September 22, 2010

የኢሉአባቦራው የአክራሪዎች ችግር ከአንድ ቀበሌ በላይ የተዛመተ ችግር ነው

(ደጀ ሰላም፤ ሰፕቴምበር 22/2010፤ መስከረም 12/2003 ዓ.ም):-  በኢሉ አባቦራ ሀገረ ስብከት የገቺ ጻድቁ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ከጳጉሜ አምስት ቀን 2002 ዓ.ም ጀምሮ በአካባቢው በሚገኙ አክራሪ ሙስሊሞች ተከበው ለጥቃት ተጋልጠው እንደሚገኙ መዘገባችን ይታወሳል። ነገር ግን እማኞች እንደሚናገሩት ከሆነ የኢሉአባቦራው የአክራሪዎች ችግር ከአንድ ቀበሌ በላይ ባሉ አካባቢዎች የተዛመተ ችግር መሆኑ ታውቋል።

በደጀ ሰላም የተጠቀሰችው ገቺ ስትሆን ከ አ.አ 460 ኪ.ሜ  ርቀት  የኢሉባቦር ዞን የወረዳ ከተማ  ናት። በደሌ ለመድረስ 20 ኪ.ሜ  ሲቀር  ገቺን ያገኟታል፡፡ የአክራሪዎቹ ችግር በጣም ያጠቃቸው የገጠር ቀበሌዎች ከከተማው ከ1፡00 ሰዓት እስከ 1፡30 በእግር ያስኬዳሉ ሲሉ እማኞቹ መስክረዋል፡፡

“በገቺ ኢማም አሰጋጅ አቶ አበዱልሃሚድ ቀስቃሽነት በተላለፈ መልዕክት መሰረት በጊጦ ሴኮ ቀበሌ በገበር ቀበሌ በጂሳ ና ገበር  ቀበሌዎችና በጎሌ ተክለኃይማኖት እንዲሁም በወረዳዋ ገጠር አከባቢ በሚኖሩ ክርስቲያኖች ላይ ከበቶቻቸው እንዲታረዱ እንዲዘረፉና አትክልቶቻቸው እንዲመነጠሩ በተላለፈ ትዕዛዝ መሰረት በግለሰቦች ሳይሆን በበርካታ ቀበሌዎች ትብብርና ቡድን በመመስረት በምሽት ዘረፋና ድብደባ እየተፈጸመባቸው ነው፤ ይህ ችግር መከሰት የጀመረው ከነሓሴ 10/2002 አንስቶ” ነው ያሉት እነዚሁ እማኞች  “ችግሩ መፍትሔ እንዲያገኝ ቢያመለክቱም አቤቱታቸው ከቁም ነገር ባለመቆጠሩ የችግሩ ተጠቂዎች ለመሆን እንደበቁ አስረድተዋል፡፡

ከበላይ አካል ችግሮች እንዲጣሩ መተላለፉን እንደሰሙ የተናገሩት እንዚሁ እማኞች የወረዳው አስተዳዳር ግን “ምንም ችግር የለም ሌባ ነው እንደዚህ የሚያደርገው” በሚል ሽፋን መንግሥት ትኩረት እንዳይሰጠው እየተደረገ ነው ሲሉ አብራርተዋል፡፡ ሕዝቡም ተገቢው የሕግ ጥበቃ ስላልተሰጠው ዘረፋው፣ ድብደባው እና ወከባው መቀጠሉ ተነግሯል፡፡  ትናንት መስከረም 11/2003 ዓ.ም ከስምንት ቀን እገታ በኋላ ወደ ወረዳው መጥተው ያመለከቱ የገበር ቀበሌና የጊጦ ሴኮ ቀበሌ ገበሬ ማሕበር ነዋሪዎች ምንም ዓይነት ምላሽ ሳያገኙ ቀርተዋል ተብሏል፡፡

ተጎጅዎችም ጥቂት ግለሰቦች በሚለኩሱትና መርዘኛ ትምህርትና ቅስቀሳ የዋሁን ሕብረተሰብ መሳሪያ እያደረጉት እንዳለና አንድ የእምነት መሪ ሕዝቡን ማረጋጋት ሲገባው በድምጽ ማጉያ “ከኛ መካካል ይነቀሉ፣ ነቅለን ማጥፋት አለብን” ብለው ማስተማራቸው ለዚህ ዳርጎናል። እኒህ ግለሰብ ብዙውን ጊዜ በሕዝብና በመንግስት ላይ ያልተገባን ትምህርት ሲያስተምሩ ከልካይ ስላልነበራቸው አሁን ለደረሰውና ላለፉት ዓመታት ሕዝብን ለሚያቃቅር ድርጊት ዳርገዋል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም የመንግስት ሥልጣን ላይ የተቀመጡየአካባቢው አስተዳደሮች ሥራቸውን በተገቢው ሁኔታ ባለመወጣታቸውና የሕዝቡንም ደኅንነት ባለመጠበቃቸው ምክንያት ሕዝብን ከሕዝብ፣ መንግስትን ከሕዝብ፣ ሕዝብን ከመንግስት የሚያቅሩና መንግሥት የሌለበት ሀገር እስከማሰኘት የደረሱ አሰከፊ ድርጊቶችን ህብረተሰቡ ማሳለፉን እና አሁንም ምንም ለውጥ እንደሌለ እማኞች ተናግረዋል፡፡ ጉዳዩን በሚያመለክቱበት ወቅት በየገበሬ ማኅበራቱ የተሾሙት ሊቃነ መናብርት “እኛ ክርስቲያንን አናስተዳድርም፤ ለናንተም ሊቀመንበር አይደለንም” የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ችግር የደረሰባቸው ተጎጅዎች ይመሰክራሉ፡፡ መንግስት አፋጣኝ ምላሽ እንዲጣቸውም ተማጽኗቸውን እስከ አሁኑ ሰዓት ድረስ በማቅረብ ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)