August 20, 2010

‹‹የሐውልቱ ስር ቁማርተኞች›› ፀሐፊ ዘሪሁን ሙላቱ ተያዘ፤ ለሥራ አስኪያጅ ፋንታሁን ሊደረግ የታሰበው ‹‹የማጽናኛ መዋጮ›› ታገደ


(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 20/2010፤ ነሐሴ 14/2002 ዓ.ም):- ሰሞኑን በእነ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ ከፍተኛ ክትትል ሲደረግበት የቆየው ‹‹የሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች›› ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ዘሪሁን ሙላቱ ዛሬ ከቀትር በኋላ በተለምዶ ኮልፌ - 18 ማዞርያ እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ቁጥራቸው በርከት ባሉ ሲቪል የለበሱ የደኅንነት ኀይሎች እና ዘግየት ብለው ወደ አካባቢው በደረሱ ሁለት ፖሊሶች ‹‹ለጥያቄ እንፈልግሃለን›› በሚል ተይዞ መወሰዱን የዐይን እማኖች ገለጹ:: ስውሩ ጸሐፊ ዛሬ ዘጠኝ ሰዓት ተይዞ ሜክሲኮ አካባቢ ወደሚገኝ አንድ ስፍራ የተወሰደው ዳንኤል ከሚባል ጓደኛው መኖርያ ቤት መሆኑን የዐይን ምስክሮቹ ተናግረው በጸሐፊው እና በጸጥታ ኀይሎቹ መካከል ከፍተኛ ጭቅጭቅ እንደ ነበር ትዕይንቱን በርቀት ሲከታተሉ የነበሩት እኒሁ የዐይን ምስክሮች አስረድተዋል፡፡
እነ ወ/ሮ እጅጋየሁ በሳምንቱ መጀመርያ በ‹‹ሊቀ ትጉሃን›› ዘሪሁን ሙላቱ ላይ በአራዳ ክፍለ ከተማ የመጀመርያ ደረጃ ፍ/ቤት ክስ ከመሠረቱ በኋላ ደብዛውን አጥፍቶ በቆየው ስውሩ ጸሐፊ ላይ ከፍተኛ ክትትል ሲያደርጉ መቆየታቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ 
ከዚህ ቀደም ሲል ከትናንት በስቲያ ተሲዓት በኋላ ከስውሩ ጸሐፊ አዲሱ ‹መጽሐፍ› ሥርጭት ጋራ በተገናኘ አክሊል ዳምጠው የተባለ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዝሙር ፒያሳ አካባቢ ለአጭር ጊዜ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውሎ እንደ ነበር የተዘገበ ሲሆን በኋላ ‹‹በስሕተት ነው›› በሚል ወዲያው መለቀቁ ተሰምቷል፡፡ ይኸው ደቀ መዝሙር ቀደም ሲል ከግንቦት 1997ቱ ምርጫ መነሣሣት ጋራ በተያያዘ ከኮሌጁ ታግደው ከነበሩት እና ባለፈው ዓመት ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ በአስተዳደሩ ከተፈቀደላቸው ዐሥራ አንድ ደቀ መዛሙርት አንዱ መሆኑ ተመልክቷል፡፡
በተያያዘ ዜና ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ በዛሬው ዕለት ‹‹በማጽናኛ መዋጮ›› በተሰበሰበ ገንዘብ ሊደረግ ታስቦ የነበረው ስጦታ ዜናው በደጀ ሰላም ድረ ገጽ ከተዘገበ በኋላ በራሳቸው በሥራ አስኪያጁ ደብዳቤ እንዲቆም ትእዛዝ መተላለፉን ለመረዳት ተችሏል፡፡ በቁጥራቸው ስድሳ ያህል ይሆናሉ የተባሉት የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጸሐፊዎች ሊያደርጉት አስበውት የነበረውን ይህንኑ ‹‹የማጽናኛ መዋጮ›› ሥራ አስኪያጁ፣ ‹‹ማንኛውም በስሜ የሚደረግ የገንዘብ ማሰባሰብ በአስቸኳይ እንዲቆም›› በሚል ደብዳቤ ማገዳቸውን የሀገረ ስብከቱ ምንጮች አስረድተዋል፡፡
ጸሐፊዎቹ በተጠቀሰው አኳኋን ተቆርቋሪነታቸውን ሊያሳዩ ያቀዱት ከሚበዙት የሀገረ ስብከቱ አድባራት እና ገዳማት አስተዳዳሪዎች በተቃራኒ ከሥራ አስኪያጁ ጋራ በመሠረቱት በጥቅም ላይ የተመሠረተ ልዩ ግንኙነት ምክንያት እንደ ሆነ ተጠቁሟል፡፡ ይኸውም ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ ጸሐፊዎቹን፣ የጸሐፊዎቹን ዘመድ አዝማድ እና ወዳጆች በተለያዩ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን በማስቀጠር እና አግባብነት የሌለው ዕድገት እና ዝውውር በመስጠት የሚገለጽ ሲሆን ጸሐፊዎቹ በበኩላቸው ደግሞ በዋናነት ለሥራ አስኪያጁ ውለታ በሚያበረክቱላቸው በዐሥር ሺሕ ብሮች የሚቆጠር እጅ መንሻ እና ሌሎች የዐይነት ስጦታዎች የሚፈጸም ነው፡፡ ሥራ አስኪያጁ ከአጥቢያ ሰበካ ጉባኤያት ጸሐፊዎች ጋራ በመሠረቱት ልዩ የጥቅም ግንኙነት ሳቢያ የተማረሩ የአጥቢያዎቹ አስተዳዳሪዎች አቤቱታቸውን ፓትርያሪኩ ዘንድ እስከ ማቅረብ ደርሰው እንደ ነበር እኒሁ የሀገረ ስብከቱ ምንጮች ጨምረው ገልጸዋል፡፡ ለሥራ አስኪያጁ ‹‹የማጽናኛ መዋጮ›› ለማበርከት ሰበብ ሆኖ የተጠቀሰው ‹‹የሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች›› በሚል ርእስ በስውሩ ጸሐፊ ‹‹ሊቀ ትጉሃን›› ዘሪሁን ሙላቱ በቅርቡ ‹‹የተጦመረው›› አሸማቃቂ ጽሑፍ ግላዊ ሕይወታቸውን፣ ማኅበራዊ ግንኙነታቸውን እና የሥራ ተነሣሽነታቸውን በእጅጉ በመጉዳቱ እንደ ሆነ ተገልጧል፡፡

7 comments:

Anonymous said...

ሊቀ ማእምራን የወሰዱት እርምጃ የሚያስመሰግን ነው።

እውነትን እውነት፣ ሐሰትን ሐሰት said...

ሊ.ማ. የሚነቀፉበት ሁሉ እንዳለ ሆኖ በዚህ አደነቅኳቸው። ፓትርያርኩስ እንደዚ ሃውልቱን ይቅርብኝ ቢሉ ኖሮ ...

Anonymous said...

Thank you Deje selam. I read the book " Yehawiltu Sir kumartegnoch".
Who ever wrote it, it is so shameful. Let alone Christian, pagan who had no moral ground wont write such a book.
I am not trying to cover those guys and that insane lady Ejigayehu had. But the way the book was written is so shameful and beyong acceptance

Anonymous said...

ለምን ጸሃፊውን እንደምትነቅፍት አልገባኝም።

እነዚያ ቤተክርስትያናችንን የሚያርክሱ ዋልጌ ግለሰቦችን በሚገባቸው ቋንቋ የሚገባቸውን ቢነግራቸው ምንድ ነው ችገሩ ? ሌባ ሌባ ይባላል እንጂ ሌላ ሊባል አይችልም።

ዘሪሁን የተናገረው እውነቱን ከሆነ ደግ አደረገ።እነዚያ ሰውንም እግዜሩንም የማይፈሩ ደፋሮችን ህዝብ እንዲውቃቸው ስላደረግ እኔ በበኩሌ አመሰግነዋለሁ።

ቤተክርስቲያንቱን እንዲህ የሚያዋርዱትን በማጋለጡ አመሰግነዋለሁ።

ማህበረ፡ክርስቲያን said...

anonymous እነዚያ ሰውንም እግዜሩንም፡ተብሎ አይፃፍም፡ሰውንም፡እግዚአብሔርንም፡ተብሎ፡እንጂ፡ አለበለዚያ፡በፈጣሪ፡ላይ፡መታበይ፡ይሆናል፡፡
አስተካክለህ፡ፃፍ፡አደራ፡፡

Anonymous said...

Yigermal: Zerihun, Begashaw, Ejigayehu... minamin minamin kiristyanoch aydelum kiristyan yesewun bedel yemiyawtawu besiratu lememarya endaydegem new enji lemebekel Aydelem... Ahun Ahun Memhir Zemedkunin Madnek Endemigeba Yitayegnal bzawu keqtle!!!
KAB DIFRET HATIYAT Yisewrena

wendmchu ke Adigrat Ethiopia

Anonymous said...

Yigermal: Zerihun, Begashaw, Ejigayehu... minamin minamin kiristyanoch aydelum kiristyan yesewun bedel yemiyawtawu besiratu lememarya endaydegem new enji lemebekel Aydelem... Ahun Ahun Memhir Zemedkunin Madnek Endemigeba Yitayegnal bzawu keqtle!!!
KAB DIFRET HATIYAT Yisewrena

wendmchu ke Adigrat Ethiopia

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)