September 8, 2010

የሐምቡርግ ኪዳነ ምሕረት ቅዳሴ ቤት ተከበረ(ደጀ ሰላም፤ ሰፕቴምበር 8/2010፤ ጳጉሜን 3/2002 ዓ.ም):- በሀገረ ጀርመን የሐምቡርግ ኪዳነ ምሕረት ቅዳሴ ቤት ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ ምሥራቅ አውሮፓ ሊቀ ጳጳስ በመሩት ደማቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ተከበረ፡፡

ነሐሴ 23 እና 24 ቀን 2002 ዓ.ም. የተከበረው በዓል ልዩ ልዩ መንፈሳውያት ዝግጅቶች የቀረቡበት ነበር፡፡ ቅዳሜ ነሐሴ 23 ቀን 2002ዓ.ም. ከመላ ጀርመን የተሰባሰቡ ካህናትና ምእመናን የተሳተፉበት ዐውደ ጥናት ተካሂዷል፡፡ በዐውደ ጥናቱ „የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምሥረታና ታሪክ በሀገረ ጀርመን“ በሚል ርእስ በመልአከ ሰላም ዶ.ር መርዐዊ ተበጀ፤ እና “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ ወቅታዊ ሁኔታ” በሚል ርእስ በዲ.ን ዶ.ር መርሻ አለኸኝ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ምእመናኑ ተወያይተውባቸዋል፡፡ ከዐውደ ጥናቱ ጋር በተያያዘም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጀርመን ከምሥረታዋ ጀምሮ እስከ አሁን ያደረገችውን የአገልግሎት ጉዞ የሚያስቃኝ ዐውደ ርእይ ተከፍቶ በምእመናኑ ተጎብኝቷል፡፡ የሕጻናት ዐውደ ትእይንትና ልዩ ልዩ መንፈሳውያት ቁሳቁሶች ለሽያጭ የቀረቡበት ባዛርም የዕለቱ መርሐ ግብር አካላት ነበሩ፡፡

በመጨረሻም የሰርክ ጸሎትና ስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር በሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ተከናውኖ ካህናቱ ወደ ማረፊያቸው ከተሸኙ በሁዋላ በዓሉን ለማክበር ከመላ ጀርመን የተሰባሰቡ ምእመናን ሲማማሩና በመዝሙር እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ አድረዋል፡፡ እሑድ ነሐሴ 24 ቀን 2002ዓ.ም. ከጠዋቱ 1 ሰዓት ጀምሮ በብፁዕ አቡነ ዮሴፍ መሪነት ለዕለቱ የሚያስፈልጉት ልዩ ልዩ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ተፈጽመው ሥርዓተ ቅዳሴው ከተከናወነ በኋላ የቃል ኪዳኑ ታቦት በታላቅ መንፈሳዊ ሐሴት ከብሯል፡፡ በሥርዓተ ንግሡም ልዩ ልዩ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክቶች ተላልፈዋል፡፡

በዓሉን አስመልክቶ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ በጽሑፍ ያስተላለፉት መልእክት በቆሞስ አባ ብርሃነ መስቀል ተድላ የበርሊን ቅ/አማኑኤልና የሐምቡርግ ኪዳነ ምሕረት አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪ በንባብ ተሰምቷል፡፡ ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው በሐምቡርግና አካባቢ የሚኖሩ ምእመናን ከሚያገለግሏቸው ካህናት ጋር በመተባበር ለዚህ ደረጃ በመድረሳቸው “እንኳን ደስ አላችሁ” ካሉ በኋላ ለወደፊትም በፍቅርና በአንድነት በመኾን ቤተ ክርስቲያናቸውን የበለጠ እንዲያጠናክሩ አደራ ብለዋል፡፡ በጀርመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ካህናት መልአከ ሰላም ዶ.ር መርዐዊ ተበጀም “በሐምቡርግ ለሚኖሩ ምእመናን ቤተ ክርስቲያን ለማቋቋም እንቅስቃሴ ከተጀመረ ሃያ ሁለት ዓመታት እንደ ተቆጠሩ” በማውሳት ጥረቱ ሁሉ ሰምሮ የአካባቢው ምእመናን ለዚህ በመድረሳቸው “እንኳን ደስ አላችሁ” ብለዋል፡፡ አያይዘውም ምእመናኑ ቤተ ክርስቲያናቸውን እዚህ ካደረሱ ዘንድ አሁንም የበለጠ በመጠናከር በመካከላቸው ተቀምጦ የሚያገለግላቸው ካህን ለማስመጣት እንዲተጉ አሳስበዋል፡፡ በተጨማሪም የሐምቡርግ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ሐላፊ የኾኑት ፓስተር ወ/ሮ ዜቨሪን ካይዘር ባስተላለፉት መልእክት “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሐምቡርግ መጠናከር ለእኛ ውበት ይጨምርልናል፡፡ ቤተ ክስርቲያናችሁ ውበት የተመላች ናትና አሁንም በርቱልን” ብለዋል፡፡ በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ባስተላለፉት ቃለ ምእዳንና ትምህርት የበዓሉ ፍጻሜ ኾኗል፡፡ የበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ አባላትና የአጥቢያው ምእመናን በዓሉ በደመቀ ሁኔታ በመከበሩ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡

8 comments:

Anonymous said...

እንኩዋን ደስ አላችሁ!

ሠናይ

ሰናይ said...

እግዚአብሔር ይመስገን!!!

Anonymous said...

Many thanks to Him. Yabrtachihu!!
GKidan, Austria

Anonymous said...

Be ezih bal tekafiye nebere. Be ewunet betam des yemil beal neber kemejmriaw jemro eske mechereshaw. yasfesimilin.

Anonymous said...

እግዚአሔር ይመስግን! እንኳን ለዚህ አበቃችሁ!

Anonymous said...

It was indeed a very good ceremony. on Saturday we discussed too, about the church situation in Ethiopia. Some church members had the courage to talk about the outrage of church administration specially in recent time. But not all Kahnat were ready to talk about it. Some tried to defend and some tried to show an act of condemnation. But the Diakon has hold an interesting speech about the church situation in presence. For me it is since then very clear that all Kahnat and Memenan, we must talk about the situation of our church. Let us talk about the problem and solution of our mother church as true Christians do and let us pray to God to help us out.

+++
ENQUAN DES ALACHU! sELSEMU YETMSGEN YEHUN! BETSELOTNA BE MESGAN BEBETU YEMTEGA WAGA ALEWWNA BERTU! MELKAM YEMSKEL BALE!
+++
SIRGUT

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)