August 5, 2010

የብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ መኪና በድንጋይ ተደበደበ፤ በሰዎች ላይ ምንም አደጋ አለመድረሱ ታወቀ

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 4/2010):- ከአገልግሎት በመመለስ ላይ በነበሩት በጅማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ መኪና ላይ በተሰነዘረ የድንጋይ ውርወራ የመኪናቸው መስተዋት ሲረግፍ በእርሳቸውም ሆነ መኪናው ውስጥ በነበሩት በሌሎች ሰዎች ላይ ምንም አደጋ አለመድረሱ ታወቀ።

አደጋው የደረሰው ብፁዕነታቸው ሰኞ (26/11/2002) ከቀኑ 10፡00 ላይ ጦላይ ኪዳነ ምሕረት በነበረ ጉባኤ ላይ ቡራኬ ሰጥተው ወደ ጅማ ሲመለሱ መሆኑን እማኞች ገልፀዋል።
ከጅማ አዲስ አበባ መስመር  ኦሞ ናዳ ወረዳ በደነባ እና አሰንዳቦ መካከል በምትገኝ ቦታ ላይ በተደራጀ ሁኔታ የብፁዕነታቸው መኪና ላይ አደጋ የጣሉት ሰዎች ከድንጋይ ውርወራ ባለፈ ሌላ ዓላማ ይኑራቸው አይኑራቸው ለጊዜው የታወቀ ነገር ባይኖርም ጉዳዩ ግን ለጅማ ፖሊስ ሪፖርት እንደተደረገ ተነግሯል።

በጅማ ከተማ የሚገኘው ሕዝበ ክርስቲያን ማክስኞ ከ8፡00-12፡00 ሰዓት ውይይት አድርጓል የተባለ ሲሆን ጉዳዩ በ1999 ዓ.ም በአካባቢው ከተፈጠረው የክርስቲያኖች ጭፍጨፋ አንጻር በቀላል እንዳልታየ ታውቋል፡፡

5 comments:

አግናጢዎስ ዘጋስጫ said...

ማን ከማን ያንሳል

ሁለት ሃውልቶች ቆመው ከአደባባይ
ውይይት ጀመሩ ስለ ሃገር ጉዳይ
እኔ አባ ጴጥሮስ ነኝ ከዚህ የቆምኩት
አሉና ጀመሩ አንዱ ትልቅ አባት
ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረራት ጊዜ
ትዕቢት ተጠናውቶት የክህደት አባዜ
ፋሽስቱ ቢሞክር በገንዘብ ሊገዛኝ
ከተዋህዶ እምነት ከኢትዮጵያ ሊለየኝ
እንኳን ህዝቧንና መሬቷን ገዘትኳት
እምቢ አሻፈረኝ አለገዛም አልኩት
ግና ፋሽስቱ አሻፈረኝ ብሎ
ሊገድለኝ ቢመጣ መትረየስ ደግኖ
ድፍረት ባይኖረኝም ራሴን ለመስጠት
ጽናት እንድሰጠኝ አምላኬን ለመንኩት
እርሱም ፈጥኖ ደርሶ አፀናኝ በእምነቴ
ራሴን ሰውቼ ያው ና ሐውልቴ
ብለው ሲጨርሱ ንግግራቸውን
ሌላው ሃውልት አለ የሚከተለውን
እኔ ደግም እንዳንተ ቁምነገር ባልሰራም
ከዚህ መገተሬ አገር ባያኮራም
ታሪክ የማይረሳው ሥራ ሰርቻለሁ
ብዙ ተሃድሶ ከሃዲ አፍርቻለሁ
እናም ሊዘክሩት ይህን ታላቅ ዝና
በደጋፊዎቼ ቆምኩኝ ትናንትና
ለእኔ ሃፍረት ቢሆን ህዝብም ባይደግፈው
ማን ከማን ያንሳል መቆሜ ግድ ነው
ሰው በሞት ሳይለይ ሳለ በህይወቱ
እንግዳ ቢሆንም ሐውልት ማሰራቱ
ለእኔ ግን ደስታ ነው ሐውልት ማሰራቴ
አፈር ሳይጫነኝ ሳለሁ በህይወቴ
ስለዚህ ልዝናና በዚች ምድር ሳለሁ
በሰማይ ያለውን እኔ ምን አውቃለሁ::

selamawi said...

እግዚአብሔር እንከን ከክፉ ነገር አባታችንን ሰወረልን //

Anonymous said...

Hmmmm.... Jimmana Ilubabor yalewu yeberede endayimeslachihu gobez. Betam kebabad maseltegnawoch tekeftewu course endemisetu beAyine ayichalehu.

Egnih abat degimo bedenb hizbekiristianun eyatsinanu silehone elama wust gebitewal. Enam kegonachewu enihun.

Lelawun Egziabher yimelisilinal.

Unknown said...

ምን ይባላል እግዚአብሔር ሁሉን ያውቀዋል ።

Unknown said...

የመገርም ነው ። ምስጢሩ ብዙ ነው።

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)