September 20, 2010

አቡነ ፋኑኤል ከሐላፊነታቸው እንዲነሡ ተጠየቀ

  • የሐዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሰበካ ጉባኤን በሕገ ወጥ መንገድ ለማስመረጥ የተደረገው ሙከራ በምእመናን ተቃውሞ ከሸፈ
  • ሊቀ ጳጳሱ የአጣሪ ኮሚቴውን ተግባር ለማሰናከል እየጣሩ ነው
(ደጀ ሰላም፤ ሰፕቴምበር 20/2010፤ መስከረም 10/2003 ዓ.ም):-  ለካህናት እና ምእመናን ያላቸውን ንቀት እና አነስተኛ አባታዊ ክብር በተደጋጋሚ በማሳየት የሚታወቁት የሲዳማ፣ ጌዲኦ፣ አማሮ እና ቡርጂ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፋኑኤል ሀገረ ስብከቱን ለመምራት ባለባቸው ከፍተኛ የብቃት ማነስ እና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገረ ስብከቱ እየተባባሱ ለመጡት ውዝግቦች መንሥኤ በመሆናቸው ከሐላፊነታቸው እንዲነሡ የሐዋሳ ከተማ ምእመናን ጠየቁ፡፡ ምእመናኑ ከሊቀ ጳጳሱ በተጨማሪ በእርሳቸው አቅራቢነት ከፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት በተጻፈ ደብዳቤ በሕገ ወጥ መንገድ የተሾሙት መልአከ ኀይል አባ ገብረ ጊዮርጊስ አብርሃም ከደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አስተዳዳሪነት ሐላፊነታቸው እንዲወገዱ ጠይቀዋል፤ ይህንኑ ጥያቄ ለሚመለከታቸው የመንግሥት እና የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አካላት አቅርበው እና ተከታትለው የሚያስፈጽሙ የምእመናን ተወካዮችንም መርጠዋል፡፡

ምእመናኑ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት በትናንትናው ዕለት እሑድ፣ መስከረም ዘጠኝ ቀን 2003 ዓ.ም ጠዋት የሐዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳምን ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በቃለ ዓዋዲው ከተመለከተው ውጭ በአቡነ ፋኑኤል ቀጥተኛ ትእዛዝ በተጠቆሙ አስመራጭ ኮሚቴዎች እና በደንቡ ከተደነገገው የምርጫ ሥነ ሥርዐት በተፃራሪ ምርጫውን ለማስፈጸም የተደረገውን ሙከራ ባከሸፉበት ወቅት ነው፡፡ ቀደም ሲል ሊቀ ጳጳሱ በክልሉ የፍትሕ፣ ጸጥታ እና አስተዳደር ጉዳዮች ቢሮ ሐላፊዎች ፊት ተንበርክከው ይቅርታ በመጠየቅ የገዳሙን ሰበካ ጉባኤ ምርጫ የሰበካው መታወቂያ ያላቸው(የሚጠበቅባቸውን አስተዋፅኦ በተወጡ) የአጥቢያው ምእመናን ብቻ ተሳታፊ በሚሆኑበት መልኩ በአግባቡ በመፈጸም ዕርቅ እና ሰላም ለማውረድ ቃል ገብተው እንደ ነበር ተዘግቧል፡፡ የሰበካ ጉባኤው አባላት የሆኑ የፍትሕ እና ልማት ኮሚቴ ሽማግሌዎች ባለፈው ሳምንት ዓርብ አቡነ ፋኑኤል ይህን የዕርቀ ሰላም ስምምነታቸውን በማክበር የሰበካ ጉባኤ ግዴታቸውን ያልተወጡ የእርሳቸው ፈቃድ ፈጻሚዎች እና የማፊያ ቡድኑ አባላት የሆኑ ግለሰቦች በምርጫው ላይ እንዲሳተፉ ከማድረግ እንዲታቀቡ ተማፅነዋቸው ነበር፡፡

ይሁንና ከሀገረ አሜሪካ ኑሯቸው ጀምሮ አምና የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን አስተዳደር ለማሻሻል እስከተደረገው የውስጥ ትግል ድረስ ባላቸው መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ ግንኙነት(አሁን በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት አስመልክቶ በኦፌሴል ከተናገሩት ፖሊቲካዊ አቋም ፍጹም ተቃራኒ የሆነ እምነት በማራመድ ጭምር) በቃላቸው ባለማደር የሚታወቁት ሊቀ ጳጳሱ፣ ‹‹እናንተ የእነርሱ መሳተፍ ተገቢ አይደለም የምትሉትን ያህል ሌሎቹ ደግሞ ተገቢ ነው የሚሉበት ሁኔታ አለ፤ የምርጫውን ሂደት በተመለከተ ተቃውሟችሁን እዚያው ማሰማት ትችላላችሁ›› በማለት የዕርቀ ሰላም ስምምነቱን የሚሽር፣ አለመግባባቱን የጠብ መሣሪያ እና የወገናዊነት ማሳያ የሚያደርግ ምላሽ ሰጥተዋቸዋል፡፡

በትናንትናው ዕለት ጠዋት ለ‹አስመራጮቹ› ምርጫው የሚካሄድበት መንገድ ተገቢ አለመሆኑን ተቃውሟቸውን የሚገልጹ የምእመናን ተወካዮችን በእነ ያሬድ አደመ እና በጋሻው ደሳለኝ የተደራጁ የሊቀ ጳጳሱ ደጋፊዎች ለመደብደብ እና ሁከት ለመቀስቀስ ሲጋበዙ የነበረ ቢሆንም ቀደም ብሎ የሁኔታውን ውጥረት የተረዳው የከተማው አስተዳደር ያዘጋጃቸው የጸጥታ ኀይሎች ከምእመናኑ ጋራ በመተባበር ፍጥጫውን አረጋግተዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ውይይቱ በመግባባት ቀጥሎ የምእመናን ተወካዮች የሆኑ የአገር ሽማግሌዎች ለተሰብሳቢው ተገቢውን ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ማብራሪያውን ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች የተሰጡ ቢሆንም አብዛኞቹ ሐሳቦች ያተኮሩት እና ጠንክረው የወጡት ግን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፋኑኤል እስከ አሁን በሀገረ ስብከቱ ለሚነሡት ውዝግቦች መንሥኤ እንደሆኑ እና በጊዜ ቆይታም ከአንድ ብፁዕ አባት በሚጠበቅ መልኩ ሀገረ ስብከቱን በመንፈሳዊ ልዕልና እና ሁሉንም በሚያስማማ ተጨባጭ አስተዳደራዊ ክሂል ለመምራት ያላቸው ችሎታ አጠያያቂ እንደ ሆነ መረጋገጡን የተመለከቱ ነበሩ፡፡ አቡነ ፋኑኤል በአዲስ አበባ ከአንድም ሁለት(አንዱ ቪላ ‹የሐዋሳ መንበረ ጵጵስና› እስከ መባል ደርሷል) ቪላዎችን ያሠሩ፣ አንዱን ቪላቸውን እስከ 25‚000 ብር ድረስ የሚያከራዩ፣ ይህም አልበቃ ብሏቸው በሀገረ ስብከታቸው ሥር በሚገኙ ወረዳዎች ከሥራ አስኪያጁ መልአከ ሕይወት ፀሐይ መልአኩ ጋራ ሲዘዋወሩ በስጦታ በሚቀርብላቸው ሳይሆን በቃላቸው ትእዛዝ ቅቤ እና ማር አዘውትረው የሚያስጭኑ፣ ለቤተ ክርስቲያን ቀናዒ ከሆኑ ካህናት፣ ሊቃውንት እና ወጣቶች ጋራ ከመሥራት ይልቅ ማንኛውንም ፍላጎታቸውን ለማስፈጸም ፈቃደኛ የሆኑ ማፊያዎችን የመሰብሰብ እና ከእነርሱም ጋራ የመሥራት ልማድ ያላቸው እንደሆኑ ይነገርላቸዋል፡፡ ከእርሳቸውም ጋራ በዐውደ ምሕረቱ እንዳይቆም የተከለከለውን እና አቡነ ፋኑኤልም ከክልሉ ባለሥልጣናት በተደረገ ውይይት የተስማሙበትን የያሬድ አደመን እግድ ማስፈጸም የተሳናቸው የገዳሙ አስተዳዳሪም መልአከ ኀይል አባ ጊዮርጊስ አብርሃም ለሁከቱ ምክንያት በመሆናቸው እሳቸውም ከሐላፊነታቸው እንዲነሡ ተጠይቋል፡፡

በመሆኑም ምእመናኑ ለሀገረ ስብከቱ መንፈሳዊ አገልግሎት ዕድገት እና ለልማቱ መጠናከር ሲባል የሊቀ ጳጳሱ እና እርሳቸው በሕገ ወጥ መንገድ እንዲሾሙ ያደረጓቸው የታላቁ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አስተዳዳሪ ከሐላፊነታቸው እንዲነሡ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ በመጨረሻም ይህንኑ ጥያቄዎቻቸውን ለሚመለከታቸው የመንግሥት እና የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አካላት በማቅረብ የሚያስፈጽሙላቸውን ተወካዮቻቸውን በመምረጥ ስብሰባውን አጠናቅቀዋል፡፡ ስለዚህም በአገልግሎት ላይ ያለውን የሐዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ በሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ደንብ(ቃለ ዓዋዲ) እና በገዳሙ የውስጥ አስተዳደር ከተደነገገው ውጭ ከሀገረ ስብከቱ በተላከ ግለሰብ በተጠቆሙ አስመራጮች ለማካሄድ ታቅዶ የነበረው ምርጫ በገዳሙ አጥቢያ ነዋሪ በሆኑ ምእመናን እና በምእመናኑ በተመረጡ የፍትሕ እና ልማት ኮሚቴ አባላት በገጠመው ጠንካራ ተቃውሞ ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በ1965 ዓ.ም በወጣ ዐዋጅ በካህናት እና ምእመናን ኅብረት በሰበካ ጉባኤ እንድትደራጅ የተደረገው በአስተዳደር፣ በፍትሕ መንፈሳዊ፣ በአገልግሎት እና በምጣኔ ሀብት በኩል በራሷ ሕግ እና ሥርዐት በመመራት እና በመደራጀት እንድትሠራ ለማድረግ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ከአንድ ሳምንት በፊት በአቡነ ፋኑኤል በተሰጣቸው ትእዛዝ ከሀገረ ስብከቱ የተላኩት የሰበካ ጉባኤ መምሪያ ሐላፊ ቀሲስ አማረ በገዳሙ አስተዳደር የማይታወቅ የተድበሰበሰ ሪፖርት በሰበካ ጉባኤው ምክትል ሊቀ መንበር አማካይነት እንዲቀርብ ካስደረጉ በኋላ ራሳቸው በዐውደ ምሕረቱ ቆመው ከምእመኑ መካከል ቀድመው ያዘጋጇቸውን ሦስት ግለሰቦች በድርጅታዊ አሠራር እንዲጠቆሙ በማድረግ አስመራጭ ኮሚቴ ሠይመዋል፡፡ በቃለ ዓዋዲው አንቀጽ ስምንት ንኡስ አንቀጽ 1 - 5 እና አንቀጽ ዘጠኝ በተዘረዘረው መሠረት የሰበካውን የምርጫ ሥነ ሥርዐት የሚያስፈጽሙት ከሰበካው ቤተ ክርስቲያን ልዩ ልዩ ቀበሌዎች የተውጣጡ ካህናት፣ ምእመናን እና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች የሚገኙበት ከአምስት ያላነሱ ከዐሥራ አምስት ያልበለጡ ሆነው በካህናት፣ መነኮሳት እና ምእመናን ምልዓተ ጉባኤ በመሠየም ነው፡፡ እኒህ የምልዓተ ጉባኤው ሥዩማን የአስመራጭ ኮሚቴ አባላት በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖታቸው የታወቁ፣ በሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው ተመዝግበው የሚገባቸውን አስተዋፅኦ የተወጡ፣ በመንፈሳዊነታቸው፣ በግብረ ገብነታቸው እና በአስተዋይነታቸው የታወቁ እንዲሁም በሕገ ቤተ ክርስቲያን የጸኑ መሆን እንደሚኖርባቸው በዚሁ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ ሦስት እና አራት ላይ ተገልጧል፡፡

ይህን ለማስፈጸም ምርጫው ከመካሄዱ በፊት በሰበካው ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ወይም ጉዳዩ በሚመለከታቸው አካላት አማካይነት ለአጥቢያው ካህናት እና ምእመናን ትምህርት እና ቅስቀሳ መደረግ እንደሚኖርበት፣ ጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤው በቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ እንደሚመራ፣ ጉባኤውም ሕግንና ሥርዐትን ተከትሎ እርስ በርስ በመፈቃቀር፣ በስምምነት፣ በሰላም እና በጸጥታ መፈጸም እና ማስፈጸም እንደሚያስፈልገው፣ ድምፅ የሚሰጥባቸውን ጉዳዮችንም በድምፅ ብልጫ መወሰን እንደሚገባው በንኡስ አንቀጽ አንድ እና ሁለት ላይ ያዝዛል፡፡ ከዚህም ባሻገር በዚሁ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ አምስት እና አንቀጽ 11 ንኡስ አንቀጽ ሦስት መሠረት አዲስ የሰበካ ጉባኤ ምርጫ ከመካሄዱ ከአንድ ወር በፊት በሥራ ላይ የነበረው የሰበካው አስተዳደር ጉባኤ በአገልግሎት ዘመኑ የፈጸማቸውን እና ያስፈጸማቸውን እንዲሁም በዕቅድ የያዛቸውን ተግባራት አጠቃላይ የሥራ እና የፋይናንስ ሪፖርት ለካህናት እና ምእመናን ምልዓተ ጉባኤ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ በቃለ ዓዋዲው አንቀጽ 11 ንኡስ አንቀጽ አንድ መሠረት የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በአጥቢያው ቤተ ክርስቲያን የተፈጸመውን ምርጫ የሚያጸደቀው፣ የሚያሻሽለው ወይም የሚሽረው በወረዳ ቤተ ክህነቱ አማካይነት ውጤቱ ከቀረበለት አልያም የምርጫው አፈጻጸም ትክክል ሆኖ ሳያገኘው ሲቀር ጉዳዩን በአስተዳደር ጉባኤ ከተመለከተው በኋላ ነው፡፡

ከአንድ ሳምንት በፊት በነበረው እሑድ በሐዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የሆነው እና የታየው ግን ከዚህ የቃለ ዓዋዲው ደንብ ቢያንስ ገሚሱን እንኳን ያሟላ አልነበረም፡፡ አቡነ ፋኑኤል ከእሑዱ የይስሙላ ትዕይንት በፊት የምርጫ አስፈጻሚዎችን በቀጥታ ልከው የነበረ ሲሆን በምእመኑ ከፍተኛ ተቃውሞ ሕገ ወጥ ተልእኴቸውን ሳያሳኩ መመለሳቸው ይታወሳል፡፡ ከዚህ ትምህርት ያልወሰዱት ሊቀ ጳጳሱ የገዳሙ አጥቢያ ካህናት እና ምእመናን ምልዓተ ጉባኤ ሳይደረግ፣ የምርጫው መካሄድ ታውቆ በቂ ቅስቅሳ እና ትምህርት ሳይሰጥ፣ በሥራ ላይ ያለው ሰበካ ጉባኤ በኀባር የመከረበት የክንውን እና ዕቅድ ሪፖርት ሳይቀርብ፣ በሕገ ወጥ መንገድ ከተሾሙት የገዳሙ አስተዳዳሪ እና ከሰንበት ት/ቤቱ አመራር ጋራ በተያያዘ የተፈጠሩት ችግሮች ተፈትተው የእርስ በርስ ስምምነት፣ ሰላም እና ጸጥታ መስፈኑ ሳይረጋገጥ የሀገረ ስብከቱን ሰበካ ጉባኤ መምሪያ ልኡክ በድንገት በመስደድ ቀድመው ለአስመራጭነት ልከዋቸው የነበሩትን ሦስት ግለሰቦች በቡድናዊ አሠራር እንዲጠቆሙ፣ የተጠቆሙት ግለሰቦች ከኦርቶዶክሳዊነታቸው፣ የሚጠበቅባቸውን አስተዋፅኦ ከመወጣታቸው፣ ከመንፈሳዊነታቸው፣ ግብረ ገባዊነታቸው እና ሞያዊ ብቃታቸው አኳያ የድጋፍ እና ተቃውሞ አስተያየት ሳይደመጥባቸው የቃለ ዓዋዲውን ቃል እና መንፈስ ፈጽሞ በተፃረረ አኳኋን የአስመራጭ ኮሚቴ ተብዬዎች ‹‹ምርጫ›› እንዲካሄድ አድርገዋል፡፡ ሁኔታውን የበለጠ አሳፋሪ የሚያደርገው ደግሞ በዚህ የአስመራጭ ኮሚቴ ተብዬዎች ‹‹ምርጫ›› የተጠቆሙት ሦስት ግለሰቦች ቀደም ሲል በሊቀ ጳጳሱ ተልከው ምእመኑ የተቃወማቸው መሆናቸው እንደ ሆነ የሰበካው ምእመናን ለደጀ ሰላም አስረድተዋል፡፡ በዕለቱ ለቅዳሴ በገዳሙ የተገኙት ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች የአስመራጭ ኮሚቴ ተብዬው ‹‹ምርጫ›› ሂደት ሕጋዊ አለመሆኑን ቢቃወሙም ሰሚ እንዳላገኙ በስፍራው የነበሩ ደጀ ሰላማውያን ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ይህ ውዝግብ በታላቁ የሐዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሲፈጠር በአዲስ አበባ የተቀመጡት አቡነ ፋኑኤል ከሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ጋራ ቀደም ሲል በሐዋሳ ከተማ ምእመናን ተወካዮች እንዲሁም በገዳሙ ሰበካ ጉባኤና ልማት ኮሚቴ አባላት የቀረበባቸውን የአስተዳደራዊ በደል እና ምዝበራ አቤቱታ እንዲያጣራ በመንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የተሠየመውን አጣሪ ኮሚቴ ተግባር የሚያስናክሉበትን መንገድ በመፈለግ ላይ ነበሩ፡፡ ሊቀ ጳጳሱ የሐዋሳ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን አንዳንድ አስተዳዳሪዎች ወደ መንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ድረስ እንዲመጡ በማዘዝ፣ ‹‹ዕርቅ ፈጥረናል፤ ተስማምተናል፤ አጣሪ ኮሚቴው ይቅር›› ለማሰኘት ሞክረዋል፡፡ ‹‹ዕርቅ ፈጥረናል›› የተባለው ሊቀ ጳጳሱ በክልሉ የአስተዳደር እና ጸጥታ ጉዳዮች ቢሮ ትእዛዝ በባለሥልጣናቱ ፊት ተንበርክከው የበደሏቸውን የምእመናን እና ካህናት ወገኖች ይቅርታ የጠየቁበትን አጋጣሚ ነው፡፡

ይሁንና ይህ ይቅርታ በአባት እና ልጅ መንፈሳዊ ዝምድና የተደረገ በመሆኑ ያለው ዋጋ እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨባጭ የተፈጸመው አስተዳደራዊ በደል ደግሞ በአግባቡ ተጣርቶ ሊታወቅ እንደሚገባ አቋማቸውን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ሊቀ ጳጳሱ በዘመን መለወጫ ማግሥት ቃሊቲ በሚገኘው ቪላቸው ፓትርያሪኩን ጨምሮ ለቋሚ ሲኖዶስ እና አንዳንድ የአጣሪ ኮሚቴውን አባላት ምሳ መጋበዛቸው ተሰምቷል፡፡ ይህ የአቡኑ ‹የማግባባት› እና ረብ የለሽ የሕዝብ ግንኙነት ምስነት የማጣራት ሂደቱን እንዳያስተጓጉለው የፍትሕ እና ልማት ኮሚቴው አባላት ያደረባቸውን ስጋት ተናግረዋል፡፡17 comments:

Anonymous said...

የሐዋሳ ምዕመናን የእናንተ መነሳሳት ሌላውንም ለህገ-ቤተቤተክርስቲያን መከበር እንድንቆም ያነሳሳል እና በርቱ።አረሙን ከስንዴው ለመለየት የሚወሰደው መስዋዕትነትም ቀላል ስላልሆነ ማስተዋል እና ትዕግስት አይለያችሁ። እግዚአብሔር ያበርታችሁ።

Anonymous said...

Thank you. Can you make your report a little shorter so that we can read and quickly understand it?! I don't for others, but for me it is too long.

From what I am observing, I can see how enemies of the church are getting effective in executing their evil plans.

temesgen said...

This is what we want , honestly heአቡነ ፋኑኤል did not think & speak as a father. /I was the one who entered last friday with the elders& ልማት ኮሚቴ /.I think this was the last chance they have but they did not use it.Our aim was to make the ሀገረ ስብከቱ አስኪያጅremoved ,on the way to this God show us the root causes /the pope ,yared ademe,dn. begashaw/
They are careless for the church , even they don't care who preach,what is the about;they are slaves of money , so they should be removed by any means spiritual.
may God be with us .
Pray for us!

መልአከ ሳሌም አባ ገብረኪዳን እጅጉ said...

ደጀ ሰላማዉያን ሰላም ለእናንተ ይሁን።
የአዋሳዉ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሁኔታ ይችን ትንሽ ጽሁፍ እንድጽፍ አነሳሳኝ
እረ እግዚኦ እንበል ጎብዝ ወደት እንግባ ቤተ ክርስቲያንን በፈተና ቀሥፎ የያዘዉ ሰይጣን ምነው አለቅ አላት በመንበረ ፓትርያርኩ አካባቢ ያለው ፈተና ሳያበቃ ደግሞ ወደ ሀገረ ስብከትም ተዘዋወረ ምነው አቡነ ፋኑኤልን ተው የሚላቸው ዘመድ የለም እንደ ምነው ሁሉንም ዝም ስንል የማናውቅ አደረጉን? ትላንት ምን ነበሩ ዛሬስ ምን ተሰማቸው አሁን ላሉበት ደረጃ እኰ የደረሱት በዚችው ቤተ ክርስቲያን ተንጠልጥለው ነው።ከነፋስ ስልክ ት/ቤት እስከ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን ከመኪና ሥፌት እስከ ምክትል አስተዳዳሪነት ከዚያም እስከ ሀገረ አሜሪካ ያደረሰች እኮ ይችው አሁን የሚያጉላሏት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት በዋሽግተን ዲሲ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለረጅም ዘመን የአሁኑን ፓትርያርክ እና መንግሥትን ሳይቀር በመቃወም ፍርድ ጎደለ ድሀ ተበደለ ሰባዊ መብት ተጣሰ በሚል በዋሽግተን አደባባይ ከፓለቲከኞች ጋር በመሆን በጣም ብዙ ብዙ ነገሮችን ሲሉ ቆይተው ፎር ጉድ አገራቸው ገቡ ተባልን ብዙዎቻችን እሰየው በታም ጥሩ አደረጉ ሥንል ሌሎች ደግሞ የለም ሹመት ሸቷቸው ነው እነጅ ፎር ጉድ አይደለም ለማየት ያብቃችሁ አሉ ።በድንገት ቤተ ክርስቲያኑን ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን ሊአስገቡ ነው ተባለ በጣም ደስ አለን አዲስ አበባ ለሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስም ቤተ ክርስቲያኑን እጅ መንሻ አድርጋቸሁ ተቀበሉኝ አሉ ፓትርያርኩም ሆኑ ሌሎች አባቶች እሰየው እንድህ ነው የቁርጥ ቀን ልጅ ተባለና ለትልቁ ማዕረግ ታቀዱ እናም ተሾሙ ቅ.ሲኖዶስም ይበሉ የለፉበትን ቤተ ክርስቲያንና ባካባቢው ያሉትን አብያተ ክርስቲያናት በአባትነት ይጠብቁ ይባርኩ የሀገሩን ሰርዶ በሀገሩ በሬ ተባለና ወደ አሜሪካ ተላኩ ሲመለሱ ግን እንደጠበቁት ሆኖ አላገኙትም የቤተ ክርስቲያኑ ቦርድና ምዕመናን በመጡበት እግራቸው መልሶ አሰናበታቸው ኪዚያም ለቅዱስ ሲኖዶስ ጉዳዮን ሲያስረዱ ሀገሩም እንዳልተቀበላቸው ሲናገሩ ታላቁን እና ነባሩን የሲዳሞ ሀገረ ስብከትን እነደ እድል ሆኖ በሰለጠነው ሀገር ኑረዋል ተባለና እንዲያለሙ ሀገረ ስብከቱን እንዲያስፋፉ አደራው ተሠጣቸው እሰየው አዋሳ ቀን ወጣለት አልን ደስም አለን። አብያተ ክርስቲያናትን ማስፋፋት ብሎም የቤተ ክርስቲያን ይዞታ የሆኑትን ቦታዎች አጥር አሳጠሩ ግንብ አስገነቡ ተባለ አሁንም በጣም ደስ አለን ሥራውና ሠራተኛው ተገናኙ ተባለ።ግን የቤተ ክርስቲያን አባቶችን በመግፋት አዲስ ከሠለጠኑ ባዲስ ልሳን እንናገራለን ብለው የቀኑን መንፈሳዊ ጉባኤ ወደ ሌሊት የቀየሩ የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት እያፋለሱ እንደ ይሁዳ የሰላሳ ብር ከረጢት ሳይሆን የሽ ብሮችን ከረጢት አንግበው በዬ አብያተ ክርስቲያናቱ ሕዝቡን የሚያደነቁር ድምጽ ማጉያ በመኪና ላይ አስተክለው ንግድ በማጧጧፍ ላይ ከሚገኙ እንደነ በጋሳው፣እነደነ ጠንቋዩ ጌታቸው ዶኒ ፣ የሰው ግጥም እየሰበሰበ በመጽሐፍ መልክ እያሳተመ በመቸብቸብ ከሚታወቀው፣ የአዋሳ ቅዱስ ገብርኤልን ቤተ ክርስቲያን ከልጅነት እስካሁን አጽመ ርስት አድርጎ ባደራጀው የማፊያቡድን እየታገዘ እኛ ካልፈቀድን ደቡብን ማንም አይረግጣት ከሚለው።ከዚህም በላይ የኦርቶዶክስ ካባ ደርቦ በውስጥ ግን የመናፍቃን አቀንቃኝ ከሆነው ያሬድ አደመ እና ከመሳሰሉት ጋር በመሆን አቡነ ፋኑኤል ቤተ ክርስቲያኒቱን ምስቅልቅሏን እያወጡት ነው የሚገርመው ጳጳሱ የነበጋሻው፣የነያሬድ አደመ ግብር አብይ ሆነው መገኛታቸው ነው። ስለዚህ ወገኖች አጥብቀን እግዚኦ እንበል አንዳንድ አባቶቻችን ለተሾሙበት መንፈሳዊ ሥልጣን ሲሉ ለክብራቸው የሚመጥን ሥራ ቢሠሩ መልካም ነው እንላለን እንደገና እመለሳለሁ።ቸር ይግጠመን። ቤተ ክርስቲያናችንን እግዚአብሔር ይጠብቅልን፡ አሜን።

Anonymous said...

በየቦታው የሚሰማው ኁሉ አንድ አይነት ይመስላል በጀርመን ፍራንክ ፈርት ቅድስት ማርያም ቤተክርቲጃን የተከሰተውም ከዚህ ጋር ስለሚመሳሰል እነሆ ዜናው ።ጠቅላላውን ዘገባ ባጠቃላይ ስለአለው ስለጀርመን ቤተ ክርስቲያን መልካም ፈቃድአችሁ ብዘግቡልን


ታምቆ የኖረው የፍራንክ ፈርት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርቲያን ጉዳይ
አስማሚ ኮሚቴ እንዲያው ተደረገለ
ለብዙ ዓመታት ብዙሃኑ ህዝብ ሲያለቅስበት ለቅዳሴ መሄድ እንኴን ሲሳቀቅ የነበረው
ድምጹን ያሰማበት ቀን ነበር ስሜቱንም የገለጸበት ነበር ቢባል ማጋነን አይሆንም
ከችግሮቹ
፩ኛ አስተዳደሩን ሁሉንም የቤተክርስቲያኑ እንደራሳቸው ስሜት ብቻ የሕዝብን ፍላጎት
ባልጠበቀ መልኩ በመምራት
፪ኛ የቤተ ክርቲያኑን ገንዘብ ሕጋዊ ባልሆነ መልኩ ለግላቸው በማዋላቸው
፫ኛ ሕዝቡን ሊሳደብና ሊዘልፍ የሚችል ለ15 ዓመታት ቅስናውን ትቶ ፓስተር የሆነውን
አቶ ገዳሙ የተባለው ሰው በማምጣት ሲያሰድቡት በመኖራቸው
፬ኛ ይህ አልበቃ ብሎ ጉዳያቸውን እየተከታተለ ለሕዝብ ያቀርብ የነበረውን የሰበካ ጉባዬ
ቃለ አዋዲው በማይደግፈው መልኩ ሊያፈርሱ አዲስ ለመምረጥ በመነሳታቸውና።
ስለዚህም ሕዝቡ ታምቆ የነበረውን ስሜትና ተቃውሞ ለመጀመሪያ ጊዜ በማሰማቱ
ለጊዜው ቤተ ክርስቲያንን ሳይሆን በአስተዳዳሪው ዙሪያ በማወቅም በማለማወቀም
ሽር ጉድ የሚሉ ሰዎች ጉባዬውን ለመረበሽ ሞክረው ቢሆንም በእግዚአብሔር ፈቃድ
ከሃገር ቤት ለማስተማር በመጡ መምህራን አረጋጊነት አስማሚ የሆነ ኮሚቴ
እንዲያየው በማድረግ ተጠናቌል።

ዘ ሐመረ ኖህ said...

ሰላም ደጀ ሰላሞችና ደጀ ሰላማውያን የቁርጥ ቀን ልጆች ናችሁና በርቱ እግዚአብሔር ይጠብቃችሁ የችገሮች ሁሉ ምንጭ ጳጳስ መሆን የማይገባው ሰው ጳጳስ ስለሆነ ነው ካህን መሆን የማይገባው ካህን ስለሆነ ነው ማቴ 6 16 20መዋሸት ማምታታት መገለባበጥ የተራ ፖለቲከኛ ባህሪ ነው ፓትርያርኩ አጣሪ ኮሚቴ ላኩ ሲባል በጣም የዋህ ብቻ ሳይሆን ሞኝ የሆነ ሰው እውነት ሊመስለው ይችላል አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ እንዲሉ አባ ጳውሎስ እሳቸውን ስለ እውነት የሚቃወመውን ሁሉ እንዴት አርገው እንደሚበቀሉ በተደጋጋሚ አይተናልና የአባ ጳውሎስ እንባ ጠባቂ ወይም ቲፎዞ ከሆኑ ደግሞ ይስረቁም ይቅጠፉም ማንም አይነካቸውም እንደውም በአደባባይ ይሾማሉ ይሸለማሉ ማን አግብቶት አጣሪ ኮሚቴ ምናምን የሚባለው ለይስሙላና ለሽንገላ ነው ይልቅ በሌላ ብሎግ ለመግለጽ እንደሞከርኩት መንግስት ለራሱ ሰላም ሲል ከአባ ጳውሎስና ከጥቂት አንጃዎቻቸው ይልቅ ሰፊው ምእመን ይበልጥብኛል ብሎ ማሰብ የጀመረ ወይም መባነን የጀመረ ስለመሆኑ ምልክቶች እየታዩ ነው ስለዚህ እሾህን በሾህ መንቀሉ ስለሚበጅ በዋናነት ወደ እግዚአብሔር እየጮሁ በተጓዳኝ መንግስትም መጠየቅ ተገቢ ነው

Anonymous said...

I am really disgusted with what these so called fathers are doing and acting. As God ordered them ..'Go and teach and preach all of the world. You shouldn't have anything of your own except the cloth you wearing.'. That was the word , the mission that they have been sent, but now they all are looking for money, property and so on. What a shame, I think the people, followers of the Faith are doing far more better than these Fathers.

May God protect our Church and Faith, just by his power, I don't think the prayers of any of such fathers will bring God near us rather will make us dolls for Satan.

On the other hand lets keep our faith and do whatever we can to keep our Orthodox faith and May God help us to do that.

Anonymous said...

ሊላይ ነኝ። አማኝ ሰው የናፈቅኝ፤ መንፈሳዊ አባት የራበኝ፣ ትምህርቱ፣ ምግባሩ፣ አርአያነቱ የማረከኝ ሰው በጠፋበት ዘመን የተወለድኩ(ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት) ሳይዘነጉ ማለቴ ነው፣ እነሆ ከድመት ባነሰ ኅሊና ላይ ሆነው የክፉ ተግባር ኩሳቸውን እንኳን አርፎና ሰብሰብ ብሎ በመቀመጥ መሸፈን ያልቻሉትን ጳጳሳት እንወርፍ፣ እንነግራቸው ዘመን ላይ ደረስኩና ቤተክርስቲያኔ ሸፍና ያቆየቻቸውን ያህል ሸፍነው ሊጠብቋት ቀርቶ በኃጢአት ብዛት የደደረ ጨካኝ ልባቸው «ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ» እንዲሉ ሆነና ቢያምሷት፣ ቢያውኳት ከእኔ ወዲያ ማን ምስክር ሊሆናት ብዬ እኚህን ሰውዬ አባ ፋኑኤል ተብዬውን አደብ እንዲገዙ እስኪ ጥቂት ልንገራቸው አልኩ። ሐዋርያው ጳውሎስ ለደቀመዝሙሩ ጢሞቴዎስ እንዲህ ብሎት እንደነበር «የተሰጠህን መልካሙን አደራ፣ በእኛ ውስጥ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ ጠብቅ» የሚል ዐብይ ቃል አለ። እንግዲህ ቤተክርስቲያንን በፍቅር፣ በኅብረት፣ በሰላምና በመንፈሳዊ የምግባር ምስክርነት ማስተዳደር ይገባ ዘንድ የተነገረው ቃል የሚያስረዳን ነገር ቢኖር በሚመራቸው በውስጣቸው በሚኖረው መንፈስ ቅዱስ ኃይል መስራት ሲችሉ ብቻ እንጂ ሁከትን «ጠብ ያለሽ በዳቦ» እያሉ እንደሚጣሩት አባ ፋኑኤል ዓይነቶቹ ሊሆን እንደማይችል እኔ ሳልሆን ቃሉ በግልጽ ያስተምረናል። መንፈስ ቅዱስ በነሲሞን ቤት ያድር ዘንድ ባህርይው አይደለምና ሃዋሳዎች ቤተክርስቲያናችሁን ጠንክራችሁ ጠብቁ ማለትን እወዳለሁ። እኚህ ያልታደሉ ግን ለጥፋት ይሁን ለልማት ለጊዜው በሰማይ መዝገባቸው ተከማችቶ ይቆየንና በሹመት በዕድገት የታደሉ አባ ፋኑኤል!!!ምነው ከድመቷ ተምረው ገመናዎትን ደብቀው አርፈው ቪላዎት ውስጥ እስከጊዜው ቢቀመጡ? በደልና ኃጢአትዎን ንገሩልኝ፣ አውጁልኝ የሚሉት እኮ ራስዎ ከድነው፣ ሰብሰብ ብለው ማስቀመጥ ባለመቻልዎ ነው። ዱርዬና ማፍያ በአውደምህረት እንዲናኙ መፍቀድዎ የእርስዎን ማንነት ማሳያ መስታዎት መሆኑን ስለማያውቁ እኛ እንነግርዎታለን። እርስዎም እንደእነርሱ የመሆን ጥንተ ልማድዎ እየሳበ ያስቸግርዎታል ማለት ነው። የሃዋሳው ቅዱስ ገብርኤል አስተዳዳሪ የነበሩት አባ ገ/ዋህድ የዘጉትን በር እርስዎ ከፍተው የሰጡት ክፍት ቤት ይወዳሉ ማለት ነው። እኔን የሚያሳዝነኝ ስንት ብጹዓን አባቶች ተብለው በተጠሩበት ማዕረግ (እነ አቡነ ጎርጎርዮስ የሸዋ ሊቀጳጳስ ፣አራት ዓይናው መርሃ ክርስቶስ)በነበሩበት ማዕርግ እርስዎ ተገኝተው ከኤቢሲዲው ወይ ከቅዳሴው ወይ ከአርአያ ክህነቱ የሚታወቅና የሚነገር፣ የሚመሰከርልዎ ሳይኖር ያዙኝ፣ ልቀቁኝ በጥብጥ በጥብጥ ይለኛል በማለት ለያዥ፣ ለገራዥ ማስቸገርዎ ነው የገረመኝ። በማጠቃለያዬ የምልዎ እስከነገበናዎ እባክዎ ተሸፋፍነው አርፈው ይቀመጡ!!! እርስዎ መሸፈን ያልቻሉትን እኛ ልንከድንልዎ አንችልም እልዎታለሁ። ጢሞቴዎስ« በብዙ ምስክሮች ፊት እውነተኛውን እምነት ተጋደል» (1ኛ ጢሞ6፤12)ተብሏል። እስኪ የምንመሰክርልዎ እውነተኛ ተጋድሎዎ ምንድነው? እኛ እናውቅዎታለን፤ ለነፍስዎ ራስዎትን ይጠይቁ!!!

መልአከ ሳሌም አባ ገብረኪዳን እጅጉ said...

ደጀ ሰላማዉያን ሰላም ለእናንተ ይሁን።
የአዋሳዉ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሁኔታ ይችን ትንሽ ጽሁፍ እንድጽፍ አነሳሳኝ
እረ እግዚኦ እንበል ጎብዝ ወደት እንግባ ቤተ ክርስቲያንን በፈተና ቀሥፎ የያዘዉ ሰይጣን ምነው አለቅ አላት በመንበረ ፓትርያርኩ አካባቢ ያለው ፈተና ሳያበቃ ደግሞ ወደ ሀገረ ስብከትም ተዘዋወረ ምነው አቡነ ፋኑኤልን ተው የሚላቸው ዘመድ የለም እንደ ምነው ሁሉንም ዝም ስንል የማናውቅ አደረጉን? ትላንት ምን ነበሩ ዛሬስ ምን ተሰማቸው አሁን ላሉበት ደረጃ እኰ የደረሱት በዚችው ቤተ ክርስቲያን ተንጠልጥለው ነው።ከነፋስ ስልክ ት/ቤት እስከ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን ከመኪና ሥፌት እስከ ምክትል አስተዳዳሪነት ከዚያም እስከ ሀገረ አሜሪካ ያደረሰች እኮ ይችው አሁን የሚያጉላሏት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት በዋሽግተን ዲሲ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለረጅም ዘመን የአሁኑን ፓትርያርክ እና መንግሥትን ሳይቀር በመቃወም ፍርድ ጎደለ ድሀ ተበደለ ሰባዊ መብት ተጣሰ በሚል በዋሽግተን አደባባይ ከፓለቲከኞች ጋር በመሆን በጣም ብዙ ብዙ ነገሮችን ሲሉ ቆይተው ፎር ጉድ አገራቸው ገቡ ተባልን ብዙዎቻችን እሰየው በታም ጥሩ አደረጉ ሥንል ሌሎች ደግሞ የለም ሹመት ሸቷቸው ነው እነጅ ፎር ጉድ አይደለም ለማየት ያብቃችሁ አሉ ።በድንገት ቤተ ክርስቲያኑን ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን ሊአስገቡ ነው ተባለ በጣም ደስ አለን አዲስ አበባ ለሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስም ቤተ ክርስቲያኑን እጅ መንሻ አድርጋቸሁ ተቀበሉኝ አሉ ፓትርያርኩም ሆኑ ሌሎች አባቶች እሰየው እንድህ ነው የቁርጥ ቀን ልጅ ተባለና ለትልቁ ማዕረግ ታቀዱ እናም ተሾሙ ቅ.ሲኖዶስም ይበሉ የለፉበትን ቤተ ክርስቲያንና ባካባቢው ያሉትን አብያተ ክርስቲያናት በአባትነት ይጠብቁ ይባርኩ የሀገሩን ሰርዶ በሀገሩ በሬ ተባለና ወደ አሜሪካ ተላኩ ሲመለሱ ግን እንደጠበቁት ሆኖ አላገኙትም የቤተ ክርስቲያኑ ቦርድና ምዕመናን በመጡበት እግራቸው መልሶ አሰናበታቸው ኪዚያም ለቅዱስ ሲኖዶስ ጉዳዮን ሲያስረዱ ሀገሩም እንዳልተቀበላቸው ሲናገሩ ታላቁን እና ነባሩን የሲዳሞ ሀገረ ስብከትን እነደ እድል ሆኖ በሰለጠነው ሀገር ኑረዋል ተባለና እንዲያለሙ ሀገረ ስብከቱን እንዲያስፋፉ አደራው ተሠጣቸው እሰየው አዋሳ ቀን ወጣለት አልን ደስም አለን። አብያተ ክርስቲያናትን ማስፋፋት ብሎም የቤተ ክርስቲያን ይዞታ የሆኑትን ቦታዎች አጥር አሳጠሩ ግንብ አስገነቡ ተባለ አሁንም በጣም ደስ አለን ሥራውና ሠራተኛው ተገናኙ ተባለ።ግን የቤተ ክርስቲያን አባቶችን በመግፋት አዲስ ከሠለጠኑ ባዲስ ልሳን እንናገራለን ብለው የቀኑን መንፈሳዊ ጉባኤ ወደ ሌሊት የቀየሩ የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት እያፋለሱ እንደ ይሁዳ የሰላሳ ብር ከረጢት ሳይሆን የሽ ብሮችን ከረጢት አንግበው በዬ አብያተ ክርስቲያናቱ ሕዝቡን የሚያደነቁር ድምጽ ማጉያ በመኪና ላይ አስተክለው ንግድ በማጧጧፍ ላይ ከሚገኙ እንደነ በጋሳው፣እነደነ ጠንቋዩ ጌታቸው ዶኒ ፣ የሰው ግጥም እየሰበሰበ በመጽሐፍ መልክ እያሳተመ በመቸብቸብ ከሚታወቀው፣ የአዋሳ ቅዱስ ገብርኤልን ቤተ ክርስቲያን ከልጅነት እስካሁን አጽመ ርስት አድርጎ ባደራጀው የማፊያቡድን እየታገዘ እኛ ካልፈቀድን ደቡብን ማንም አይረግጣት ከሚለው።ከዚህም በላይ የኦርቶዶክስ ካባ ደርቦ በውስጥ ግን የመናፍቃን አቀንቃኝ ከሆነው ያሬድ አደመ እና ከመሳሰሉት ጋር በመሆን አቡነ ፋኑኤል ቤተ ክርስቲያኒቱን ምስቅልቅሏን እያወጡት ነው የሚገርመው ጳጳሱ የነበጋሻው፣የነያሬድ አደመ ግብር አብይ ሆነው መገኛታቸው ነው። ስለዚህ ወገኖች አጥብቀን እግዚኦ እንበል አንዳንድ አባቶቻችን ለተሾሙበት መንፈሳዊ ሥልጣን ሲሉ ለክብራቸው የሚመጥን ሥራ ቢሠሩ መልካም ነው እንላለን እንደገና እመለሳለሁ።ቸር ይግጠመን። ቤተ ክርስቲያናችንን እግዚአብሔር ይጠብቅልን፡ አሜን።

SendekAlama said...

+++

ምን አይነት ዘመን ነው የደረስነው (ወይንስ ዘመኑን የእኛው ክፉ ስራ አከረፋው? እንደየአመለካከታች!) ከማዕረጋት ሁሉ በላይ የሆነውን ማዕረግ ይዘው እንዲህ አዕነት ቅሌት ውስጥ እንዴት ይገባሉ? እንኩዋንስ ሊቀ ጵጵስና ደረጃ ተደርሶ ይቅርና ገና ዲቁና ሲሾሙ እኮ የሕይወት መስመር ተለወጠ እንደ ምዕመን ማሰብና መመኘት ቀረ ማለት አልነበረም እንዴ? እኔስ የበለጠ የሚያስፈራኝ ለጵጵስና ሹመት ቁዋፍ ላይ ነን ብለው የሹመታቸውን ቀን የሚናፍቁ በሕይወታቸው ከምዕመን በታች ዝቅጥ ያሉ በተለይ በውጭው ዓለም በ «ምንኩስና» ያሉ አባቶችን ሳስብ እንዲዚያ የሚያስፈራኝና የሚያሳዝነኝ የለም።

Anonymous said...

abetu yehonebinin asib abetu
abetu yehonebinin asib abetu

Anonymous said...

+++
besime silase tiketekit keise

የወንድም በጋሻዉ ያዓመቱ ምርጥ ተሸላሚ አባት ምን ነካቸዉ ጎበዝ!
ሰላም እግዚአብሔር አይለየን

Anonymous said...

Graet

How is Yared? Still banned from all service in Awasa?

How about his friend begashaw? Abune Fanuel? update

Thanks

Anonymous said...

ያሬድ የሚባለው አገልግሎት እየሰጠ አይደለም፣

Anonymous said...

abate weshet telante yastemarew yared new

Anonymous said...

first of all become a bishop is not easy. the guy doesn't have any background or experience or any type of education nothing. he came from sundy school. that is it. noda education or monstary experience. he was in DC and he nominated with corruption. so what do you expect from this guy?

Anonymous said...

wegentegninet aynur bebizuhan meteraterin yfetiral ebakachihu bhimanaotachin enitsena ewnet eskitweta betigistna betselot entebikat kemanim anwegin

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)