September 1, 2010

ያሬድ አደመ በኮፒ ራይት ጥሰት ሊከሰስ ነው

(ደጀ ሰላም፤ ሰፕቴምበር 1/2001፤ ነሐሴ 26/2002 ዓ.ም):- የሐውልቱ ቡድን አባል የሆነው እና በቅርቡ በሲዳማ፣ ጌዲኦ፣ አማሮ እና ቡርጂ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤት ማደራጃ መምሪያ ሐላፊ ሆኖ በአቡነ ፋኑኤል የተሾመው ላእከ ወንጌል ያሬድ አደመ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ቁጥር 496/10 ስለ አእምሯዊ ንብረት መብት ጥበቃ የተደነገገውን በመተላለፍ ያለባለቤቶቹ ፈቃድ ባሳተማቸው አራት የመዝሙር መጻሕፍት፣ “ያልተገባ ጥቅም አግኝቷል፤ በአሳታሚዎቹ ላይ ከሃያ ሚሊዮን ብር ያላነሰ ኪሳራ አድርሷል” በሚል በኢትዮጵያ ኦዲዮ ቪዥዋል አሳታሚዎች ማኅበር ክስ ሊመሠረትበት ነው፡፡

ያሬድ አደመ “መዝሙረ ተዋሕዶ ዘኦርቶዶክስ” በሚል ርእስ በአራት ተከታታይ ቅጽ በተከታታይ ባሳተማቸው የመዝሙር መጻሕፍት ፈቃዳቸውን እንዳልጠየቃቸው፣ ከሽያጩ ከሚያገኘው ገቢም ዘማርያኑ፣ የግጥም እና ዜማ ደራስያኑ እንዲሁም አሳታሚዎቹ አንዳች ጥቅም አለማግኘታቸውን በተለይም አሳታሚዎቹ ከኻያ ሚልዮን ብር ያላነሰ ኪሳራ እንዳደረሰባቸው የገለጹት፡-

  1. ጌልጌላ መንፈሳዊ መዝሙር ቤት - መ/ር ዘመድኩን በቀለ
  2. አጋፔ መንፈሳዊ መዝሙር ቤት - ዲያቆን እንግዳወርቅ በቀለ
  3. መቅደላ መንፈሳዊ መዝሙር ቤት - አቶ ታዬ ዘለቀ
  4. አምባሰል ሙዚቃ ቤት - አቶ ፈቃዱ ዋሪ
  5. ዘማሪ ታዴዎስ ግርማ እና ሌሎችም
የሕግ ውክልና አባል ለሆኑበት ለኢትዮጵያ ኦዲዮ ቪዥዋል አሳታሚዎች ማኅበር ሰጥተዋል፤ ማኅበሩም የክስ ቻርጁን በሕግ ባለሞያው በኩል በማዘጋጀት ላይ መሆኑ ታውቋል፡፡

በብራና ማተሚያ ድርጅት ታትሞ፣ በአርያም መንፈሳዊ መዝሙር ቤት እና በሰማን መጻሕፍት ማከፋፈያ አከፋፋይነት በብዙ ሺሕ መቶ ቅጂ እንደተሰራጨ በሚገመተው በዚሁ ሕገ ወጥ የመጽሐፍ ኅትመት ያሬድ አደመ ‹‹የመዝሙሩን ግጥም በመስጠት ተባብረውኛል፤›› ያላቸውን ዘማርያን አመስግኗል፡፡ ይኹንና የአብዛኞቹ ግጥም እና ዜማዎች ድርሰት ግን የዘማርያኑ ሳይሆኑ የሌሎች ግለሰቦች እና በተወሰነ መልኩም የአሳታሚዎቹ አበርክቶዎች እንደ ሆኑ፣ ዘማርያኑ የመፍቀድ መብት እንደሌላቸው ነው ባለጉዳዮቹ የሚያስረዱት፡፡ ስለሆነም አሳታሚዎቹ በደረሰባቸው ኪሳራ ሳቢያ ከኻያ ሚልዮን ብር ያላነሰ ካሳ ከያሬድ አደመ እንደሚጠይቁ ይገልጻሉ፡፡ ያሬድ አደመ ከዚህ ቀደም በሐዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም መግቢያ እና በዙሪያው ‹‹የአስፋልት መንገድ አስነጥፋለሁ›› በሚል ያለሕጋዊ ደረሰኝ በሰበሰበው ልኩ የማይታወቅ ገንዘብ በሐዋሳ፣ ዲላ፣ ክብረ መንግሥት እና ሻሸመኔ ከተሞች እንደ ዐጸደ ሕፃናት፣ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት እና ዳቦ ቤት የመሳሰሉትን ድርጅቶች በማቋቋም ለግሉ እንደተጠቀመበት ይነገራል፡፡

5 comments:

The awaasa said...

I know Yared since he was A kid and high school . He his so devoted his life for our beloved church especially in southern part. pleaase stop gossiping and backward charge. please stop be mercenery and charge him on money. As far as I know he has different personaly which we can suspect him bucause he is so agrasive on truth.

Anonymous said...

Wud Dejeselam betam tiru mereja new.

Bezih metsehaf zuria zemarian ena asatami dirijitu bicha sayhonu besenbet t/bet agelgilot yalen ena saniwed begid "Mezmure tewahido"slemil bicha lemezemer yetegedednew hulachin chimir, endihum baltaremut mezmuroch sabia lemeweyayet enquan bemeferarat agelgilotun yastagolin hulachinim be iwnetegnaw dagna fit sinimogitachew neberna yihe huneta endih melk meyazu tiru timihirt new biye asbalehu. Leks likerbu yalutinim wendimachinin amlakachin melkam tiretachewin tekeblo kesihtetachew yemitaremubetin yehalafinetin menfes yadililin.

Bertu, birtatun yistachihu.

zkere said...

egziabhre bgizew srawne ysral

muluken said...

ማህበረ ቅዱሳን ነበርኩ፣ አሁን አሁን ግን ነገሮችን ረጋ ብየ እንድመለከት እግዚአብሔር ረዳኝ
መጀመሪያ ለቅድስት ተዋህዶ እምነታችን ተቆርቋሪ ይመስሉኝ ነበር። ከሆኑ

አቡነ ጳውሎስ ነጭ ሲለብሱ እና ኑፋቄ ካሰሙ
አቡነ ገብርኤል ኑፋቄ ካስተማሩ
አለቃ አያሌው ስለ እመቤታችን ከተሳሳቱ
ብጹዕ አቡነ ጎርጎሪዎስ በመብል ሰው አይረክስም ሲሉ
ባህታዊ ገብረ መስቀል ሲያምታቱ
ለመን አይናገሩም አባ ወልደተንሳኤን እና ሌሎችን ብቻ አብዝቶ ማሳደድ ለምን?

አኑን ከባለ ጊዜ ጋር መሆንን እየመረጡ ደጀሰላምን እየነቀፉ ነው፡ ይህ እውነት ጥሩ አይደለም ለቤ/ክ አይጠቅምም፣

teme said...

This is good news!
This man is still a parasite for our church;he made division on the sunday school in Hawassa{st.Gebriel}.
He is not for the church & I think it's God's time now...

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)