August 18, 2010

ለሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ ‹‹የማጽናኛ መዋጮ›› ሊበረክትላቸው ነው

 •     መዋጮውን የአጥቢያ ሰበካ ጉባኤያት ጸሐፊዎች ያስተባብራሉ  • (ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 18/2010፤ ነሐሴ 12/2002 ዓ.ም):- በቁጥር ከስድሳ የማያንሱ እና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤያት ጸሐፊዎች እና አንዳንድ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች ለአወዛጋቢው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ ‹‹የማጽናኛ መዋጮ›› ሊያበረክቱ ማቀዳቸው ተሰማ፡፡ የሀገረ ስብከቱ ምንጮች ለደጀ ሰላም ያደረሱት መረጃ እንደሚጠቁመው፣ ‹‹የማጽናኛውን መዋጮ›› ለማስፈጸም በዋናነት እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ጸሐፊዎች እና አንዳንድ አስተዳዳሪዎች ሲሆኑ ማጽናኛው የሚከናወነው ጸሐፊዎቹ ባሰባሰቡት የገንዘብ አስተዋፅኦ ነው፡፡
   እንደ ምንጮቹ ገለጻ እስከ አሁን ድረስ ሥራ አስኪያጁ በግላዊ እና ማኅበራዊ ኑሯቸው ከደረሰባቸው የሞራል ጉዳት ለማጽናናት ታስቦ እየተደረገ ያለው የገንዘብ አስተዋፅኦ መጠኑ 30‚000 ብር ገደማ መድረሱ የተመለከተ ሲሆን ከነገ በስቲያ ዓርብ ለሥራ አስኪያጁ እንደሚበረክትላቸው ለመረዳት ተችሏል፡፡ ሰሞኑን የሐውልት ሥራውን የሚቃወም ጽሑፍ አዘጋጅተው በመንበረ ፓትርያሪክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ዐጸድ ዙሪያ ሲለጥፉ በመገኘታቸው ብቻ ‹‹የሕዝብን ሰላም ማደፍረስ›› በሚል በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለው ከአራት ቀናት እስር በኋላ የተለቀቁትን የድጓውን ሊቅ ሊቀ መዘምራን መንግሥቱ ገብረ አብን  ወዳጆቻቸው ‹‹የመንግሥቱ ማኒፌስቶ›› ያሉላቸውን የተቃውሞ መግለጫ ይዘት በትክክል ለማወቅ ባይቻልም ዐቃቤ ሕግ ድርጊቱ ‹‹የሕዝብን ሰላም ማደፍረስ ነው›› በሚል ባለፈው ዓርብ ዕለት ክስ መሥርቶባቸው እንደ ነበር ተሰምቷል፤ ይኹንና ወዲያው ከክሱ በነጻ ተሰናብተዋል፡፡ ታዛቢዎቹ ሁኔታውን እነ ሊቀ ኅሩያን ያሬድ ለሐውልት ሥራው ተቃዋሚዎች ሊኖራቸው ከሚችለው አጋርነት ጋራ ያገናኙታል፡፡ ሊቀ መዘምራን መንግሥቱ ከ1960 ዓ.ም ጀምሮ በትግራይ ሽሬ እና መቐለ ወንበር ዘርግተው ሲያስተምሩ የቆዩ አንጋፋ ምሁር የነበሩ ሲሆኑ በ1988 ዓ.ም በሲኖዶሱ ትእዛዝ ከተዘጋጀ በኋላ የትምህርተ ሃይማኖት ሕጸጽ እንዳለበት ተገልጾ የነበረውን መጽሐፍ እና በሀገረ ስብከቱ ይታይ የነበረውን አስተዳደራዊ በደል በመቃወም ምእመኑን ለሰላማዊ ሰልፍ እስከ ማስተባበር የደረሰ ተደማጭነት ነበራቸው፡፡ በመ/ፓ/ቅ/ቅ/ ማርያም ገዳም የዝማሬ መዋስዕት እና የአቋቋሙ መምህር ሆነው ሲያገልግሉ የቆዩት ሊቀ መዘምራን መንግሥቱ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት የዜማ መምህር ሆነው በመሥራት ላይ ይገኛሉ፡፡

  14 comments:

  Anonymous said...

  በዚች ቤተ ክርስቲያን ስንቱ ብልጣብልጥ ሌቦች ተደራጅተውባታል እንዴት ያለ ዘመን ነው እናንተ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጨ የሚስለመው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እና በየአጥቢያው አይን ያወጣ ሙስና እያስፋፋ የቤተ ክርስቲያኒቱን ንብረት ስለዘረፈ ነው ወይ በጣም ይገርማል
  እንተ ደጀሰላሞች ስለእውነተኛዋ ተዋህድ ሃይማኖታችን እና ስለሀቅ ብላችሁ ስለምትጽፉልን ሁሉ ላመሰግናችው እወዳለሁ

  Anonymous said...

  ውድ ደጀ-ሰላማውያን በሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ላይ የቀረበው ክስ ግነት እንዳይኖረው ሰጋሁ።ሰውን ስለጠላነው ብቻ ያለ የሌለ ጥፋቱን ባንደርትበት።እርሳቸውን ለመንቀፍ በገሃድ እየፈፀሟቸው ያሉት ጥፋቶች ከበቂ በላይ ናቸው።እኔ እስከ ማውቀው ሌላው ቢቀር የሚያሳዝን የትዳር ህይወታቸው(ባለቤታቸውን በሚያሳዝን ሁኔታ በሞት ተነጥቀዋል) እና የት/ት ችሎታቸው በአደባባይ የሚያስነቅፋቸው አይመስለኝም።

  Dan said...

  We have to start to PRACTICE NONVIOLENT RESISTANCE.

  Do not salute or exchange peace with these wicked with the appearance of religiousness and righteousness, but are denying power of the LORD.

  We should all AVOID THESE people. DON’T EVEN TOUCH THE CROSS THEY CARY WITH THEM.

  Do not PARTAKE the Sacrament from these corrupt deacons, priests and bishop.

  Do not acknowledge them at all, including aba paulos, and all those who are operating with them to destroy our church.

  Remember the 11 or so bishops and archbishops who blessed the idol statue of aba paulos?

  Do you think these people have the power of the Holly Spirit?

  2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ
  ምዕራፍ 3
  1 ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ።
  2 ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፥ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥
  3 ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥
  4 ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፤
  5 የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ።
  6-7 ወደ ቤቶች ሾልከው እየገቡ፥ ኃጢአታቸው የተከመረባቸውን በልዩ ልዩ ምኞትንም የሚወሰዱትን ሁልጊዜም እየተማሩ እውነትን ወደ ማወቅ ሊደርሱ ከቶ የማይችሉትን ሞኞችን ሴቶች የሚማርኩ፥ ከእነዚህ ዘንድ ናቸውና።
  8 ኢያኔስና ኢያንበሬስም ሙሴን እንደ ተቃወሙት፥ እንዲሁ እነዚህ ደግሞ አእምሮአቸው የጠፋባቸው ስለ እምነትም የተጣሉ ሰዎች ሆነው፥ እውነትን ይቃወማሉ።
  9 ዳሩ ግን የእነዚያ ሞኝነት ደግሞ ግልጥ እንደ ሆነ፥ ሞኝነታቸው ለሁሉ ይገለጣልና ከፊት ይልቅ አይቀናላቸውም።
  10 አንተ ግን ትምህርቴንና አካሄዴን አሳቤንም እምነቴንም ትዕግሥቴንም ፍቅሬንም መጽናቴንም ስደቴንም መከራዬንም ተከተልህ፤
  11 በአንጾኪያና በኢቆንዮን በልስጥራንም የሆነብኝን የታገሥሁትንም ስደት ታውቃለህ፤ ጌታም ከሁሉ አዳነኝ።
  12 በእውነትም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ።
  13 ነገር ግን ክፉዎች ሰዎችና አታላዮች፥ እያሳቱና እየሳቱ፥ በክፋት እየባሱ ይሄዳሉ።
  14 አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር፥ ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና፤
  15 ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል።
  16-17 የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።
  የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ።

  We should not wait until they get rotten and drop like flies. Act NOW.

  ዝም ብዬ አላነብም said...

  ይሄ "መጽሀፍ" ባለፈው እንደጻፋችሁት ገንዘብ ማግኛ ግሳንግስ ሳይሆን አይቀርም። ባለቤታቸው ከአመታት በፊት በአሳዛኝ ሁኔታ እንዳረፈችባቸው ስለማውቅ በትዳራቸው ላይ ፈጸሙ የተባሉትን ወንጀል ባነብ ደስ ይለኝ ነበር። በትምህርትም ምናልባት ማትሪክ አልተሳካላቸው ይሆናል እንጂ (አላውቅም) በቅድስት ስላሴ ኮሌጅም ሆነ በውጪ የነበራቸውን ውጤት የሚያውቅ ያውቀዋል!!!

  ሰውን በክፉ ምግባሩ መምከርና መገሰጽ የሚያስፈልገውን ያህል እንዲሁ ገንዘብ ለመሰብሰብ ግን የሆነ ያልሆነውን መዘላበድ የከፋ በደል ነው።

  ለሁላችንም ልቡና ይስጠን

  Tazabiw said...

  Selam DS Editor and visitors: How is 'tsome filseta'?
  Thank you DS for bringing us news on our Church...

  But after reading the article on ''LM Fantahun", I agree with the second anony.. comment writer.
  I am not crazy about the ppl around Abba Pawlos and his office, they are not the kind of people that we need... But First, the article is a bit harsh, brash and not spiritually sensitive... Eventhough the guy could be accused of many things (we have heard so many), unless we have the facts to back up our accusations, let us not be harsh to demolish the man (let the person do it himself), like others in the 'liberal' media. They don't care who they hurt as long us they can sell some papers. But you, DS Editor, should stay objective and report only the facts, not the 'gossips'. You are expected to be the conservative (objective and standing for the truth) media. Otherwise you could offend more of your readers and lose them. I don't want DS to become a site for church gossip. That is my observation.

  I hope you understand my concern and make changes and be objective in your future reports.

  God bless His Church and the true followers,

  Melkam tsome filseta,

  Tazabiw from AD

  Tesfa said...

  Dear DS,

  I apprecaite your effort to provide timely information. But I believe you need to be careful about the credibility of the information you are writting. For instance some of the info written about Leqemaemran Fantahun is really false. You do not have to write everything what others criticize, because every body has their own objective for writting something. Let me give an eyewitness about LM Fantahun. I know him for two years when I was in Vienna and he was my soul father for two years. His wife died unexpectedly due to health complications. He was serving the church in Vienna with Committment. He was not sworn to be a catholic priest. Not only him but also two other fathers have got the catholic scholarship. We even used and still are using the catholic church for Sunday services. This does not mean that he is sworn to be a catholic priest. Or the writer has to prove his claims with detailed and factual evidence. The other thing I know about him was his effort to establish a working system when he was the dean of Saint Paul college for one year. His effort was appreciated by many at that time. Actually I do not have any contact with him after he became the manager of Addis Ababa Hagere sibket. This is because I am not living in Ethiopia. To make it clear I am not saying you do not have to write about any body but you need to be careful not to be a media to promote the objective of others by even quoting them. Otherwise it will lower the quality and credibility of DS.

  Tesfa said...

  Dear DS,

  I apprecaite your effort to provide timely information. But I believe you need to be careful about the credibility of the information you are writting. For instance some of the info written about Leqemaemran Fantahun is really false. You do not have to write everything what others criticize, because every body has their own objective for writting something. Let me give an eyewitness about LM Fantahun. I know him for two years when I was in Vienna and he was my soul father for two years. His wife died unexpectedly due to health complications. He was serving the church in Vienna with Committment. He was not sworn to be a catholic priest. Not only him but also two other fathers have got the catholic scholarship. We even used and still are using the catholic church for Sunday services. This does not mean that he is sworn to be a catholic priest. Or the writer has to prove his claims with detailed and factual evidence. The claim that he was a lazy student seems false too. What I know is after he finished his masters he was given another scholarship by his professor to continue his PhD. He studied his masters in German language which was really difficult. I have seen his master thesis and his grade results. He finished his masters by great distinction with only A and B grades. The other thing I know about him was his effort to establish a working system when he was the dean of Saint Paul college for one year. His effort was appreciated by many at that time. Actually I do not have any contact with him after he became the manager of Addis Ababa Hagere sibket. This is because I am not living in Ethiopia. To make it clear I am not saying you do not have to write about any body but you need to be careful not to be a media to promote the objective of others by even quoting them. Otherwise it will lower the quality and credibility of DS.

  Let us stand with the truth not with those who seem to write our feelings.

  Thank you

  Dan said...

  Mr. Tesfa said...
  You said " Let me give an eyewitness about LM Fantahun. I know him for two years when I was in Vienna and he was my soul father for two years"

  And you continued..

  " Actually I do not have any contact with him after he became the manager of Addis Ababa Hagere sibket. This is because I am not living in Ethiopia. ..... you need to be careful not to be a media .... Otherwise it will lower the quality and credibility of DS."

  Why should anyone believe what you write?

  Everyone should have access to information and then make an informed judgment.

  By the way what do you mean by "he was my soul father for two years"?

  "የነፍስ አባት" ማለትህ ነው? or Confessor አናዛዠ?

  የነፍሳችን አባት አምላካችን እግዚአብሔር ብቻ ነው:

  In Orthodox theology the confession is not made to the priest, but to Christ, and the priest stands only as witness and guide.

  Every christian, including a Patriarch, bishop, priest, deacon, all christians confess to Christ, and with a priest ካህን (ቄስ ወይም ጳጳስ) standing as a witness.

  ሕዝባችንን በድንቁርና አስረውት ክርስትና መሠረቱን አናግተው ይኸው አዘቅት ውስጥ ወድቀናል::

  Anonymous said...

  ende... enezih menafqan tehadsowoch simachewun eyeqeyayeru yadenabirunal ende Deje selamoch:: Sineqabachew teqorquari meslew "Nisiha abat ayasfeligim" malet jemeru? Huwey guuuuuuud?

  Cher were yaseman!

  Anonymous said...

  ሊቀ ማእምራን ፋንታሁንን አስመልክቶ ስለተዘጋጀው መዋጮ ስሰማ በእጅጉ ነው የተገረምኩት ይህ መዋጮ ስለተፈጠሩት ነገሮች በምንም መልኩ ማካካሻ ሊሆን አይችልም ።
  ፋንታሁን ሁለት ጥሩ ነገሮች አሉት የመጀመርያው መናፍቅ አለመሆኑ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ጥሩ የትምህርት ደረጃና አንደበተ ርቱዕ መሆኑ ነው። ነገር ግን እነዚህ ብቻ አንድን ሰው ጥሩ ሊያስብሉት ባይችሉም ይህን ታልቅ እድል ተጠቅሞ አዲሰ አበባ ሀገረ ስብከትን በዘመናዊ አሰራር ሊለውጠው የሚችልበትን እድል አግኝቶ እንደነበር ግን መጠቆም እፈልጋለሁ። ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ለምንድን ነው ቀደም ሲል ለቤተ ክርስቲያን የነበረውን መቆርቆር ትቶ በዚህ አይንት የተጨማለቀና ለእርሱም ሆነ ለቤተክርስቲያኑ አሳዛኝ በሆነ ጉዞ ውስጥ ሊገባ የቻለው ?ብለን ብንጠይቅ የተወሰኑ መላ ምቶችን ልንጠቅስ እንችል ይሆናል።
  1 ሲኖዶሱ ሹመቱን በጊዛዊ ሀላፊነት ስለነበር የሰጠው በዚህ የቆይታው ወቅት በገንዘብ ደርጅቶና ተጠቅሞ እንዲለቅ በሚጎተጉቱት ሰዎች ግፊት በተለይም አቶ ያሬድ ክበደውና በነ ቀሲስ ሽታ የቀጨኔ ጸሀፊ ብሎም በነቀሲስ ክብሩ የእግዚአብሄር አብ አለቃ
  አማካኝነት ዓይን ወዳወጣ የሙስና ተግባር እንዲገባ አድርጎታል።
  2 አቡነ ጳውሎስ ባለቸው ከፍተኛ የገንዘብ ፍላጎትና በየግዜው ይህን አድርግ ይህን አታድርግ እያሉ በሚፈጥሩበት ተጽእኖ ውስጥ በመውደቁ እርሳቸው ትልቁ ለቤተ ክረስቲያን የማያዘኑ ከሆነ እኔን ምን ገዶኝ የሚለው መንፈስ ተጸናውቶት ሀገረስብከቱን ለምዝበራ እንዲዳረግ አድርጎታል።
  3 ሌላኛው ምክንያት ደግሞ የሚውላቸው ሰዎቸ በተለይም የድራፍት ቡዱኑ የፈጠረበት ተጽእኖ የነበረውን መልካም ነገሮች ሁሉ እንዲያጣ አድርጎታል።
  ዛሬም በየመጽሀፉ ለመሰደቡ ትልቁ ምክንያት የድራፍት ቡዱኑ መሪ ያሬደ ክበደው እንዲገብርለትና እንዲሰራ የሚያዘውን ነገር ለመፈጸም ማንገራገሩ ነው። በተለይም ያለምንም ችሎታውና ልምዱ በአራዳ ጊዮርጊሰ ተመድቦ የነበረው ቄስ በቀለንዘውዴን በመደገፍ ያሬድ እና አቶ ዳዊት የተባለ የኦሮምያ ተወላጅና ኦፒድዮ ነኝ በማለት የቤተ ክህነቱን ገቢ የሚያመሰው ሰው ትናንት በአቡነ ሳሙኤል ላይ የጳጳሱ ቅሌት
  የሚለውን መጽሀፍ አሳትመው እንደበተኑት ዛሬም ለፋንታሁን ይህንኑ ጽዋ እንዲጠጣ አድርገውታል ።
  4 የጉቦ አቀባባይ ደላሎች በሚያቀርቡለት ማስጎምጀት ምክንያት መስመሩን ሊስት ችላል ። ጉቦ በማቀበልና በማስቀበል በእነ ሊቀ ካህናት ሀይለስላሴ፤በነ አለቃ መኮንን ፤ በነ ዮሀንሰ ዋለ ዘመን ጀምሮ ከፍተኛ ልምደ ያላቸው እነ ቀሲስ ሽታ የቀጨኔ ጸሀፊ እና ሩፋኤል የማነ ፤ መሀሪ አድማሱና የማነ ዘመንፈስቅዱስ መሪነት ሳይለፋ የሚቀርበለትን የ አስር ፤ አሰር ሺ ብር ስጦታ እንቢ ለማለት ባለመቻሉ ለዚህ ችግር ሊዳረገ ቸሏል። ስለዚህ የአሁኑ መዋጮ ሊያስደንቀን አይገባም። በተለይም አቡነ ሳሙኤልን ከመንግስት ሰዎች ተገቢውን ሁሉ ድጋፍ አግኝቻለሁ እያለ በምክክርና በሰላም ሊያልቀ የሚችሉ ነገሮችን ሁሉ በማክበድ ሲያወሳስበ የነበረውን በሀላ አቡነ ሳሙኤልን ክዶ ትግሉ ሳያል ከፓትርያሪኩ የተቀላቀለው መርጌታ ሀይለ ማርያም አሁን የልደታ ጸሀፊ ነው አሁን ደግሞ ዲያቆን የማነህን አስነስቶ ቦሌ መድሀኔ አለምን ለመያዝ እንዲመቸውየመዋጭ ስራ ለይ ቢጠመድ የሚያስደንቅ አደለም ነገር ግን ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ያለውን ችሎታ እንዲጠቀም ከዚህ አሰራር የሚወጣበትን መንገድ ቢያፈላልግ ለቤተ ክርስቲያንጠቃሚ ሰው መሆኑን ልመሰክር እወዳለሁ።

  Belay said...

  የዚሀ መፅሓፍ በኢንተርኔት መውጣት ኅጋዊነቱን ባላቅም እጅግ እየፈለግሁት ስለነበረ ደጀሰላም ላይ ሳገኘው በጉጉት ወድያው አነበብኩት:: ደጀሰ. አመሰግናለሁ!
  ምንም እንኳን በአሁኑ ሰዓት ቤተክህነት ከላይ እሰከታች ቤተሙስና ቢባል ምንም የሚያስገርም ባይሆንም መፅሓፉ ላይ ለተጠቀሱት እጅግ አሳፋሪ ምግባሮችና ድርጊቶች በማስረጃ ስላልተደገፈ አጠራጣሪነቱ አይቀሬ ነው:: ሆኖም ግን የተጠቀሱት ግለሰቦች ከሙስና ነፃ ናቸው ብዬ አላምንም:: ከላይ ዋናው ካልተስተካከለ ከታች ያለው እነዴት ጤነኛ ሊሆን ይችላል? አበው ሲመስሉ የአሣ ግማቱ ካናቱ አይደል የሚሉ! ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአዲሱ አመት ለቤተክርስቲያናችን ፍፁም ሰላምን አንድነትን ለሀገራችን ፍርኃ እግዚአብሔር የተሞላ መንግስትን ይስጥልን! አሜን!

  Yenoah Merkeb said...

  በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ አሜን፡፡
  ለመናፍቅDan እናንተ እኮ መናፍቃን እንደሆናችሁ በግልፅ ይታወቃል፡፡ ስለዚህ ለምንድነው አይታወቅብንም እያላችሁ እንደ እርጎ ዝንብ በሰው ጉዳይ ጥልቅ የምትሉት? በእርግጥ ለስንዴና ለዘይት ስትሉ ተዋሕዶን ካዳችሁ እንጂ ከልባችሁ እንዳልሆነ እናውቃለን፡፡ እኛ ኦርቶዶክሳውያን እኮ ከቆጫችሁ ቤታችሁ ከናፈቃችሁ እና ተቆርቋሪ ነን ካላችሁ እጃችንን ዘርግተን እንቀበላችኋለን፡፡ ለምን ቄስ ዳቆን እያላችሁ ታቃልላላችሁ? ቄስና ዳቆን እኮ እንደናንተ ቃሉን አዛብተው በአዳራሽ ውስጥ አያነበንቡም፡፡ የሰለሞን ጥበብ የተፃፈበትን የግዕዝ ቋንቋ አሁን የአለም ሐያላን የሰለሞንን ሚስጥር ለማወቅ የሚማሩትን ግዕዝ በሚገባ አጢነውና በስንት ነገር ተፈትነው ነው እንጂ እንደናንተ በስሙ ባልታነፀ አዳራሽ ውስጥ ዝም ብለው በመለፍለፍ አይደለም፡፡ አታውቅም እንጂ አንተ በሰላም የምትኖረው በመላዕክትና በቅዱሳን ፀሎትና ምልጃ ነው፡፡ ለሚያጠፋው ሰው ዋጋ ከፋዩ ፈጣሪ ነው፡፡ ደግሞ እኛ የጉዳዩ ባለቤት ኦርቶዶክሳውያን እያለን እናንተ መናፍቃኖች ሳንደርስባችሁ አይታወቅብንም እያላችሁ ሐይማኖታችንን እና ዲያቆን ቄስ እያላችሁ መሳደባችሁን ብታቆሙ መልካም ነው፡፡

  ቸሩ አምላካችን አስተዋይ ልቦና ይስጠን፡፡ አሜን!!
  መርከቤ ንጉሴ
  ከአዲስ አበባ

  Blog Archive

  የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

  ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)