August 4, 2010

ሰበር ዜና፦ እርቀ ሰላሙ ሳይጀመር ተፈጸመ፣ ሳይታሰር ተበተነ

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 3/2010)፦ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአባቶች የሰላምና የዕርቅ ድርድር ሳይጀመር ተፈጸመ፣ ልዑካኑም ሳይወያዩ ተበተኑ።
ከትናንት በስቲያ ሰኞ ይጀመራል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ይህ “የሰላምና የእርቅ ጉባዔ” በተሸማጋዬቹ መካከል ማድረግ የፈለገውን ውይይት ማድረግ ሳይችል፣ ሁለቱን ልዑካን ፊት ለፊት ማገናኘት ሳይችል፣ በቅድመ ሁኔታ ላይ ብቻ ሲደራደር ቆይቶ እንዲሁ ተበትኗል። ይኸው ውይይት ውጤት እንደማያመጣ በታወቀ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ የአሜሪካው ወገን ቀድሞ ያዘጋጀው የሚመስለውን መግለጫ በ “ቋጠሮ” ድረ ገጽ  ላይ አውጥቶታል። ዝርዝሩን እንደደረሰን እናቀርባለን።
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

20 comments:

Anonymous said...

እባካችሁ ሽማግሌዎች የተፈጠረውን ንገሩን እውነቱን እንወቀው:: ብልጣ ብልጥ መነኮሳትን አጋልጡልን:: እውነቱ የሚጠራበትን ጊዜ እውነቱን በመናገር እርዱት፣ለመገለጥ እንዲችል:: ሁለቱም ለተሃድሶው እኮ ሳይነጋገሩ የተስማሙ ናቸው:: ምናልባት ያልተስማሙት በጊዜ ሠሌዳው ነው እርሱም በጋራ ስላልጀመሩት ነው ይህንንም ያደረጉት ቀጣሪዎቻቸው ናቸው:: የስደተኞቹ የታወቀ በተለያየ መንገድ ራሳቸውም ሳይቀሩ የገለጡት ነው:: የአዲስአበባው ግንአዲሱ ተሃዲሶ ነው:: የፓትርያርኩ ተከታዮች በማስታዎሻዎቻቸው የሚለዋወጧቸው መረጃወች እየነገሩን ነው:: እና እነዚህን ላለመስማማት የተስማሙ ብልጦች ትተን የገጠመንን ቤተ ክርስቲያንንየማዳከም ሴራ ገለልተኛ የለ ባለኃውልቱ ፓትርያርክና ተከታዮቻቸው የለ፣ ስደተኛ የለ ተሃድሶ የለ ሁሉንም እንታገል ::

Anonymous said...

Agree with USA Delegates, the person who doesn't accept the 3rd and the 4th patriach shouldn't attend the meeting either he has to be confess or remove himself from attending the meeting. peace is not fake.

Anonymous said...

የዳንኤል እይታዎች የብርጭቆው ወይስ የምንጩ ውኃ ክፍል 2
አንዳንድ ጊዜኮ እኛ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አለን፤ ቤተ ክርስቲያን ግን ከእኛ ውስጥ ወጥታለች፤ እኛ በክርስትና ውስጥ ነን፤ ክርስትና ግን ከእኛ ውስጥ ወጥቷል፤እኛ በክህነቱ ልብስ ውስጥ ነን፤ ክህነቱ ግን ከእኛ ውስጥ ወጥቷል፤ እኛ በስብከቱ ቀሚስ ውስጥ ነን፤ ስብከቱ ግን ከውስጣችን ወጥቷል፡፡ እኛ በገዳም እንኖራለን፤ ገዳማዊ ሕይወት ግን በኛ ውስጥ የለም፡፡ ለአንዳንዶቻችን ጵጵስና ፕሮፌሽን ነው፤ ቅስና ፕሮፌሽን ነው፣ ሰባኪነት ፕሮፌሽን ነው፤ ምንኩስና ፕሮፌሽን ነው፤ዝማሬ ፕሮፌሽን ነው፣ እንደ ጥብቅና፣ እንደ ንግድ፣ እንደ ሕክምና፣ እንደ ጋዜጠኛነት፣ እንደ ምሕንድስና፣ የእንጀራ ማግኛ ሞያ፡፡ ታድያ እንዴት መንፈሳውያን መሆን ይቻላል?
በመጽሐፈ መነኮሳት እንደ ተጻፈው በቤተ መንግሥት ውስጥ ሆነው እንደ ቤተ ክህነት የሚኖሩ፣ በቤተ ክህነትም ሆነው እንደ ቤተ መንግሥት የሚኖሩ ነበሩ፤ አሉ፡፡ ይሁዳ በአካል ከክርስቶስ ጋር ነበር፤ ልቡ ግን ከነ ሊቀ ካህናት ቀያፋ ጋር ጌታን ለመስቀል ያድማል፤ ማርያም እንተ እፍረት በአካል ከአመንዝሮች ጋር ነበረች፤ ልቧ ግን ክርስቶስን ይፈልግ ነበርና ከእግዚአብሔር ጋር ነበር፡፡ ይሁዳም ልቡ ወዳለበት ሄደ፤ ማርያምም ልቧ ወደ ነበረበት መጣች፡፡ ለመሆኑ ከሁለቱ ሰዎች መንፈሳዊው ማን ነበር?
በአንድ ወቅት አንድ አባት የተናገሩትን እዚህ ላይ ማንሣት ያስፈልጋል፡፡ ለስብሰባ ወደ አንድ መንግሥታዊ ድርጅት ሄጄ ከባለሥልጣናት ጋር ተሰብስቤ ነበር፡፡ በስብሰባው መካከል አንደኛው ባለ ሥልጣን በግእዝ ሲጠቅስ ሰማሁት፤ ተገረምኩ፡፡ ስብሰባው ሲያበቃ ጠብቄ ያንን ሰው «አንተ የቤተ ክህነት ሰው ነህ እንዴ? ቅድም አንድ ነገር ስትናገር ሰምቼሃለሁ» አልኩት፡፡ ሰውዬውም «አዎ ነኝ፤ ምነው ገረመዎት እንዴ» አለኝ፡፡ «የቤተ ክህነት ሰው እንዲህ ባለ ሥፍራ ይኖራል ብዬ አልገምትም ነበር?» ብዬ መለስኩለት፡፡ እርሱም «አባቴ የቤተ ክህነት ሰውኮ በየቦታው አለ፡፡ የቤተ ክህነት ሰው የሌለው ቤተ ክህነት ውስጥ ብቻ ነው» አለኝ ብለው ነገሩን፡፡

Anonymous said...

weyi..gude...yenafeqenewenim sanagegn endihu mena qere?....yasazenale!

Anonymous said...

ተመስገን ሁሉም ለበጎነው
ሌላ በሽታ ሌጨመር ነበር እሰይ እሰይ ,,,,,,,,,መቼም ቤሆን
ከሱባኤ በፊት የተጀመረ አርቅ ምን እንደሜያጋጥመው የተማርን ይመስለኛ
ደግሰው አና ደግ ዘመን እስኪመጣ መጠበቅ ይሻለናል
ሁሉም ቢሆን ከነ አጀንዳቸው አንድቀን መጠራታቸው አይቀሬ ነው
ያኔ አንሄድም አይሉ ያኔ የነሱን አጀንዳ ማንም አያገላብጥላቸውም
በቻ ለኛ አድሜ ይስመን ፣ ሁሉንም እናየዋለን

Anonymous said...

+++
The so called negotiating fathers of the church in both sides are far away from discipline and innocence now a days than the lay people of the church and even the politicians. They have a goal to hurt their people and the church, otherwise they would subject themselves to prayer and isolation in the holy monastries. They play the life of controversy until they pass away. The fact is that they caused choas and mess in the church Dogma and cannon wherever they go.
What shall we do? We always hoped and prayed for good but they just play a joke!
Let us send our message to Almighy God! Yerahelin enba yetekeble Amklak Yisman!!!

Anonymous said...

aba pauwlos,aba merkorios,aba melkesedek,
Ebakachu Siltanachun begeza fekadachu Likeku Benante mikneyat haymanotachin tesedebe bakachu bakachu bakachu yesiltanen neger Kederg,Ena Kesadam Temaru.
yesiltan Edme Aystachu Amen!!!

Anonymous said...

ነገር ሁሉ ለበጎ ነው

መቼም እግዚአብሔር ይህችን ቤተ ክርስቲያን በአባቶች ፀሎት እየጠበቃት ስለምትንቀሳቀስ የአሁኑም ማለፉ የእርሱ የባለቤቱ
ፈቃድ ነው።

Anonymous said...

ለፓትርያርክ አባ ጳውሎስ ሐውልት ሊቆም መታሰቡን በመቃወም የቀረበ መግለጫ።

«እውነትን ዐውቀው በክፋታቸው በሚለውጡአት በዐመፀኛውና በኃጢአተኛው ሰው ሁሉ ላይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መቅሠፍት ከሰማይ ይመጣል። እግዚአብሔርን ማወቅ በእነሱ ዘንድ የተገለጠ ነውና፤ እግዚአብሔርም ገለጠባቸው። ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ታይቶ የማይታወቅ እግዚአብሔር የፈጠረውን ፍጥረት በማሰብ በመመርመር ይታወቃል፤ ከሃሊነቱ፥ የዘለዓለም ጌትነቱም እንዲህ ይታወቃል፤ መልስ የሚሰጡበት ምክንያት እንዳያገኙ። እግዚአብሔርን ሲያውቁት እንደ እግዚአብሔርነቱ አላመኑትም፤ አላመሰገኑትምና፤ ካዱት እንጂ፤ በገዛ ዐሳባቸው ረከሱ፤ ልቡናቸውም ባለማወቅ ተሸፈነ። እንራቀቃለን ሲሉ ደነቆሩ። የማይሞተውን የእግዚአብሔርን ክብር ለውጠዋልና፤ የሚሞት የሰውን መልክ አምሳያ አድርገዋልና፤ በእንስሳ አምሳያ፥ በአራዊት አምሳያ፥ በአዕዋፍ አምሳያ አድርገዋልና። ስለዚህም መልሶ ተዋቸው፤ በገዛ እጃቸው ራሳቸውን እንዲያረክሱ፤ ሰውነታቸውንም እንዲያጎሰቁሉ። የእግዚአብሔርንም አምላክነት ሐሰት አድርገዋታልና፤ ተዋርደውም ፍጥረቱን አምልከዋልና፤ ሁሉን የፈጠረውን ግን ተዉት፤ ይኸውም ለዘለዓለም የሚኖር የባሕርይ አምላክ ነው።» (ሮሜ፤ ፩፥ ፲፰ - ፳፭።)

የተወደዳችሁ ምእመናን!

በቅርቡ በመገናኛ ብዙኃን (አዲስ አድማስ ጋዜጣ፥ ሰኔ ፳፮ ቀን ፳፻፪ ዓ. ም.) የቀረበውን ለፓትርያርክ አባ ጳውሎስ በአዲስ አበባ ቦሌ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ሐውልት ሊቆም መታሰቡን በመግለጽ የቀረበውን ዜና በኀዘን አንብበናል። ይህ ሐሳብ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት፥ ሥርዓትና ባህል ውጪ በመሆኑ፤ በኢትዮጵያ አምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የምንቃመው መሆኑን እየገለጽን ክቡር አባታችን አለቃ አያሌው ታምሩ የዛሬ ፲፬ ዓመት በገናናው ጋዜጣ አማካይነት ያስተላለፉትን ሁለተኛ ቃለ ግዝት እንድታነቡ እንጋብዛለን።

ገናናው ጋዜጣ፤ ሐምሌ ፭ ቀን ፲፱፻፹፰ ዓ. ም.
አለቃ አያሌው ታምሩ ሁለተኛውን ቃለ ግዝታቸውን ሰጡ።

«አንበሳ አገሣ፤ የማይፈራ ማነው? ጌታ እግዚአብሔር ተናገረ፤ የማይደነግጥ፥ የማይታዘዝ፥ የማይፈራ፥ የማይናገር ማነው?»

ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምእመናን በሙሉ! በአሁኑ ጊዜ በኦርቶዶክሳዊው የሊቃውንት ጉባኤና በእምቢተኞች የቤተ ክርስቲያን መሪዎች መካከል በዚህ ዓመት በተለይም ከመጋቢት እስከ ዛሬ የሚደረገውን፥ በመደረግ ላይ ያለውን ሃይማኖታዊ ትግል በልዩ ልዩ መንገድ እንደ ተከታተላችሁ አምናለሁ።

አባቶቼ ካህናት፥ ወንድሞቼ፥ እኅቶቼ ምእመናንና ምእመናት! የሌኒን ጣዖት በአፍሪካ አንድነት ድርጅት አጠገብ፤ የሌኒን፥ የማርክስ፥ የኤንግልስ ጣዖታት ምስሎች በአብዮት ዐደባባይ፤ የልዩ ልዩ ወታደሮች ምስል በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አጠገብ በተሠራው ሐውልት ላይ፤ እንዲሁም በልዩ ልዩ ስፍራ ልዩ ልዩ ምስሎች ተሠይመው ማንም የአበባ ገጸ በረከት መሥዋዕት ሳይቀር ያቀርብላቸው በነበረበት፥ በየዐደባባዩ የደም መፍሰስ፥ የለቅሶ፥ የዋይታ ድምፅ ሲያስተጋባ በነበረበት በዚያ የ፲፯ ዓመት ትዝታ ማንም አባት ዐብሮአችሁ ያልነበረ ሲሆን በትግላችሁ ያልተለየሁ እግዚአብሔር የሾመላችሁ የወንጌል ሰባኪ ሐዋርያ እንደ ሆንኩ አምላኬም፥ እናንተም ምስክሮች ናችሁ።


ይሻላል ያሉት ኩል ዐይን አጠፋ ሆነና ይሆናሉ የተባሉ አባቶች በማንኛውም ጊዜ በዐደራ የተቀበሏትን ቤተ ክርስቲያንና ምእመናኖቿን በአምላካቸው ስም መጠበቅ ሲገባቸው ትናንትም ዛሬም የመንግሥት ደጋፊ ሆነው እያስቸገሩን ነው። ብዙ መናገር ይቻላል፤ ግን እታገሣለሁ። ሆኖም ቁም ነገሩን ማለፍ አልችልም። የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአበው ውግዘት ተጣሰ፤ የቤተ ክርስቲያን ክብር ተገሠሠ እያልን አቤቱታችንን እያሰማን መንግሥት በሃይማኖት አያገባኝም ብሎ እጁን አውጥቷል። አይጠይቀንም በማለት ይመስላል። የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎች በዕብሪት፥ በትዕቢት በበደል ላይ በደል ሲጨምሩ፥ ኦርቶዶክሳዊውን የሊቃውንት ጉባኤ ሊያፈርሱ ሲፈልጉ በጉልበታቸው በሥልጣናቸው ተጠቅመው የቤተ ክርስቲያኒቱን አባሎች ከሥራና ከደመወዝ ሲያባርሩ፥ ይህም አልበቃ ብሎአቸው በክስ ሲያጉላሉ፤ ይህን ሁሉ እየሰማ፥ እያወቀ ፍርድ ሊሰጥ፥ ዐመፀኞችን ሊቀጣ፥ ቤተ ክርስቲያንን ከደረሰባት በደል ነጻ ሊያወጣ የሚገባው ሲኖዶስ የግፍ ግፍ ሚያዝያ ፴ ቀን ፲፱፻፹፰ ዓመተ ምሕረት አጽድቆ ባወጀው፥ ሕገ ቤተ ክርስቲያን ሲል በጠራው የአምልኮ ጣዖት ሕግ ፓትርያርኩን በመንፈስ ቅዱስ ፈንታ በሲኖዶስ ሥልጣንና ተግባር አመራር ሰጪ፥ የሲኖዶሱን አባሎችም ለቤተ ክርስቲያን ተጠሪ መሆናቸው ቀርቶ ለፓትርያርኩ ተጠሪዎች በማድረግ በቤተ ክርስቲያን ላይ የአመልኮ ጣዖት ዐዋጅ ዐውጆአል።

ለዚህም ሐምሌ ፮ ቀን ፲፱፻፹፰ ዓመተ ምሕረት በዓሉን ለማክበር በመዘጋጀት ላይ ስለ ሆነ ይህ ስሕተት እንዲታረም በዓሉ ከመድረሱ በፊት ሕጉን ጳጳሳት ተሰብስበው ሚያዝያ ፴ ቀን ፲፱፻፹፰ ዓመተ ምሕረት አምልኮ ጣዖት ያወጁበትን፥ መንበረ ማርቆስን ነቅለው መንበረ ጣዖት የተከሉበትን ሕግ እንዲሽሩ፥ ወደ ጣዖትነት ያደጉትን ፓትርያርክም ከሥልጣን እንዲያነሡ በቃለ ግዝት ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፹፰ ዓመተ ምሕረት በነጻው ፕሬስ በኩል በመብሩክ ጋዜጣ በፈጣሪዬ ስም መልእክት ማስተላለፌ ይታወሳል። እነሱ ግን ምንም እርምጃ አልወሰዱም፤ ጥያቄዬንም አልተቀበሉም። እግዚአብሔር አምላክ ግን ቦታውን ለጣዖት አልሰጠም፤ መንበሩንም አልለቀቀም። የሚሰማው ቢያገኝ እየተናገረ፥ ምክርና ተግሣፅ እየሰጠ ነው።

በሥልጣናቸው ተደግፈው እግዚአብሔርንና ቤተ ክርስቲያንን የሚዋጉትና በመንፈስ ቅዱስ አንዳኝም በማለት ትግላቸውን የቀጠሉት አቡነ ገሪማ፥ እንዲሁም የፓትርያርኩ አጋፋሪ ብርሃኑ መኮንን ግን የአድባራትን፥ የገዳማትን አስተዳዳሪዎችንና ካህናትን በማስተባበር በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ሥላሴን መንግሥት ሽረው ጣዖት ሊያገለግሉ፥ በዓል ሊያከብሩ ፕሮግራም አውጥተዋል። ከልዩ ልዩ ጌጣጌጥ ጀምሮ እስከ ዊስኪ መጠጥ፥ ጮማ ቁርጥ ድረስ በብዙ ሺሕ የሚቆጠር የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ እየወጣ ድግስ እየተዘጋጀ ነው። ስለዚህ እነሱ ቢንቁኝ አልደነቅም። ቃሉ ደግሞ አይናቅም። በጠቅላላ ቤተ ክህነትና መሪዎቹ ለእግዚአብሔር አንታዘዝም ያሉ ስለ ሆነ ካህናትና ምእመናን ለዐመፅ እንዳትተባበሯቸው፥ በዓሉን እንዳታከብሩ፥ ድግሱንም እንዳትበሉ በቤተ ክርስቲያን አምላክ ስም፥ በኢትዮጵያ አምላክ ስም እጠይቃችኋለሁ። ሊቃነ ጳጳሳት፥ ኤጲስ ቆጶሳት በአምልኮ ጣዖት ስም ሚያዝያ ፴ ቀን ያወጃችሁትን ሕግ እንድሽሩ፥ የሠየማችኋቸውንም እንድታነሡ፥ በቤተ ክርስቲያንና በምእመናኖቿ ላይ የጫናችሁትን ቀንበር እንድታስወግዱ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እጠይቃችኋለሁ። እምቢ ብትሉ ግን በቃለ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ፥ በቃለ ሐዋርያቱ አሁንም ገዝቼአለሁ።

የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ አለቃ አያሌው ታምሩ ዘዲማ ጊዮርጊስ።

tesfa said...

why one riligious person can`t make forgivennes?
i do not understand about religious man.religious man is not spritual man.becoase the religious man can`t make forgivennes.that is the difference b/n religious man and spritual man.
don`t west your time on religious person.

zekre said...

yelebe mezegachte kelele menem bibal wtete aynorewm mekniatum yegeziabherkal yelebe mezegaget kesew new yemelas melse gen kegziabher new.yelale kegziabher melse lemagegnet lebene bthetena mazegagete yasfelegal.

Anonymous said...

you guys don't worry, as long as the current government in power don't expect any peace soon. peace is not likable in the current government.one think I agree before peace all ethiopian should be pray once a day for the holiy church to be unified. first pray ,then start talk. this is not politics. we know some people they don't like the unification the church specially those who live in ethiopia

Anonymous said...

First of all to label the discussion as negotiation is a misnomer. It is my understanding there is no negotiation when it comes to the truth. Be as it maybe Christian Ethiopians should praise God for opening the doors to rectify the problems that have plagued our church for almost two decade now. The latest discussion between the legal Synod in exile and the one in Ethiopia is a step in the right direction. The exiled Synod has shown great humility and unweaving commitment to truth and the church by attending this discussion even though they are ones who were victimized in the first place. More importantly it is a testament of their willingness to mend history and restore peace in our church whatever the personal sacrifices may be. However, they also have moral and spiritual responsibility to be on the side of truth. In doing so it is impossible to proceed with the discussion with a group that does not recognize the 3rd and 4th Patriarchs (Betsu Abune Tekelehaimanot and Betsu Abune Merkerios) as stated in the press release. This assertion is very pivotal and incomprehensible to anyone with a logical mind. This statement erases the 20 years of history of church including the ordination of the 4 clergy men that were sent from Ethiopia. In fact we should be outraged that the group from Ethiopia is not willing to retract such a damaging statement. To request this precondition by the exiled Synod is their moral obligation on behalf of the tens of millions of people they lead. To destroy the history of our church and the legacy of the deceased Betsu Abne Tekelehaimanot because they can not speak for themselves is despicable and shameful on many levels. However, we the people have to be the voice for the dead Betsu Abune Tekelehaimanot and history itself. More importantly we have to realize the problem in our church is not personal, but rather fundamental principles that are at the very core of our historic church. Last, but not least we should always strive to be on the side of truth and pray for both sides so that cooler heads, truth, our church can prevail.

TEWAHEDO said...

The person implicated in the press release of the exiled synod is Abuna Gerima. If this bishop insists in rejecting the patriarchy of both Abuna T/Haimanot and Abuna Merkorios he is also invalidating his own episcopate because he was ordained by Abuna T/Haimanot as a bishop in 1971 E.C. He is ignorant enough to overlook this fact.

Secondly, Abuna Gerima has borrowed this idea from the current Coptic Orthodox Church Pope. Though H. H. Pope Shenouda III is a spiritual father, when it comes to the controversy b/n his church and the Ethiopian Orthodox Church (for e.g. the case of Dare Sultan) he is very stubborn. His Synod was the first to reject the consecration of Abuna T/Haimanot. Even if Abuna T/Haimanot's consecration was illegal as it was done by the direct interference of the DERG regime, it was well known that Abuna Teweflos was assassinated shortly after the consecration of Patriarch T/Haimanot. Thus, one cannot give legitimacy to the illegal consecration of Abba Paulos for the sole reason that he officially unearthed the remains of Patriarch Teweflos and presided over his funeral. The Coptic Church rejected the patriarchy of both T/Haimanot and Merkorios wishfully hoping to regain its a century-and-half old primacy over the Ethiopian Church. To propagate this stand is to side with the Copts and damage the independence of our mother church (the Ethiopian Orthodox). Abuna Gerima reflected this poisonous Coptic stand to protect the illegal consecration of his flamboyant and immoral boss (Abba Paulos) without noticing that the stand invalidtes his own episcopal ordination.

But the crux of the matter is that, other than Patriarchs Basilios and Tewoflos, Abuna Merkorios is the only Patriarch who was LEGALLY consecrated - because he was ordained long after the assassination of Abuna Teweflos and the natural death of his immediate predecessor (Abuna T/Haimanot). Needless to say, after 3 years service, Abuna Merkorios was illegally deposed by the direct order of the WEYANE officials which was supported by some archbishops (their names are known to us) who selfishly thought would usurp the patriarchal throne. Bu the way, Abuna Melketsedek was the only arch-bishop who staunchly opposed from the VERY BEGINNING the dethronement of Patriarch Merkorios and the election of a new patriarch. That is why Abuna Melkesedek firmly stands for the truth as he did during that tumultuous period (1983-4 E.C.)

So what is the next likely step?

As long as the current oppressive regime is in power our divided Mother Church cannot be united. But after the downfall of this malicious regime, its hired puppet (Abba Paulos) will be rightly deposed (he probably will flee to overseas) and the legal Patriarch (Abuna Merkorios) will be RE-INSTATED.

In the coming season of FILSETA, let us all earnestly pray for the peace of our Mother Church.

Emuye said...

Yerasachew guday newu, dirom alamaregnem.

TEWAHEDO said...

ሳይነገር የታወቀ ሳይታለም የተፈታ።
ፆም እና ጸሎት፣ እርቅ እና ይቅርታ፣ ሰላም እና ፍቅር በአፍ ላይ ብቻ ሆነና ወደ ተግባር እንዲለወጥ ጥረት ሲደረግ መቀነቴ አደናቀፈኝ ለእኔ የሚስማማኝ እገሌ እንጂ ታሪኩን ከጥንት የማያውቀው ምን ያደርግልኛል? በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ስደተኛውን ሲኖዶስ ያልወቀሰ ብቻ ነው ተወካይ ሆኖ መቅረብ ያለበት እያላችሁ የአስታራቂዎችን ጊዜ እና የምእመናኑን ተስፋ እያጠፋችሁ መሆኑን ፍርድ የሚያውቅ እግዚአብሔር መልሱን እንደ ግብራችሁ ይሰጣችኋል። አሁን በእናንተ ውስጥስ ለድርድር ተወክላችሁ የቀረባችሁት በእጃችሁ እርም የሌላችሁ ንፁሐን ሆናችሁ ነው? ግንድ በዓይናችሁ እያለ ጉድፍ የምታጠሩ ሆናችሁ ተገኝታችኋል። ማነው በዚህ ዘመን በሃይማኖት ስትጫወቱ እያየ እና እናንተን የሚያህል ረባሽ በምድር ላይ መኖሩን እያወቀ አፉን ዘግቶ የተቀመጠ ሰው? በሕዝብ ለመቀለድ አንደኞች ናችሁ። ከሕዝብ ጋር ለመኖርና የይቅርታ ሰዎች ናቸው እንድትባሉ ደግሞ አስታራቂዎች ለሞከራችሁት ሙከራ ከልብ እናመሰግናለን ትላላችሁ። ንፁሕ ይመስል ንፁሓን ያናግሩን ስትሉ አትፈሩም? ከእናንተ አባባል እንደተረዳሁት እና ብልጣ ብልጥ አካሄዳችሁን አይቼ እንደተገነዘብኩት ባሕር ውስጥ ገብቶ ውኃ ሳይነካው የወጣ ሰው ብቻ ለድርድር ይቅረብ ነው የምትሉት። አሁን ይኼ ሁሉ ሁከት ስለ ክብራችሁ ስትሉ ነው እንጂ ስለሃይማኖት ቀናኢ ሆናችሁ እንዳልሆነ ሳይነገር የታወቀ ሳይታለም የተፈታ ነው።
እመቤታችንን ከክብሯ አውርዳችሁ ስትጥሉ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን መንበር አልባ ስታደርጉ ቅር ያልተሰኛችሁ ሰዎች ሕጋዊው ሲኖዶስ እያላችሁ በአፍ ብቻ ብታታክቱን ምን ይረባችኋል? እኛን የሰደበ ለእርቅ አይደራደርም ስትሉ እመቤታችንን የሰደበ አስተርአዬ የተሰኘ ጉድ እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብቶ የተደበቀ ምሳሌ የተባለ ተሐድሶ ይዛችሁ ስትቀርቡ ማነው እናንተንስ የሚጠይቃችሁ? ዛሬስ ሁሉ ነገር ውስብስብ ሆኖ ታየንና ግራ ገባን እንጂ እግዚአብሔር ምርቱን ከግርዱ፣ መልካሙን ከመጥፎው የሚለይበትን መንሹንና ፍርዱን ይዞ የተነሣ ዕለት መግቢያችሁ የት ይሆን? ከላይ እንደገለጽኩት ፆም እና ጸሎት፣ እርቅ እና ይቅርታ፣ ሰላም እና ፍቅር በአፍ ላይ ብቻ ተወስኖ ማወናበጃ ሆኖ ቀረ እንጂ ጸሎታችሁ ወደ እግዚአብሔርማ ቢሆን ኖሮ እስከ ዛሬ መልስ ይገኝ ነበር። ከእግዚአብሔር ይልቅ መታመኛ ያደረጋችሁት ሥጋ ለባሹን ወገን ሆነና የአንዱ ፖለቲካ ሲወድቅ የእኛ ይነሣል በማለት ለጥያቄአችሁ መልስ የምትጠብቁት ከሰው ነው።
አስቀድሞውኑ ተወጋግዛችሁ የተላለቃችሁ ሁሉ ለስብሰባ ለመቅረብ ድርድር የያዛችሁት ሞክረን ነበር አልተሳካልንም ጥረን ነበር አልሆነልንም ለማለት እንጂ ልባችሁ ያልተዘጋጀ ሰዎች ናችሁ። እናንተን ለማስታረቅ የጠፋው ጊዜና በሃይማኖት ስም ለሁለት ተከፍላችሁ ሕዝቡን ስታምሱ የቆያችሁበት ጊዜ የሥራ ጊዜ ሆኖ ቢሆን ኖሮ ወደ እምነት እየተመለሰ እና ቤተ ክርስቲያኔን እያለ ያለው ወጣት ታሪክ በቀየረ፣ ኦርቶዶክስን ባሳደገ ነበረ። ግን ምን ያደርጋል እግዚአብሔር በትውልዱ ላይ እርም አግኝቷልና እርማችንን ጥለን ለእውነተኛው ዕርቅ ስንደራደር የእግዚብሔር እጅ ያን ጊዜ ሥራ ይሠራል። ይቆየን።

Anonymous said...

Selam all;

There are three groups who would not like to succeed the legitimate Holy synod in the diaspora.
1. Aba Gebremedihin( the illegitimate patriarch.
2. those who are using this division for their own financial thirst
3. those who are village minded intellectuals.
Why the Holy synod needs to agree to participate in the negotiation? EOTC is in a terrible shape. It loses its own people by the multi enemies. From Catholics to Pentes to Fundamental islamist. I applaud the Holy synod in the diaspora that it is ready any time for any thing brings peace,national reconciliation. Those of you who consider becoming refugee is a luxery, I will pray for you until you got the wisdom from God.Amen

Anonymous said...

...yikirta arigulign wegenoche... ene gin sasibew, meftihe kehone, minew hulum bemotuna barefin.. neger alemun abelashitew huletum sikelidubin eyaye fetari zim sill yigerimegnal... ene yikirta arigulign enji, tselote, huletunim wisedachew eyalikugn new. enem yemalireba negnina kasifelege enem memot alebign... betekirstianin endih mechawecha kemadireg, memot eko tilik erefit new.... fechi bitefa, tarik abelashu tebilen, bayihon yemimetaw tiwilid enkuan beselam yinur enji.... ere weladite amlak bekachihu beyin, Hatiyatachin eko akatelen.... bezih zemen begna kifat seyitanim sayigerem ayikerem!! ho ..cherun yaseman ere.

Anonymous said...

ብስማሙ ነበር የሚገርመዉ!

selamawi said...

በስመ ስላሴ አሃዱ አምላክ አሜን

ወገኖቼ አልታደልንም የሰላም ዜና ለመስማት አልተፈቀደልንም ለምን ይሆን?

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)