August 31, 2010

አዲስ የጡመራ መድረክ (ብሎግ) በቀሲስ ያሬድ ገ/መድኅን

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 31/2010፤ ነሐሴ 25/2002 ዓ.ም)፦ ምእመናን ስለ ቤተ ክርስቲያናቸው ወቅታዊ ሁናቴ የሚያውቁባቸው አዳዲስ የጡመራ መድረኮች በየጊዜ እየተመለከትን ነው። ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ላለፉት አራት ወራት ግሩም ግሩም ጽሑፎችን እና የመወያያ ነጥቦችን እያነሣ ሲሆን ሌላው ሰባኬ ወንጌል ቀሲስ ያሬድ ገ/መድኅንም በበኩላቸው የራሳቸውን መጦመሪያ (የጡመራ መድረክ http://www.kesisyaredgebremedhin.com/)  ፈጥረዋል። ደስ የሚያሰኝ ነው። ባወጡት መርሐ ግብር እንዲዘልቁም እንመኝላቸዋለን።   ማስታወቂያቸው እንደሚከተለው ይነበባል።
-----------------------------------------------------------------

August 30, 2010

"Anyuak Media" against our Church???

(Deje Selam; August 29/2010):- In our website browsing, we encountered a concerning report by a certain "Anyuak Media", which labels the Ethiopian Church as "Abyssinizer". We quote the report in length as follows.

ፍርድ ቤቱ በ‹‹የሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች›› ደራሲ ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቀደ


(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 29/2001፤ ነሐሴ 23/2002 ዓ.ም):- በ‹‹የሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች›› መጽሐፍ ምክንያት በወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ፣ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ እና በጋሻው ደሳለኝ የስም ማጥፋት ወንጀል ክስ በቀረበበት ሊቀ ትጉሃን ዘሪሁን ሙላቱ ላይ ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሳቢያ ጉዳዩ ለነሐሴ 25 ቀን 2002 ዓ.ም ተቀጠረ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት እጁ ታስሮበት ከነበረው ካቴና ተፈትቶ የቀረበው ዘሪሁን ሙላቱ በበኩሉ፣ ‹‹ስለ መጽሐፉ አንዳችም የማውቀው ነገር የለም፤ ከቤተሰቦቼም ይሁን ከሌሎች ጓደኞቼ ጋራ እንዳልገናኝ ተከልክያለሁ፤ በአ.አ.ዩ የፒ.ኤች.ዲ ተማሪ ነኝ፤ ከእኔ በቀር ረዳት የሌላት ታማሚ እናት አለችኝ፤›› በማለት የዋስትና መብቱ እንዲከበርለት ያቀረበው ጥያቄ ዳኛው ፖሊስ ምርመራውን በሚገባ አጣርቶ እንዲቀርብ አንድ ተጨማሪ ቀጠሮ ልስጥ በማለታቸው ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል፡፡

August 26, 2010

አቤቱ እንድናስተውል እርዳን

(Kiduse wwek)ከጊዜ ወደ ጊዜ የቤተክርስቲያን ፈተና እያየለ መምጣቱ ግልፅ ነው ፡፡ ከዚህ አንጻር ከእኛ የሚጠበቀውንና መፍትሔ ይሆናሉ ያልኳቸውን ጽፌላችኋለሁ፡፡ ጠቃሚ ነው ካላችሁ የጠመመውን አቅንታችሁ የተሳሳተውን አርማችሁ ለንባብ አብቋት ፡፡1ኛ. ወንጀል ሲፈጸም እያዩ ዝም ማለት እንኳን በፈጣሪ ዘንድ በምድራዊ መንግስትም ዘንድ ስለሚያስጠይቅ በሰበካ ጉባኤ ፣በህንጻ አሰሪ ኮሚቴ ፣በሰ/ት/ቤት በማኅበራት ውስጥ የምናገለግል ሁሉ የነቃ ተሳትፎ ማድረግና ለሙስናና ለፈተና የማያጋልጥ አሰራር መስራት አለብን፡፡ ከዚህ ባለፈ የሚሰሩትን ወንጀሎች ትክክለኛ መረጃ በማሰባሰብ ማጋለጥ ይጠበቅብናል፡፡

August 25, 2010

ENOUGH IS ENOUGH!

(By Tewahedo)
These wolves  in sheep-clothing should be removed from our church ones for all. They have understood the psychology of the fathers (including that of the politically-minded patriarch) and thus are playing a game for their own advantage. As the saying goes:YE'ASA GIMATU KANATU - since the patriarch himself is void of spirituality, Begashaw, Zerihun and their allies have become confident that no one will confront them for their disturbingly immoral deeds. They know that they can buy the hand of the patriarch and use him for their own advantages as we saw in the statue shameful drama. Hence, let me propose a few points to clean the mess in our mother Church:

August 24, 2010

ዘሪሁን ሙላቱ እና በጋሻው ደሳለኝ እንዲወገዙ እና እንዲከሰሱ ሰባክያነ ወንጌል ጠየቁ

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 24/2010፤ ነሐሴ 18/2002 ዓ.ም):- በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት አስቸኳይ ስብሰባ የተጠሩ በሀገረ ስብከቱ ገዳማት እና አድባራት ተመድበው የሚያገለግሉ ሰባክያነ ወንጌል፣ ‹‹ለወቅቱ የቤተ ክርስቲያን ችግር እና ለአባቶች ክብር መደፈር መንሥኤ ነው›› ያሉት በጋሻው ደሳለኝ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በተገኙበት ጉባኤ እንዲወገዝ እና ክስ እንዲመሠረትበት፣ ‹ሊቀ ትጉሃን› ዘሪቱ ሙላቱ ደግሞ እንዲወገዝ ጥያቄ የሚያቀርብ የአቋም መገለጫ አወጡ፡፡ ስብሰባው ‹‹በሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች›› መጽሐፍ የተነሣ ክፉኛ ለተረበሹት ለሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ በመወገን፣ ሰባኪውን በፀረ ዘሪሁን አቋም ዙሪያ አስተባብሮ በቅዱስ ሲኖዶስ እንዲወገዝ ለመጠየቅ እና መጽሐፉን በማሰራጨት ረገድ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል የተባሉትን ሰባክያነ ወንጌል ለማስጠንቀቅ ታስቦ የተጠራ ነበር፡፡

August 22, 2010

‹‹የሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች›› ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ዘሪሁን ሙላቱ ፍ/ቤት ቀረበ

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 21/2010፤ ነሐሴ 15/2002 ዓ.ም):- ትናንት አርብ ተሲዓት በኋላ ከአንድ ጓደኛው መኖርያ ቤት ሳለ የተያዘው ‹‹የሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች›› ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ዘሪሁን ሙላቱ በዛሬው ዕለት ጠዋት አራዳ ክፍለ ከተማ በሚገኝ የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት መቅረቡ ታውቋል፡፡ እነ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ ‹‹በስም ማጥፋት›› ወንጀል ክስ የመሠረቱበት ይኸው ጸሐፊ ለኀሙስ፣ ነሐሴ 20 ቀን 2002 ዓ.ም (ኦገስት 26/2010) ዳግመኛ እንዲቀርብ ከተወሰነ በኋላ በፖሊስ ተይዞ የተወሰደ ሲሆን ከሳሾችም በርግጥም ‹‹የሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች›› ፀሐፊ እርሱ መሆኑን የሚያረጋግጡላቸውን አስረጅ ምስክሮች በዕለቱ እንዲያቀርቡ ታዝዘዋል፡፡ ምንም ዓይነት አካላዊ ጉዳት ያልደረሰበት ፀሐፊው ሊያዝ የበቃው የቅርብ በሚላቸው ጓደኞቹ ጠቋሚነት እንደሆነ ተነግሯል፡፡

August 20, 2010

እጅጋየሁ እና ፋንታሁን ከፓትርያርኩ ጋራ መከሩ

 • ታግዶ የቆየውን የእነ በጋሻው የአሰበ ተፈሪ ጉባኤ አስፈቀዱ
(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 20/2010፤ ነሐሴ 14/2002 ዓ.ም):- ‹‹የሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች›› በሚለው ‹መጽሐፍ› ‹‹ቅዱስ ፓትርያሪኩን ማስፈራሪያ እና የንግድ ምልክት ያደረጉ የዘመናችን አፍኒን እና ፊንሐስ›› የተባሉት ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ እና ወይዘሮ እጅጋየሁ በየነ በሊቀ ትጉሃን ዘሪሁን ሙላቱ ጉዳይ ላይ የሱባኤውን መጠናቀቅ ሳይታገሡ ፓትርያሪኩ ወደሚገኙበት ድሬዳዋ በርረው መክረው መመለሳቸው ተሰማ፡፡ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ነሐሴ ስምንት ቀን 2002 ዓ.ም ምሽት ፓትርያሪኩ ለሱባኤው ሄደው ባረፉበት በድሬዳዋ መካነ ቅዱሳን አቡነ አረጋዊ ወአርሴማ ገዳም የደረሱት ወ/ሮ እጅጋየሁ እና ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን መጽሐፉን ስላዘጋጀው ‹‹ስውሩ ጸሐፊ››፣ በመጽሐፉ ይዘት እና መጽሐፉን በማሳተም ረድተዋል ብለው በሚጠረጥሯቸው አካላት ማንነት ዙሪያ ከአቡነ ጳውሎስ ጋራ ሲመክሩ አምሽተው (8pm - 4:30AM) እሑድ ዕለት ጎሕ ሳይቀድ (ምሽት 02፡30 ገብተው ሌሊት 10፡30) ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸውን የድሬዳዋ ምንጮች ለደጀ ሰላም አስረድተዋል፡፡

‹‹የሐውልቱ ስር ቁማርተኞች›› ፀሐፊ ዘሪሁን ሙላቱ ተያዘ፤ ለሥራ አስኪያጅ ፋንታሁን ሊደረግ የታሰበው ‹‹የማጽናኛ መዋጮ›› ታገደ


(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 20/2010፤ ነሐሴ 14/2002 ዓ.ም):- ሰሞኑን በእነ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ ከፍተኛ ክትትል ሲደረግበት የቆየው ‹‹የሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች›› ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ዘሪሁን ሙላቱ ዛሬ ከቀትር በኋላ በተለምዶ ኮልፌ - 18 ማዞርያ እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ቁጥራቸው በርከት ባሉ ሲቪል የለበሱ የደኅንነት ኀይሎች እና ዘግየት ብለው ወደ አካባቢው በደረሱ ሁለት ፖሊሶች ‹‹ለጥያቄ እንፈልግሃለን›› በሚል ተይዞ መወሰዱን የዐይን እማኖች ገለጹ:: ስውሩ ጸሐፊ ዛሬ ዘጠኝ ሰዓት ተይዞ ሜክሲኮ አካባቢ ወደሚገኝ አንድ ስፍራ የተወሰደው ዳንኤል ከሚባል ጓደኛው መኖርያ ቤት መሆኑን የዐይን ምስክሮቹ ተናግረው በጸሐፊው እና በጸጥታ ኀይሎቹ መካከል ከፍተኛ ጭቅጭቅ እንደ ነበር ትዕይንቱን በርቀት ሲከታተሉ የነበሩት እኒሁ የዐይን ምስክሮች አስረድተዋል፡፡

August 19, 2010

አለቃ አያሌው ታምሩ እና ትምህርታቸው፦ ፫ኛ ዓመት ዕረፍት መታሰቢያ(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 19/2010)፦ ቤተ ክርስቲያን በተለያዩ ዘመናት እንደ ሰማይ ኮከብ፣ እንደ ምድር አሸዋ የሚበዙ ሊቃውንት አፍርታለች። ከነዚህ ሊቃውንት መካከል ደግሞ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት አለቃ አያሌው ታምሩ አንዱ ናቸው። ስለ ሕይወት ታሪካቸው፣ ሥራዎቻቸውና ተያያዥ ጉዳዮች በስማቸው የተሰየመውን ድረ ገጽ እንድትመለከቱ እየጋበዝን ስለ ትምህርታቸው የሚናገረውን ክፍል ቀንጭበን ለማቅረብ ወደድን።

“የሐውልቱ ስር ቁማርተኞች”ን ማንበብ ከፈለጉ ...

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 18/2010)፦ የፓትርያርኩና የማፊያው ቡድን “ስውር ፀሐፊ” (Ghost Writer) ዘሪሁን ሙላቱ ስለ ፓትርያርኩ ሐውልትና ተያያዥ ጉዳዮች  ባለ 50 ገጽ መጽሐፍ ማውጣቱን፤ እነ በጋሻው ደሳለኝና ኤልዛቤል የምትባለው ወ/ሮ እጅጋየሁ እንደተጠቀሱበት፤ ዲያቆን ሲባል ቆይቶ በቅርቡ ሊቀ ትጉሃን የሚል የማዕረግ ስም የደረበው Ghost Writer ዘሪሁን ሙላቱ ጊዜውን በቶሎ በማጥናት እና የፓትርያርኩ ሐውልት ብዙ ተቃውሞ እንደበዛበት ሲመለከት፣ የሐውልቱ ተቃዋሚዎች ያሉትን በመሰብሰብና መጽሐፍ አድርጎ በማሳተም ሲያሳዝነው የሰነበተውን ምእመን አሁን ደግሞ ገንዘቡን ሊበላው ይህንን ፓምፍሌት (መጽሐፍ ለማለት ይከብዳል) ማሳተሙን በተከታታይ መዘገባችን ይታወሳል። መጽሐፉን ማንበብ ለፍርድ ይመቻልና እነሆ እንዲህ አዘጋጅተነዋል። ለማንበብ ይህንን (አስነብበኝ) ይጫኑ።

August 18, 2010

ለሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ ‹‹የማጽናኛ መዋጮ›› ሊበረክትላቸው ነው

 •     መዋጮውን የአጥቢያ ሰበካ ጉባኤያት ጸሐፊዎች ያስተባብራሉ  • (ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 18/2010፤ ነሐሴ 12/2002 ዓ.ም):- በቁጥር ከስድሳ የማያንሱ እና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤያት ጸሐፊዎች እና አንዳንድ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች ለአወዛጋቢው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ ‹‹የማጽናኛ መዋጮ›› ሊያበረክቱ ማቀዳቸው ተሰማ፡፡ የሀገረ ስብከቱ ምንጮች ለደጀ ሰላም ያደረሱት መረጃ እንደሚጠቁመው፣ ‹‹የማጽናኛውን መዋጮ›› ለማስፈጸም በዋናነት እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ጸሐፊዎች እና አንዳንድ አስተዳዳሪዎች ሲሆኑ ማጽናኛው የሚከናወነው ጸሐፊዎቹ ባሰባሰቡት የገንዘብ አስተዋፅኦ ነው፡፡

  August 15, 2010

  እነ ወ/ሮ እጅጋየሁ የ “ሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች ”መጽሐፍ ደራሲን ለመክሰስ በዝግጅት ላይ ናቸው

  • ሊቀ ትጉሃን ዘሪሁን ሙላቱ በሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ቀርበው ሪፖርት እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ወጣባቸው፤  
  (ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 15/2010፤ ነሐሴ 8/2002 ዓ.ም):- በቅርቡ ‹‹የሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች›› በሚል ርእስ፣ ፈታሔ በጽድቅ በሚል የፈጠራ ስም የሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬን፣ የወ/ሮ እጅጋየሁ በየነን፣ የበጋሻው ደሳለኝን እና የያሬድ አደመን “ገመና፣ ኀጢአት እና የሙስና ድርጊቶች” በማጋለጥ ባለ ኀምሳ ገጽ ጽሑፍ ያወጣው ስውሩ ጸሐፊ ዘሪሁን ሙላቱ ከዓርብ ነሐሴ ሰባት ቀን 2002 ዓ.ም (ኦገስት 13/2010) ጀምሮ በሚታሰቡ አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ቀርቦ ሪፖርት እንዲያደርግ የሚያዝዝ ማሳሰቢያ ወጣበት፡፡

  August 14, 2010

  በርግጥ መጋቤ ብሉይ የተናገሩት የእርቁ እንቅፋት ሊሆን ይገባ ነበር?

  (ገብር ሔር ዘመ/መንግሥት እንደጻፈው፤ ኦገስት 14/2010፤ ነሐሴ 8/2002 ዓ.ም)፦ በአንድ ወቅት መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ በሰሜን አሜሪካ ለሚሰራጨው የሀገር ፍቅር ሬዲዮ የሰጡት መግለጫ ሰሜን አሜሪካንን ለአስራ ስምንት ዓመታት ላላነሰ ግዜ መኖሪያ ባደረጉት “ስደተኛ አባቶች” ዘንድ አቡዋራ ማስነሳቱን በተባራሪ ወሬ ሰምቼው ነበር። ሳይጀመር ለተጠናቀቀው የሰላምና ዕርቅ መሰናክል የሆነውም ይኸው መግለጫ እነደሆነ ይፋ ሲሆን ሊቁ የተናገሩትን ወይም የሰጡትን መግለጫ ለመስማት ልቡናዬ ተጋ። ግን ከየት አግኝቼ ማድመጥ እችላለሁ? እያልኩ ሳሰላስል የመረጃ ጎተራ የሆነችው ደጀ ሰላም በግራም በቀኝም፤ በድጋፍም በጥላቻም ለተሰለፈው ሁሉ ዕርቀ ሰላሙ ሳይጀመር እንዲያልቅ ምክንያት ሆነ የተባለውን የመጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴን ቃለ መጠይቅ እነሆ ብላ የመረጃ መረብ ሰሌዳዋ ላይ አወጣችውና የመረጃ ፍላጎት ጥማቴን አስታገሰችልኝ፡፡ በዚሁ እግረ መንገዴን ትጉሁን የደጀ ሰላም (የእርሱን አባባል ልጋራና) ጦማሪ (በልቶ ጠጥቶ ጠግቦ ረክቶ ሳያመሰግን ሹልክ ብሎ እንደሚሄድ ሰው እንዳይመስልብኝ) እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛልህ እላለሁ፡፡

  August 10, 2010

  የመጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስ የቀብር ሥነ ሥርዐት ሪፖርታዥ

  የመጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስን አጭር ታሪክ ለማንበብ (እዚህ PDF) ይጫኑ።
  • ‹‹ማወቅ ትርጉም ያገኘው በመጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ነው፤ ከካባቸው በላይ ሊቅነታቸው ጎልቶ ይታይ ነበር፤ ሊቅነት ብቻ ሳይኾን ይህ ጎደለህ የማይባል መልካም ጠባይዕ ነበራቸው፤ ለእርሳቸው እንዲህ ያለ አቋራጭ ጊዜ ይመጣል ብለን አልጠበቅንም፤ ሰላምን ለማምጣት በመፋጠን ላይ እንዳሉ ከረጅም መንገድ መጥተው ወደ ረጅም መንገድ ሄዱ - የሰላም መልእክተኛ ኾነው ሁሉንም በፍቅር እና በትዕግሥት እያዩ ነው የሄዱት፤ ይኼ ራሱ ትልቅ ምስክርነት ነው እኮ!!›› (ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ)    
  • ‹‹በቅንነት እና በታማኝነት ያገለገሏት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባታል፡፡›› (የኀዘን መግለጫው)
  (ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 10/2010፤ ነሐሴ 4/2002 ዓ.ም) ነሐሴ አንድ ቀን 2002 ዓ.ም ጠዋት በድንገተኛ ሕመም በተወለዱ በስድሳ ሰባት ዓመታቸው ያረፉት እና በመ/ፓ/ጠቅ/ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የሊቃውንት ጉባኤ መምሪያ ሐላፊ የኾኑት የመጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስ የቀብር ሥነ ሥርዐት በትናንትናው ዕለት ከጠዋቱ 3፡00 - 9፡00 ሰዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በተካሄደ የጸሎተ ፍትሐት እና ጸሎተ ቅዳሴ ሥነ ሥርዐት ተፈጸመ፡፡

  August 9, 2010

  የሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች:- የስውሩ ፀሐፊ “ስም አጥፊ” አዲስ መጽሐፍ


  • ‹‹ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ ድሮም ዘንድሮም ወደፊትም ያው ናቸው፡፡ ነገሮች ሁሉ ባልተለወጡበት እና ባሉበት ኹኔታ እየቀጠሉ በጋሻውን የለወጠው ኹኔታ ስታሰብ የጥቅሙን ስፍራ ከማዘዋወር በቀር የሚገባን ነገር የለም፡፡››
  • ወ/ሮ እጅጋየሁ ‹‹የቤተ ክርስቲያኑን አስተዳደር አየር ባየር ትመራለች፡፡››           
  • ‹‹የአቡነ ጳውሎስን ሐውልት መቶ ሺሕ ብር አውጥቶ ያስገነባው በጋሻው ስርየት የሌለው ጥፋት ውስጥ የገባ የራሱን ጥቅም ማዕከል በማድረግ ነው፡፡››
  •  ስለ ሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒን ምንም አለመናገሩ ብዙዎችን አስገርሟል፡፡  
  (ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 8/2010)፦ የፓትርያርኩና የማፊያው ቡድን “ስውር ፀሐፊ” (Ghost Writer) ዘሪሁን ሙላቱ ስለ ፓትርያርኩ ሐውልትና ተያያዥ ጉዳዮች  ባለ 50 ገጽ መጽሐፍ አወጣ፤ እነ በጋሻው ደሳለኝና ኤልዛቤል የምትባለው ወ/ሮ እጅጋየሁ ተጠቅሰውበታል። ዲያቆን ሲባል ቆይቶ በቅርቡ ሊቀ ትጉሃን የሚል የማዕረግ ስም የደረበው Ghost Writer ዘሪሁን ሙላቱ ጊዜውን በቶሎ በማጥናት እና የፓትርያርኩ ሐውልት ብዙ ተቃውሞ እንደበዛበት ሲመለከት፣ የሐውልቱ ተቃዋሚዎች ያሉትን በመሰብሰብና መጽሐፍ አድርጎ በማሳተም ሲያሳዝነው የሰነበተውን ምእመን አሁን ደግሞ ገንዘቡን ሊበላው ይህንን ፓምፍሌት (መጽሐፍ ለማለት ይከብዳል) አሳትሟል። መታሰቢያነቱንም በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት ለተለዩት ለብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ በማድረግ መጽሐፉ ተቀባይነት እንዲያገኝ ለማድረግ ሞክሯል። ርእሱን ደግሞ በቅርቡ እኛም ካወጣነው (በአዲስ አበባ በጋዜጣ ከወጣ) አንድ ጽሑፍ ላይ የወሰደው ነው።

  August 8, 2010

  የመጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስ የቀብር ሥነ ሥርዐት ሰኞ ይፈጸማል


  (ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 8/2010)፦ በትላንት ዕለት በድንገተኛ ሕመም ሕይወታቸው ያለፈው የመጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስ የቀብር ሥነ ሥርዐት ሰኞ፣ ነሐሴ ሦስት ቀን 2002 ዓ.ም በስምንት ሰዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል፡፡

  በትላንትናው ዕለት ረፋድ ላይ ለእርቅ እና ድርድር ጉባኤ የሄዱበትን የአሜሪካ ተልእኮ አጠናቀው አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም ዓቀፍ አየር ማረፊያ እንደ ደረሱ ራሳቸውን የማቃጠል እና ልባቸውን የመውጋት ስሜት እንደተሰማቸው አብረዋቸው ለተጓዙት የልኡካን ቡድኑ አባላት የተናገሩት መጋቤ ብሉይ ሰይፈ፣ አስቸኳይ ሕክምና ሊያገኙ ይችሉ ከነበረበት ስፍራ ርቆ እና ከጊዜው ዘግይቶ አራት ኪሎ አካባቢ ቀድሞ ‹‹ጉድሸፐርድ›› አሁን ‹‹አዲስ የሕፃናት እና እናቶች ሆስፒታል›› በሚባለው የሕክምና ተቋም ውስጥ የመጀመርያ ደረጃ ምርመራ እየተደረገላቸው ሳለ ነበር ሕይወታቸው ያለፈው፡፡ ወዲያኑ አስከሬናቸው በቅዱስ ገብርኤል እና በዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታሎች ከፍተኛ ምርመራ ከተካሄደለት በኋላ ዛሬ ቀትር ላይ ሰበካቸው በሚገኝበት እና በአገልግሎት ብዙ በደከሙበት በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን እንዲያርፍ ተደርጓል፡፡

  August 7, 2010

  ሰበር ዜና፦ መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስ አረፉ

  (ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 7/2010)፦ ሰሞኑን ለአባቶች ድርድር አሜሪካ የሰነበቱትና አርብ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ተነሥተው ቅዳሜ ጠዋት አዲስ አበባ የደረሱት መጋቤ ብሉይ ሰይፈ፣ ቤታቸው እንኳን ሳይደርሱ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ በዚህ ጊዜ አሉ ከሚባሉት ሊቃውንት መካከል ተጠቃሽ ሲሆኑ በአንደበት ርቱዕነታቸው፣ በቅኔ አዋቂነታቸው፣ በሰባኪነታቸው የተመሰገኑና የተከበሩ ነበሩ።

  መግለጫዎቹ መግጫ፣ መገጫ፣ መገጫጫ ባይሆኑ


  (ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 6/2010):- እነሆ አባቶችን ለማስታረቅ የተደረገው ሙከራ የተፈለገውን ያህል ሳይራመድ መቅረቱን ስንዘግብ ቆይተናል፤ አሁን ደግሞ አሸማጋዩ ክፍል “መግለጫ”ውን አውጥቶ የሄደበትን ሒደት እና የደረሰበትን፣ እንዲሁም ድርድሩ የፈረሰበትን ምክንያት ነግሮናል። ከዚህኛው ጋር በድምሩ ሦስት መግለጫ አንብበናል ማለት ነው። ነገ ደግሞ ሌላ መግለጫ ሊመጣ፣ ለዚያ መልስ የሚሰጥ ሌላ መግለጫ እንዳይወጣ፣ ያንን የሚያስተባብል ሌላ መግለጫ እንዳይከተል እና መግለጫዎቹ መግለጫነታቸው ተረስቶ “መግጫ፣ መገጫ እና መገጫጫ” እንዳይሆኑ ከወዲሁ ለመጠቆም ወደድን።

  “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባዔ” መግለጫውን አወጣ፤ ድርድሩ በሦስት/አራት ወራት ውስጥ ይቀጥላል
  (ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 6/2010):- በቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል ያለውን መለያየት ለማስወገድ የማሸማገል ተግባር ሲፈጽም የነበረው የሰላምና የአንድነት ጉባዔ መግለጫውን አውጥቷል፤ ድርድሩ ከሦስት እስከ አራት ወራት ውስጥ እንደሚቀጥል አስታውቋል። የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ ይህንን (PRESS RELEASE) ይጫኑ።

  ቸር ወሬ ያሰማን፣አሜን


  August 5, 2010

  ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ስለ ሰላምና አንድነት ከተላከው ልዑክ የተሰጠ መግለጫ

  (ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 28/2010)፦ ከአምስተኛው ፓትርያርክ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሲመት ማግስት ጀምሮ በቤተ ክርስቲያኒቱ የተነሣውን መከፋፈል ለማቆምና በአባቶች መካከልም የተፈጠረውን እስከ መወጋገዝ የሚያደርስ ልዩነት በእርቅ ለመጨረስ የተጀመረው ድርድር ሁለቱን ተደራዳሪ ወገኖች ፊት ለፊት ለማገናኘት እንኳን ሳይችል መክኖ መቅረቱን ተከትሎ ቅ/ሲኖዶስን ወክሎ ለመደራደር ከአዲስ አበባ የመጣው ልዑክ መግለጫውን ዛሬ አውጥቷል። ልዑኩ ያወጣውን መግለጫ ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ (http://www.eotcdc.org/) ይጫኑ። በተያያዘ ዜና የአሜሪካው ወገን ቀድሞ ያዘጋጀው የሚመስለውን መግለጫ በ “ቋጠሮ” ድረ ገጽ  ላይ በትናንትናው ዕለት ማውጣቱን መዘገባችን ይታወሳል። የአሜሪካውን ወገን መግለጫ ለማንበብ እዚህ (መግለጫ) ይጫኑ።

  ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን

  እርቅ በማያውቁ አባቶች እና በ“ሰላም ድርድራቸው” ዙሪያ መታወቅ ያለባቸው ነጥቦች

  (ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 4/2010):- ሰላምን ልትሰብክ በተመሠረተች፣ ስትሰብክም በምትኖር ቤተ ክርስቲያን ላይ በተሾሙ አባቶች መካከል ሰላም ከራቀ፤ ከደካማ ሥጋችን በእውነት የተዋሐደውን አምላክ እየሰበከች «ተዋሕዶ» የምትባልን ቤተ ክርስቲያን እንዲመሩ በተሾሙ አባቶች መካከል  በእውነት መዋሐድ ከጠፋ ይኸውና አንድ ሕጻን ተወልዶ ለዐቅመ አዳም ደረሰ፡፡ በእነሱ ሳይኾን በፈጠሩት ችግር ዕድሜ መጠን ሲያስቡ ቆይተው ይመስላል፤ ይኸውና ችግሩ 19 ዓመት ሞልቶት ለአካለ መጠን ሲደርስ ሰላምን በመካከላቸው ለማውረድ ለውይይት መቀመጣቸውን ሰምተን፣ በዚህም በእጅጉ ደስ ብሎን ነበር። ምክንያቱም በደሙ የመሠረታትን ቤተ ክርስቲያን ይጠብቁ፣ መንጋውንም ይሰበስቡ ዘንድ የተቀመጡትን አባቶች መለያየት እያየን፤ ያንንም ተገን አድርጎ በየደረጃው ባለው የቤተ ክርስቲያን ምልአት የሚፈጠሩ የጥፋት ሆያ ሆዬዎችን እያየን ስናዝን ኖረናልና፡፡

  የብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ መኪና በድንጋይ ተደበደበ፤ በሰዎች ላይ ምንም አደጋ አለመድረሱ ታወቀ

  (ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 4/2010):- ከአገልግሎት በመመለስ ላይ በነበሩት በጅማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ መኪና ላይ በተሰነዘረ የድንጋይ ውርወራ የመኪናቸው መስተዋት ሲረግፍ በእርሳቸውም ሆነ መኪናው ውስጥ በነበሩት በሌሎች ሰዎች ላይ ምንም አደጋ አለመድረሱ ታወቀ።

  አደጋው የደረሰው ብፁዕነታቸው ሰኞ (26/11/2002) ከቀኑ 10፡00 ላይ ጦላይ ኪዳነ ምሕረት በነበረ ጉባኤ ላይ ቡራኬ ሰጥተው ወደ ጅማ ሲመለሱ መሆኑን እማኞች ገልፀዋል።

  August 4, 2010

  ሰበር ዜና፦ እርቀ ሰላሙ ሳይጀመር ተፈጸመ፣ ሳይታሰር ተበተነ

  (ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 3/2010)፦ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአባቶች የሰላምና የዕርቅ ድርድር ሳይጀመር ተፈጸመ፣ ልዑካኑም ሳይወያዩ ተበተኑ።
  ከትናንት በስቲያ ሰኞ ይጀመራል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ይህ “የሰላምና የእርቅ ጉባዔ” በተሸማጋዬቹ መካከል ማድረግ የፈለገውን ውይይት ማድረግ ሳይችል፣ ሁለቱን ልዑካን ፊት ለፊት ማገናኘት ሳይችል፣ በቅድመ ሁኔታ ላይ ብቻ ሲደራደር ቆይቶ እንዲሁ ተበትኗል። ይኸው ውይይት ውጤት እንደማያመጣ በታወቀ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ የአሜሪካው ወገን ቀድሞ ያዘጋጀው የሚመስለውን መግለጫ በ “ቋጠሮ” ድረ ገጽ  ላይ አውጥቶታል። ዝርዝሩን እንደደረሰን እናቀርባለን።
  ቸር ወሬ ያሰማን፣
  አሜን

  August 2, 2010

  በሐዋሳ የአጥቢያ ሰበካ ጉባኤያት እና የሀገረ ስብከቱ ‹ልኡካን› ውዝግብ

  • ‹‹ከእኛ ወገን አልያም ከዐመፀኛ ኀይሎች ጋራ ለመኾናችሁ ሚናችኹን ለዩ! በእንጀራችኹ ፍረዱ!! ፓትርያሪኩም ቢኾኑ አያድኗችኹም!!›› (አቡነ ፋኑኤል)
  • ‹‹በእንጀራችሁ ፍረዱ!›› (ሥራ አስኪያጁ)
  (ደጀ ሰላም፣ ኦገስት 2/2010)፦ በሲዳማ፣ ጌዲኦ፣ አማሮ እና ቡርጂ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ሀገረ ስብከት በሐዋሳ ከተማ በሚገኙ ሦስት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ከቃለ ዐዋዲው ውጭ የሰበካ ጉባኤ አባላትን እንዲያስመርጡ ከሀገረ ስብከቱ በተላኩ ግለሰቦች ሳቢያ ውዝግብ ተቀሰቀሰ፤ በውዝግቡ የተልእኮው አስፈጻሚ እና ተባባሪ ኾነው የመጡ ራሱን ‹‹ተስፋ ኪዳነ ምሕረት ፀረ - ኤድስ ማኅበር›› እያለ የሚጠራው ቡድን አባላት በተቃወሟቸው የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ላይ አካላዊ ጥቃት አድርሰዋል፡፡

  የሐዋሳ ከተማ ምእመናን ተወካዮች ከፓትርያርኩ ጋራ ተወያዩ

  • የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ከሐላፊነታቸው እንዲነሡ ተጠየቀ፤
  • ችግሩን አጥንቶ የመፍትሔ ሐሳብ የሚያቀርብ ኮሚቴ እንዲቋቋም ተወሰነ፤
  • ‹‹ተፈሣሕኩ እስመ ይቤሉኒ ኀበ ሐዋሳ ንሐውር፤. . . የሐዋሳን ሕዝብ  ከመውደዴ የተነሣ እኔ ራሴን የአጣሪ ኮሚቴው አባል ባደርግ ደስ ይለኝ ነበር፤›› (አቡነ ጳውሎስ)
  •  ‹‹ምእመኑ ቤተ ክርስቲያን ተሳልሞ ከመመለስ ውጭ የሚያገባው ጉዳይ የለም፤ የቅዱስ ሲኖዶሱን ሕገጋት የማወጣም ኾነ የምሽር እኔ ነኝ፤›› (አቡነ ፋኑኤል) 
  (ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 2/2010)፦ በሲዳማ፣ ጌዲኦ፣ አማሮ እና ቡርጂ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ሀገረ ስብከት የሐዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አስተዳዳሪ ያለአግባብ በመነሣታቸው እንዲሁም በሀገረ ስብከቱ የሚፈጸመው አስተዳደራዊ በደል እና ሙስና እየተባባሰ በመሄዱ ሳቢያ አፋጣኝ ፍትሕ እንዲሰጣቸው አቤቱታ ያቀረቡት የሐዋሳ ከተማ ምእመናን ተወካዮች ከፓትርያርኩ ጋራ ባደረጉት ውይይት ችግሩን አጥንቶ የመፍትሔ ሐሳብ የሚያቀርብ ኮሚቴ እንዲቋቋም ስምምነት ላይ የተደረሰ መኾኑን የስብሰባው ምንጮች ገለጹ፡፡

  ውይይቱና ሽምግልናው በምን ዙሪያ?

  (ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 1/2010)፦ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአባቶች የሰላምና የዕርቅ ድርድር በነገው ዕለት ማለትም ሰኞ ኦገስት 2/2010 (ሐምሌ 26/2002 ዓ.ም) ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል። ከሁለቱም በኩል ያሉ ተወካይ “የሰላም ልዑካን” ዋሺንግተን ዲሲ አካባቢ ተሰባስበዋል። እንደተለመደው ውይይቱ እንደሚደረግ በደፈናው ከመታወቁ ውጪ በምን ዙሪያ፣ እንዴት የሚለው ጉዳይ “በምስጢር” ስለተያዘ ብዙም ለማለት አያስደፍርም። ቤተ ክህነቱን የብልሹ አሠራር ምንጭ ያደረገውና ለዚህ ሁሉ ውድቀት ያበቃን ዋነኛው ምክንያት ነገሮችን ከሚመለከተው አካልና ምእመን ደብቆ የመሥራት አባዜ ስለሆነ ይህ ብልሹ አመለካከት ይሰበር ዘንድ ዝምታው ይሰበር፣ መጋረጃው ይቀደድ እንላለን፤ ስለዚህም እንጽፋለን።

  August 1, 2010

  ሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሲዘከሩ

  (በሔኖክ ያሬድ):- ሐምሌ 22 ቀን 2002 ዓ.ም. ሐሙስ በአዲስ አበባ በ"ባሕር" አቅጣጫ (በሰሜናዊ ምዕራብ አቅጣጫ) ጉለሌ አካባቢ ካንድ ዐውደ ጥናት ተገኝቼ በ10 ሰዓት አካባቢ ወደ ፒያሳ ሳመራ ቀልቤን የገዛ ክስተት ተመለከትኩ፡፡ የቀድሞውን የኢትዮጵያ ራዲዮ ጣቢያ፣ የአሁኑን የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ፋኩልቲ እንዳለፍኩ፣ በርካታ ሰዎች የተሰባሰቡበት ትዕይንት እየተካሄደ መሆኑን አስተዋልኩ፡፡

  የአቡነ ጴጥሮስን ሐውልት የከበቡትን ሰዎች መካከል ልብሰ ጵጵስና የለበሱ ከመሐል ኾነው በርቀት ሲናገሩ ይታየኛል፤ የሚኒባስ ታክሲ ሹፌሩን እንዲያወርደኝ አድርጌ ታዳሚውን ተቀላቀልኩ፡፡

  Blog Archive

  የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

  ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)