July 14, 2010

ወ/ሮ እጅጋየሁና ዲ/ን በጋሻው በፓትርያርኩ ተሸለሙ፤ ቅ/ሲኖዶስ ስብሰባውን ጀመረ

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 13/2010)፦ ቅ/ፓትርያርኩ ሰኞ ማታ በተዘጋጀ የራት ግብዣ ላይ "በዓለ ሲመታቸውን ላሳመሩ" ሰዎችና ማህበራት የምስጋና ሰርተፊኬት ሰጥተዋል። ሰርተፊኬቱን ያሰራውና የተሸለመው ራሱ ሐውልቱን ያሰራው የነ ወ/ሮ እጅጋየሁ ኮሚቴ እና የነ ዲ/ን በጋሻው ማህበር የሆነው "የቅ/ማርያም የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ማህበር" የተባለው ነው።  ከሁለት ሳምንት በፊት በአዋሳ ከተማ እንዳያስተምሩ የታገዱት ዲ/ን በጋሻውና የሚመራቸው መዘምራን ከፓትርያርኩ እጅ የተቀበሉት የምስክር ወረቀት የታገደባቸውን ጉባዔ ለማካሄድ አንድ እመርታ ፈጥሮላቸዋል። የታገዱትን ጉባዔ በድጋሚ ለማካሄድ ድርድር ላይ እንደሚገኙም ታውቋል። ጉባዔውን ያሳገዱት የቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪም በፓትርያርኩ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ከሥልጣናቸው እንዲነሱ ተደርገዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዛሬ ማክሰኞ ጀምሮ የሚደረገው የቅ/ሲኖዶስ ጉባዔ የተጀመረ ሲሆን በዛሬው ውሎው አጀንዳዎችን ለማጽደቅ ሲነጋገር ቆይቷል። በዚህም ወቅት በዛሬው ዓመት ክርክር ግንባር ቀደም የነበሩት እና አሁን ያለ ሠራ እንዲቀመጡ የተገደዱት ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ፓትርያርኩን እና ሌሎች የቅ/ሲኖዶስ አባላት በይፋ የገሰፁ ሲሆን ፓትርያርኩ በበኩላቸው "እኔ እንደ ልጄ ነው የምወድህ" ሲሏቸው ተሰምተዋል። ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ እየተደረገ ያለውን ነገር በመቃወም የመረረ ትችት ማሰማታቸው ታውቋል። የንግግራቸው መንፈስ "ቤተ ክርስቲያኔን ትጠብቋት ዘንድ - ለመንጋውና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ!" የሚለው ጽሑፍ እንደነበረም ታውቋል።

በሌላ በኩል እነ ዲ/ን በጋሻውንና ወ/ሮ እጅጋየሁን በመምከር የሐውልቱ መሥራቱንና የጉባዔውን መንፈስ ያነሳሳው ቀሲስ ሰሎሞን ሙሉጌታ ባለፈው ቅዳሜ ሊያስተምርበት ከሄደበት ጉባዔ "እንድታስተምረን አንፈልግም" ተብሎ መመለሱ ታውቋል። ቀሲስ ሰሎሞን በአንድ በኩል በማህበረ ቅዱሳን አባልነቱ፣ በሌላ በኩል በነዲ/ን በጋሻው መሪነቱ በሁለት እግር ሁለት ዛፍ ላይ ለመውጣት በሚያደርገው ሙከራ ምዕመናን በመበሳጨት እንደተናገሩት ታውቋል። ይኸው ቀሲስ ሰሎሞን በአረብ አገር (በዱባይ) በፈጠረው ግርግር የራሱን ግሩፕ ከቤተ ክርስቲያን ገንጥሎ በማውጣት በአገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ዲሜጥሮስ ላይ ተቃውሞ ያስነሳ ሲሆን በዚህም ምክንያት በስደት አገር ያለው አገልግሎት ላይ እንቅፋት የፈጠረ እንደሆነ የአካባቢው ምእመናን ይናገራሉ።

አሁን ባለው ሁኔታ ቤተ ክርስቲያን ስትደማ ከነወ/ሮ እጅጋየሁ የዝርፊያ አሰራር ጋር የቆሙት ቀሲስ ሰሎሞን እና ዲ/ን በጋሻው ከዚህ በላይ በምእመናን ላይ ሊቀልዱ ይገባ ይሆን?

ቸር ወሬ አሰማን፣
አሜን

24 comments:

ታደሰ said...

ለብፁዕ አቡነ ሳሙኤልን ቃለ ሒይወት ያሰማልን።
እግዚአብሔር አምላክ የበለጠ ለመጋደል ለመስራት ያድሎት። ለቅድስት ቤተ ክርስትያን መስራት/መሞት መታደል ነውና።
የቅድስት ቤተ ክርስትያናችንን የቅ. ሲኖዶሳችንን መስተካከል ለማየት ያብቃን። እኛም የእርሶ አይነት አባት ያብዛልን።

እግዚአብሔር አምላክ የቤተ ክርስትያናችንን ጥፋት ከማየት ይጠብቅን። የኛም ጥፋት ነውና።

Anonymous said...

To:AbunePaulos,Begashaw,Ejigayehu private limited company
My prescription for U guys is a one way trip to Tsadkane Mariam with out return coverage so that U stay there for one full month practicing prayers and then God will give U the answers.Don't waste your time this is a big time discount for your life.If U don't use it U'll lose it!!!

selamawi said...

በስመስላሴ አሃዱ አምላክ አሜን

የቅዱስ ፓውሎስ መልእክት ለሁላችንም የተላከ

2ኛ ጢሞ 3፥1
ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ።

ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፥ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥

ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥

ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፤

የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ።

,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,

መጽሐፈ መክብብ 5፥8 ከፍ ካለው በላይ ከፍ ያለ ይመለከታልና፥ ከእነርሱም በላይ ደግሞ ሌሎች ከፍ ይላሉና በአገሩ ድሆች ሲገፉ፥ ፍርድና ጽድቅም ሲነጠቅ ባየህ ጊዜ በዚህ ነገር አታድንቅ።

እግዚአብሔር ከኛ ጋር ከሆነ ይህ ሁሉ ለምን ሆነብን እግዚአብሔር ፊቱን ከኛ መልሷል እናስተውል ይህ ሁሉ የመጣው በእኛ በደል ነው አንድ ሰው ቤተክርስቲያናችን ትጣ ?

መዝ 14፥3 ሁሉ ዐመፁ በአንድነትም ረከሱ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም፤ አንድም ስንኳ የለም።

ጕሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው፥ በምላሳቸው ሸነገሉ፤

ከከንፈራቸው በታች የእባብ መርዝ አለ፤ አፋቸው መርገምንና መራራን ተሞልቶአል፤

ደምን ለማፍሰስ እግራቸው ፈጣን ነው፤ ጥፋትና ጕስቍልና በመንገዳቸው አለ፥ የሰላምን መንገድ አላወቁአትምና፤ እግዚአብሔርን መፍራት በዓይናቸው ፊት የለም።
ሕዝቤን እንደ እንጀራ የሚበሉ ኃጢአት የሚሠሩ ሁሉ በውኑ አያውቁምን? እግዚአብሔርንም አይጠሩትም።

ኢትግድፈነ ወኢትመንነነ
አምላከ ሰላም ተራድአነ

እግዝእትነ ነጽሪ ኃቤነ
ሰላመ ወልድኪ የኃሉ ምስሌነ

Anonymous said...

እግዚአብሔር ቤተ ክርስትያንን ከጥፋት ይጠብቃት ዘንድ ኢታርእየነ ሙስናሃ ለቤተ ክርስትያን እያልን እንፀልይ፡፡

Anonymous said...

መከራችንን ያበዛው መጀመሪያውን ትንንሽ የመሰሉንን ጥቃቅን ስህተቶች ሳናስተውላቸው እንዲስተካከሉ ጥረት አለማድረጋችን ነው:: አባ ጳዉሎስ እነዚያን ጥቃቅን ስህተቶች ሲሰሩ የምእመናኑን ሁኔታ እየታዘቡ ነበር:: ዝምታችንን ተረማመዱበትና እዚህ ደረሱ:: ከአሁን በኋላ የሚስተካከሉት ነገር ይኖራል ብየ አላስብም:: የማስበው ቤተ ክርስቲያናችንን እንደት ከጠላቶቿ ማስመለስ እንችላለን የሚለውን እንድንነጋገር ነው::
"ከበጣም ክፉ፣ ክፉ ይሻላል" የሚለው አባባል ጥሩ ይመስል በጉቦ እና በሌላም ስም አይጠሩ ሙስና የተዘፈቁ ሰዎችን፣ኣባ ጳዉሎስ ችግራቸውን እያወቁ ስለሾሟቸው ብቻ ኣባ ኣባ ማለቱን እናቁም:: ለዛም ነው አጥብቀው መጮህ የማይችሉት ምክንያቱም በደፋር ደጋፊዎቻቸው ያሰድቧቸዋል መጽሐፍ ከነፎቶ ያወጡባቸዋል እናም አፍ የለሾች ናቸው:: አንዳንዶቹ ለቤተ ክርስቲያናችን የሚቆረቆሩ ቢሆኑም የህ ያለፈ ክፉ ስራቸው ማነቆ የሆነባቸው አሉ ሌሎች ደግሞ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማጥፋት በሚደረገው ዱለታ ውስጥ ስላሉበት ለነሱ ምንም አልተፈጠረም ባይ ናቸው ሌሎቹ ደግሞ እነሱ በሚወዱት ነገር ላይ አባ ጳውሎስ ጥሩ አቋም ስላላቸው ከቅድስናቸው ሌላ አይታያቸውም( ለምሳሌ የአቡነ ቴዎፍሎስን
አጽም ማስወጣታቸውን እጠቅሳለሁ) ይህንን ስራ ማንም የቤተ ክርስቲያን መሪ የመንግስትን ለውጥ አጋጥሞት ይተወዋል ብየ አላስብም:: ነገር ግን ቅዱስነታቸውን የሚወዱ ቢሁኑ አላማቸውን፣ፈለጋቸውን በተከተሉ ነበር:: ቅዱስነታቸው( አቡነ ቴዎፍሎስ) በክፉ ቀን የነበሩ ነገር ግን በዛ ክፉ ቀን ለቤተ ክርስቲያን እንደ ብርሃን የነበሩ ነበሩ:: ጥሩ ሰው የማይበረክትላት ቤት ስለኆነች ተነጠቀች:: እናም አንዳንዶቹ ይህንን ብቻ በማየት ሌላው ነገር ይሰወርባቸዋል እና የሳቸው ጥፋት አይታያቸው :: የቀሩት የመፍትሄ ዘደያቸውን ማስተባበር ስላልቻሉ ለየብቻ ይታገሉና ይወድቃሉ:: እናም ለቤተ ክርስቲያን የሚቆሙት በጣም ጥቂት ናቸው:: እኛም ይህንን አውቀን ነው ቤተክርስቲያናችንን ከጠላቶቿ እጅ ፈልቅቀን ለማውጣት መዘጋጀት ያለብን:: አንዳንድ ሰባኪያን ዘመኑ የሰማእትነት አይደለም ሲሉ እሰማለሁ ታዳ ካልሆነ የምንድነው? ወደእውቀት የማያደርሰውን የነሱን ትምህርት ዝምብሎ መማር
ይህ የሞኝ ንግግር እንጅ ትምህርት አልለዉም ያለመስዋእትነት ከነአባ ጳውሎስ እና ከኩባንያቸው እጅ ማስለቀቅ ይቻላል ብሎ ማሰብ ከተረት የቀለለ ነው:: ህጻን ልጅ እንኳ ብትጠይቁት ይስቅባችኋል:: ስለዚህ ወገኖቼ ዘርፈ ብዙ ትግል ይጠብቀናል:: የጸሎት ጸጋ ያለው የምሩን ይጸልይ:: የጾም ጸጋ ያለው ይጹም:: አስተማሪዎቹም ሰውን ወደ እውቀት የሚያደርሰውን አስተምሩ:: ታዲያ ሁላችሁም ቤተ ክርስቲያናችንን ከጠላቶቿ ለመታደግ እንዲቻል አላማችሁን እርሱን አድርጉ:: በመሃከሉ የኔ ይበልጣል በሚል ፈሊጥ እንዳትነቃቀፉ ተጠንቀቁ::
ሌሎቻችን ደግሞ አያቶቻችን በሽምብራ ቁሬ እንዳደረጉት ለመግደል ባንችል ለመሞት መዘገጀት አለብን:: የቤተ ክርስቲያናችን ፍቅር እስከሞት መሆን አለበት:: ፍቅራችንን ለመወጣት መግደልን ሳናስቀድም በመሞት ብቻ ድል ልናደርግ እንችላለን:: የደብረ ሊባኖስ መነኮሳት ወራሪው ግራኝ ገዳሙን ባቃጠለው ጊዜ ያደረጉትን እናስታውስ::

yemelaku bariya said...

really shaming to abun paulos and his friends!! what is doing abun paulos???? and what are they doing the other "papasat" why they are choosing silence!!!! abun paulos is now clearlly decleared that he is working only for his bussness and for the mission of the protestantism. please let's work together and avoid him and his follower from the source.

Anonymous said...

@ Tadesse....Really it's a great blessing to die for the truth (church)!....Abune Samueal.God be with you..you gave us hope..God hasn't left us!

elsa tilahun said...

betekiristian layi sitikelidu hatinorum degimom mot hale.

mebrud said...

I prefre to say "ስረይ ሎሙ በዘኢየአምሩ ይገብሩ".
Imagine if GOD listens our prayer & starts punishment.
ባደገብህን ሁሉ በእውነት አደረግበህን፡፡ይህም ስለኃጢአታችን ሆነብን፡፡
አቤቱ ይቅር በለን(በዜማ)፡፡

ZEKERE said...

ABETU AMELAKE HOYE EBAKEHE BMHERETEHE TEMELKETENE LENETEFA NEWENA DERESELENE ASETEWAYE MERI ADELENE GETA HOY TECHENEKENALENA ERARALEN

Anonymous said...

ምን ? እውነታቸችሁን ነው ግን?
ብጹ አባታችን ምን ሆኑ ? ሰማያዊ ስልጣን እና ሓላፊነት ነው እኮ! በቅዱስ ጴጥሮስ እግር ተተክተው በጎቼን :ጠቦቶቼን: ግልገሎቼን ጠብቅ የተባሉት አኮ አረሶ እና መሰሎቾ ናችሁ፡፡ እርሶን የሚመለከቱ ሚሊኖች በጎች እንዳሉ አስዉለዋል ? አዳዎት ምን ያህል እንደሆነ ያስቡ፡፡ ከሰሩ ደግሞ ክብሮን፡፡
በአንድ ወቅት የግብጹ ፓትርያርክ አቡነ ሺኖዳ ለእረሶ የተናገሩትን ያስተዉሉ
"እኔ 3 ሚሊዮን ህዝብ ማስተዳደር ያቃተኝ የኢትዮጵያው ፓትርያርክ ምን ያህል ብቃት ቢኖራቸው ነው ይህንን ያህል ሚሊዮን ህዝብ የሚያስተዳድሩት" ....ትክክል ነው ግን?
ስርዓተ ቤተ ክርስቲያን ማፋለስ ጤንነት ወይስ? ለተኩላስ መሸለም ቤተ ክርስቲያን አንድትፈርስ መፍቀድ አይደለም እንዴ?
ለሚያልፈው አለም አነዴት የማያልፈውን መንግስት ማጣት?
ቤተ ክርስቲያንን እንደሆነ የሲኦል ደጆችም አያናዉጧትም እኛ ግን እንደ ተረፈ አሪዎስ ጠፍተን እንቀራለን ብንጠነቀቅስ
አቤቱ የቤተ ክርስቲያን አምላክ ሆይ ታደገን

Anonymous said...

እኒህ ሠውን ለመፈተን የተፈጠሩ ሰውየ እኮ ፈተካችንን አሳዩን:: ሁልጊዜም እንደ አምባገነን አዳድስ አሳፋሪ ክስተቶችን እየፈጠሩ ለምን የሕዝቡን ልቦና ወዳ ወዲህ እንደሚያደርጉ የገባን አልመሰለኝም:: በዋናነት ቤተ ክርስቲያኒቱን የመጥፋቱን ሥራ በሚገባ እያከናወኑ ነው :: ለምንድነው ከስልጣን እንድወርዱ ቀጥታ የማንጠይቀው:: ነው የቤተ ክርስቲያናችንን ነገር አደራ የተባሉት መነክሴ የሆኑት ብቻ ናቸው በሚለው ተስማምተናል:: እነደዛስ ከሆነ ምን ያክሉመነኩሴዎች ናቸው:: ዝምታው የሚበቃ ይመስለኛል:: እኒያ ሁለት መንገደኞች በጨለማ ከነፍርሃታቸው ተኝተው ፣ አንዱ አጥንት ሲቆረጠም የሚያሰማውን ድምጽ ይሰማና ለሌላው ጓደኛው ምንድን ነው የምሰማው ቢለው ተው ዝም በል ጅቡ የኔን እግር እየበላው ነ አለ ይባላል:: አሁን እዛ ደረጃ ላይ የደረሰ ለምን ብሎ ይፈራል:: የሚፈራው እኮ ከዚያ ሁኔታ ላይ ላለመድረስ ነው:: እኛም አሁን ያለንበት ደረጃ ከዛ የባሰ ነው:: ፍርሃት በቃ :: በቃ ይውረዱ ለፍርድ ይቅረቡ የተመዘበረው የአገር ንብረት አይደለም? ፍርድ እነደ ዘራፊነታቸው አያስፈልጋቸው ? ይህንን ለፍጻሜ ለማብቃት ጠንክረን እንስራ:: መነኮሳቱ( ጳጳሳቱ አብዛኛዎቹ እንዳይናገሩ ብዙ የሚይዛቸው ነገር አለ) በነሱ ላይ ብዙም ተስፋ የለኝም ይልቅስ እርሱን የድንግልን ልጅ ተስፋ አድርገን ቤታችንን እናጽዳ

Anonymous said...

yezemenachin nabukedenetsor(aba paulos) ena elizabel(ejigayehu) amilak menorun taminalachihu? geta libachihun yimelis. lelolochum yetifat taot honachihu tesetachihu. egiziyabiher yeniseha geze setitonal. ebakachihu yibika. ayinachihu megelet kalichale yeamilak kin fird bederese gize yekefa yihonalina zaren tetekemubat. enebegashaw, kesis solomon yehilina eda enidet yaderigachihu yihon. lehulet ayinet melik yetaserachihu esiregnoch yesebekachihut yeniseha timihirt wedelibachihu yimeles ena behulet hasab kemanekes beewunetegnaw kal tsinu. lelochachihu betinikola ena belebinet hiwotachihun bemulu yasalefachiut yezerewochu yeaba paulos anijawoch yibikachihu esti

Anonymous said...

+ + +

Dear Dejeselam,

Why dont you interview kesis Solomon Muluget to shed light on his exact role of in this issue? Please also try to incorporate the idea of Mahiber kidusan. What will be its stand if one of its member practice against the will of the church and people? Please pleas....

Anonymous said...

I am not sure if we all are worried about our church. If for sure we did this honestly and for our church, I don't see any positive issues in these posted NEWS. As much as we read negatives I would expect positives as well. Otherwise our church back home is being divided and stretched in to two groups with hatred to each other, Those who are supporters and those who are against His Holiness. For me things will ease down if we are fair and acknowledge the positives and oppose the negative. I don't see a balanced News since the beginning of Dejeselam.

Amlak Yitadegen!

ሲላስ said...

እኔ የማሳስበው በምንም ኣይነት መመዘኛ መንግስት ይህንን እያየና እየሰማ ዝም ብሎ የሚያይበት ምክንያት ስለሌለ የቤተ ክህነቱን የገንዘብና የኦዲት ኣያያዝ መመርመር ይገባዋል ባይ ነኝ። መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ ኣይገባም ማለት የህዝብ ገንዘብ ሲዘረፍ ዝም ብሎ ይመለከታል ማለት አንዳልሆነ ነው ለእኔ የሚገባኝ ። በየገዳማቱ እና በየበረሃው በረሃብ እየተቆላ የሚያልቀው መነኩሴ የህዝቡ ኣንድ ኣካል ነው የነሱም ረሃብና ሰቆቃ መንግስትን ሊሰማው ይገባል። ህዝብ ኣቤቱታውን ለመንግስት ማቅረብ እንዳለበት ኣምናለሁ። ወንበር ዘርግተው የሚያስተምሩት የቤተ ክርስቲያን ምሁራን በችግር እና በችጋር እየተዘጉ ባሉበት ጊዜ የሦስት ሚልዮን መኪና ማስገዛት እና መግዛት ጤንነት ነው ኣልልም። መንግስት ህዝቤን ከድህነት ኣወጣለሁ ብሎ በኣራቱም ኣቅጣጫ በሚባዝንበት ሰኣት እንደዚህ ኣይነት ቅምጥል ይዞ መጙዋዝ በጣም ይከብዳል። በሃገሪቱ ውስጥ ኣንድ መንግስት እንዳለ ነው የምናምነው። ይህን ጉዳይ መንግስት ኣትኩሮት መስጠት ኣለበት። በቁምስ ሃውልትስ ማቆም ምን ይባላል? ለነገሩ ሰውየው ከሞቱ ቆይተዋል። ወስብሃት ለእግዚኣብሄር።

Anonymous said...

+++
ኡ ኡ ኡ ...

ትሰማለህ አሉ የድሃ ኡኡታ፣
እነሆ እንጮሃለን ስማን የኛ ጌታ፣
የሃይማኖት ንግዱ እጅጉን በረታ፣
በዛብን እሮሮ የዓለም ጨዋታ።

የሰዉ ሃይማኖቱ ሲሆን ፍቅረ-ንዋይ፣
እባክህ ዝም አትበል ሃይልህን አሳይ፣
የቸርነትህን ያህል ቁጣህንም እንይ።

ከለንደን

Anonymous said...

ፍርዱን ለፈጣሪ ልተውና
እኔ በበኩሌ ምነው አፌን በዘጋው እነዛን ቅዱሳን የግብጽ ጳጳሳትላይ
የፈረድኩባቸዉ .የኛዎቹ በገዛ ህዝባቸዉላይ እንዲህያለ መከራ ሲያርሱ
በት አይዘገንንም ?የ ሚገርመው አባ ሳሙኤልን ስታሞግሱ ፤
አረተዉ ግዲላችሁም አንሸወድ፤ ሁሉም ጎተራው ሲጎድል መጣላቱ አይቀርም
ለማንኛውም በኔ በኩል ተስፋስለቆረጥኩኝ ፣ሁሉንም አላውቃቸውም፤ማናቸውም ቤሆኑ እኔ በበኩሌ አይወክሉኝም የተዋህዶ አባቶችንን እስከማገኛቸው ድረስ.ማንም ካቶሊካዊ
አባቴሌ ሆን አልፈቅድም.
መድሐኒያለም ይቅርይበለን

Anonymous said...

ጊዜ ያመጣዉን ጊዜ ይመልሰዉ።

መቼም ጊዜ የእገዚአብሔር ገንዘብ ቢሆንም ዘመነኞች ጊዜ በሰጣቸዉ ዕድል መጠቀማቸዉ አይቀሬ ነዉ። ጊዜ ያነሳዉን ጊዜ ይጥለዋልና የጊዜ ቁማርተኞችን ለጊዜ መተዉ ብልህነት ነዉ። ጊዜ የሾመዉን ጊዜ እስኪጥለዉ ተብሎ የሚተዉ ታሪክ ባይኖርም እነ ዺ/ን በጋሻዉንና ወ/ሮ እጅጋየሁን በአባታቸዉ በአቡነ ጳዉሎስ ጥላ ሥር አሰባስቦ ቤተ ክርስቲያንን ሲያዋርዱ ለማየት መብቃትጊዜ ያመጣዉ ነዉና ለጊዜዉ ለቀቅ ማድረግ ያሻል። ጊዜ ነዉና ያነሳቸዉ ጊዜ ያሰያናልና እንረጋጋ ። ለእነርሱ ከንቱ የልጅ ጨዋታ መላ ስንሻ ለቤተ ክርሰትያናችን መሥራት የሚገባንን መልካም ነገር እንዳንተዉና እንዳንዘናጋ። የሚያሳዝነዉ ግን የዓለም አብያተ ክርስቲያን ፕረዜደንት ፓትሪያርካችን አደግን የሚሏትን እናት ቤተ ክርስቲያንና ያፈራቻቸዉን ቅዱሳን ናቅ አድርገዉ መተዋቸዉ ነዉ። ያ ሁሉ ባይሆን ኖሮ አቦ አቦ ባሏቸዉ ሁሉ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ሲጣስ ዝም ባላሉ ነበር። "በመስቀሉ ሥር ቁማርተኞች" ጸጋቸዉን የተገፈፉት ብጹዕነታቸዉ ገና ቁስላቸዉ ሳይሽር በሐዉልት ምረቃ ለሙት መታሰቢያነት ባልበቁም ነበር። ይቆየኝ። ብዕሩ ይናገር

Anonymous said...

ጊዜ ያመጣዉን ጊዜ ይመልሰዉ።

መቼም ጊዜ የእገዚአብሔር ገንዘብ ቢሆንም ዘመነኞች ጊዜ በሰጣቸዉ ዕድል መጠቀማቸዉ አይቀሬ ነዉ። ጊዜ ያነሳዉን ጊዜ ይጥለዋልና የጊዜ ቁማርተኞችን ለጊዜ መተዉ ብልህነት ነዉ። ጊዜ የሾመዉን ጊዜ እስኪጥለዉ ተብሎ የሚተዉ ታሪክ ባይኖርም እነ ዺ/ን በጋሻዉንና ወ/ሮ እጅጋየሁን በአባታቸዉ በአቡነ ጳዉሎስ ጥላ ሥር አሰባስቦ ቤተ ክርስቲያንን ሲያዋርዱ ለማየት መብቃትጊዜ ያመጣዉ ነዉና ለጊዜዉ ለቀቅ ማድረግ ያሻል። ጊዜ ነዉና ያነሳቸዉ ጊዜ ያሰያናልና እንረጋጋ ። ለእነርሱ ከንቱ የልጅ ጨዋታ መላ ስንሻ ለቤተ ክርሰትያናችን መሥራት የሚገባንን መልካም ነገር እንዳንተዉና እንዳንዘናጋ። የሚያሳዝነዉ ግን የዓለም አብያተ ክርስቲያን ፕረዜደንትፓትሪያርካችን አደግን የሚሏትን እናት ቤተ ክርስቲያንና ያፈራቻቸዉን ቅዱሳን ናቅ አድርገዉ መተዋቸዉ ነዉ። ያ ሁሉ ባይሆን ኖሮ አቦ አቦ ባሏቸዉ ሁሉ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ሲጣስ ዝም ባላሉም ነበር። "በመስቀሉ ሥር ቁማርተኞች" ጸጋቸዉን የተገፈፉት ብጹዕነታቸዉ ገና ቁስላቸዉ ሳይሽር በሐዉልት ምረቃ ለሙት መታሰቢያነት ባልበቁም ነበር። ይቆየኝ። ብዕሩ ይናገር

Anonymous said...

የሚያሳዝነው ነገር: እኔን መጣላት ያማረኝ: ከእግዚአብሔር ጋር መሆኑ ነው:: እኛ እኮ ሰዎች ነን እንጂ መላእክት አይደለንም:: ቅዱሳንን የምናውቃቸው በመጽሐፍ ብቻ ሆኖዋል:: አንድ የሚያበረታታን ተስፋ ሳይኖረን ለዚህ ብሽቅ ዘመን አሳልፎ እግዚአብሔር እንዴት ይሰጠናል? ከእኛ ቀድሞ የነበሩ ትውልዶች: እርሱ ላይ አምጸው እግዚአብሔር የለም ብለው ሊሆን ይችላል፤ እኛ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን ብለን ወደርሱ ብንመጣ እንዲህ ዓይነት ሰዎች ጋር ያፋጥጠናል እንዴ? እኛ ምንድነው ተስፋችን? እግዚአብሔርን ተስፋ ለማድረግ በራሱ የጸሎታችን ድምጽ ሊሰማ ይገባዋል?! እኛ ስንት ርግማንና ውግዘት ተሸክመን: ደኅና የሚናዝዝ ካህን እንኩዋን አጥተን: የእምነ በረድ ግድግዳ ሠርቶብናል::ጸሎታችን እንዴት ያርግልን? በዓለም ውስጥ ነው ያለነው_ ጻድቃን አይደለንም_ታድያ ተስፋችን ማነው? ያቺ እናቱ ነበረች_እሷም ድምጿን አጥፍታለች:: እኔ እግዚአብሔር ለአበው ያደረገላቸውን ቸርነት ብቻ በማሰብ "ቸርነቱ በእኛ ላይ ስለበዛ" እያልኩ ዘወትር ልዘምርለት አልችልም:: እኔም የርሱን ቸርነት ማየት እፈልጋለሁኛ! ሳልቀምሰው ይጥማል ማለት እችላለሁ እንዴ? ነው ወይስ የዘመኑ ፈተና "ቸርነቴን ሳታዩ ሳትቀምሱ አምልኩኝ" የሚል ነው? እግዚአብሔር መልስ ቢመልስ መልካም ነበር::ዳሩ__ለኛ እርሱ መልስ አይመልስም:: የእንጀራ ልጆች አደረገን መሰል አሁንስ፤ ኤጭ!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)