September 8, 2010

በዋስ እንዲለቀቅ የተወሰነለት ዘሪሁን ዳግመኛ ተይዞ ፍርድ ቤት ቀረበ

(ደጀ ሰላም፤ ሰፕቴምበር 8/2010፤ ጳጉሜን 3/2002 ዓ.ም):-  በእነ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ፣ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ እና በጋሻው ደሳለኝ የስም ማጥፋት ወንጀል ክስ የቀረበበት ዘሪሁን ሙላቱ በተከሰሰበት ጉዳይ በቂ ማስረጃ ያልቀረበበት በመሆኑ በትናንትናው ዕለት በ2500 ብር ዋስ እንዲለቀቅ በአዲስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍረድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የተወሰነለት ቢሆንም “የግል ተበዳይ ነን” ያሉት እነ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ፣ ‹‹ፖሊስ አላግባብ ለቆብናል›› በሚል በፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ይግባኝ በመጠየቅ ባመለከቱት መሠረት ተጠርጣሪው ከመንገድ ተይዞ በማረፊያ ቤት ካደረ በኋላ ዛሬ ጠዋት በችሎቱ እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡

በፍርድ ቤቱ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ፣ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ እና በጋሻው ደሳለኝ በምስክርነት ያቀረቧቸው የአራት ምስክሮች (ቀሲስ ሳሙኤል እሸቱ፣ ዲያቆን ዳንኤል፣ መምህር መሐሪ አድማሱ እና ራሱ በጋሻው ደሳለኝ) ቃል ተደምጧል፡፡ ‹‹የሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች›› በሚለው መጽሐፍ ጉዳይ ምንም የሚያውቀው ነገር እንደሌለ ቃሉን የሰጠው ዘሪሁን ሙላቱ መከላከያ ማስረጃውን እና የሰው ምስክሮቹን እንዲያቀርብ ለዛሬ ከሰዓት በኋላ ተቀጥሮ የነበረ ቢሆንም ጉዳዩን የያዙት ዳኛ ባለመገኘታቸው ጉዳዩ ለነገ ጠዋት አድሯል፡፡ ተጠርጣሪውም በሰነበተበት ማረፊያ ቤት ለመመለስ ተገድዷል፡፡ እነ ወ/ሮ እጅጋየሁ ይህን የፍርድ ቤት ጉዳይ የሚከታተሉት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከቱ መኪና በመሯሯጥ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በሀገረ ስብከቱ ከፍተኛ የባለጉዳዮች መጉላላት፣ በጉዳዩ ደጋፊ የሆኑት ሲጠቀሙ ተቃዋሚ የሆኑት ደግሞ እንዲገለሉ መደረጋቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
በሌላ በኩል በጋሻው ደሳለኝ ዛሬ ጠዋት በፍርድ ቤቱ የተገኘው በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ በተደረገለት ጥሪ ትላንት ጳጉሜ ሁለት ቀን 2002 ዓ.ም ‹‹የስድብ አፍ›› ሆኖ የዋለበትን የድሬዳዋ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ጉባኤ አቋርጦ በአውሮፕላን በመመለስ ነው፡፡ በጉባኤው ላይ የተገኙ የዐይን ምስክሮች ለደጀ ሰላም እንዳስረዱት በጋሻው በዐውደ ምሕረቱ ላይ ፈር በለቀቁ የተለመዱ አገላለጾቹ አበው ካህናትን፣ ‹‹እናንተ ከሳሾች ካህናት፣ እገሌ ሰባኪ እንዳይመጣ፣ እገሌ እንዳይቀር እያላችሁ የምትከሱ እነማን ናችሁ? ለፍትሐት ሲሏችሁ መስቀል ይዛችሁ ትሮጣላችሁ፤. . .›› በሚሉ ቃላት ሲዛለፍ ውሏል፡፡ አንዳንድ ምእመናን ሁኔታውን ለፍትሕ አካላት እና ለሕግ አስከባሪ ኀይሎች በመጠቆም ምላሽ እየተጠባበቁ መሆናቸውን ለመረዳት ተችሏል፡፡ ከዚህ ቀደም ይኸው አጉራ ዘለል ግለሰብ በዚሁ ሀገረ ስብከት በማኅበረ ቅዱሳን ላይ፣ ‹‹እናንተ ሆዳሞች፣ ደም አፍሳሾች፣ ደም መጣቾች፣ ከሳሾች፣ ቀማኞች…›› ወዘተ ብሎ በመናገሩ የስም ማጥፋት ወንጀል ክስ ቀርቦበት በፖሊስ ታስሮ እንዲቀርብ መደረጉ ይታወሳል፡፡

3 comments:

selamawi said...

በስመ ስላሴ አሃዱ አምላክ አሜን

እንኳን ለዘመነ ሉቃስ ዋዜማ በሰላም አደረሳችሁ

እውነተኛውን ሕይወት ይይዙ ዘንድ፥ ለሚመጣው ዘመን ለራሳቸው መልካም መሠረት የሚሆንላቸውን መዝገብ እየሰበሰቡ፥ መልካምን እንዲያደርጉ በበጎም ሥራ ባለ ጠጎች እንዲሆኑ፥ ሊረዱና ሊያካፍሉም የተዘጋጁ እንዲሆኑ ምከራቸው። 1ኛ ጢሞ 6፥18

ምነው ቤተክርስቲያን ስትሰደብና በአህዛብ ስትቃጠል ካህናትና ምዕመናን በሰይፍ ሲቀሉ እንደዚህ አልተሮጠላቸው በወቅቱ ትዝ ይለኛል በጅማ በበሻሻ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ካህናቱ እና ምዕመናኑ በሰይፍ ታርደው አስከሬናቸው በእሳት ሲቃጠል የብዙ ምዕመናንን ልብ የነካ ነበር ታዲያ ለአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት የጸሎተ ፍትሃት እንዲደረግ ጥያቄ ሲቀርብ ከዋኖቹ የተሰጠው መልስ ነገር ታባብሳላችሁ አርፋችሁ ተቀመጡ የሚል ነበር ዛሬ ግን ቤተክርስቲያኒቱን እንደፈለጉ የሚያሽከረክሯት ማንነታቸውን ቤተክርስቲያንም ሆነች ልጆቿ የማያውቋቸው ግለሰቦች በንብረቷና በገንዘቧ ይቀልዱበታል መጨረሻቸው ምን ይሆን ጊዜው ቅርብ ነው እናየዋለን አምላከ ቅዱሳን የዘገየ ቢመስልም የሚቀድመው የለም ቸር ይግጠመን

Anonymous said...

Ahun Leman ytazenal???

Anonymous said...

ሰላም ለናንተ ይሁን
ነገሩ በጣም የሚያሳዝን ነው.መፅሐፉ ካንድ ሊቀ ትጉሀን ከተባለ ሰው የሚጠበቅ አይደለም በጣም አሳፋሪ መፅሐፍ ነው.እሱ ብቻ ሳይሆን ዲያቆን በጋሻው ተብየውም ቢሆን የሚፅፋቸው ፅሁፎች በጣም አሳዛኝ አንገት የሚያስደፋ ነው.እንደኔ ሁለቱንም ቤተ ክርስትያንዋ ልትገስፃቸው ይገባል ነው የምለው.
አምላከ ቅዱሳን ሀገራችን ኢትዮጵያንና ቤተክርስትያናችንን ይጠብቅልን

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)