽዱ መልእክት በተለያዩ መንገዶች በህብረት ቢያሰሙ፥
4.ቀደም ብሎ በሌላ ጽሃፊ እንደተገለጽው ወደፊት ቤተ ክርስቲያን ከአድር ባዮቸ የጸዳች ትሆን ዘንድ
ከካህናት እና ከምእመናን የተውጣጣ የቤተ ክርስቲያንን ችግሮቸ እየተከታተለ ለቅዱስ ሲኖዶስ ፥ለሊቃውን ጉባኤ
እና ለምእመናን ጉባኤ የሚቀርብ ካውንሲል ቢቋቋም፥
ወገኖቼ እግዚአብሔር ለቤቱ ፥ ለሕጉ እና ለሥረዓቱ እንደ እነ ነቢዩ ኤልያስ እንደ እነ ሰማዕቱ ቅዱስ እሰጢፋኖስ እና ቅዱስ ጴጥሮስ የሚቀኑ ልጆቸን ይፈልጋል!!! በተለይ በቅርብ የእግዚአብሔር በሆነችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሚፈጽመውን የምታውቁ አባቶች ጳጳሳት፥ መነኮሳት፥ ካህናት፥ሊቃውንት፥ ዲያቆናት ፥ መምህራን፥ የሰበካ ጉባኤ አባላት ፥ የሰንበት ት.ቤት አባልት እና ምእመናን በእውነት መንፈሳውያን ፥ በእውነት የእግዚአብሔር ልጆች፥ በእውነት በሀልዎተ እግዚአብሔርን የምናምን ከሆን ከእግዚአብሔር ርቱዕ ፍርዱ እናመልጣለን ብላችሁ ይሆን?!!!
አምላካችን እግዚአብሔር ይመጣል ግልጽ ሆኖ ይመጣል ዝምም አይልም የወጉትም ያዩታል!!! አምላካቺንን ዛሬ መስቀሉን የጨበጣችሁ እየወጋችሁት አይደለም? በደሙ በመሰረታት ቅድስ ቤተክርስቲያን የምትፈጽሙት ሁሉ ግፍ !!!
አምላከ ቅዱሳን ለቤተ ክርስቲያን ሰው ይስጣት! አሜን።

Ps DS remove the redundant message by the Anony. It will hinder readers from seeing continuing comments

Dan said...

ብቃት የሌለው አላግባብ ያውም በጉቦ- በቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ኃላፊንት ሲቀመጥ ሳይውል ሳያድር ይጋለጣል....."ለካህናት እና ምእመናን ያላቸውን ንቀት እና አነስተኛ አባታዊ ክብር በተደጋጋሚ በማሳየት የሚታወቁት የሲዳማ፣ ጌዲኦ፣ አማሮ እና ቡርጂ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፋኑኤል ሀገረ ስብከቱን ለመምራት ባለባቸው ከፍተኛ የብቃት ማነስ ...... ከሐላፊነታቸው እንዲነሡ የሐዋሳ ከተማ ምእመናን ጠየቁ፡፡"

አባ መላኩ -አቡነ ፋኑኤል እና መሰሎች በማናቸውም ሀገረ ስብከት መሾም የለባቸውም:: ከሲኖዶሱም አባልነት መወገድ ያለባቸው ሌሎችም አሉ::

ቤተ ክርስቲያንን ለመምራት ብቃት የሌላቸው የተሰገሱበት ሲኖዶስን ማጽዳት ቀጥሎም አባ ጳውሎስን ወደ ገዳም ማስገባት ከዛም በየሀገረ ስብከቱ ተመሳሳይ በመስወድ ለመንፈስ ቅዱስ ታዛዦች ቤተ ክርስቲያንን የሚጠብቁ ምእመናንን የሚያግለግሉ
ማስነሳት - ሳይዘገይ አሁን ነው::

Anonymous said...

“And be kind to one another, tender-hearted, forgiving each other, just as God in Christ also has forgiven you.”

Hi deje betbetoch,

We all know that this is " MAHIBER KIDUSAN" blog which is linked with the association website, danielkibret website and yared febremedhin website. We know who is doing this with whom in the states. Guys, christianity is by far different from politics. If you are christian, like our apostles come out and say what you want to say for the Ethiopian orthodox followers. To me what you are doing id "GOSIP" HAHAHAHA!! tHIS IS NOT WHAT WE HAVE LEARNED FROM OUR FOREFATHERS. wHAT gOD SAYS " BE'DEBABAY YEMESEKERELIGN" not like waht you did now.Of course this is your usual strategy, it is becouse you do not know the church very well as you guys said. If you are our brothers and sisters, why you distort us. What is the need of posting this unrelevent information. Is it the approach that our forfathers were using for the growth of the church. My God... Please Please Please stop doing this kind of things.We know that, becouse of your hidden agenda/politics,you are fighting with the Government of ethiopia, holysynod members,sunday school department of EOTC, Theologians,Preachers and so on. So,why not you try to work closely and discuss with your fathers, brothers, sisters in the church instead of continuiong your hidden agenda in America with Abune.....

Please believe me this is God's time to respond for those victims of your association (Abune Mereha Kirstos and other holysynod members, M.B Seife Selassie,Many theologians, Preachers, Zemarians and Sunday School Students). They were crying to God to interfere and solve the problem that the church is facing since MAHIBER KIDUSAN WAS ESTABLISHED.

“I know the plans I have for you, declares the Lord, plans to prosper you and not to harm you, plans to give you hope and a future. (Jeremiah 29:11)”

Anonymous said...

Woy Enate Betekiristian!!!
Bicha Tinsaeshin yasayen!!!

Anonymous said...

some of the solutions may sound good but you all miss the point. Before we ever come to human solution, we should submit and surrender to God in prayer. We should pray for our religous leaders to show them the right path. If they don't return, they will be judged by God. Trust me it will not take a long time. The problem is we try to play God and prolong our suffering. The minute we try to take over, God leaves and our problems continue. But if we surrender and call our God, he will show up in time and clean up the mess. God have mercy on us

Anonymous said...

Well written and tell as it is love it,in the above pictures may be,i mean may be one or 2 of the are a little bit clean the rest they all crooks who doesn't care about anything except their wealth and most Mahiberati including MK didn't do anything to expose it, i did applaude Mk when they did expose those Tehdeso menokosati and sebakiwochi,wt is this different from them?

Dear Dejeselam i think it is time to expose them wt kind off wealth this "papasati" have one by one and lets know who is who are they one of us or they are Haynas i gave u this job since u are good at in finding the truth,and if u do that we going down in to the list.

Anonymous said...

Dear anonymous 3rd could you please read this http://eotc-mkidusan.org/site/index.php?option=com_content&task=view&id=366&Itemid=21

Anonymous said...

Dear Dejeselam,

You guys are doing great job. Keep it up. Please list the properties of the church leaders including their income ke telequ sewye beker.Everyone knows the wealth he possessed.Please please.This is very important!We need change.We need spiritual leaders!We are invaded by enemies in and out.We need a geniune leader who unite us, lead us, teach us and pray for us.Hope you will do this assignment very soon.

Anonymous said...

ደጀ ሰላሞች በቅድሚያ መንፈሳዊ ሰላምታየን አቀርባለሁ
ለመሆኑ እናንተ መንፈሳውያን ናችሁ ? ወይስ መሰሎች ይገርማል
ዘፍጥረት 27 ፤ 22 ምን ይላል “ያዕቆብም ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ ቀረበ፤ ዳሰሰውም ፤ እንዲህም አለው
ይህ ድምፅ የያዕቆብ ድምፅ ነው እጆች ግን የዔሳው እጆች ናቸው አለው ’’ ይህን ያልኩበት ምክንያት መንፈሳውያን ነን ከሚል ወይም
የቤተ ክርስቲያን ተቆርቋሪ ከሆነ እንዲህ አይነት ፅሑፍ አይጠበቅም ምን አልባት ድምፁ የያዕቆብ እጁ የሌላ ከሆነ ብናስተውል መልካም ነው፡፡ አንድ ጥያቄ አለኝ ጳጳሳትን የሃይማኖት መሪዎቻችንን በናንተ እይታ አዋረዳችሁ ወይም ኃጢአታቸውን ዘረዘራችሁ እሽ ስንት ሰው አነጻችሁበት? አባቶቻችን እንደአስተማሩን እግዚአብሔር ጳጳሳትን ፤ ካህናትን ፤ዲያቆናትን የሚቀጣው በውስተ ውሳጤ መንጦላእት ነው፡፡ ይህን እናምናለን ነገር ግን የሆነ ያልሆነውን በመጻፍ ቤተ ክርስቲያኗን ለመናፍቃን መሳለቂያ አታድርጓት
“ ኦ መደልው አውጽዕ ሰርዌ እምውስተ አይንከ ወእምዝ ትሬኢ ለአውጽኦ ሐሰር እምውስተ ዓይነ እሁከ ‘’ እያሉ ሰባክያነ ወንጌሉ
ያስተምሩናል እኛም አማኞች ይህን መጠበቅ ይገባናል፡፡ ስለዚህ ደጀ ሰላማውያን ሁላችሁ የሚያንፀውን አስተምሩን ፡፡
“ አንትሙሰ ፡ ሕቱ እንተ አፍአ ወአኮ እንተ ውስጥ ፡ ወእንተ ውስጥሰ እግዚአብሔር የአምር፡ ወይፈትን በማህቶተ ዚአሁ’’ይላሉ
ካህናቱ በቅዳሴአቸው፡ እናንተስ የውስጡን ያይደለ የአፍአውን መርምሩ የውስጡን ግን እግዚአብሔር ያውቃል በርሱ መብራትም ይመረምራል፡፡ ቃሉ የሚያስተምረን ይህን ነውና እናስተውል፡፡

This is a reality. But you should be spesfie the name like aba melaku and make more clear for the reders,then you save the name of appostelic real fathers.

Anonymous said...

HI THIS IS VERY GOOD MESSAGE

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)