September 21, 2010

የገቺ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ምእመናን በአክራሪ ሙስሊሞች ተከበዋል


(ደጀ ሰላም፤ ሰፕቴምበር 21/2010፤ መስከረም 11/2003 ዓ.ም):-  በኢሉ አባቦራ ሀገረ ስብከት የገቺ ጻድቁ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ከጳጉሜ አምስት ቀን 2002 ዓ.ም ጀምሮ በአካባቢው በሚገኙ አክራሪ ሙስሊሞች ተከበው ለጥቃት ተጋልጠው እንደሚገኙ በስፍራው የሚገኙ የዐይን ምስክሮች ለደጀ ሰላም ገለጹ፡፡
የረመዳን ጾም ፍቺ በዓል ተከብሮ በዋለበት ጳጉሜን አምስት ቀን 2002 ዓ.ም ከገቺ ሁለት ሰዓት ርቆ በሚገኘው እና ሙስሊሞቹ በቁጥር በሚበዙበት አካባቢ የሚገኙት ምእመናን ሰብሎች ከብቶች ተለቀውባቸው እንዲበሉ እና እንዲጠፉ ተደርገዋል፤ የምእመናኑ ከብቶች ተዘርፈዋል፤ ከዚሁ ጋራ በተያያዘ በተነሣ ግጭትም በአንድ ምእመን ላይ በስለት ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተዘግቧል፡፡

የገቺ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ሰበካ በደንቢ እና በመቱ መካከል የምትገኝ ስትሆን በሀገረ ስብከቱ የተረሳ እና ተገቢውን ክትትል የማይደረግለት መሆኑ ተመልክቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት በሰበካው የሚገኙት ጥቂት ምእመናን በቁጥር በሚበዙ አክራሪ ሙስሊሞች ተከበው የሚገኙ ሲሆን ጉዳዩን ለሚመለከተው የበላይ አካል እንዲታወቅ ተደርጓል ከመባሉ በቀር አንዳችም የተወሰደ ርምጃ እንደሌለ የዜናው ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)