August 5, 2010

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ስለ ሰላምና አንድነት ከተላከው ልዑክ የተሰጠ መግለጫ

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 28/2010)፦ ከአምስተኛው ፓትርያርክ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሲመት ማግስት ጀምሮ በቤተ ክርስቲያኒቱ የተነሣውን መከፋፈል ለማቆምና በአባቶች መካከልም የተፈጠረውን እስከ መወጋገዝ የሚያደርስ ልዩነት በእርቅ ለመጨረስ የተጀመረው ድርድር ሁለቱን ተደራዳሪ ወገኖች ፊት ለፊት ለማገናኘት እንኳን ሳይችል መክኖ መቅረቱን ተከትሎ ቅ/ሲኖዶስን ወክሎ ለመደራደር ከአዲስ አበባ የመጣው ልዑክ መግለጫውን ዛሬ አውጥቷል። ልዑኩ ያወጣውን መግለጫ ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ (http://www.eotcdc.org/) ይጫኑ። በተያያዘ ዜና የአሜሪካው ወገን ቀድሞ ያዘጋጀው የሚመስለውን መግለጫ በ “ቋጠሮ” ድረ ገጽ  ላይ በትናንትናው ዕለት ማውጣቱን መዘገባችን ይታወሳል። የአሜሪካውን ወገን መግለጫ ለማንበብ እዚህ (መግለጫ) ይጫኑ።

ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን

9 comments:

Anonymous said...

Bo Gize le kulo. Just Pray one day evrey thing will be ok.

Anonymous said...

It is very hard to blame any group at this time. I know only no one is ready to build the holiy church and no one also accept his or theirs weakness. I am sorry to all my ethiopian brother and sisters.Our future is darken by greedy power lovers.

TEWAHEDO said...

All of us have cried unto people, as we thought the solution would come from them. We bowed unto them so that they would listen to us. We have abandoned our brothers and sisters for the sake of our fathers, as we thought again they would negotiate and bring peace some day. Now it is time to cry unto God, as He is the only one who can bring solution. Let God speak and the world tremble. Let God speak and powerful leaders shudder. Let God speak and stubborns shake.Let us stand firm in front of our enemies, who have been trying to eradicate our tradition and dogma. God is always with us if we follow the right path. When Moses was praying, Aaron was fighting. Let us keep praying and fighting until we get the solution. God's word tells us through Jeremiah to call unto him. "Call unto me, and I will answer thee, and shew thee great and mighty things, which thou knowest not." Jer.33:3

Anonymous said...

I want to say that this is a sad occasion.

I want to point the all the priests to look to Psalm 49(Mezmur 49), let it be a warning as to what they will be held responsible for in the siight of GOD on judgment day...He is not going to ask them as to what anyone else did about the truth....only what they did about the the truth and for the truth. All we can do as believers is to pray that God's will will be done.

Amen

Anonymous said...

ደጀ ሰላሞች
መቸም ደጀ ሰላም የሰላም ቦታ ነው ብዬ አምናለሁ። እናንተም እንደ ስማችሁ መሆን ይኖርባችኋል። በእውነት ለቤተ ክርስቲያን ሰላም የምታስቡ ከሆነ በአንድ ወገን መቆም አይኖርባችሁም። ቢቻል ለመልካም ነገር ምክንያት መሆን ጥሩ ነው ካልሆነ ግን ለሁሉም ባለቤት ለሆነው ለእግዚአብሔር መጸለይ ይሻላችኋል። በተደጋጋሚ ስትታዩ በአንድ ወገን ቁማችሁ በስደት ያሉትን አባቶች ስታውግዙ ትታያላችሁ። ስለስብሰባው ያወጡትን መግለጫ ሳይቀር "ቀደም ብሎ የተዘጋጀ የሚመስል" በማለት ታንቋሽሻላችሁ። የቤተ ክርስስቲያን ሊቃውንት ያለምንም ዝግጅት ቅኔ እንደሚዘርፉ እየታወቀ ሁለት ገጽ ደብዳቤ መጻፍ ምን ያህል ሰዓት አስፈልጎ ነው እንዲህ ሊባል የቻለው? ወይንስ በእናንተው ምርታማነት መጠን ለክታችኋቸው ነው? በዚህ አያያዛችሁ ሰላምን በእውነት ትፈልጉታላችሁ ወይ? ምንአልባት የእናንተ ህልውና የተመሠረተው በአባቶች ልዩነት ይሆን?
አባቶች ሰላምን ካልፈለጉ ለምን ጊዜያቸውን ያጠፋሉ? በውጭም ሆነ በአገር ውስጥ ያሉት አባቶች ጊዜ ያለአግባብ እንዲጠፋ ይፈልጋሉ ብዬ አላምንም። እባካችሁ አባትን ማክበር ሃይማኖ ታዊ ብቻ ሳይሆን ባህላችንም ነውና አባቶች የሚገባቸውን ክብር ስጧቸው።

ተሻገር

Anonymous said...

እኔ ግን አንድ ደስ የሚለኝን ነገር ልንገራችሁ?! ...ይህች ቤተክርስቲያን እየነጋላት ነው:: ሊነጋጋ ሲል በጣም ይጨልማል ሆኖ ተቸገረች እንጂ ጊዜው ደርሶአል:: ... እያያችሁ ነው: አሁን እኮ ሰው ሁሉ የሚመካበት ጠፍቶ "አምላክ ሆይ ምነው ተውከን: እመብርሃን ምነው ዝም አልሽን.. እስከመቼ ነው?" እያለ ነው እኮ:: በቃ ይሄ አይደል የሚፈለገው: ትምክህታችን እግዚአብሔር ከሆነ እርሱም ይረዳናል:: ደሮም እኮ ፈጣሪ የሚፈልገው ይሄንን ነው:: ወገኖቼ አይዞአችሁ የፈጠረን አምላክ አይረሳንም:: እንዲህ ሆድ ብሶን ስንንገላታ ያያና ይራራልናል:: ... ተመስገን እኔ የምናፍቀው ይህን ጊዜ ነበር:: በሰው ያለንን ዕምነት ትተን ተስፋ ቆርጠን እግዚአብሔርን ".. ምን ተሻለን?" ስንለው ማየት:: በተረፈ አሁን የቀረው ጊዜ ትንሽ ነው ብቻ እንዲህ በቤተክርስቲያናችንም ላይ በሰውም ላይ የተጫወታችሁ ሁሉ "...ወየው ለኔ ለበደለኛው!!"

Unknown said...

ያሳዝናል በጣም ያሳዝናል ።

Anonymous said...

መግለጫው ነገር ቆስቋሽ እንዳይሆን ያለፈው ጭቅጭቅ ይበቃናል።

Anonymous said...

Betam yigermal

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)