August 19, 2010

“የሐውልቱ ስር ቁማርተኞች”ን ማንበብ ከፈለጉ ...

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 18/2010)፦ የፓትርያርኩና የማፊያው ቡድን “ስውር ፀሐፊ” (Ghost Writer) ዘሪሁን ሙላቱ ስለ ፓትርያርኩ ሐውልትና ተያያዥ ጉዳዮች  ባለ 50 ገጽ መጽሐፍ ማውጣቱን፤ እነ በጋሻው ደሳለኝና ኤልዛቤል የምትባለው ወ/ሮ እጅጋየሁ እንደተጠቀሱበት፤ ዲያቆን ሲባል ቆይቶ በቅርቡ ሊቀ ትጉሃን የሚል የማዕረግ ስም የደረበው Ghost Writer ዘሪሁን ሙላቱ ጊዜውን በቶሎ በማጥናት እና የፓትርያርኩ ሐውልት ብዙ ተቃውሞ እንደበዛበት ሲመለከት፣ የሐውልቱ ተቃዋሚዎች ያሉትን በመሰብሰብና መጽሐፍ አድርጎ በማሳተም ሲያሳዝነው የሰነበተውን ምእመን አሁን ደግሞ ገንዘቡን ሊበላው ይህንን ፓምፍሌት (መጽሐፍ ለማለት ይከብዳል) ማሳተሙን በተከታታይ መዘገባችን ይታወሳል። መጽሐፉን ማንበብ ለፍርድ ይመቻልና እነሆ እንዲህ አዘጋጅተነዋል። ለማንበብ ይህንን (አስነብበኝ) ይጫኑ።

23 comments:

Anonymous said...

እግዚአብሔር ይስጥልን።
አክሊል ነኝ

yihunetame said...

sima ante dejeselam yemaitekim wore kemitfelefl min ale melkam zena bitawera?

Anonymous said...

i don't think , the book is not important . Please people don't spend any time on this area. it is fasting time. we have to pray to almight.

Anonymous said...

I have read the one he wrote on Abune Samuel, I didn't trust him then and I don't trust him now. Zerihun is full of anger and hatred. May Almight God give him relief and calmness in his life. I think he must be suicidal. For me the issue is neithe Fantahun, Ejigayehu, Begashaw nor Abune Paulos. It is Zerihun. He needs help.

Anonymous said...

Amazing. When I save the text, I found out that the book was saved as 'ye mesqelser qumartegnoch#. It might be a good idea if you post the 'ye mesqelser qumartegnoch' too. Of course if you have it.

Anonymous said...

ሊቀ ማእምራን ፋንታሁንን አስመልክቶ ስለተዘጋጀው መዋጮ ስሰማ በእጅጉ ነው የተገረምኩት ይህ መዋጮ ስለተፈጠሩት ነገሮች በምንም መልኩ ማካካሻ ሊሆን አይችልም ።
ፋንታሁን ሁለት ጥሩ ነገሮች አሉት የመጀመርያው መናፍቅ አለመሆኑ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ጥሩ የትምህርት ደረጃና አንደበተ ርቱዕ መሆኑ ነው። ነገር ግን እነዚህ ብቻ አንድን ሰው ጥሩ ሊያስብሉት ባይችሉም ይህን ታልቅ እድል ተጠቅሞ አዲሰ አበባ ሀገረ ስብከትን በዘመናዊ አሰራር ሊለውጠው የሚችልበትን እድል አግኝቶ እንደነበር ግን መጠቆም እፈልጋለሁ። ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ለምንድን ነው ቀደም ሲል ለቤተ ክርስቲያን የነበረውን መቆርቆር ትቶ በዚህ አይንት የተጨማለቀና ለእርሱም ሆነ ለቤተክርስቲያኑ አሳዛኝ በሆነ ጉዞ ውስጥ ሊገባ የቻለው ?ብለን ብንጠይቅ የተወሰኑ መላ ምቶችን ልንጠቅስ እንችል ይሆናል።
1 ሲኖዶሱ ሹመቱን በጊዛዊ ሀላፊነት ስለነበር የሰጠው በዚህ የቆይታው ወቅት በገንዘብ ደርጅቶና ተጠቅሞ እንዲለቅ በሚጎተጉቱት ሰዎች ግፊት በተለይም አቶ ያሬድ ክበደውና በነ ቀሲስ ሽታ የቀጨኔ ጸሀፊ ብሎም በነቀሲስ ክብሩ የእግዚአብሄር አብ አለቃ
አማካኝነት ዓይን ወዳወጣ የሙስና ተግባር እንዲገባ አድርጎታል።
2 አቡነ ጳውሎስ ባለቸው ከፍተኛ የገንዘብ ፍላጎትና በየግዜው ይህን አድርግ ይህን አታድርግ እያሉ በሚፈጥሩበት ተጽእኖ ውስጥ በመውደቁ እርሳቸው ትልቁ ለቤተ ክረስቲያን የማያዘኑ ከሆነ እኔን ምን ገዶኝ የሚለው መንፈስ ተጸናውቶት ሀገረስብከቱን ለምዝበራ እንዲዳረግ አድርጎታል።
3 ሌላኛው ምክንያት ደግሞ የሚውላቸው ሰዎቸ በተለይም የድራፍት ቡዱኑ የፈጠረበት ተጽእኖ የነበረውን መልካም ነገሮች ሁሉ እንዲያጣ አድርጎታል።
ዛሬም በየመጽሀፉ ለመሰደቡ ትልቁ ምክንያት የድራፍት ቡዱኑ መሪ ያሬደ ክበደው እንዲገብርለትና እንዲሰራ የሚያዘውን ነገር ለመፈጸም ማንገራገሩ ነው። በተለይም ያለምንም ችሎታውና ልምዱ በአራዳ ጊዮርጊሰ ተመድቦ የነበረው ቄስ በቀለንዘውዴን በመደገፍ ያሬድ እና አቶ ዳዊት የተባለ የኦሮምያ ተወላጅና ኦፒድዮ ነኝ በማለት የቤተ ክህነቱን ገቢ የሚያመሰው ሰው ትናንት በአቡነ ሳሙኤል ላይ የጳጳሱ ቅሌት
የሚለውን መጽሀፍ አሳትመው እንደበተኑት ዛሬም ለፋንታሁን ይህንኑ ጽዋ እንዲጠጣ አድርገውታል ።
4 የጉቦ አቀባባይ ደላሎች በሚያቀርቡለት ማስጎምጀት ምክንያት መስመሩን ሊስት ችላል ። ጉቦ በማቀበልና በማስቀበል በእነ ሊቀ ካህናት ሀይለስላሴ፤በነ አለቃ መኮንን ፤ በነ ዮሀንሰ ዋለ ዘመን ጀምሮ ከፍተኛ ልምደ ያላቸው እነ ቀሲስ ሽታ የቀጨኔ ጸሀፊ እና ሩፋኤል የማነ ፤ መሀሪ አድማሱና የማነ ዘመንፈስቅዱስ መሪነት ሳይለፋ የሚቀርበለትን የ አስር ፤ አሰር ሺ ብር ስጦታ እንቢ ለማለት ባለመቻሉ ለዚህ ችግር ሊዳረገ ቸሏል። ስለዚህ የአሁኑ መዋጮ ሊያስደንቀን አይገባም። በተለይም አቡነ ሳሙኤልን ከመንግስት ሰዎች ተገቢውን ሁሉ ድጋፍ አግኝቻለሁ እያለ በምክክርና በሰላም ሊያልቀ የሚችሉ ነገሮችን ሁሉ በማክበድ ሲያወሳስበ የነበረውን በሀላ አቡነ ሳሙኤልን ክዶ ትግሉ ሳያል ከፓትርያሪኩ የተቀላቀለው መርጌታ ሀይለ ማርያም አሁን የልደታ ጸሀፊ ነው አሁን ደግሞ ዲያቆን የማነህን አስነስቶ ቦሌ መድሀኔ አለምን ለመያዝ እንዲመቸውየመዋጭ ስራ ለይ ቢጠመድ የሚያስደንቅ አደለም ነገር ግን ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ያለውን ችሎታ እንዲጠቀም ከዚህ አሰራር የሚወጣበትን መንገድ ቢያፈላልግ ለቤተ ክርስቲያንጠቃሚ ሰው መሆኑን ልመሰክር እወዳለሁ።

Egzio said...

ውድ የደጀ ሰላም አዘጋጆች! በቅድሚያ ይህንን መጽሐፍ ለንባብ በመለጠፋችሁ በጣም እንዳዘንኩባችሁ ለመግለጽ እወዳለሁ። ለእኔ እንዲህ አይነት አዕምሮን የሚያቆሽሽ የዱርዩ ስድብ መለጠፉ እናንተን የሚያስገምት ነው። ባለፈው ጨምቃችሁ ያቀረባችሁት ሪፖርት እኮ በቂ ነበር። አሁን ሙሉዉን መጽሐፍ ማስቀመጣችሁ ህሊናችንን የበለጠ እንዲቆሽሽ የሚያደርግ ነው።

እኔ ስለግለሰቦቹ እየተከራከርኩ አይደለም። ነግርግን ግለሰቦቹ የተባለውን ሁሉ ፈጽመውት ቢሆን እንኳን ይመከራሉ ይዘከራሉ እንጂ ኃጢአታቸው ፀሐይ ላይ አይሰጣም። ምንም የሚያስተምረው ነገር የለም። ራሳችንን የምናይበትን ዓይን ከማሳወሩ በስተቀር።

ለወደፊት ግን የምታገኙትን ወሬ ሁሉ ከመለጠፋችሁ በፊት ሊያስገኝ የሚችለውን ጥቅም በሚገባ ታይቶ ቢሆን መልካም ነው። ደጀ ሰላም ስለቤተክርስቲያናችን አገልግሎት የምንወያይባት በመንፈሳዊ ሕይወታችንም የምንታነጽባት መድረክ ልትሆን ይገባታል እንጂ እንዲህ አይነት ለጆሮ የሚሰቀጥጥ ነገር የምናነብባት ልትሆን አይገባም።

ደግሞ ቆይ ምን አስቸኮላችሁ። ሱባኤው እስኪያልቅ እንኳን አትጠብቁም ነበር? እግዚአብሔር ልብ ይስጣችሁ። እስኪ በዚህች የተቀደሰች የፆም ወራት እንዲህ አይነት ነገር እናንብብ።

አቤቱ መድኃኒታችን እግዚአብሔር ሆይ
በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ህሊና ህትምት ስለ ሆነች ስለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ብለህ በደምህ የዋጀሃትን ቅድስት ቤተክርስቲያንን ጠብቃት። አቤቱ ማረን ይቅርም በለን። በደላችንን ተመልክተህ አታጥፋን!

Anonymous said...

Dear Dejeselamawiyan,

I appreciate your efforts of sharing informtion among us (your audience).

Let me share you information too which is associated with October 20, 2010. It is the 3rd year memorial of the rest of Likelikawent Ayalew Tamiru. I read very interesting and helpfull article on the Memorial Foundtion web site. Would you pls. refer to that web site and prepare something on your web site for the honer of this great father.

Thank you,

Anonymous said...

ውድ ደጀ ሰላሞች

እባካችሁ የ ወ\ሮ እጅጋየሁን የስራ ድርሻ በቤተክህነት ውስጥ ብታስረዱኝ በጣም ደስተኛ ነኝ። ምክንያቱም እየተሰራ ያለው ወይም ደግሞ ለ ወ\ሮዋ የተሰጣቸው ድርሻ ከተራ ምዕመን ድርሻ ወጣ ስላለብኝ ምናልባት የሆነ የስራ ድርሻ ማለቴ በቅጥር ይኖራቸዋል የሚል ግምት አድሮብኝ ነው። እንደ ተራ ምዕመን ሆነው አማካሪ በግል ከሆነ በ እውነቱ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ሰው እንደሌለ ቆጥረን መቀመጡ ይሻለናል። ግን ሳስበው እንደው የሆነ አንገት ማስገቢያ ኖሯቸው እያሰፉት መጥተው ይሆናል።

DEREJE THE AWASSA said...

dear dejeselams
thank you for posting this 'book" now i can have personal judjment.this is my comment: I am very very sure this person is ubnormal.

Anonymous said...

Basically this book(leaf let)is so disgusting.But I cant see any mistake of deje selam posting the book.Even though it is terible to read the entire book ,it might help us to know the kind of people around the church.

from the content of the book one can easily understand that the writer himself has't any care to the church.He didn;t write the book to benift the church :but either to make some money or to announce his deep hatered to the people he mentioned therein.
In the mean while we might get some idea about the people surounding the church.consdering the fact the spritual situation the people are in :I am afraid we are in huge crises of all time.

who can save us from this evil time?

Dereje said...

Really Sorry,
Let alone from Diacon and Priest,This type of "dirty" article is not expect from an ordinary Christian.
The Other jok of the writer is found on the introduction part-the dream about goat, hayna and donkey .kikikikiki..is he telling us"kids tereteret?" he condomn people for their wrong doing,the same time he is trying to chit people in the name of "God" and "dream"

let alone to write,even it's very difficult to read some words like :-" ye mayfewos diwuy"
the only thing I assure from this
garbage is that the writer does not has a little fear of God.
may God forgive us!

Anonymous said...

Dear deje selamoch Tsegawen yabezalachu.


security info:

when you pust the cursser on pdf shows user/seleshi/download/....
please take care for such security.

enezih netakiwoch kagnut lewedfit ke endezih ayent info enkwaretalen


just weste endetsefelachu asgededogn new;
Emebet tebarekachu.

Anonymous said...

Response to Dereje,

Dereje, the Awassa, you told us that the writer is ubnormal, as he wrote the truth. Where has gone your personal judjment? At least you should appreciate the writer before throwing words without observing pros and cons of the content. He revealed the sealed secret that has never been thought it will be disclosed. Of course, the Church is being devoured by these vagabonds with their groups. Nothing is remained concealed. No one would have told us this truth unless the writer had revealed the secret of our house messes. All of us are the victims of this tragedy. Our money shouldn't be kept in the pocket of some vicious people. I do appreciate the writer, as he revealed the secret of these MENAFIKAN. Bravo the writer. May God bless you.

GUD FELA said...

አሁን በቤተ ክህነት አካባቢ በጥቂቱም ቢሆን ፈሪሀ እግዚአብሔር ያለው ሰው ካለ ፍርሐት እና መንቀጥቀጥ ይሆናል። ኃጢአት እጅግ ስለበዛ በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ በእግዚአብሔር ቤት ያሉ ሰዎች ታሪካቸው ገሐድ ወጣ። እስከ መቼ ይደበቃል? እግዚአብሔር በቃ የሚልበት ሰዓት ከደረሰ ተቃዋሚው ማነው? በደል ለበደለው ሰው እግዚአብሔር ቅጣቱን ሲፈጽምና በለምጽ ሲቀጣ ለምጹ መቼ በጀርባቸው ልይ ወጣ? ሁሉም ሰው ያየው ዘንድ በግምባራቸው ላይ ወጣ እንጂ። አሁንም ሁሉ ያውቀው ዘንድ ጉዳቸውን ከጫፍ እስከ ጫፍ የተረዳው ሰው ከመካከላቸው ተነሣ። በጉያቸው ያለ እሳት ሲፈጃቸው እኛ ምን ቤት ነንና እንቃወማለን? ዳግም እንዲህ ያለ ሥራ በቤተ መቅደሱ እንዳይሠራ እግዚአብሔር ይኼን አደረገ እላለሁ። አቤቱ ደግ ሰው አልቋልና የተባለው ቃል ይፈጸም ዘንድ ግድ ሆነ። እውነትም ይሁን ውሸት ከፕሮቴስታንት ፓስተር ጋር በፍቅር የጦፈች እጅጋየሁ ፍቅሯ እስኪያልቅ ድረስ ያዘዟትን ከማድረግ ወደ ኋላ ትላለች ብላችሁ ታስባላችሁ? መናፍቃን ቤታችንን ሊነጥቁን በተዘጋጁበት ሰዓት እንዲህ እያደረገ ታሪካቸውን የሚነግረን ሰው ሲገኝ ግብሩ የተሳሳተ ቢሆን እንኳን ምክሩን ሰምቶ ተግባራዊ ማድረግ ብልጥነት እንጂ ሞኝነት አይመስለኝም። ሲሰርቁን፣ ሲገፉን እና ሞኝ አድርገው ሲመለከቱን ዝም ብለን ስንቀመጥ ፈሪ እንባላለን። እውነት የሚጽፍ ሰው ሲነሣ ደፋር ክርስትና ያልገባው እንላለን። የእኛነታችንን ነገር ለእኛ እንተወውና እንዲህ ሲደፈርስ ሊጠራ ነው ብለን ስንዴውን ከእንክርዳዱ የምንለይበት አጋጣሚ ሲገኝ ጸሐፊውንም የተጻፈባቸውንም አብረን አንውቀጣቸው። ጸሐፊው ሌላ የሚነግረን ነገር ካላ ትንሽ ቢጨምርልን መጥፎነቱ አይታየኝም። ጥይት አንዴ ተተኩሶ ካልተደገመ የጅራፍ ያህል ይቆጠራልና ቶሎ ቶሎ አጋልጦልን ስለስማቸው ሲሉ ላለመጋለጥ ዝም ብለው እንዲቀመጡ አንድ ሁለት ካለ ይበል ብሎ ማናገር ይገባል። አይመስላችሁም?

Anonymous said...

ምን ነካህ እግዚኦ!
ይኽን መጽሐፍ ደጀ ሰላም ያወጣው ብዙዎች ስለጠየቁ ነው። ምናልባት አንተ አብዛኛውን መልእክት የምታገኘው ከደጀ-ሰላም ብቻ ይሆናል እንጂ ኢትዮጵያ ውስጥ አንዱ መጽሐፍ እስከ ሠላሳ ብር እየተሸጠ መሆኑን አልሰማህ ከሆነ ዛሬ ስማ። ገበያ ላይ የወጣ ጸሑፍና የአደባባይ ምስጢር የሆነውን ነገር ደጀ-ሰላም ሸፈነውም ገለጠውም ከመነበብ እና ሰው ጆሮ ከመድረስ የሚያግደው የለም። አንተስ የዋሁ ሰምተህ ቆሸሽኩ እያልክ ነው፤ ሠርተው ያልቆሸሹ የመሰላቸው ሰዎች ስላሉ ሥራቸውን እነርሱ እንዲያነቡት እና እንደተነቃባቸው እንዲያውቁት ተጻፈ እንጂ እኔና አንተ አውቀን እንድንቆስልበት አይመስለኝም። ሌባ እድሜ ልኩን እየቀናው ሲሰርቅ ቢኖር ያጠፋ አይመስለውም፤ ሌብነቱን ከሥራ ስለሚቆጥረው ይብስ ይጨማምርበታል እንጂ። ምናልባት ግን ሌቦች እየታሰሱ ተይዘው ለብዙ ዓመታት ከጉልበት ሥራ ጋር እንዲታሠሩ ተበይኖባቸዋል ቢባል ያልተያዘው ሌባ እንደተነቃበት በማወቅ መታቀብ ይጀምራል። የዛሬው ታሪክ የዛሬውን ግብራቸውን ብቻ አይደለም የነገረን፤ ከትናንት በስቲያ ጀምረው እየሠሩት ያለውን ነው እንጂ። በእርግጥ ጆሮአችን መልካም ቢሰማ ሁላችን በወደድን ነበር፤ አጋጣሚው ግን የረዳን አልመሰለኝም። ኢየሱስ ክርስቶስ ያቺን በለስ የረገማት እና እንድትደርቅ ያደረጋት በአንድ ቀን ሔዶ ፍሬ ስላጣባት ሳይሆን ተመላልሶ ሔዶ ያው ሆና ስላገኛት ነው። የዛሬው ጽሑፍ እንዲህ ቁማርተኞቹን ያጋለጠው የትናንት በስቲያው ግብር ትናንት የበለጠ አድጎ የትናንቱ ግብር ዛሬ ከወትሮው ጨምሮ ስለተገኘ ማንም ይሸፍነው ዘንድ ስላልተቻለው ነው። እንግዲህ እግዚኦ ደጀ ሰላሞችን "ደግሞ ቆይ ምን አስቸኮላችሁ። ሱባኤው እስኪያልቅ እንኳን አትጠብቁም ነበር? እግዚአብሔር ልብ ይስጣችሁ። እስኪ በዚህች የተቀደሰች የፆም ወራት እንዲህ አይነት ነገር እናንብብ።" ብለህ እንዳልካቸው አንተስ ምን ነበር ሱባዔው እስኪያልቅ ድረስ ማንበብህን ብትተው! ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ አንብበህ ልብ ይስጣችሁ አልካቸው?

Anonymous said...

ምን ነካህ እግዚኦ!
ይኽን መጽሐፍ ደጀ ሰላም ያወጣው ብዙዎች ስለጠየቁ ነው። ምናልባት አንተ አብዛኛውን መልእክት የምታገኘው ከደጀ-ሰላም ብቻ ይሆናል እንጂ ኢትዮጵያ ውስጥ አንዱ መጽሐፍ እስከ ሠላሳ ብር እየተሸጠ መሆኑን አልሰማህ ከሆነ ዛሬ ስማ። ገበያ ላይ የወጣ ጸሑፍና የአደባባይ ምስጢር የሆነውን ነገር ደጀ-ሰላም ሸፈነውም ገለጠውም ከመነበብ እና ሰው ጆሮ ከመድረስ የሚያግደው የለም። አንተስ የዋሁ ሰምተህ ቆሸሽኩ እያልክ ነው፤ ሠርተው ያልቆሸሹ የመሰላቸው ሰዎች ስላሉ ሥራቸውን እነርሱ እንዲያነቡት እና እንደተነቃባቸው እንዲያውቁት ተጻፈ እንጂ እኔና አንተ አውቀን እንድንቆስልበት አይመስለኝም። ሌባ እድሜ ልኩን እየቀናው ሲሰርቅ ቢኖር ያጠፋ አይመስለውም፤ ሌብነቱን ከሥራ ስለሚቆጥረው ይብስ ይጨማምርበታል እንጂ። ምናልባት ግን ሌቦች እየታሰሱ ተይዘው ለብዙ ዓመታት ከጉልበት ሥራ ጋር እንዲታሠሩ ተበይኖባቸዋል ቢባል ያልተያዘው ሌባ እንደተነቃበት በማወቅ መታቀብ ይጀምራል። የዛሬው ታሪክ የዛሬውን ግብራቸውን ብቻ አይደለም የነገረን፤ ከትናንት በስቲያ ጀምረው እየሠሩት ያለውን ነው እንጂ። በእርግጥ ጆሮአችን መልካም ቢሰማ ሁላችን በወደድን ነበር፤ አጋጣሚው ግን የረዳን አልመሰለኝም። ኢየሱስ ክርስቶስ ያቺን በለስ የረገማት እና እንድትደርቅ ያደረጋት በአንድ ቀን ሔዶ ፍሬ ስላጣባት ሳይሆን ተመላልሶ ሔዶ ያው ሆና ስላገኛት ነው። የዛሬው ጽሑፍ እንዲህ ቁማርተኞቹን ያጋለጠው የትናንት በስቲያው ግብር ትናንት የበለጠ አድጎ የትናንቱ ግብር ዛሬ ከወትሮው ጨምሮ ስለተገኘ ማንም ይሸፍነው ዘንድ ስላልተቻለው ነው። እንግዲህ እግዚኦ ደጀ ሰላሞችን "ደግሞ ቆይ ምን አስቸኮላችሁ። ሱባኤው እስኪያልቅ እንኳን አትጠብቁም ነበር? እግዚአብሔር ልብ ይስጣችሁ። እስኪ በዚህች የተቀደሰች የፆም ወራት እንዲህ አይነት ነገር እናንብብ።" ብለህ እንዳልካቸው አንተስ ምን ነበር ሱባዔው እስኪያልቅ ድረስ ማንበብህን ብትተው! ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ አንብበህ ልብ ይስጣችሁ አልካቸው?

Anonymous said...

Thanks a lot dejeselam . it will serve as data though it is not important. wonderful, you make zeruhun to lose thousends of birr.
Bertulign ,ewadachihualehu, amlak birtatun yistachihu

Dan said...

ይህ "Anonymous who said.ምን ነካህ እግዚኦ!" ብሎ የጻፈን ለማመስገን ነው::

እንዳንተ/ቺ ያሉ እየጻፉ ሌሎችን ቢያሳውቁ ጥሩ ነው::

This is in praise of the commenter "Anonymous who said...ምን ነካህ እግዚኦ!"

I am pleasantly surprised to learn there are people like you who write a good comment,that is sensible and logical.

I wish there are many like you who will write and educate those who make no sense and ramble in their comments.

Dereje said...

Hi Anonymous,
In the first place ,am not Dereje of Hawasa.am another Dereje of Wollo and now in Holland.
I commented above not to protect Ejigayehu or Begashaw. I don't know them and have not adequate info. to support or condemn this or that group.they might be wrong people beyond they mentioned on the article. but, but as a Christian such type of "critisim" is not acceptable.after all who are we to judje others personal life? if the writer critism was all about to protect our church,I agree with U. but he makes it too personal. look this words again please:-"Drunker, setegna adari,diwuy,lemtsam and so on
are these important to solve the problem in church?

DEREJE THE AWASSA said...

Let me react
Dear Anonymous I have observed the pros and cons of the content. Let me have at least the following arguments
1. on page 5 paragraph 2 it is written as if he was observed a vision with three animals after an Angel took him to the heaven………… Dear Anonymous, do you expect such type of joke from physiologically normal person?
2. page 24 paragraph 1 it is read as ‘W/ro Ejgayehu is the one whose livelihood is based to sell her reproductive organ’’ the Amharic Version ‘ yichi set mejemeriya hafrete sigawan yemiticherechir…..”. Whatever the sin might a person perform it is not the way to judge it. Normal person who has the fear of God will think about Merry the Magdolon.
3. page 26 paragraph 2 it discuss about the Embryo transfer and Flask Fetus technology. I am a biologist specialization in genetics (MSc- in genetics) and I can assure you the technical complexity of embryo transfer. I can tell you how much it is expensive even for American billionaires . And thus how could W/ro Ejigayehu afforded such type of technology ,first of all, being Ethiopian?
4. on this page there are two controversial ideas. The writer said she is menopause(too old to ovulate) . But as a professional to transplant an embryo there must be a fertile ova(egg). This idea by itself has fallacy and the writer is not have know how about this technology. (you can have deep knowledge of this technology just by browsing Google) He simply write this to abuse her moral. And this kind of word must be from abnormal person.
I can have many evidences for abnormality, but I think this is enough.

Dear Anonymous, we should do everything for the benefit of our mother church. Everyone in the church Knows how much these 4 Persons (Ejigayehu, Yared, Begashaw and Fantahun) are killing the church and exchange their religion for money. But this is not the way to teach them. Some fact( especially for Begashaw and Yared) are available. However the way he present and use words are not from normal and spiritual person. How could a normal person use such type of taboo words?
Long live Tewahido.

Anonymous said...

ሁሉን ነገር ስታደርጉና ስትጽፉ በጌታ ፈቃድ አደረጋችሁትን ?

Amlak Yiferdal said...

Lik'e minamin lik'e minamen eyalu heywot yelelachewen hulu kemet'rat chewaw ena yewahu me'emen 100 geze yeshalal. Gin betekerestian atasazenachihum? Enersu min godelebachew negeru... Musenawun ende gud yibelutal... 5 ena 10 dekaki santimoch yas'edkugnal bela yemtesetew enate sanitmua enersu kis megbatu... Gize gebir le Egziabher... Ye Amlak ferd k'in new... Me'emenan hoy be te'egest entebek...

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)