September 27, 2010

የኢሉ-አባ-ቦራው የአክራሪዎች ችግር እና ሃይማኖታዊ ምልከታዎቹ

(ደጀ ሰላማዊው)
በኢሉ-አባ-ቦራ (ገቺ) አካባቢ የቀረበው ዘገባ ብዙ ነገሮች ከውስጣችን እንዲያቃጭሉብን ከማድረጉም በላይ ብዙ ነገሮችን ዞር ብለን እንዳስታውስ አስገድዶናል :: የሆነው ሆኖ ግን ችግሩን ከውስጥም ብንመለከተው መልካም እይታ ስለመሰለን የራሳችንን እይታ እንደሚከተለው አናቅርባለን፡፡ ጣታችንን ወደ ጠላታችን ስንጠቁም ሦስቱ ወደኛ ስለሚያመለክት ከራሳችን እንጀምርና የመፍትሔውን ሐሳብ አብረን እናክልበታለን፡፡
 

 ሀ.  መግቢያ፡- ኢሉባቦርና አብሮ አደግነት
የዚህ ሀገረ ስብከት እስልምና እንደማንኛውም የቀድሞው ኢትዮጵያዊ እስልምና ነበር፡፡ ሰላምንና ኢትጵያዊ አንድነትን የሚሰብክ ነበረ። የዛሬውን አያድርገውና ክርስትና ሃይማኖት በኢሉባቦር ከፍለ ሀገር  ክርስቲያኑም ሆነ እስላሙ የቤተሰቦቻችንን ኃይማኖት እየዘከርን በፍቅር አብረን ያደግንበት አካባቢ ነበረ፡፡ ከሙስሊም ወንድሞቻችን ጋር ውሃ እየተራጨን፣ የማገዶ እንጨት በተራ (ደቦ) እየገባን እየለቀምን፣ ከብቶቻችንን አብረን በማኅበር እያገድን፣ ቤተሰቦቻችንን እየረዳን፣ ያደግንበት ክፍለ ሀገር ነበረ፡፡

ከዚያም አልፎ ተርፎ ሐያና ሰላሳ ኪሎ ሜትር ስንቆቻችንን ሸክፈን ዘመናዊውን ዕውቀት ፍለጋ ስንጓዝ ተሻምተን እየበላን፣ ያደግንባት ክርስቶስ በፀጋው ካደላት ልምላሜ የሚወጣውን ሽታ እየተጋራን፣ ሳንነቃቀፍ፣ አብረን ማደጋችንን ዛሬም ቢሆን የማንክደው ሃቅ ነበረ፡፡ የእኛ አብሮ አደግነታችን ከሃይማኖት አነፃርም ሲገመገም እንደ ምሳሌ የምንጠቅሳቸው አያለ እውነታዎች እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አሻራቸው ይታይ ነበረ፡፡ “ቤተ ክርስቲያን ሲሰራ ምስጥ የማይበላው መድን እንጨት ከደጋማው ክፍል ጠርቦ በማምጣት ሙስሊሙ ይተባበር ነበረ” ብለውን ነበር አንድ አባት በአንድ ወቅት:: ያረጁት አብያተ ክርስቲያናት ሲታደሱ አንዳንድ ቋሚዎች አልነቀል ብለው ሲያሰቸግሩም መታየታቸው ያንን ይጠቁማሉ፡፡ እንደዛሬው ምስማር ሳይለመድ አጠንክሮ የሚያስር ሐረግ ከቆላማው አካባቢም በማምጣት ተባብረዋቸዋል:: ክርስቲያኖቹም ቢሆኑ በመስጊድ ሥራ ተመሣሣይ ተግባር ላይ ከመሣተፍ ወደኋላ እንዳላሉ እኛም ለእነርሱ እነርሱም ለእኛ ምስክረሮች ነን፡፡ የኛም የልጆቻቸው አብሮ በፍቅር ማደግ ከዚህ ትሥሥሮሽ የመነጨ ነበረ::

ታዲያ በዚህ አካባቢ ካለው ፍቅር ባሻገር ኢሉ አባቦራን የእግዚብሔር ፀጋ እንዳልራቃት የምንረዳው በ1977 ዓ.ም. ተከስቶ የነበረው ድርቅ የሰሜኑን የሀገራችንን ክፍል ክፉኛ ሲጎዳ በወቅቱ የነበረው መንግስት ብዙ ወገኖቻችንን አምጥቶ እዚያ ሲያሰፍር እኛው የትናንቱ አብሮ አደጎች የዛሬዎቹ ባላንጣዎች አብረን ማስተናገዳችን የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡: በዚያ ጊዜ ከተከሰቱት አደገኛ ክስተቶች ግን የማንክደው ሃቅ ዛሬ በኢሉባቦር እንደ አሸን የፈሉት የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች በሠፈራ ለመጡት ወገኖቻችን ስንዴ ይዘው ከመጡት ዜጎች ጋር ከባድ ጠንቅ (ነቀርሳ) መግባቱን ነው:: የመጡትም ወገኖቻችን ሃይማኖታቸውም ጎሳቸውም እንደ እኛው የተለያዩ መሆናቸውን የምንዘነጋው አይደለም፡፡ ነገር ግን ለሠፋሪዎቹ እርዳታ ተብሎ ከስንዴው ጋር የገባው መጤው እምነት በዕድሜም የእኛ ታናሽ ነውና ከቁጥር የምናስገባው ጉዳይ አይሆንም፡፡ ጥሩ ማረጋገጫም የሚሆነን የዛሬዎቹ አክራሪ ሙስሊሞች እነርሱን ከመጤፍ አለመቁጠራቸውና በጥንታዊቷ ሃይማኖት ላይ ማነጣጠራቸውን ልብ ልንለው ይገባል፡፡ ቅርስ ፍለጋ የሚኬደው ቅርስ ካለው ጋር ነውና ፡፡ የእነርሱን ለእነርሱ ትተን ስለ እኛው እንነጋገር ለጊዜው፡፡
እንግዲህ ከላይ የጠቀስናቸው የአብሮነት ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ያለው ጉዳይ ግን አስጊነቱ የሚካድ አይደለም፡፡ እስካሁን ስናትት የነበረው “ነበር!” እያልን ነው፡፡ ቁጭት ነውና ነበር! እንላለን፡፡ አቀራረባችንን ለማሳጠር ግን ወደ ዋናው ጉዳይ እንምጣና ችግራችን እውነት የአክራሪ እስልምና ጫና ብቻ ነውን? አይደለም!! ምክንያቱን እንደሚከተለው ለማየት እንሞክራለን፡፡


ለ. የችግሮቹ ዋና ዋና መገለጫዎች 

  1. ሀገረ ስብከቱ ለችግሮች ትኩረት አለመስጠት
ይህ ሀገረ ስብከት በጳጳሳት (በሊቃነ ጳጳሳት) መመራት ካቆመ ሰንበትበት ብሏል፡፡ ምነው የአባቶችን ሥራ መና አስቀራችሁ እንደማትሉን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ያልንበትን ምክንያት ግን ዓባይን በጭልፋ እንደሚባለው አንድ ሁለት ምሣሌ ብቻ እናውጋችሁ፡፡
በተጠቀሰቺው በገቺ ወረዳ (ሥዕላዊ መግለጫውን ይመልከቱ)  ሥር 9 አብያተ ክርስቲያናት ሲኖሩ ከዘጠኙ ሙሉ ቅዳሴ የሚቀደሰው በሁለቱ ብቻ እንደሆነ የቅርብ መረጃ አለን፡፡ የሚገርመው እዚያው በገጠሪቷ በአንዱዋ ቤተ ክርስቲያን ተቀጥረው የሚያገለግሉ አንድ ካህን ኑሮ በጣም ሲወደድ  “ኑሮ ከብዶኛል እዚህ ቦታ ማገልገል አልቻልኩም እባካችሁ 50 ብር ጨምሩልኝና ደሞዜ 200 ብር እንኳን ትሁንልኝ” ብለው የሚመጸኑ አባታ መስማት ምንኛ ያስደነግጥ ይሆን፡፡  

አንድ አሳዛኝ ምሳሌ እንድገም፡፡ ከዚህች ወረዳ ቀጥላ ያለችው የቦረቻ ወረዳ (ሥዕላዊ መግለጫውን ይመልከቱ) ውስጥ የኪዳነ ምህረት ጽላት በሌቦች ተሰርቆ ይጠፋል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን አባታችን (ሊቀ ጳጳሱ) የሰሙት ነገሩ ውሎ ካደረ በኋላ ነው፡፡ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያያጅ ስለ ሁኔታው እንዲያጣሩ ተልከው መኪና ቦታው መድረስ ባለመቻሉ ነገር ዓለሙን ትተው ማርና ቅቤ እንዲሁም ጤፍ ለሆቴላቸው ገዝተው መመለሳቸው ከማሳዘንም አልፎ አንገት የሚያስደፋ ነው፡፡  አባቶች መጡ ሲባል ጠብ እርግፍ እያለ ለሚያስተናግደው ለኢሉባቦር ክርስቲያን ሕዝብ፣ ያውም የኪዳነ ምህረትን ታቦት ለተነጠቀ ወገን የማፅናኛ መልዕክት እንኩዋን ሣይለግሱ መመለስ ምንኛ ይጎዳ ይሆን፡፡ እንዳልናችሁ የችግሩ ብዛት የትየለሌ ስለሆነ ለምሳሌ ያህል ይህንን ካየን ለጊዜው ይበቃል፡፡

የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ እውነት ለመናገር ቅንና ጥሩ አባት እንደሆኑ ሳንናገር ማለፍ ግን አልፈልግም፡፡ቆመው ሲያስተምሩና ቡራኬ ሲሰጡ ከልብ የሚያጽናኑ አባት ናቸው፡፡  ነገር ግን አባታዊ ቅንነትና አስተዳደራዊ ብቃት የተለያዩ ነገሮች ሆነውብናል በዚህ ሀገረ ስብከት፡፡ አልፎ ተርፎም ካላቸው የሥራ ድርርቦሽ የተነሳ ሀገረ ስብከቱን “በተልዕኮ” ማስተዳደራቸው ከባድ ተፅዕኖ እንደፈጠረ ሳንጠቅስ አናልፍም፡፡ የትንሳኤ ዘጉባኤ የበላይ ጠባቂነትን፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅነትን፣ የኢሉባቦር እና የጋምቤላ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስነትን የቅዱስ ሲኖዶስ ቋሚ አባልነትን... አንድ ላይ አስተባብሮ ማስኬድ በእግዚአብሔር ረዳትነትና በአባታዊ ፀጋቸው ይቻላል ተብሎ ቢገመትም አሁን በሀገረ ስብከቱ ላይ ያለው አሉታዊ ተፅእኖ ቀላል አይደለም፡፡

እንደው ነገሩን ጠለቅ ብሎ መጥቀስ ካስፈለገ የጂማው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እኮ ተመሣሣይ ችግር ከዚህ በፊት ሲከሰት ከሕብረተሰቡ ጋር ቦታው ላይ ነበሩ፡፡ ምነው እኛስ አባት የለንም እንዴ? አጽናኝ ማጣት ነበረብን? ስለዚህ ለቅሶ ደራሽ ሣይሆን አብሮን የሚያለቅስ አባት አስፈልጎናል አሁን፡፡ ለሚነሱት ችግሮች በሙሉ ሀገረ ስብከቱ ሳይሆን ህዝቡ ነው ትኩረት ሰጥቶ በመሥራት ላይ ያለውና እባካችሁ አባቶች ኣባት ሁኑን እንላለን፡፡ የጓዳችን ችግር መቼም የሚያልቅ አይደለምና እርሱ እንደተከደነው እስኪበስል ይህ መንጋ እናንተ እያያችሁ ተበትኗልና ሰብስቡን፡፡ ችግሮች ሲከሰቱ እንኳን ህዝቡ ብዙ መከራ ካየ በኋላ ነው እየመጣችሁ ያላችሁት፡፡ በዚህ ረገድ ከመንግስት በኩል የተሰጠን አፋጣኝ ምላሽ ከእናንተ አባታዊ ጥበቃ የተሻለ መሆኑን በድፍረት ለመናገር ተገድደናል፡፡
2.    
     የምዕመናን መሠረታዊ የክርስትና ትምህርት አለማግኘት
ከመግቢያው ለመጥቀስ እንደሞከርነው ክርስቲያኑ ሕብረተሰብ ከሌሎች እምነቶች ጋር ያለው ልዩነትና አብሮነት ከመንፈሳዊ ትስስር ይልቅ ባህላዊዉን ግንኙነት የሚያጎላ ሆኖ ይታያል፡፡ ክርስቲያኑ ሕብረተሰብ በሰንበት ትምህርት ቤቶች ገብቶ የሚማረው ጥቂት ነው። ከዚያ በተሻለ አብዛኛው የጽዋ ማኅበራትንና ሰንበቴ ሲያዘወትር ይታያል፡፡ የሰበካ አባልነት መታወቂያ ያለውና በንግስ ክብረ በዓላት ላይ የሚታየው ምዕመን ቁጥሩ ፍጹም የተለያየ ነው፡፡ ክርስትና ተነሥቶ የክርስትና ማስረጃ (ሰርተፍኬት) ያለው ምዕመንም ጥቂት ነው፡፡ የክርስትና ማስረጃም እንዳለ የሚያውቅ በርግጥ ጥቂት መሆኑ የሚያስገርም አይደለም፡፡ አሁን አሁንማ ብዙሃኑ የቤተ ክርስቲያን አስፈላጊ መዋጮን ከፍሎ ተገቢውን አገልግሎት ከማግኘት ይልቅ በዕድር ተመዝግቦ የቀብሩን ሁኔታ አስቀድሞ ማሰብ የጀመረ ይመስላል፡፡ ምክንያቱም መቀበሪያ ወደደችም ጠላችም ቤተክርስቲያን አለችና፡፡ ግን አስደናቂው ነገር ለሰበካ አባልነት የሚከፈለው ዓመታዊ  መዋጮ ከዕድር ወርሃዊ መዋጮ ማነሱን እንኩዋን የሚያውቅ ጥቂት ነው፡፡
የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችም ቢሆኑ መዝሙሮችን ከማጥናትና በበዓላት ቀን መዝሙርና ሥነ ጽሁፎችን ከማቅረብ ያለፈ አንድ ምዕመን ማግኘት የሚገባውን መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት እያገኙ አይደለም፡፡ ለነገሩ የሰንበት ትምህርት ቤት ያለውም ቤተ ክርስቲያን በጣም ጥቂት ነው፡፡ ለዚህም ነው አሁን አሁን ከክርስቲያኑ መሃል እያፈተለኩ ሃይማኖታቸውን ቀይረው ሙስሊሙን ኅብረተሰብ የሚቀላቀሉ ወጣቶች እየታዩ የመጡት፡፡ ጠንካሮች ናቸው፣ ብዙ ለውጥ ያመጣሉ ተብለው ከዚሁ ሀገረ ስብከት ወደ መንፈሳው ኮሌጅ የሚገቡ ወጣቶች (ዲያቆናት) ደግሞ በዚያው የውሃ ሽታ ሆነው ይቀራሉ፡፡
ስለዚህ ለዚህ ምዕመን ሃይማኖታዊ መሠረት ማበጀትና መሠረታዊ የክርስትና ሃይማኖት ትምህርት መስጠት ተገቢና ወሳኝ እርምጃ ቢሆንም ማን ይስጥ? እንዴት ይሰጥ? መች ይሰጥ  የሚሉት ጥያቄዎች.... ተንጠልጥለው የቀሩና ምላሽ የሚፈልጉ ናቸው፡፡

3.   የአክራሪ ሙስሊሞች ስልታዊ አካሄድ

በመግቢያችን ላይ ለመጥቀስ እንደሞከርነው በዚህ ሀገረ ስብከት የእስልምና እምነትን ወቅታዊ ሁኔት ከቀድሞው አንፃር ስናነፃፅረው ብዙ ልዩነቶች ይታዩበታል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ የአረብ ሀገራት ተጉዘው የእስልምና ትምህርትን የቀሰሙ ወገኖች ወደዚህ አካቢ ተመልሰው የጥላቻን ትምህርት ማስፋፋት እንደ ዋነኛ ስልት የሚታይ ጉዳይ ነው፡፡ ከመንግሥት በኩል የሚመጣውን ጫና መከላከያ መንገዳቸው ደግሞ በተቻለ መጠን በከፍተኛ (ከወረዳ እስከ ዞን) የአመራር ቦታዎች ላይ ለእነርሱ (ለእምነታቸው) ከለላና ታማኝ የሆኑ ሰዎች እንዲገቡ ማንኛውንም መስዋዕትነት መክፈል መቻላቸው ነው፡፡

ሌላው አካሄድ በኣካል የማጥፋት ጥቃቱና ጭፍጨፋው በሚካሄድበት ወቅት በገንዘብም ሆነ በጉልበት አስፈላጊውን ትብብር ከማድረግ ባሻገር የሚፈጠረውን ጉዳት የግል ቂም ወይም ተራ የሰዎች ግጭት እንደሆነ አድርገው ማድበስበስ መቻላቸው ነው፡፡  ይህ በጠቅላላው እየተተገበረ ያለ ነገር ሲሆን የክርስቲያኑ ምዕመን ከኃላፊነት ቦታዎች መሸሽ አስፈላጊውን እገዛ ለእነርሱ ከመስጠቱም ባሻገር ለቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ሀገረ ስብከት መዳከም ከባድ ሚና እየተጫወተ መሆኑም በግልዕ የሚታይ ጉዳይ ሆኗል፡፡ የአመራር ብቃት ያላቸውና በዓለማዊውም ትምህርት አንቱ የሚባሉ የሕዝበ ክርስቲያኑ የዚህ አካባቢ ተወላጆች ወደ አካባቢው ተመልሰው በሥራ መሠማራት አለመፈለግ የዚሁ ተዛማጅ ችግር መገለጫ ነው፡፡
ወደ ገጠራማው ቀበሌዎች ስንወርድ ደግሞ ከመግቢያው ላይ የጠቀስናቸውን የማሕበራዊ ሕይወት ማዳከም ትልቁ የአክራሪዎች ተግባር ነው፡፡ አስሰጋጆቹ የሚሰጡትም ትምህርት የዋዛ ስላልሆነ ለክርስቲያኖቹ ቀላል ፈተና አይደለም፡፡ ለምሳሌ፡- እነርሱ  “ካፍራ ናቸው” (ካፍራ ማለት ያላመነ ማለት ነው)፣ “ነጀሳ ናቸው” (ነጀሳ ማለት እርኩስ ወይም የበከተ ማለት ነው) “ስለዚህ እነርሱን የነካ የተነጀሰ ነው፤ ከእኛም የተለየ ነው” በማለት ትምህርት ስለሚሰጡ በየቦታው የማግለል ተግባር ከመፈፀማቸው ባለፈ “ሃይማኖታችንን ካልተቀላቀላችሁ ከእናንተ ጋር ደቦ አንካፈልም፣ ቡናም አንጠጣም፣ ብትሞቱም አንቀብራችሁም” በማለት ጫና እየፈጥሩ ክርስቲያኖቹን ሃይማኖታቸውን እንዲቀይሩ ያስገድዷቸዋል፡፡ በኢኮኖሚ አቅም ደከም ያሉትን ደግሞ በገንዘብ አታልለው ወደ ራሳቸው የመውሰድ ሥራ በቀላሉ የሚታለፍ ነገር አይደለም፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ለወደፊት ዘለቄታ ያለው አካሄዳቸው ደግሞ ይበልጡን ስጋት የሚፈጥር ጉዳይ ነው፡፡ ይኸውም አካሄድ ተተኪ ተረካቢዎቻቸውን ኮትኩተው የሚያሳድጉበት ስልት ነው፡፡ ማንኛውም የአንድ ሙስሊም ልጅ በተቻለ መጠን የእነርሱን ትምህርት የማግኘት ሒደቱን ገና በጨቅላ ዕድሜው ይቀላቀላል፡፡ ሲያድግም ከዚህን በፊት የተደረጉትን ክስተቶች ከማሳወጅ ወደኋላ የማያስብል ትምህርት እያገኘ ያድጋል ማለት ነው፡፡
ለዚህ ሁሉ ማስተግበሪያ የሚውል ገንዘብ በአብዛኛው ከሩቅ የሚመጣ አይምሰላችሁ፡፡ ኢሉ አባቦራ የሀገሪቷን ኢኮኖሚ የሚደግፈውን ቡና በማምረት ቀዳሚውን ሚና የምትጫወት አካባቢ ስለሆነች የቡና ንግድ ላይ የተሠማሩት ነጋዴዎችም “እስላማዊ ግዴታቸውን” የሚወጡት ከትርፋቸው በሚለግሱት እርዳታ መሆኑን ልብ ልንለው ይገባል፡፡ ሌላው አስገራሚው ብዙ ሚስት ማግባት ስለሚፈቀድ የሕዝብ ብዛትን በመጨመር በቁጥር ከክርስቲያኖቹ ልቀው የመገኘት ደግሞ ወሳኙ የረጅም ጊዜ ዕቅዳቸው ነው፡፡

ሐ.     የመፍትሔ አቅጣጫዎች ጥቆማ
ከላይ የጠቀስናቸው ችግሮች ባለን ውሱን የአገላለጽ  አቅማችን ለመጠቆም ሞከርን እንጂ የዚህ ሀገረ ስብከት ጉዳይ ስለእውነት በቀላል የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም፡፡ የሆነው ሆኖ ግን አንባቢው ሁሉ ችግራችሁ ችግራችን ነው ብሎ የመፍትሔ አቅጣጫ እንዲጠቁመንና እንዲተባበረን አደራ እያልን ምን እናድርግ የሚለውን በሚከተለው መልኩ የትኩረት አቅጣጫዎችን ለመጠቆም እንወዳለን፡፡  
1.     
     የአጭር ጊዜ የመፍትሔ አቅጣጫዎች፡
  • ለገዳማውያንና ለመናንያን ችግራችንን ነግራችሁ በጸሎት እንዲያስቡን ብታደርጉልን፤
  • የሀገረ ስብከቱ አስተዳደራዊ መዋቅር የሚጠናከርበትንና የሚሻሻልበትን መንገድ ከሚመለከተው ክፍል ጋር እንድትነጋገሩልን፤
  • ሊቀ ጳጳሱ በርቀት ሆነው አሁን ከተጋረጠብን አደጋ ሊታደጉን ስለማይችሉ እሣቸው ባሉበት ሆነው በጸሎት እንዲያስቡን እየጠየቅን ለእኛ ግን ዕለት ተዕለት ከእኛ ጋር ሊተጋ የሚችል አባት የምናገኝበት እንዲታሰብልን፤
  •  ሰንበት ትምህርትቤቶች ባሉበት ቦታ መሠረታዊ የቤተክርስቲያን ትምህርት በሚገባ የሚሰጡ መምህራንን ወጪአቸውን ሸፍናችሁ (ለምሳሌ፡- ከአንድ ወር እስከ ሦስት ወር የሚቆይ) እንድታስተምሩልን- ሞንታርቦ ይዞ የሚመጣ ሣይሆን በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ቁጭ አድርጎ የሚያስተምር ከነጣቂ ተኩላዎች የሚጠብቅ ትምህርት የሚሰጥ መምህር እንድትልኩልን፤
  •  በአሁኑ ሰዓት በገቺ ወረዳ ያሉትን የአከባቢውን ወጣቶች አስፈላጊውን የቤተክርስቲያን አገልግሎት ያካሄዱ ዘንድ የቀረጹአቸውን ፕሮጀክቶች በመገምገም እንድ ናሙና ፕሮጀክት ወስዳችሁ እንድትረዱን፤

2.     የረጅም ጊዜ የመፍትሔ አቅጣጫዎች፡
  •  ሀገረ ስብከቱ ውስጥ ተወልደው አድገው የሚያስተምሩ ተተኪ ካህናትን የምናፈራበትን የዕቅድ ሳይሆን የተግባር መንገድ ብትቀይሱልን (ካሴትና ቨሲዲ ለማሳተም ሳይሆን ሕዝቡን ተመልሰው የሚያገለግሉ)፤
  • ካህናት የሌላቸው አብያተ ክርስቲያናት ላይ ቋሚ ካህናት ብታስቀጥሩልን፤
  •  ተተኪ ሰባኪያን፡ ካህናት በየጊዜው ተከታታይ ትምህርት የሚያገኙበትን ዕቅዶች በመንደፍ ብትረዱን፤
  •  አብዛኞቹ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ሰፊ መሬት ስላላቸው የንብ እርባታ፣ ከብት ማድለቢያ፣ እና የተለያዩ የእርሻ ሥራዎችን በመደገፍ ወሳኝ ሚና ብትጫወቱልንና አቢያተ ክርስቲያናቱ ራሳቸውን እንዲችሉ ብታደርጉልን፤
ከብዙ በጥቂቱ ይህንን ስመስሉ በጎደለው እሱ ይሙላልን እንላለን;;

6 comments:

Anonymous said...

ይህ ችግር አንድን ወረዳ ብቻ የሚወክል አይመስለኝም ምክንያቱም ሁሉም የኢሉባቦር ወረዳዎች በሙሉ ከአክራሪው እስልምናና ከ ፕሮቴስታንቶች የቀስጣ ት/ት ይልቅ በጣም አብያተ ክርስቲያናቱን የጎዳቸው የሀገረ ስብከቱ የሚበልጠውን ቦታ ይይዛል፡፡ ስለዚህ የአስተዳደር ለውጥ የግድ ነው ካልሆነ ግን "ኢሉባቦር በክርስትና ታሪክ ለ37 ዓመት ፍትህና ማን ነህ ባይ እንዳጣች ሁሉ አሁንም ይቀጥላል፡፡ ሰው ህሊና እያለው ከ50%ወደ 3% ሲገባ ገንዘብን ብቻ ማሳደዱ ይሄ ሰውነት እውነት ሰው ነው ወይስ አውሬ ያሰኛል፡፡

የኢሉባቦር ተወላጆች የሆናችሁ በሙሉ ሰምቶ እንዳልሰማ መሆን እና እንደነ መ/ር ምህረተአብ አሰፋና መሰሎቻቸው አዲሰ አበባ ላይና የሞቀ ጉባዔ መታደምና መጮህ ብቻ ከሆነ ከክርስቲያን ይሄ አይጠበቅም ሁሉም ያልፋል መሰረታችንን ያደግንበት ቀየ ምዕመናን ቤ/ክ ስትፈታ ከማየት አሳፋሪ ነገር ያለ አይመስለኝም ስለዚህ ያለፈው አልፈዋል አሁን ግን ሁላችንም በጋራ ተነስተን የአሰተዳደር ለውጥ እንዲመጣ ድምጻችንን ማሰማት ያለብን ይመስለኛል፡፡ምክንያቱም ቤ/ክ ለግለሰብ ወይስ ቤ/ክ ለምዕመናኖቻ?

እግዚአብሔር ከታሪክ ተወቃሽነት ያድነን...

ኢሉባቦር ለ37 ዓመት የቤ/ክ አገልግሎት አልነበራትም አሁን አንድ ብላ እንድትጀምር የጠፉት እንዲመለሱ ያዘኑት እንዲጽናኑ ያልበረቱት እንዲበረቱ የቅ/ሲኖዶስ አፋጣኝ ምላሽን ትጠባበቃለች፡፡

ኤልሮኢ ዘ ገቺ said...

ይህ ችግር አንድን ወረዳ ብቻ የሚወክል አይመስለኝም ምክንያቱም ሁሉም የኢሉባቦር ወረዳዎች በሙሉ ከአክራሪው እስልምናና ከ ፕሮቴስታንቶች የቀስጣ ት/ት ይልቅ በጣም አብያተ ክርስቲያናቱን የጎዳቸው የሀገረ ስብከቱ የሚበልጠውን ቦታ ይይዛል፡፡ ስለዚህ የአስተዳደር ለውጥ የግድ ነው ካልሆነ ግን "ኢሉባቦር በክርስትና ታሪክ ለ37 ዓመት ፍትህና ማን ነህ ባይ እንዳጣች ሁሉ አሁንም ይቀጥላል፡፡ ሰው ህሊና እያለው ከ50%ወደ 3% ሲገባ ገንዘብን ብቻ ማሳደዱ ይሄ ሰውነት እውነት ሰው ነው ወይስ አውሬ ያሰኛል፡፡

የኢሉባቦር ተወላጆች የሆናችሁ በሙሉ ሰምቶ እንዳልሰማ መሆን እና እንደነ መ/ር ምህረተአብ አሰፋና መሰሎቻቸው አዲሰ አበባ ላይና የሞቀ ጉባዔ መታደምና መጮህ ብቻ ከሆነ ከክርስቲያን ይሄ አይጠበቅም ሁሉም ያልፋል መሰረታችንን ያደግንበት ቀየ ምዕመናን ቤ/ክ ስትፈታ ከማየት አሳፋሪ ነገር ያለ አይመስለኝም ስለዚህ ያለፈው አልፈዋል አሁን ግን ሁላችንም በጋራ ተነስተን የአሰተዳደር ለውጥ እንዲመጣ ድምጻችንን ማሰማት ያለብን ይመስለኛል፡፡ምክንያቱም ቤ/ክ ለግለሰብ ወይስ ቤ/ክ ለምዕመናኖቻ?

እግዚአብሔር ከታሪክ ተወቃሽነት ያድነን...

ኢሉባቦር ለ37 ዓመት የቤ/ክ አገልግሎት አልነበራትም አሁን አንድ ብላ እንድትጀምር የጠፉት እንዲመለሱ ያዘኑት እንዲጽናኑ ያልበረቱት እንዲበረቱ የቅ/ሲኖዶስ አፋጣኝ ምላሽን ትጠባበቃለች፡፡

Z'yismanigus said...

Good!Kale hiwot yasemalin "Dejeselamawiwu"
Personally what I think is adjusting spiritual journey to the place and feel what is happening and try to help the causuals.we should also think of constructing institution in which church scholars(dekemezamurt) will be born.

By the way what 'Dejeselamawiwu' expressed is fully tangible,even we can find this strategy everywhere in the country and it seems "a written dogma" for expansion.If u see,there are plenty of mosques in ONE OR TWO kilometer distance(take Kemissie,Dire Dawa,Addis Ababa,...).
So the only way we have is share such movements and take quick measures.
If we are asked to do sth,let's be ready.
May almighty God keep our mother church!!

Anonymous said...

Hmmmmm.... betikikil ayitehachewal wodaje.

Yedejeselamawiwu yemeftihe akitachawoch tiru silehonu esti endet mesirat endalebin tikoma situn.

Anonymous said...

• በሃገረ ስብከቱ የመዋቅር ደካማነት የተቀመጠዉን ትክክል ስለመሆኑ ምስክርነቴን መስጠት እፈልጋለሁ፡፡በተለይም በአገልግሎት ላይ የሚገኙት ንጹሐን አገልጋዮች በሃገረ ስብከቱ ጸሐፊዉ እየተካሔደባቸዉ ተጽዕኖ በሃገረ ስብከቱ በሳምንት ቅዳሴ የሚካሔድባቸዉን አብያተ ክርስቲያናትን ጥለዉ እንዳይሰደዱ ያሰጋል፡፡ ጸሐፊዉ ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ከመትጋት በመቱ ከተማ ባቋቋሟቸዉ የንግድ ስራዎች ተጠምደዉ ይዉላሉ፡፡በተለይ የሃገረ ስብከቱ ነዋሪዎች ይህንን በቤተክርስቲያኑ እየተፈጸመ ያለዉን ደባ፣ለምዕመናን መነጠቅ ምክንያት የሆኑትን፣የቤተክርስቲያን ቅጥር መደፈር ምክንያቱ ዉጫዊ ሳይሆን እነዚሁ በፍቅረ ንዋይ የነደዱ፣እንጀራዋን የሚበሉ፣የተሰጣቸዉን ትልቅ ኃላፊነት ያልተወጡ የሃገረ ስብከቱ ተጠሪዎች መሆናቸዉን እናዉቃለን፡፡ ክርስቲያን ቤተሰቦቼ በሃገረ ስብከቱ የሚገኘዉን የአስተዳደር ብልሹነትና የአገልጋዮችን ችግር ልገልጽ የምችልበት አንደበት የለኝም፡፡ የቤተ ክርስቲያን ጠባቂ እግዚአብሔር በዘመድ አዝማድ፣ በወንዝ አባዜ የቆሸሸዉን የሃገረ ስብከቱን መዋቅር እስኪያጸዳዉ በዚያ ስላሉት ምዕመና እና ቤተክርስቲያን ልዕልና ሁላችሁም በጸሎት አስቧቸዉ፡፡ የዋሁን የኢሉባቦር ምዕመንን እግዚአብሔር ያስበዉ! ድንግል ማርያም የሚመክር መምህር፣ መልካም እረኛ ይላክልን! በፍቅረ ንዋይ የነደዱትን የምዕመናን ነፍስ እንዲገዳቸዉ እግዚአብሔር ማስዋልን ይስጣቸዉ! አሜን!!!

Anonymous said...

i feel sory when i hear this.it needs such termendous measure even to reduce such a movement and it is post by the indigeneous pepole since they are familiar with the the culture and languadge.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)