July 16, 2010

ዘሪሁን ሙላቱ፦ የፓትርያርኩና የማፊያው ቡድን “ስውር ፀሐፊ” (Ghost Writer)


(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 15/2010)፦ Ghost Writer የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል “ስውር ፀሐፊ” የሚለው ቃል ሙሉ በሙሉ አይተካውም። ነገር ግን በደምሳሳው(A ghostwriter is a professional writer who is paid to write books, articles, stories, reports, or other texts that are officially credited to another person. Celebrities, executives, and political leaders often hire ghostwriters to draft or edit autobiographies, magazine articles, or other written material.)  (Ghost Writer) ማለት በሌላ ሰው ስም ለሚታተም ነገር ገንዘብ እየተቀበለ ክሽን ያለ ጽሑፍ የሚጽፍ ሰው ማለት ነው። “ስውር ፀሐፊነት” ሙያ እንጂ ወንጀል አይደለም። በአገራችን ይህ “ስውር ፀሐፊነት” የተለመደ ባይሆንም ቤተ ክህነቱ አሁን እየተጠቀመበት ነው። ችግሩ ለበጎ ተግባር ሳይሆን ለጥፋት መሆኑ ነው። ቤተ ክህነቱ የሚጠቀምበት ግንባር ቀደም “Ghost Writer” ዘሪሁን ሙላቱ ይባላል።
ዲያቆን ሲባል ቆይቶ በቅርቡ ሊቀ ትጉሃን የሚል የማዕረግ ስም ደርቧል። ለዚህ “ኢትዮጵያዊ Ghost Writer” ጠቀም ያለ ብር የሚከፍሉት ደግሞ ቅዱስ ፓትርያርኩ እና “የማፊያው ቡድን” የሚባለው በቤተ ክህነቱ ውስጥ የተወሸቀው የዝርፊያ  ቡድን ነው።Ghost Writer ዘሪሁን ሙላቱ “የሚታወቅባቸው ሥራዎቹ” በሙሉ ፓትርያርኩን የሚያጸድቁ እና ሌሎችን የሚያንቋሽሹ ሲሆኑ ከነዚህም ውስጥ ሁለቱ ዋነኛ መጽሐፎቹ ለዲ/ን በጋሻው “የመስቀሉ ሥር ቁማርተኞች” መልስ የሰጠበት “የስድብ አፍ” እና ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልን “የሚያዋርድ” ስድብ ያሳተመበት መጽሐፉ ናቸው። የመጀመሪያውን መጽሐፉን በጻፈበት ወቅት ቅ/ፓትርያርኩ 60 ሺህ ብር ጥሬ ገንዘብ እንደሰጡት ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ። መጽሐፉንም እያንዳንዱ ቤተ ክርስቲያን በግድ እየወሰደ እንዲያከፋፍል፣ ካህናቱም በነፍስ ወከፍ እያንዳንዳቸው አምስት አምስት እንዲወስዱና እንዲሸጡ፣ ገንዘቡ ግን ከደሞዛቸው በግድ እንዲቆረጥ ተደርጎ ነበር።  ይህ ግለሰብ በቀደም ዕለት በተደረገው ሽልማት ላይ ስለዚሁ ስውር ሥራው (ከነ ዲ/ን በጋሻው ጋር) ከቅዱስ ፓትርያርኩ እጅ በአደባባይ ሽልማት ተበርክቶለታል።

Ghost Writer ዘሪሁን ሙላቱ የሚጽፋቸው ጽሑፎች ተጠቃሚ ከሆኑት ግለሰቦች አንዱ በስሙ በየጋዜጣው ጽሑፍ የሚያሳትመው “ባለ ሽጉጡ ቄስ” ሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ ነው። ሊቀ ካህናት ጌታቸው “የመንበረ ፓትርያርክ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሕጋዊ ወኪል” በሚለው ማዕረጉ ይታወቃል። በየጋዜጣው የሚጽፋቸው ጽሑፎች ግን የዘሪሁን ሙላት ናቸው። ሊቀ ካህናት ጌታቸው በፓትርያርኩ የሐውልት ምረቃ ወቅት ባቀረበው ሪፖርት ላይ በየመካከሉ የተጠቀሱትን የእንግሊዝኛ ቃላት ለማነበብ ሲቸገር ላየ ሰው ጽሑፉ የእርሱ አለመሆኑን ይረዳል። ጽሑፉማ የዘሪሁን ነው። ይኸው አሳዛኝ ግለሰብ በሰሞኑ በፓትርያርኩ ላይ የተነሣውን ተቃውሞ ለማብረድ ከዘሪሁን እየተዘጋጁ የሚመጡለትን ጽሑፎች በየጋዜጣው ለማሳተም በዝግጅት ላይ ነው። የደጀ ሰላም ውስጥ አዋቂዎች ከሰሞኑ በየጋዜጣው ሊወጡ ከተዘጋጁት ጽሑፎች መካከል ባለ 14 ገጽ የሆነ አንድ ጽሑፍ አግኝቶ ለመመልከት ችሎ ነበር። የዚህ ጽሑፍ ምንጭ “ከኮምፒውተር አድራሻው” ላይ እንደሚያመለክተው “Zer8.doc” በሚል ከዘሪሁን ዶኩመንቶች መካከል የወጣ ሆኖ ተገኝቷል። ዘሪሁን “የፋይሉን ስም (File Name)” ሳያስተካክል ነበር የላከው። ፀሐፊው ተብሎ የተጠቀሰው ግን “ሊቀ ካህናት ጌታቸው የመንበረ ፓትርያርክ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሕጋዊ ወኪል” ተብሎ ነው።

ጽሑፉ በአጭሩ ፓትያርኩን የሚያሞግስ፣ ሐውልት አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እና ኦርቶዶክሳዊ መሆኑን ለማስረዳት የሚሞክር፣ የዚህ የሐውልት ሥራ ተቃዋሚዎች ናቸው የሚላቸውን ሰዎች “ሰይጣኖች” ብሎ የሚያወግዝ፣ ዲ/ን በጋሻውን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ነው። ትናንት በጋሻውን እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ አድርጎ በሰደበበት ብዕሩ አሁን ደግሞ ሰማየ ሰማያት ያደርሰዋል። ሰሞኑን እንዳልነው “ገንዘብ ተቀብሎ ስለ እግዚአብሔር የሚሰብክ የበለጠ ገንዘብ ከተሰጠው ስለ ሰይጣንም ይሰብካል” ነው ነገሩ።

የፖለቲካ ልሒቃን “በፖለቲካ ውስጥ ዘላቂ ወዳጅነት እና ዘላቂ ጠላትነት የለም” እንደሚሉት አሁን ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን በመዝረፉ ውድድር ውስጥ ዘላቂ ጠላትም፣ ዘላቂ ወዳጅም የለም። በጋሻው ትናንት ስለ ፓትርያርኩ ሲጽፍ “በፕትርክና ዘመንዎ ሁሉ፣ አልታዘዝ ባሉት አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ላይ እንደ ጦር ጄኔራል ጦር ዚያዘምቱ፣ ቆመጥና ጥይት የያዙ ወታደሮች ሲበትኑ ሰነበቱ” ብሎ ነበር። ዛሬ ደግሞ ኢ-ኦርቶዶክሳዊ ይትባህል ይዞ ሐውልት ያስገነባላቸዋል። ምክንያቱም በዝርፊያ ውስጥ “ዘላቂ ወዳጅነትም፣ ዘላቂ ጠላትነትም” የለማ። ዘሪሁን በብዕሩ ያሞግሰዋል፣ ፓትርያርኩም በሽልማት ያምነሸንሹታል። በዚህ ሁሉ መካከል የሚጎዳው ግን የዋሁ ምዕመን፣ እያንዳንዳችን የመንፈሳዊነት ሕይወት እና እናት ቤተ ክርስቲያን ናት።

“ስውሩ ፀሐፊ” ዘሪሁን በሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ ስም፣ በፓትርያርኩ ቡራኬ የሐውልትን ትምህርት፣ የምስልን ኦርቶዶክሳዊነት እየሰበኩ ነው። ሊቃውንቱስ ምን ይሉ ይሆን? ነው ወይስ ሳናውቀው እምነታችን ተቀይሮ ይሆን?

20 comments:

ታ said...

አረ ለማን ኡ ኡ እንብል? ኡ ኡ ኡ ኡ ኡ ኡ ኡ ኡ ኡ ኡ ኡ ኡ ኡ ኡ ኡ ኡ...! አረ ያምላክ ያለህ። አረ ምን ይሆን መጨረሻችን? አረ አምላክ ሆይ ይቅር በለን፤ አረ እመአምላክ ሆይ አማልጅን፤ አረ ፈጣኑ ቅ. ገብርኤ ድረስልን፤ የት እንግባ ምን ይዋጠን? "ውሃ ቢያንቅ በምን ይዋጣል?" "ቅዱሳን" ጳጳሳቱ ስራ ሲፈቱስ ምን ... ? እፎይ ምን ይዋጠን? ምን እንሁን? የት እንግባ?

Anonymous said...

Oh! God keep us from thinking and living only for what we eat.

K.T, USA

Anonymous said...

Zerihun I sewer to GOD you will get your price after few days you will see

Anonymous said...

I knew a priest who used to take money from church for his private buisness and u know what happen to him... prior to finishing his building...he developed a big time stroke and now he couldn't even serve the church and had to stay at home.GOD has different ways to punish and teach people.Therefore U MAFIA group ...U better watch out!!!

Anonymous said...

Ato zerihun BIG DOG!!!

Anonymous said...

እግዚአብሔር ይስጥልን ደጀሰላሞች በርቱ ብዙ የደባ ምስጢር አለ ገና ሰው ሆኖ ፈጣሪን ከማታለል የበለጠ በደል ምን ይኖር ይሆን? እውነተኛ የበጎች እረኛ የሆነ አምላካችን ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን

Anonymous said...

Dear Dejeselamaweyan, Endet nachihu?
"lehulet getoch megezat atichilum" aydel yetebalew. sijemer Amlakun kemayawuk sew min litebek yichilal? kewusit telat ene ariwos, kewuchi ene giragn mohammed... yalatefuatin tewahido manim ayinekenikatim. Honom gin ebakachihu yetewahido lijoch hulachnim balenibet bertiten entseliy. yekidusan amlak yihin zemen betolo asalfot neber bilen lemawurat yabikan! Amen!

Genet K

selamawi said...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

እስቲ በስመ አብ ብየ ልጀምር

እናንተ ይኸማ ቁርጥ አልቃይዳ አይደል እንዴ ለመሆኑ ፎቶው ላይ እንደምናየው ነው መልኩ? የጺሙን አቆራረጥ አይታችሁታል? በስመ አብ ወገኖቼ በጣም እየፈራሁ ነው እንደቀላል እያየነው የነበረው ነገር ሁሉ በጣም አደገኛ እየሆነ ነው በቤተክርስቲያን ላይ እየተጫረ ያለው ጠባሳ በጥናትና ከፍተኛ የጥፋት ተልኮን ለማስፈጸም ልዩ ስልጠና በወሰዱ ሰዎች መሆኑ ለወደፊት ከፍተኛ ስጋት ይፈጥራል ይህን ስል ግን የቤተክርስቲያን አምላክ በደሙ የዋጃትን የሰማይ ደጅ ተብላ የምትጠራ ቤተክርስቲያንን ይተዋታል ብየ አላምንም ነገር ግን በሰዎች በደል ምክንያት ከፊት የተጋረጠብን መከራ ያስፈራል እግዚአብሔር በቸርነቱ ይርዳን ወላዲተ አምላክ በምልጃዋ አትለየን የቤተክርስቲያናችንን ጠላቶች ያስታግስልን ያጥፋልን ብለን አንጸልይም ወደ በጎ ይመልስልን ቤተክርስቲያናችን ያስተማረችን ለሚያሳድዱዋችሁ ጸልዩ ስለሆነ ለሁሉም ልብ እንዲሰጥልን እንጸልያለን

eleni said...

egzio meharene kiristos!!!

New generation said...

By the way he has a strong attachment with extreem muslims.He was assisted by them to distribute his book on Abune Samuel.

werkamaw said...

If we still think that,Patriarch Paulos and his blind supporters are just working for their strong desire of fame ,wealth and power we are still in deep sleep.

oh brothers and sisters ,of course there are a lot of people around the patriarch working for their own interest of fame ,power, and wealth.But the patriarch and other few dangerous people are not there just to collect money.had they been there for the purpose of making money our challege would have been relatively simple and easy.but we not lucky they are not there as the rest of the people around them.But they are there with a planned and well studied mission of destroying the church with all her dogma and kenona.
who is the biggest power behind the patriarch? the mafia group ?Begashaw?the woyane regim? the other selfish pops and individuals?ofcourse all these groups are behind the patriarch but they are not the main one!!!all these groups are behind the patriarc not in big mission and consipracy as the main one.The main Groups behind the patriarch are the catholics who were fighting to destroy the one and the only true church of the world.they have tried a lot since the 7th centuary either to catolicaized or destroy the true church .after a long fight they found patriarch paulos to realize their dreams.why patriarch paulos ? patriarch paulos dosen't belive on tewahdo teachings and he is against ethiopianism .so they belive he can finalise their long waiting project .would they be successful ?

it is upto these generation!!

ሃገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ said...

እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ!እግዚኦ እግዚኦ እግዚኦ!

Anonymous said...

betu

Anonymous said...

I am tired read & talk about it but i am not doing anything to make change.Please guys let us do some thing i do no what but i feel we need to organize ourself & do something Those who has the gift to cry & pray do it those who can get idea let us bring it here or if we have to help with money let us do it.We can creat some kind of group for change i mean i do no what to say i feel guilty of doing nothing.

Anonymous said...

እረ ግድ የላችሁም ጳጳሱ አዕምሮአቸዉን ስተዋል።ታመዋል። እንዲሁ ዘመድ ተብዬዎች ዙሪያቸዉን ከበዉ አንቱ አንቱ ከሚሏቸዉ ይልቅ ወደ ጸበል ቢወስዷቸዉ መልካም ነዉ ። ክብር የማይገባቸዉ የመናፍስት ዳኞች እነ ዘሪሁን፣ በጋሻዉ እና እጅጋየሁ አዋሽ አርባ ወርዳችሁ ምን አለበት እርሻ ብታርሱ። ድሮ ልጅ እያለሁ ትዝ ይለኛል አንድ ሰዉ ከጋዜጣ አነበብኩ ብለዉ "አርቆ ማሰብ የማይችልና ጠርሙስ አንድ ናቸዉ፤ ሆድና አንገት ሲኖራቸዉ ጭንቅላት የላቸዉም" ያሉኝ ከላይ እስከታች ሁላችሁም አስተዋይ ልቦና ያድላችሁ።

Anonymous said...

ምነዉ ለቤተ ክርስቲያናችን ፈተናዋ መብዛቱ?
የወርቃማዉ ዘመን ወርቅ ልጆች እነ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣ ቅዱስ ያሬድ፣አጼ ዘረ ያዕቆብ፣ ወዘተ ደገኞቹ እንዳልተፈጠሩባት እነኚህ የዛሬዎቹ ዘረ ቁርጦች መብቀላቸዉ ከወዴት መጡ መንቲያ ፍጥረቶች። እረ የወገን ያለህ አዋጅ! አዋጅ! አዋጅ! " ስማ ስማ መስማሚያ ይስጥህ" ነበር የሀገሬ የጥነቱ አዋጅ። ሁሉም በየዘርፉ ለዝናዉ ከሮጠ "ምንን ካሳደገ የገደለ ይጸድቃልና" ነዉና ዉርሳችን በህብረት ሆነን እዉነተኞቹን አባቶቻችንን እንታደጋቸዉ።

Anonymous said...

Anbabew yastewel.

Anonymous said...

ብዙኃን እለ ይቤሉ መኑ ያርእየነ ሠናይቶ(መዝ 4-6)
ይድረስ ከላይ ከፓትርያሪኩ እታች እስካለው ምዕመን ድረስ። በዚህ ሰዓት ሁላችንም እንዲህ እያልን ነው በጎውን ማን ያሳየናል? መልሱ ግን መጸሐፍ ቅዱስ ላይ አለ። ከኛ የሚጠበቀው አንብቦ ማስተዋል ነው።
ማቴዎስ 24- ከቊጥር 4-15 ይህን ሊሆን ግድ ነው ብሏል ጌታ ማመን ያለብን የጌታን ቃል ወይስ ሰዎች የሚያደርጉትን። ጌታ ስለቃሉ እንዲህ ብሏል። ሰማይና ምድር ያልፋሉ እንጂ ቃሌ ግን አያልፍም። ታዲያ የዚህን ወንጌል ምዕራፍ ዋና መልእክት ።
ይህ ሊሆን ግድ ነው። ምን ሊሆን ነው ግድ፤የተመረጡት ሊስቱ፣ ጦርን ፣ወሬን፣ ልንሰማ ግድ ነው ግን አትደንግጡ ይህ የምጥ መጀመሪያ ነው። ብዙ አሳቾች ይነሳሉ ፤ከዓመፃ ብዛት የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች እስከ መጨረሻው የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። ይላል ታዲያ በሰው ሳንፈርድ ሰውን ሳናሰናክል ጸንቶ ለመዳን ይህን ቃል እናንብብ ማቴ 24- 15 የጥፋትን ርኵሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ እንባቢው ያስተውል።
አሁን በተቀደሰችው ሥፍራ ጥፋት ርኵሰት ቆሞአል።
የቆሙት ጥፋቶች ሀውልት ብቻ አይደለም
ጥፋት 1- የኖረው ሥርዓት የማዕረግ ስም የሚሰጠው በጳጳስ ነው ታዲያ ዲ/ን በጋሻው ጵጵስና አለው ማለት ነው እኛ ሳናውቅ ??? ለፓትርያሪኩ ሰማዕት ዘእንበለ ደም ብሎ ስም የሰየመላቸው። ምናልባት ፓትርያሪካችን እርሱ ይሆን እንዴ?አሁን እንደ ሆነ ሁሉም ነገር በሲኖዶስ ሳይሆን በግለሰብ ነው የሚጸድቀው ወደ ሲኖዶስ ከቀረበ መንፈስ ቅዱስ አይሆንም ይላል ስለዚህ አጽድቆ ማምጣት እና መግለጫ ማውጣት ብቻ ነው ። መቼም ደጀሰላምን የማያነብ የለም ወደ ቤተክነት ቀረብ ያላችሁ ይህንን ጠይቁና ቁርጡን እንወቅ። ሲያልቅ አያምር እኮ ነው ነገሩ ዘንድሮ። አሊያም ለፓትርያሪኩ ንገሩልን እንዴት በዲ/ን ስም ሲሰየምሎት ይቀበላሉ። ከዚያም በላይ ይህ ስም የወጣሎት ውዳሴ ማርያም ባልደገመ ሰው ነው ውዳሴ ማርያም ተምሮ ቢሆን ሰማዕትነት ያለ ደም እንደ ማይሰጥ ያውቅ ነበር ።
የሀሙስ ውዳሴ ማርያም እንዲህ ፡ይላል ርዕሱ ዳዊት ዘነግሠ ለእስራኤል 6ኛ ተራ ላይ ይገኛል።
ስለ ሰማዕታት ሲናገር ፦ አማን መነኑ ሰማዕታት ጣዕማ ለዛ ዓለም ወከዓው ደሞሙ በእንተ እግዚአብሔር ወተዓገሡ ሞተ መሪረ ይላል፡ ትርጉም ሰማዕታት የዚህን ዓለም ጣዕም ናቁ መራራ ሞትን ታግሠው ደማቸውንም ስለ እግዚአብሔር አፈሰሱ።
በታሪክ ሳይሞቱ ሀውልት የቆመላቸው ብቸኛውና የመጀመሪያው ፓትርያሪክ አቡነ ጳውሎስ ደም ሳያፈሱ ሰማዕትነታቸው በ6ኛው ፓትርያሪካችን ዲያቆኑ ተረጋገጠላቸው። ነገ ደግሞ ቤ/ክን በስማቸው ይታነጽ እንዳትሉን።

Tewahedo said...

Selam Deje Selamoche,

Please keep on revealing such crimes in our church so that everybody will know what is going on around our church. I know such a thing is shameful and painful for all of us. Though we can't take legal actions on those evil acts, at least we will pray to God to make things right. Betam silekochegne egzer betun enditebki elemnalehu.

Cher were yaseman!

Anonymous said...

በጣም የሚገርመው ነገር በአንድ ዱርየ መቸገራቺን ነዉ ጉልበት ብናጣ ፊቱ ላይ ደም መድፋት ያቅተናል?

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)