July 22, 2010

ትንቢቱ ሲፈጸም

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 22/2010)፦
(አግናጢዎስ ዘጋስጫ)
ትንቢቱ ሲፈጸም በመጽሐፍ ያለው፣
ወገኔ አትደንግጡ ይህ ሊሆን ግድ ነው።
ቅዱሳን ሳይቀሩ የተመረጡቱ፣
በመጨረሻው ቀን በዓለም እንዲስቱ፣
ቀድሞ በመጽሐፍ ተነግሯል ትንቢቱ።

የእውነት ደብዛ ጠፍቶ ሐሰት መሰልጠኑ፣
ሥርዓት ተጥሶ ነውሩ ጌጥ መሆኑ፣
አይቀሬ ነውና ወገን አትደንግጡ፣
ከመጣብን ቁጣ በጸሎት አምልጡ።

የእግዚአብሔር ሰገነት ሲቀየር በጣዖት፣
በቅዱሱ ሥፍራ ሲፈጸም እርኩሰት፣
በአደባባይ ሲታይ ሰይጣን አካል ነሥቶ፣
ከዚህ የበለጠ ምን ይመጣል ከቶ?

ቅዱሳን ተናቁ አፈኞች ተሾሙ፣
ንጹሐን ተዋርደው ሌቦች ተሸለሙ።

በቅዱስ መስቀሉ በድኅነት ምልክት፣
የእብነ በረድ ሐውልት ጣዖት ባረኩበት፣
ጸጋ ቢሰጣቸው መንጋ እንዲጠብቁ፣
በውዳሴ ከንቱ በገንዘብ ወደቁ።

ብዙ ፈርኦኖች በኢትዮጵያ ነገሱ፣
የአባቶችን ድንበር ሥርዓት አፈረሱ፣
በውል ሳይታወቅ ማን እንደሾማቸው፣
በቤቱ ቀለዱ እነርሱ እንዳሻቸው፣
አየ የጥፋት ቀን የዓለም መጨረሻ፣
የሐሳዊ መሲህ የአውሬው መንገሻ፣
እጅግ ያሳዝናል ኢትዮጵያ መሆኗ፣
ትንሽ ሳታገግም ከትናንት ሀዘኗ።
በገንዘብ ተገዝተው ሀሰት ቢናገሩ፣
በውዳሴ ከንቱ በዓለም ቢኖሩ፣
ሁዋላ አይጠቅምም ከቶ በሞት ስንጠራ፣
እግዚአብሔር ፊት ሲቀርብ የሠራነው ሥራ፣
መሳሳት ያለ ነው መውደቅ መነሳቱ፣
ፍጹም ስላልሆነ ሰው በሰውነቱ፣
ነገር ግን ትልቁ ሊያድን የሚችለው፣
ሰው ስህተቱን አውቆ ሲመለስ ብቻ ነው፣
ስለዚህ ኤልዛቤል አክዓቦችም ሁሉ፣
የናቡቴን ርስት እንቀማ ስትሉ፣
አምላክ ተቆጥቶ እንዳያጠፋችሁ፣
መመለስ ይሻላል ከክፉ ሥራችሁ።

እናንተም አባቶች አበው ቅዱሳኑ
መከራን ሳትፈሩ በእምነታችሁ

9 comments:

Anonymous said...

Dear Ethiopians,

I got this message from http://www.aleqayalewtamiru.org pls. read it. Let us cry, pray & ask the Almighty God to save guard our faith from the hands of the covcious foxes.

ለፓትርያርክ አባ ጳውሎስ ሐውልት ሊቆም መታሰቡን በመቃወም የቀረበ መግለጫ።

«እውነትን ዐውቀው በክፋታቸው በሚለውጡአት በዐመፀኛውና በኃጢአተኛው ሰው ሁሉ ላይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መቅሠፍት ከሰማይ ይመጣል። እግዚአብሔርን ማወቅ በእነሱ ዘንድ የተገለጠ ነውና፤ እግዚአብሔርም ገለጠባቸው። ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ታይቶ የማይታወቅ እግዚአብሔር የፈጠረውን ፍጥረት በማሰብ በመመርመር ይታወቃል፤ ከሃሊነቱ፥ የዘለዓለም ጌትነቱም እንዲህ ይታወቃል፤ መልስ የሚሰጡበት ምክንያት እንዳያገኙ። እግዚአብሔርን ሲያውቁት እንደ እግዚአብሔርነቱ አላመኑትም፤ አላመሰገኑትምና፤ ካዱት እንጂ፤ በገዛ ዐሳባቸው ረከሱ፤ ልቡናቸውም ባለማወቅ ተሸፈነ። እንራቀቃለን ሲሉ ደነቆሩ። የማይሞተውን የእግዚአብሔርን ክብር ለውጠዋልና፤ የሚሞት የሰውን መልክ አምሳያ አድርገዋልና፤ በእንስሳ አምሳያ፥ በአራዊት አምሳያ፥ በአዕዋፍ አምሳያ አድርገዋልና። ስለዚህም መልሶ ተዋቸው፤ በገዛ እጃቸው ራሳቸውን እንዲያረክሱ፤ ሰውነታቸውንም እንዲያጎሰቁሉ። የእግዚአብሔርንም አምላክነት ሐሰት አድርገዋታልና፤ ተዋርደውም ፍጥረቱን አምልከዋልና፤ ሁሉን የፈጠረውን ግን ተዉት፤ ይኸውም ለዘለዓለም የሚኖር የባሕርይ አምላክ ነው።» (ሮሜ፤ ፩፥ ፲፰ - ፳፭።)

የተወደዳችሁ ምእመናን!

በቅርቡ በመገናኛ ብዙኃን (አዲስ አድማስ ጋዜጣ፥ ሰኔ ፳፮ ቀን ፳፻፪ ዓ. ም.) የቀረበውን ለፓትርያርክ አባ ጳውሎስ በአዲስ አበባ ቦሌ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ሐውልት ሊቆም መታሰቡን በመግለጽ የቀረበውን ዜና በኀዘን አንብበናል። ይህ ሐሳብ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት፥ ሥርዓትና ባህል ውጪ በመሆኑ፤ በኢትዮጵያ አምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የምንቃመው መሆኑን እየገለጽን ክቡር አባታችን አለቃ አያሌው ታምሩ የዛሬ ፲፬ ዓመት በገናናው ጋዜጣ አማካይነት ያስተላለፉትን ሁለተኛ ቃለ ግዝት እንድታነቡ እንጋብዛለን።

ገናናው ጋዜጣ፤ ሐምሌ ፭ ቀን ፲፱፻፹፰ ዓ. ም.
አለቃ አያሌው ታምሩ ሁለተኛውን ቃለ ግዝታቸውን ሰጡ።

«አንበሳ አገሣ፤ የማይፈራ ማነው? ጌታ እግዚአብሔር ተናገረ፤ የማይደነግጥ፥ የማይታዘዝ፥ የማይፈራ፥ የማይናገር ማነው?»

ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምእመናን በሙሉ! በአሁኑ ጊዜ በኦርቶዶክሳዊው የሊቃውንት ጉባኤና በእምቢተኞች የቤተ ክርስቲያን መሪዎች መካከል በዚህ ዓመት በተለይም ከመጋቢት እስከ ዛሬ የሚደረገውን፥ በመደረግ ላይ ያለውን ሃይማኖታዊ ትግል በልዩ ልዩ መንገድ እንደ ተከታተላችሁ አምናለሁ።

አባቶቼ ካህናት፥ ወንድሞቼ፥ እኅቶቼ ምእመናንና ምእመናት! የሌኒን ጣዖት በአፍሪካ አንድነት ድርጅት አጠገብ፤ የሌኒን፥ የማርክስ፥ የኤንግልስ ጣዖታት ምስሎች በአብዮት ዐደባባይ፤ የልዩ ልዩ ወታደሮች ምስል በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አጠገብ በተሠራው ሐውልት ላይ፤ እንዲሁም በልዩ ልዩ ስፍራ ልዩ ልዩ ምስሎች ተሠይመው ማንም የአበባ ገጸ በረከት መሥዋዕት ሳይቀር ያቀርብላቸው በነበረበት፥ በየዐደባባዩ የደም መፍሰስ፥ የለቅሶ፥ የዋይታ ድምፅ ሲያስተጋባ በነበረበት በዚያ የ፲፯ ዓመት ትዝታ ማንም አባት ዐብሮአችሁ ያልነበረ ሲሆን በትግላችሁ ያልተለየሁ እግዚአብሔር የሾመላችሁ የወንጌል ሰባኪ ሐዋርያ እንደ ሆንኩ አምላኬም፥ እናንተም ምስክሮች ናችሁ።

ይሻላል ያሉት ኩል ዐይን አጠፋ ሆነና ይሆናሉ የተባሉ አባቶች በማንኛውም ጊዜ በዐደራ የተቀበሏትን ቤተ ክርስቲያንና ምእመናኖቿን በአምላካቸው ስም መጠበቅ ሲገባቸው ትናንትም ዛሬም የመንግሥት ደጋፊ ሆነው እያስቸገሩን ነው። ብዙ መናገር ይቻላል፤ ግን እታገሣለሁ። ሆኖም ቁም ነገሩን ማለፍ አልችልም። የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአበው ውግዘት ተጣሰ፤ የቤተ ክርስቲያን ክብር ተገሠሠ እያልን አቤቱታችንን እያሰማን መንግሥት በሃይማኖት አያገባኝም ብሎ እጁን አውጥቷል። አይጠይቀንም በማለት ይመስላል። የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎች በዕብሪት፥ በትዕቢት በበደል ላይ በደል ሲጨምሩ፥ ኦርቶዶክሳዊውን የሊቃውንት ጉባኤ ሊያፈርሱ ሲፈልጉ በጉልበታቸው በሥልጣናቸው ተጠቅመው የቤተ ክርስቲያኒቱን አባሎች ከሥራና ከደመወዝ ሲያባርሩ፥ ይህም አልበቃ ብሎአቸው በክስ ሲያጉላሉ፤ ይህን ሁሉ እየሰማ፥ እያወቀ ፍርድ ሊሰጥ፥ ዐመፀኞችን ሊቀጣ፥ ቤተ ክርስቲያንን ከደረሰባት በደል ነጻ ሊያወጣ የሚገባው ሲኖዶስ የግፍ ግፍ ሚያዝያ ፴ ቀን ፲፱፻፹፰ ዓመተ ምሕረት አጽድቆ ባወጀው፥ ሕገ ቤተ ክርስቲያን ሲል በጠራው የአምልኮ ጣዖት ሕግ ፓትርያርኩን በመንፈስ ቅዱስ ፈንታ በሲኖዶስ ሥልጣንና ተግባር አመራር ሰጪ፥ የሲኖዶሱን አባሎችም ለቤተ ክርስቲያን ተጠሪ መሆናቸው ቀርቶ ለፓትርያርኩ ተጠሪዎች በማድረግ በቤተ ክርስቲያን ላይ የአመልኮ ጣዖት ዐዋጅ ዐውጆአል።

ለዚህም ሐምሌ ፮ ቀን ፲፱፻፹፰ ዓመተ ምሕረት በዓሉን ለማክበር በመዘጋጀት ላይ ስለ ሆነ ይህ ስሕተት እንዲታረም በዓሉ ከመድረሱ በፊት ሕጉን ጳጳሳት ተሰብስበው ሚያዝያ ፴ ቀን ፲፱፻፹፰ ዓመተ ምሕረት አምልኮ ጣዖት ያወጁበትን፥ መንበረ ማርቆስን ነቅለው መንበረ ጣዖት የተከሉበትን ሕግ እንዲሽሩ፥ ወደ ጣዖትነት ያደጉትን ፓትርያርክም ከሥልጣን እንዲያነሡ በቃለ ግዝት ሰኔ ፳፯ ቀን ፲፱፻፹፰ ዓመተ ምሕረት በነጻው ፕሬስ በኩል በመብሩክ ጋዜጣ በፈጣሪዬ ስም መልእክት ማስተላለፌ ይታወሳል። እነሱ ግን ምንም እርምጃ አልወሰዱም፤ ጥያቄዬንም አልተቀበሉም። እግዚአብሔር አምላክ ግን ቦታውን ለጣዖት አልሰጠም፤ መንበሩንም አልለቀቀም። የሚሰማው ቢያገኝ እየተናገረ፥ ምክርና ተግሣፅ እየሰጠ ነው።

በሥልጣናቸው ተደግፈው እግዚአብሔርንና ቤተ ክርስቲያንን የሚዋጉትና በመንፈስ ቅዱስ አንዳኝም በማለት ትግላቸውን የቀጠሉት አቡነ ገሪማ፥ እንዲሁም የፓትርያርኩ አጋፋሪ ብርሃኑ መኮንን ግን የአድባራትን፥ የገዳማትን አስተዳዳሪዎችንና ካህናትን በማስተባበር በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ሥላሴን መንግሥት ሽረው ጣዖት ሊያገለግሉ፥ በዓል ሊያከብሩ ፕሮግራም አውጥተዋል። ከልዩ ልዩ ጌጣጌጥ ጀምሮ እስከ ዊስኪ መጠጥ፥ ጮማ ቁርጥ ድረስ በብዙ ሺሕ የሚቆጠር የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ እየወጣ ድግስ እየተዘጋጀ ነው። ስለዚህ እነሱ ቢንቁኝ አልደነቅም። ቃሉ ደግሞ አይናቅም። በጠቅላላ ቤተ ክህነትና መሪዎቹ ለእግዚአብሔር አንታዘዝም ያሉ ስለ ሆነ ካህናትና ምእመናን ለዐመፅ እንዳትተባበሯቸው፥ በዓሉን እንዳታከብሩ፥ ድግሱንም እንዳትበሉ በቤተ ክርስቲያን አምላክ ስም፥ በኢትዮጵያ አምላክ ስም እጠይቃችኋለሁ። ሊቃነ ጳጳሳት፥ ኤጲስ ቆጶሳት በአምልኮ ጣዖት ስም ሚያዝያ ፴ ቀን ያወጃችሁትን ሕግ እንድሽሩ፥ የሠየማችኋቸውንም እንድታነሡ፥ በቤተ ክርስቲያንና በምእመናኖቿ ላይ የጫናችሁትን ቀንበር እንድታስወግዱ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እጠይቃችኋለሁ። እምቢ ብትሉ ግን በቃለ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ፥ በቃለ ሐዋርያቱ አሁንም ገዝቼአለሁ።

የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ አለቃ አያሌው ታምሩ ዘዲማ ጊዮርጊስ።

MelkamTibebu said...

አግናጢዎስ ዘጋስጫ ቃለ ሕይወት ያሰማልን። በመጀመሪያ በግጥምህ መግቢያው ላይ "ቅዱሳን ሳይቀሩ የተመረጡቱ፣
በመጨረሻው ቀን በዓለም እንዲስቱ፣ ቀድሞ በመጽሐፍ ተነግሯል ትንቢቱ።" የሚለው ቢስተካከል ምክንያቱም በማቴዎስ 24፡24 ላይ እንደተጻፈ ቤዛ አለም ክርስቶስ ያለው "ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ።" ነው እንጂ የተመረጡትን ያስታሉ አላለም። የተለየ መልዕክት የሚያስተላልፍ እንዳይሆን ብዩ ነው ምክንያቱም የተመረጡት የኋላ ኋላ የሚስቱና ወደ ገሃነመ እሳት የሚጣሉ ከሆነ ማን ይድናል በሚል ምዕመናን ተስፋ ሊቆርጡ ይችላሉና።

በተጨማሪ በግጥምህ ዙሪያ እንዲሁም ፓትርያርኩ በቦሌ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ሐውልታቸውን ካስቆሙበት ጊዜ ጀምሮ በሚሰጡ አስተያየቶች ላይ ጥቂት ለማለት ፈለግሁ። የአህዛብ ሐዋርያ ብርሃነ አለም ቅዱስ ጳውሎስ እንደመከረን ንግግራችን ሁልጊዜ፥ በጨው እንደ ተቀመመ፥ በጸጋ ቢሆን መልካም ነው(ቆላ 4፡6)። ሁልጊዜ ስድብ ላይ ካተኮርን ከእኛ የሚጠበቅብንን እንዳንረሳ እሰጋለሁ። ዘመኑን ስንመረምር የሚያሳየን ሁላችንም ብንሆን የምሥጋና ባለቤት ክርስቶስ የተወልንን ምሳሌ አልተከተልንም። ቅዱስ ዳዊት ሁሉ ዐመፁ በአንድነትም ረከሱ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም አንድም ስንኳ የለም(መዝ 14፥3)ብሎ እንደተናገረ መሪውም ተመሪውም ተያይዘን ነው የጠፋነው። ስለዚህ ፍርድን ሕግን ለሚሰጥና ለሁሉም እንደሥራው ዋጋውን ለሚሰጥ ለልዑል እግዚአብሔር አሳልፈን እንስጥ። እርሱ ሁሉን ያውቃል ይመረምራልና። ደግሞም በቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንዲህ አይነት የአምባገነንነት ሥራዎችን ስንመለከት በየብሎጉ የስድብ ቃላትን ከምናዘንብ ብንበረታ ኖሮ እንደ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እንዲህ አይነት ሥራ አይገባም ብለን ፊት ለፊት ልናስጠነቅቅ ይገባ ነበር። ችግሩ እንዲህ የሚያደርግ ጀግና የት ተገኝቶ።

ከዚያ ውጪ የስድብ ዶፍ ብናወርድ እኛውኑ እንዳይጎዳ። ምክንያቱም ክፉውንም ሆነ መልካሙን አስተዳዳሪ የሚሾም የዚች ዓለም መጋቢ ሰራዒ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ማንም ካለ እግዚአብሔር ፈቃድ በራሱ ጊዜ አይነሳም። መልካምም ቢሆን ጠማማም ቢሆን። ሳኦልን ያሰነሳ እሱ ነው ዳዊትንም ያስነሳ እሱ ነው። ለዚህ ነው ቅዱስ ጴጥሮስ ሎሌዎች ሆይ፥ ለበጎዎችና ለገሮች ጌቶቻችሁ ብቻ ሳይሆን ለጠማሞች ደግሞ በፍርሃት ሁሉ ተገዙ የሚለን(1ጴጥ 2፥18)። ከእግዚአብሔር ትዕዛዝ እንዳንወጣ ልንጠነቀቅ ይገባናል። በተጨማሪም ፈራጆችን አትስደብ፥ የሕዝብህንም አለቃ አትርገመው።(ዘጸ 22፡28)ይላልና ስብሐተ እግዚአብሔር ከሚፈልቅበት አንደበታችን ስድብ መውጣት የለበትም። ለዚህ አይደል እንዴ ስለ ሙሴ ሥጋ ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ጌታ ይገስጽህ አለው እንጂ የስድብ ቃል አልወጣውም(ይሁዳ 1፡9)።

ስለ አንቺም የራሳቸውን ጠጕር ይላጫሉ ማቅም ያሸርጣሉ በነፍስምሬትም ስለ አንቺ መራራ ልቅሶ ያለቅሳሉ።(ሕዝ 27፡31) እንደተባለ ስለ አገራችንና ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ስለራሳችን የምናለቅስበትን የተሰበረ ልብ እግዚአብሔር ያድለን!

melkamtibebu said...

ቃለ ህይወት ያሰማልን! ለእነሱም አስተዋ ልቦና እግዚያብሔር ይስጣቸው።

Anonymous said...

ሐበሻ፣ ፖለቲካና ሃይማኖት

በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ የምትኖሩ
እስቲ ሐበሾች ተንፍሱ የሰማችሁትን ተናገሩ
ደግሞ ዛሬ ምን ተባለ ምን ተወራ በሀገሩ
እነማን ጠግበው ዋሉ እነማንስ ጦም አደሩ
እነማን ሳይታመሙ መቱ እነማንስ ተቀበሩ
ሰይጣን ዙፋኑን ዘርግቶ ስለ ተደላደለ በጣም
ይሰማለታል ቃሉ እሱም የሚለው አያጣም

ከቃሉ ጋር አለማምዶ ሕሊናችንን ተቆጣጥሮ
ፈሪሃ እግዚአብሔርን አሽቀንጥሮ መደፋፈርን አስተምሮ
የክርስትና ስማችን ሳይለወጥ የአምልኮት ቤታችንን ሳይቀማ
በኃጢአት ባሕር አስጥሞ አግዞን በጨለማ
ገመናችን እንዲገለጥ ጩኸታችንም እንዲሰማ
እያወጋገዘ በአደባባይ እያፋጀ እያዳማ
የውድቀት ምልክት የአዋቂ ሕዝቦች ማስጠንቀቂያ
አድርጎናል መተረቻ የዓለም ሕዝብ መሳለቂያ

ማን አለ የእሱ ወዳጅ ማን ተመቸውና ለእሱ
እንደ ሐበሻ ቅን አገልጋይ የሚገብርለት በነፍሱ
ስመ ገናና ኩሩ ሕዝብ በሩቅ ሲሰሙት ተናፋቂ
ሃይማኖተኛ መስሎ አዳሪ ወጉን ባሕሉን አጥባቂ
ሲቀርቡት የሚያስመርር ያደረጉለትን የሚረሳ
ያጎረሰውን ጣት የሚነክስ እንደተራበ አንበሳ
በወዳጁ ላይ ፈጥኖ የቁጣ ክንዱን የሚያነሳ

ወገኑን ሲያይ ልቡ አብጦ ደረቱን የሚነፋ
የማይታመን እቡይ ከጫካ ነብር የሚከፋ
ቆርጦ ቀጥሎ አስመስሎ ስምክን በሐሰት የሚያጠፋ
ለባዕድ የሚያሽቆጠቁጥ ለተወዳጅነት ተጨንቆ
ምላስ ጅራቱን የሚቆላ ምቀኛ ግብሩን ደብቆ
እውነቱን እያወቀ ልብህ በስሎ ለመኖር ከእርሱ ጋራ
እሱ ያለውን ካላልክ ካላመለከው በተራ
ወይም ልቀኸው ከታየህ ስምህ ከፍ ብሎ ከተጠራ
በምቀኝነት አጥምዶ ፍጥኖ የሚሆን ባላጋራ
ልቡ ቂመኛ ተበቃይ ለወዳጁ የማይራራ
በሰርግ ላይ የሚያለቅስ በተስካር ላይ የሚያቅራራ
ሐበሻ ማለት ይኸ ነው ላላወቀው ሰው ላልተረዳ
ሳያሳድዱት የሚያሳድድ ሳይክዱት የሚከዳ

አብሮ ያደገ ክፉ ልክፍት የጎሰኝነት በሽታ
የበቀለኝነት መንፈስ ለእውነት ለፍቅር የማይረታ
የተጠናወታቸው አባዜ የዘር ፖለቲካ ትኩሳት
እያገሳቸው እንደ አንበሳ እያቃጠላቸው እንደ እሳት
ዓለም ያወቀው ገመና ምሥጢር ሆኖባቸው ለእነርሱ
ሐበሾች መልአክ ሆነው ሐበሻነታቸውን ቢረሱ
ሌላውን እያረከሱ ራሳቸውን ቢቀድሱ
ቢጰጵሱ ቢቀስሱ እርስ በራሳቸው ቢሞጋገሱ
ቢሽሞነሞኑ የወርቅ ካባ ቢለብሱ
በጥዑም ዜማ በማኅሌት ቢፈነጥዙ በጋራ
እያመተቡ ቢያወግዙት በቀኝና በግራ
አይጨንቀውም ዲያብሎስ ይዘብታል እንጅ በተራ
እርግማንና ምርቃት በሚያፈራርቅ ቃላቸው
ነፍሳት አልቅሰው ሲበተኑ የወንጌላዊ ድምጽ ሲርቃቸው
የወደዱትን እየሾሙ የጠሉትን እያሳደዱ
ያገኛቸዋልና ተንኮል አዝለው በቃኤል መንገድ ሲሄዱ

በሰለጠነው ዓለም ቢሰደዱ ወይም በእናት ምድር ቢሆኑ
በአገልግሎት ቢተጉ በአስተምሕሮ ቢካኑ
ምሳሌ ሆነው ካልተገኙ በሥነ-ምግባር ካልጸኑ
የተከተሏቸው በጎች እረኛ አጥተው ሲባዝኑ
በሁለት ጎራ ተሰልፈው እየተዋጉ ሲበተኑ
መንገዱ ጠፍቶባቸው ለተኩላ ሲሳይ ሲሆኑ
ለእውነት ካልቆሙ ጨክነው እረኝነታቸውን ካልመዘኑ
የራስን ጥቅም አሳልፈው ለመንጋው ቤዛ ካልሆኑ
በምን ይለካል ታዲያ የቅድስና ሚዛኑ?

በሃይማኖት በፖለቲካ ከጥንት ዘመን ጀምሮ
ኮስማና ሆነን የቀረነው ዕድገታችን ተቀብሮ
ተገርጎብ ይሆን አዚም የማይፈታ መተት
ለልጆቻቸው እንዳይደርስ የአባቶቻችን በረከት
አይደለም ወገኖች ራሳችሁን አትሞግቱ
ማሳሰብ ይቅርብን ተነጥሮ ይውጣ እውነቱ
ብልጭ ክድን ሲል የኖረው ገና ከጥንቱ ከጥዋቱ
ዘረኝነት ነው ጦሱ የውድቀታችን መሠረቱ
ይኸው ነው እንግዲህ ግብሩ የሐበሻ ምንነቱ
ሐበሻን ጠልቶ ሐበሻ የሚሸሽበት ምክንያቱ

ህው ነው እንግዲህ ሐበሻ ! የሀገሬ ልጅ ሐበሻ !!
አይ ሐበሻ
የክፋት መደማምር፣ ክፉ የመጨረሻ

ቸር ወሬ ያሰማን

አግናጢዎስ ዘጋስጫ said...

July 21, 2010
ትንቢቱ ሲፈጸም
(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 22/2010)፦
(አግናጢዎስ ዘጋስጫ)
ትንቢቱ ሲፈጸም በመጽሐፍ ያለው፣
ወገኔ አትደንግጡ ይህ ሊሆን ግድ ነው።
ሐሰተኞች ነብያት በዓለም ይነሳሉ
ለብዙዎችም ጥፋት ምክንያት ይሆናሉ
ብሎ እንዳስተማረን ጌታ በወጌሉ
የእውነት ደብዛ ጠፍቶ ሐሰት መሰልጠኑ፣
ሥርዓት ተጥሶ ነውሩ ጌጥ መሆኑ፣
አይቀሬ ነውና ወገን አትደንግጡ፣
ከመጣብን ቁጣ በጸሎት አምልጡ።

የእግዚአብሔር ሰገነት ሲቀየር በጣዖት፣
በቅዱሱ ሥፍራ ሲፈጸም እርኩሰት፣
በአደባባይ ሲታይ ሰይጣን አካል ነሥቶ፣
ከዚህ የበለጠ ምን ይመጣል ከቶ?

ቅዱሳን ተናቁ አፈኞች ተሾሙ፣
ንጹሐን ተዋርደው ሌቦች ተሸለሙ።

በቅዱስ መስቀሉ በድኅነት ምልክት፣
የእብነ በረድ ሐውልት ጣዖት ባረኩበት፣
ጸጋ ቢሰጣቸው መንጋ እንዲጠብቁ፣
በውዳሴ ከንቱ በገንዘብ ወደቁ።

ብዙ ፈርኦኖች በኢትዮጵያ ነገሱ፣
የአባቶችን ድንበር ሥርዓት አፈረሱ፣
በውል ሳይታወቅ ማን እንደሾማቸው፣
በቤቱ ቀለዱ እነርሱ እንዳሻቸው፣
አየ የጥፋት ቀን የዓለም መጨረሻ፣
የሐሳዊ መሲህ የአውሬው መንገሻ፣
እጅግ ያሳዝናል ኢትዮጵያ መሆኗ፣
ትንሽ ሳታገግም ከትናንት ሀዘኗ።
በገንዘብ ተገዝተው ሀሰት ቢናገሩ፣
በውዳሴ ከንቱ በዓለም ቢኖሩ፣
ሁዋላ አይጠቅምም ከቶ በሞት ስንጠራ፣
እግዚአብሔር ፊት ሲቀርብ የሠራነው ሥራ፣
መሳሳት ያለ ነው መውደቅ መነሳቱ፣
ፍጹም ስላልሆነ ሰው በሰውነቱ፣
ነገር ግን ትልቁ ሊያድን የሚችለው፣
ሰው ስህተቱን አውቆ ሲመለስ ብቻ ነው፣
ስለዚህ ኤልዛቤል አክዓቦችም ሁሉ፣
የናቡቴን ርስት እንቀማ ስትሉ፣
አምላክ ተቆጥቶ እንዳያጠፋችሁ፣
መመለስ ይሻላል ከክፉ ሥራችሁ።

እናንተም አባቶች አበው ቅዱሳኑ
መከራን ሳትፈሩ በእምነታችሁ ጽኑ::

ማሳሰቢያ :
በቅድሚያ ወንድሜ መልካም ጥበቡ ለሰጠኝ አስተያየት በጣም አመሰግናለሁ:: ስህተቴን ሙሉ በሙሉ ተቀብያለሁ:: ስህተት የፈጠሩትን ስንኞችም አውጥቸ በሌላ ስንኞች ተክቻለሁ:: ሌላም ስህተት ሲኖር ወንድሞቸ ርማት ስጡኝ:: ደጀ ሰላሞችም እባካችሁ የመጀመሪያውን ግጥም በተስተካከለው ቀይራችሁ ብታወጡልኝ በትህትና እጠይቃለሁ::

MelkamTibebu said...

እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልህ

Anonymous said...

ሳሙኤል፡ዘአሰቦት፡said...

አግናጤዎስ፡ዘጋስጫና፣መልካም፡ጥበቡ፡ያደረ
ጋችሁት፡ማሳሌነት፡ያለው፡ትምህርታዊ፡እርማ
ት፡የማቅረብና፡የመቀበል፡በበጎ፡መንፈስ፡የተመ
ላ፡ጥረታችሁ፡እጅጉን፡አስደስቶኛል።

እንዲህ፡ነው፡እርስ፡በርስ፡መስተማማርና፡ለተዋ
ሕዶ-ኢትዮጵያ፡ሥነ፡ስርዓትና፡ክብር፡የምናደ
ርገውን፡ጥረት፡እግዚአብሔር፡በደስታ፡እንዲባር
ክልን፡ትህትናን፡ተላብሰን፡መቀራረብ፡የሚገባን።

ሁለታችሁንም፡መድኃኔ፡ዓለም፡ክልርስቶስ፡ይባር
ካችሁ።በርቱ፤እንበርታ!

ሳሙኤል፡ዘአሰቦት

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)