July 8, 2010

የፓትርያርኩ ሽልማትና የሚቆምላቸው ሐውልት ውዝግብ አስነሳ

(ደጀ ሰላም፣ ጁላይ 8/2010)፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ 18ኛ ዓመት በዓለ ፕትርክናቸውን አስመልክቶ የሚበረከትላቸው ሽልማት ውዝግብ እንዳስነሣ በቦሌ መድሃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ሊቆመላቸው የታሰበው ሐውልትም ቅሬታ እንደፈጠረ አዲስ አድማስ ጋዜጣ ዘገበ፡፡

ከዚህ ሃይማኖታዊ የበዓል አከባበር ሥርዓት በኋላ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት እና ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦች መጠናቸው ከፍተኛ ከሆኑ ኬኮች ጀምሮ የተለያዩ ስጦታዎችን በሚያበረክቱላቸው በዚህ ዓመታዊ የበዓለ ሲመት ዝግጅት ወደ 100 የሚጠጉ የአዲስ አበባ አብያተ ክርስቲያን አስተዳደሪዎች እና ፀሐፊዎች አንድ ጊዜያዊ ኮሚቴ አቋቁመው ሽልማት ለመስጠት ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸውን የዚህ ኮሚቴ አባል የነበሩ ምንጮችን ጠቅሶ ጋዜጣው ዘግቧል፡፡

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በበኩሉ የኮሚቴውን አካሄድ በመቃወም አጠቃላይ የየአድባራቱን አስተዳዳሪዎች ሰኔ 22 ቀን 2002 ዓ.ም ስብሰባ በመጥራት ከሀገረ ስብከቱ ፍቃድ ውጪ ለቅዱስ ፓትርያርኩ ሽልማት ለመስጠት መንቀሳቀስ ተገቢ እንዳልሆነ በማስገንዘብ የሽልማት ሥነ ሥርዓቱን የሚያስተባብር ሌላ ኮሚቴ እንዲቋቋም ማድረጉን የጋዜጣው ምንጮች አረጋግጠዋል ተብሏል፡፡ በሌላም በኩል በዓለ ሲመቱ ከመከበሩ አንድ ቀን አስቀድሞ ሐምሌ 4 ቀን 2002 ዓ.ም ፓትርያርኩን ለማስደነቅ የሚችል ሐውልት በቦሌ መድሃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን የውጭ አጥር አጠገብ ሊቆምላቸው እንደሆነ እንዲሁም  ፓትርያርኩ ያላወቁትን እና ያላሰሰቡትን ዝግጅት በማድረግ በድንገት ሐውልታቸውን ሊያስመርቋቸው ማሰባቸውን በጠቅላይ ቤተ ክህነት ውስጥ የሚገኙ ምንጮች እንደጠቆሙ ጋዜጣው ዘግቧል፡፡

በምንጮች ጥቆማ መሠረት ሐውልቱ ሌላ ቦታ ተሠርቶ በቤተ ክርስቲያኑ እንደሚተከል ገልጸው ለሐውልቱ ማቆሚያ ከሲሚንቶ የተሠራ ሰማያዊ ላስቲክ የተሸፈነ ኮንክሪት ማየቱን ጋዜጣው ዘግቧል፡፡ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አብያተ ክርስቲያናት የአንዱ አስተዳዳሪ የሆኑ እና ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ አባት እንደሚሉት የቅዱስ ፓትርያርኩ በዓለ ሲመት መከበሩ እና ሃይማኖታዊ የአከባበር ሥርዓቱ በቅዱስ ሲኖዶስም ሆነ በቤተ ክርስቲያኒቱ ሕገ ደንብ ተቀባይነት ያለው ተግባር ቢሆንም ባለ ሦስት ገጽ ቅርጽ (ሐውልት) እንደጣዖት አምልኮ ስለሚቆጠር ከቤተ ክርስቲያኒቱ ትውፊት እና ሥርዓት አንጻር ፓትርያርኩ በሕይወት እያሉ ሐውልት ለማቆም ማሰብ ተገቢ እንዳልሆነ አስገንዝበዋል፡፡ በዚህ ደረጃ ዝግጅት የጀመሩ ግለሰቦችም ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ መክረዋል፡፡

ከዚህ በፊትም የኢትዮጵያ ሚሊኒየም በዓልን አስመልክቶ በእያንዳንዱ አጥቢያ 10ሺህ ብር የተከፈለበት የፓትርያርኩን ፎቶ የያዘ ፓስተር መሰቀሉ በበርካታ ምዕመናን ዘንድ ቁጣን መቀስቀሱና ሐዘን ማሳደሩ ይታወሳል፡፡

30 comments:

ኦርቶዶክስ ዩናይት said...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ለመሆኑ ፓትርያርኩ አማካሪ የላቸውም ወይስ የቤተ ክርስቲያንን ትምሀርት አልተማሩም። በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትዕዛዝና የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ነው ሰው በህይወቱ እያለ ፎቶውን የሚያስለጥፈው? እንዲያው እንደ አለማዊያን ሰዎች እንኳን ይደረግላቸው ቢባል ምን መልካም ስራ ስለሰሩ ነው?
በአጠገባቸው ያላችሁ አድር ባዮችና የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ሆይ አስብቡበት። የእግዚአብሔርን ህግ እየተላለፋችሁ የቤተ ክርስቲያንን ስርዓት እያፋለሳችሁ፡ ሰውየውንም ወደ ፈተና እየወሰዳችሁ ነው።
ይህ ሐውልት የሚሰራበት የቦሌ መድሐኒያለም ምዕመናንና ካህናት ልትቃወሙት የሚገባ ጉዳይ ነው።

እግዚአብሔር ለሁሉም ማስተዋል ያድለው። ራሱን ከፍ ከፍ የሚያድርግ ዝቅ ይላልና ጳውሎስ ሆይ በእግዚአብሔር ዘንድ ከፍ ለማለት ከፈልጉ ለህዝበዎ የሚመች ነገር ያድርጉ።

Anonymous said...

ያሁኑ ይባስ

ውድ ደጀሰላማውን ከፓትርያርኩ በአለ ሲመት ጋር የተገናኘ አስገራሚ ትእይንት በአዲስ አበባ
እነበጋሻው ለፓትርያርኩ በአለ ሲመት ጉባኤ ሊያዘጋጁ መሆኑ ተሰማ ለምን አላማ እንደሚያዘጋጁ ለእኔ በጣም ግልጽ ነው /ሰሞኑን አያደረጉ ያለው ቤተክርስቲያኗን ለመናፍቀን አሳልፈው ለመስጠት የሚያደርጉት በእግዚአብሔር ድንቅ ስራ ገሀድ እየሆነባቸው ከብዙ መድረክም እየታገዱ እነሱ የሚያዘጋጇቸው መዝሙራትም ሆነ ስብከት አዳማጭ እያጣ በመምጣቱ ትልቅ ኪሳራ ላይ ስለሆኑ የእስትራቴጂ ለውጥ እየደረጉ ስለሆነ ይህ የአዲሱ እስትራቴጂያቸው አከል መሆኑ ነው/ እንጂ አቶ በጋሻው ቀድም ብሎ ሲቃወመው የነበረው ሥራ አደለም ወይ ለቅዱስነታቸው ቅኔ ለምን የቀርባል እግዚአብሔር ተረስቶ የበተክርስቲያኗ ሀብት ተበዘበዘ ሲል የነበረ አሁን ለእርሱ እስትራቴጂ አመቺ ሲሆን ግን በስማቸው ጉባኤ ለማዘጋጀት መሯሯጡ የእግዚአብሔርን ለሰው መስጠት አይሆንም/
ሌላው የሚያስገርመው ነገር የጉባኤው አዘጋጆች ጉዳይ
• ቀሲስ ሰሎሞን ሙሉጌታ / ግራ የገባው የሚያምታታ ቄስ
• ጌታቸው ዶኒ /አጥማቂ ተንቋይ/
• መምህር በሪሁን/ የበጋሻው ተሳቢ/ ሌሎችም
• የክብር እስፖንሰር የነበጋሻው ማኅበር ቅድስት ማርያም የስብከተ ወንጌል ማኅበር - ይህ ማኅበር የሚመራው ዘፋኝ ሲያስለቅስ ኖሮ በዘፈን በኩል ያለው ስራ አላዋጣ ሲል ከነበጋሻው ከነ ያሬድ አደመ ከነ ትዝታው ሳሙኤል ጋር በመሆን ለሌላ ሚሽን የተሰለፈ በቤተክርስቲያን ውስጥ ምንም ድርሻ የሌለው ተራ ነጋዴ ነው ፡፡
እባካችሁ ለቤተክርስቲያን ጸልዩ ፡፡

Anonymous said...

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን

ያሁኑ ይባስ

ውድ ደጀሰላማውን ከፓትርያርኩ በአለ ሲመት ጋር የተገናኘ አስገራሚ ትእይንት በአዲስ አበባ
እነበጋሻው ለፓትርያርኩ በአለ ሲመት ጉባኤ ሊያዘጋጁ መሆኑ ተሰማ ለምን አላማ እንደሚያዘጋጁ ለእኔ በጣም ግልጽ ነው /ሰሞኑን አያደረጉ ያለው ቤተክርስቲያኗን ለመናፍቀን አሳልፈው ለመስጠት የሚያደርጉት በእግዚአብሔር ድንቅ ስራ ገሀድ እየሆነባቸው ከብዙ መድረክም እየታገዱ እነሱ የሚያዘጋጇቸው መዝሙራትም ሆነ ስብከት አዳማጭ እያጣ በመምጣቱ ትልቅ ኪሳራ ላይ ስለሆኑ የእስትራቴጂ ለውጥ እየደረጉ ስለሆነ ይህ የአዲሱ እስትራቴጂያቸው አከል መሆኑ ነው/ እንጂ አቶ በጋሻው ቀድም ብሎ ሲቃወመው የነበረው ሥራ አደለም ወይ ለቅዱስነታቸው ቅኔ ለምን የቀርባል እግዚአብሔር ተረስቶ የበተክርስቲያኗ ሀብት ተበዘበዘ ሲል የነበረ አሁን ለእርሱ እስትራቴጂ አመቺ ሲሆን ግን በስማቸው ጉባኤ ለማዘጋጀት መሯሯጡ የእግዚአብሔርን ለሰው መስጠት አይሆንም/
ሌላው የሚያስገርመው ነገር የጉባኤው አዘጋጆች ጉዳይ
• ቀሲስ ሰሎሞን ሙሉጌታ / ግራ የገባው የሚያምታታ ቄስ
• ጌታቸው ዶኒ /አጥማቂ ተንቋይ/
• መምህር በሪሁን/ የበጋሻው ተሳቢ/ ሌሎችም
• የክብር እስፖንሰር የነበጋሻው ማኅበር ቅድስት ማርያም የስብከተ ወንጌል ማኅበር - ይህ ማኅበር የሚመራው ዘፋኝ ሲያስለቅስ ኖሮ በዘፈን በኩል ያለው ስራ አላዋጣ ሲል ከነበጋሻው ከነ ያሬድ አደመ ከነ ትዝታው ሳሙኤል ጋር በመሆን ለሌላ ሚሽን የተሰለፈ በቤተክርስቲያን ውስጥ ምንም ድርሻ የሌለው ተራ ነጋዴ ኤፍሬም የተባለው ነው ፡፡

enih tsadik kidus, tagay, woyane men yalhonut ale belew belew bedngiya lay liqertsuachew. yihen wurdet sayayu bimotu yishalachew neber. " bietekerstiyanachinm erefet tagegne nebere"

desa said...

egzioo meharne kirstose belu 41!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

Anonymous said...

Ha ha ha ha.... Mashila hoduwa eyarere ale yehagere sewu?

Desi yalegn neger gin yesachewu hawult maserat sayihon yene hatiyat esachewun yemesele yebetekiristian meri mamtatun maweke newu.

Anonymous said...

PLEASE LET'S STOP BLAMING EACH OTHER.EVERYONE WHO IS INVOLVED IN THE DRAMA WILL BE PUNISHED.CAN'T WAIT TO SEE!!!

Anonymous said...

BTHIS IS SO SHAME FOR ABBA PAULOS
IS HE REALY INTELLECTUAL AND EDUACATED? WE ARE LOOKING SO MANY BAD AND WORREST THINGS IN THE CHRCH. i THINK HE IS THE REAL ENEMY OF OUR CHURCH. SORREY FOR ALL THINGS.

Anonymous said...

this is the game b/n w.ro? eJIGAYEHU the X wife of Artist Mohamud Ahimed (welde tinsae) she divorced him as soon as he baptised and asked her to be one in Eucharist, but she refused and said that "ruchayen alchereskum"

As we know, hER enemity for the church started right there.

Anonymous said...

Ho ho ho.... Wey ኤልዛቤ...ል?

Wey Abune Petros... "Minewu Emamlak Ethiopian Chekenshibat?" Ahun gebagn yeErswo lekso.

Wey Abune Paulos bekumwot hawult aseru!!!? Lenegeru tiru misikirinet newu kemotewu ayitenanesum ersiwo. Ersiwo hawult siyaseru menafikanina eslamoch lijochachinin netkewu cheresu. Wedebetekiristian yetesheshegewun wetat letiyit asalifewu yesetu yemejemeriya Ethiopiyawi Papas! LeErsiwo hawult kaltesera leman yisera!?

Wuy wuy wuy.... Alekeskulewot zare ermen awetahu! Beka beka beka...

Anonymous said...

በእንተ ጣዖት
1.ይቤ እግዚአብሔር

...የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ።...

2.ትቤ ቤተ ክርስቲያን

ከእንግዲህ ወዲያ ጣዖት ለኤፍሬም/ለቤተ ክርስቲያንን / ምንድር ነው? እኔ ሰምቼዋለሁ፥ ወደ እርሱም እመለከታለሁ፤ እኔ እንደ ለመለመ ጥድ ነኝ፤ ፍሬህ በእኔ ዘንድ ይገኛል። ይህን ነገር የሚያስተውል ጠቢብ፥ የሚያውቃትም አስተዋይ ማን ነው? የእግዚአብሔር መንገድ ቅን ነው፥ ጻድቃንም ይሄዱበታል፤ ተላላፊዎች ግን ይወድቁበታል።
ትን.ሆሴዕ 14:8-9

3.ይቤ ምዕመን
..ሆይ፥ በዚህ ነገር እንመልስልህ ዘንድ አስፈላጊያችን አይደለም።
የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፥ ...ሆይ!ነገር ግን፥ ...ሆይ፥ እርሱ ባያድነን፥ አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ ...

ከቤተ ክርስቲያኒቱ ትውፊት እና ሥርዓት አንጻር ፓትርያርኩ በሕይወት እያሉ ሐውልት ማቆም ጣዖት አምልኮ ነው።
ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን ዕወቅ፣ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፣
የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፡፡ 2ኛጢሞ.3÷5

Anonymous said...

erqi ena selam bebetekiristianachin mayet tiru new .

Unknown said...
This comment has been removed by the author.
Unknown said...
This comment has been removed by the author.
selamawi said...

በስመ ስላሴ አሃዱ አምላክ አሜን

ሰላም በክርስቶስ ወገኖቹ ለሆናችሁ ሁሉ ሰላም ለናንተ ይሁን

መቸም ,,እለት ለእለት ትጎስእ ነቢበ ወሌሊት ለሌሊት ታየድእ ጥበበ,, እንደሚለው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ሰው በየእለቱ በሰው ልጅ የሚፈጸሙት ተግባራት በጣም የሚያሳዝኑ ናቸው ይህ ሲሆን ግን እግዚአብሔር አያውቅም ማለት አደለም እያየ ግን እንዳላየ ዝም ይላል ,, መዝሙረኛው ዳዊት 2፥4 በሰማይ የሚኖር እርሱ ይሥቃል፥ ጌታም ይሣለቅባቸዋል። ,, እንዳለው እራሳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር ከፍ ለማድረግ የሚሞክሩትንና ተከታዮቻቸውን እግዚአብሔር አንድ ቀን ጽዋው ሲሞላ ፍርዱን ይሰጣል እኔ ግን ለነሱ አዝናለሁ እንጅ ለመፍረድ አልነሳም ይገርማችኋል,,,ነገ ሌላ ቀን ነው ,, ትእግስት ብቻ ቤተክርስቲያን እንደሆነች አንድ ጊዜ በክርስቶስ ደም ተመስርታለች ማንም አያናውጻትም በመጨረሻ የምለው የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳዲዎች ለአቡነ ጳውሎስ ይህን ያህል ከሚደክሙ ጥቂት ነገር ለክርስቶስ ቢያደርጉ ምንያህል ዋጋ እንዳለው እንዴት ማወቅ ተሳናቸው ? ጊዜ ይመልሰው

Anonymous said...

Kesis Selomon Mulugeta mekari zemed yelwum wey, Ebakachihu an'd belut.
Pleas, Kesis yihen Blog yemitaneb kehone Kenezih Meseriwoch gar batitebaber yishalehal.Kalhone Yantem Yekilet zemen Teqarbual Malet newu.

Yihuna

Anonymous said...

kesis solomon lewnet yeqome ymahbertegnet semet yelelew new

Anonymous said...

ለእኔ የሚደንቀኝ የፓትርያርኩ አይደለም፡፡ የበጋሻው ሁኔታ ግን በጣም ያሳዝናል፡፡ የሱን መጽሐፍ አንብቤ መስቀል አደባባይ ድንጋይ የወረወርኩበት እጄ ለራሴ አስጠልቶኛል፡፡ በዚሁ ድረ ገጽ ላይ የበጋሻው ቲፎዞ ሆኜ ዘመድኩንና ማህበረ ቅዱሳንን (ማህበረ ሰይጣን) በማለት ከሚሳደቡት ወገን አንዱ ነበርኩኝ፡፡ አሁን ግን ስለ በጋሻው ምንም አልልም፡፡ መጀመሪያ …..ቀጥሎም ባላፈርሽ ሆኖብኛል ፡፡ በጋሻው ሆይ; አሳፈርከኝ፡፡ መምህር ጰውሎስን ግን የነሱ ደጋፊ በመሆኔ ከመሬት ተነስቼ እጠላው ነበር፡፡ የነ በጋሻው ደጋፊዎች ጥሩ ነገር ስለ ጳውሎስ ስለማያወሩልኝ ከ 3 ክፍለ ሀገር(ጎንደር፣አረካና ዝዋይ) ስለ እርሱ የሰማሁትን ቅዱስ ነገር መቀበል አቅቶኝ ነበር፡፡ ኦ አምላኬ….እኔ አጢአተኛ ነኝ፡፡(ወለተ ኪሮስ)

Anonymous said...

የተቀረጸውን ምስል የሚሠሩ ሁሉ ከንቱዎች ናቸው፥ የወደዱትም ነገር አይረባቸውም፤ ምስክሮቻቸውም አያዩምና አያውቁም፤ ስለዚህ ያፍራሉ። ኢሳ.44:9
• ቀሲስ ሰሎሞን ሙሉጌታ
• ጌታቸው ዶኒ
• መምህር በሪሁን
• አቶ በጋሻው
• ትዝታው ሳሙኤል
• ያሬድ አደመ
• ኤፍሬም
• ኤልዛቤል....የሐሰተኞችን ምልክት ከንቱ አደርጋለሁ፥ ምዋርተኞችንም አሳብዳለሁ፥ ጥበበኞቹንም ወደ ኋላ እመልሳለሁ እውቀታቸውንም ስንፍና አደርጋለሁ፤ ...ይላል እግዚአብሔር

Anonymous said...

ጥያቄ1 አቡነ መልከጸዲቅን ማን ገደላቸው፡፡
መልስ፡ እነ በጋሻውና አቡነ ጳውሎስ
ጥያቄ 2 ፡እንዴት
መልስ ፡ እነ በጋሻው ከህዝብ አጣሉአቸው፡፡
አባ ጳውሎስ …. እንደተለመደው….
ጥያቄ 3 ለምን
መልስ ፡ ሊታረቁ ነዋ፡ ያለ መስዋእት እርቅ የለማ
ጥያቄ4 እና በመልከጸዲቅ ሞት ታረቁማለትሽ ነው እንዴት ሊታመን ይችላል?
መልስ ፡ እመኚኝ ለዚህ ምልክቱ ሐውልቱ
ጥያቄ 5 ሐውልቱ?
መልስ፡ ታዲያስ እነ በጋሻው ከሞቱት ጋር ለቤተክርስቲያን በሰበሰቡት ብር በቁም ለሞተው ሐውልት እያሰሩ አይደል፡፡
ጥያቄ 6 አሃ.. ገባኝ.. ለዚህ ነዋ ሳያስቀብሩ የቀሩት…
መልስ፡ ታዲያስ እንጂ፡፡ የሞተ ሰው ህያውን አይቀብረውም ፡፡ ሙታን ሙታንን ዐይደል እንዴ
የሚቀብሩት፡፡
ጥያቄ 7፡ ልክ ነው መልከጼዲቅ ሕያው ነው፡፡ በስራው ይታወቃል፡፡ እስኪሞት ሰራ፡ ጳውሎስ ደግሞ
እስኪሞት በላ ዘረፈ በቁሙ ሞቻለሁ ሐውልት ስሩልኝ አለ፡፡ አይደል?
መልስ ትክክል ነሽ አሁን ገባኝ በጋሻውና አባ ጳውሎስ ነፍስ ገብረው ለዘረፋ ተስማሙ ማለት ነዋ?
ጥያቄ8 በትክክል
መልስ አቤት! አቤት! አቤት! ጉድ በጋሻውን የአባታችን አቡነ መልከጸዲቅ አምላክ ይፋረደዋ፡፡
ጥያቄ 9 ተይ ቢታረቀው ይሻላል፡፡
መልስ ፡ እሱስ ልክ ነሽ፡፡ እኔ የምለው የነ በጋሻውስ ይሁን የቀሲስ ሰሎሞንስ ምን የሚሉት ነው?
ጥያቄ 10 እኔኑ ጠየቅሽኝ? በይ ነገ ጠይቄ መጣለሁዋ ፡፡ የነገ ሰው ይበለን ደህና እደሪ፡፡

Anonymous said...

ወይ መሰረት አታላይ፡ “እስመ ስም ይቀድሞ ለግብር” አሉ አበው የድሮዎቹ፡፡ ድሮስ ከአታላይ ልጅ ምን ልንጠብቅ ኖሯል፡፡ ይሄ… የአባቱ ልጅ፡፡ ደግሞ በዘመናቸው ትላለክ? የዘመን ባለቤትም ሆኑ አይደል? አንተና ወ/ሮ እጅጋየሁ (የሲኖዶሱ በላይ ጠባቂት) ካላችሁ ምን ችግር አለ፡፡ሴቷ ፓትሪያርክ ካለች ሁሉ ይሆናል፡፡ አይ ጊዜ …….. እንዲሁ አይቀጥልም ባለቤቱ ብቻ አይለወጥም፡፡

ሳሙኤል፡ዘአሰቦት said:

ለአውሬው፡ሃውልት፡ያውም፡መድኃኔ፡ዓለም፡
ቤተ፡ክርስቲያን?

እጅጉን፡እናዝናለን።ሠሪዎቹንና፡አሠሪውን፡
እግዚአብሔር፡ፍርዳቸውን፡እንደሚሰጣቸው፡
አንጠራጠርም!

ሊያውስ፡ነጩ፤ልብሰ-አውሬ፡ብዙ፡አመልክቶናል፡እኮ!
ዛሬ፡ሸንጋይና፡ተሸንጋይ፡የዕምነት፡ጓዳችንን፡
ምንኛ፡እንዳረከሱት፡ዳግም፡የምንገነዘብበት፡
ወቅት፡ነው።

አቤቱ፡መድኃኔ፡ዓለም፡ክርድቶስ፡አንተ፡ፍረድልን!
ክብርና፡ምስጋና፡ለዘላለሙ፡ላንተ፡ይሁን!!!አሜን።

ሳሙኤል፡ዘአሰቦት

Anonymous said...

kesis solomon lewnet yeqome ymahbertegnet semet yelelew new

Anonymous said...

ጥያቄ1 አቡነ መልከጸዲቅን ማን ገደላቸው፡፡
መልስ፡ እነ በጋሻውና አቡነ ጳውሎስ
ጥያቄ 2 ፡እንዴት
መልስ ፡ እነ በጋሻው ከህዝብ አጣሉአቸው፡፡
አባ ጳውሎስ …. እንደተለመደው….
ጥያቄ 3 ለምን
መልስ ፡ ሊታረቁ ነዋ፡ ያለ መስዋእት እርቅ የለማ
ጥያቄ4 እና በመልከጸዲቅ ሞት ታረቁማለትሽ ነው እንዴት ሊታመን ይችላል?
መልስ ፡ እመኚኝ ለዚህ ምልክቱ ሐውልቱ
ጥያቄ 5 ሐውልቱ?
መልስ፡ ታዲያስ እነ በጋሻው ከሞቱት ጋር ለቤተክርስቲያን በሰበሰቡት ብር በቁም ለሞተው ሐውልት እያሰሩ አይደል፡፡
ጥያቄ 6 አሃ.. ገባኝ.. ለዚህ ነዋ ሳያስቀብሩ የቀሩት…
መልስ፡ ታዲያስ እንጂ፡፡ የሞተ ሰው ህያውን አይቀብረውም ፡፡ ሙታን ሙታንን ዐይደል እንዴ
የሚቀብሩት፡፡
ጥያቄ 7፡ ልክ ነው መልከጼዲቅ ሕያው ነው፡፡ በስራው ይታወቃል፡፡ እስኪሞት ሰራ፡ ጳውሎስ ደግሞ
እስኪሞት በላ ዘረፈ በቁሙ ሞቻለሁ ሐውልት ስሩልኝ አለ፡፡ አይደል?
መልስ ትክክል ነሽ አሁን ገባኝ በጋሻውና አባ ጳውሎስ ነፍስ ገብረው ለዘረፋ ተስማሙ ማለት ነዋ?
ጥያቄ8 በትክክል
መልስ አቤት! አቤት! አቤት! ጉድ በጋሻውን የአባታችን አቡነ መልከጸዲቅ አምላክ ይፋረደዋ፡፡
ጥያቄ 9 ተይ ቢታረቀው ይሻላል፡፡
መልስ ፡ እሱስ ልክ ነሽ፡፡ እኔ የምለው የነ በጋሻውስ ይሁን የቀሲስ ሰሎሞንስ ምን የሚሉት ነው?
ጥያቄ 10 እኔኑ ጠየቅሽኝ? በይ ነገ ጠይቄ መጣለሁዋ ፡፡ የነገ ሰው ይበለን ደህና እደሪ፡፡

Anonymous said...

Esachew Alismeu Yehoen ? Bismeu Kedmeo Endmaygbea Yengreu Nebir

Balen Edme Yayenew Ye Lenin Hawlit new
Ena baytsbe Genzbeu Letrbeeu Wegnoche Ena Letzgeu Gedmtoche Biwel Leraschew Bezeu Berkte Yehunlchewa

Yesmaybteu aysalem wey ?

Ebakcheu Girea Endangbea Be USA Yaluit Thadso Yehoniuten Tekbliweal Tebalen Wedagrchnem Endanzhoen Segawi Yehoen Mengied Endaytfian Entsley
EGZIABHER Yasben Amen

Anonymous said...

this is the time we have to see our sin. that is why pope paulos has constract his "hawult" when he is alive. deadline for his spirituality.

Anonymous said...

leave alone the pope; he is getting mad.
Egziabiher betecrstianin Yitebik

Anonymous said...

this is the time we have to see our sin. that is why pope paulos has constract his "hawult" when he is alive. deadline for his spirituality.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)