July 30, 2010

የቅዱስነታቸውን ሐውልት በማቆም የቅድስት ማርያም ስብከተ ወንጌል ማኅበር ከፍ ያለ አስተዋፅኦ አድርጓል›› (ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል)

  •  ፓትርያርኩ ቁልቢ አልሄዱም፣
(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 29/2010)፦ የብፁዕ ወቅዱስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስን 18ኛ ዓመት በዓለ ሢመት ‹‹በልዩ ሁኔታ ለማክበር›› በሚል በተቋቋመው የበዓል አከባበር ኮሚቴ፣ ከ300‚000 ብር በላይ ወጪ በማድረግ በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ዐጸድ ውስጥ የቆመውን እና ሐምሌ አራት ቀን 2002 ዓ.ም ፓትርያሪኩ እና ዐሥራ አንድ ብፁዓን አባቶች (ብፁዕ አቡነ ገሪማ፣ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ፣ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም፣ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ፣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ፣ ብፁዕ አቡነ ያሬድ፣ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል፣ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ ብፁዕ አቡነ ስምዖን፣ ብፁዕ አቡነ ኢሳይያስ፣ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል) በተገኙበት የተገለጠውን የፓትርያርኩን የ‹ምስክርነት ሐውልት› ለማሠራት ‹‹የቅድስት ማርያም ስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ማኅበር››  ‹‹ከፍ ያለ አስተዋፅኦ ያደረገ የቤተ ክርስቲያን ማኅበር›› መሆኑን ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ተናገሩ፡፡

አቡነ ፋኑኤል ይህን የተናገሩት ሐምሌ 19 ቀን 2002 ዓ.ም ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ አለወትሯቸው በተገኙበት በአዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በተከበረው የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ላይ ነው፡፡ ‹‹ማኅበሩ በቅዱስነታቸው ዕውቅና የተሰጠው የእነ በጋሻው ማኅበር ነው፤››  ያሉት አቡነ ፋኑኤል ማኅበሩ በፓትርያርኩ ሐውልት ሥራ እና ተከላ ላይ ግንባር ቀደም አስተዋፅኦ ማድረጉን ግልጽ አድርገዋል፡፡ አቡኑ ከጥቂት ጊዜያት ወዲህ ስለነበጋሻው ቡድን የሚያሰሙትን የድፍረት መወድስ እና የምእመናኑን ሚና የሚያናንቅ አሰልቺ ንግግራቸውን የተከታተሉ በበዓሉ ላይ የተገኙ የደጀ ሰላም ምንጮች ኹኔታውን ‹‹የዐዋጁን በጆሮ›› ብለውታል፡፡

ከ‹ምስክርነት› ሐውልቱ መገለጥ በኋላ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፣ የሐውልቱን ሐሳብ የማመንጨት ቅድምናው የማፊያው ቡድን ‹‹ስውሩ ጸሐፊ›› ዘሪሁን ሙላቱ ሲኾን ምክንያቱ ደግሞ የዲያቆን በጋሻው ደሳለኝ ውትወታ መኾኑ እየተነገረ ነው፡፡ ይኸውም ዲያቆን በጋሻው እውነተኛ ማንነቱ በተለያዩ ቀናዒያን ምእመናን ከተጋለጠ፣ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ እና በዋና ሥራ አስኪያጁ በወጣ ደብዳቤ ከታገደ እንዲሁም ‹መጋቤ ሐዲስ› በተሰኘው ያልተገባ ሹመቱ ሳቢያ በፓትርያርኩ ሳይቀር በጉባኤ ከተገሠጸ በኋላ የገጠመውን ክስረት በአቋራጭ ለመቀልበስ የቀድሞ ባላጋራውን ምንደኛውን ዘሪሁን ሙላቱን ‹‹ከጉድ አውጣኝ›› ይለዋል፡፡ ጥቅም ላሳዩት ሁሉ(ለመሐመዳውያን ሳይቀር) የጥፋት ብዕሩን ከመምዘዝ፣ ፓትርያርኩን እና ብፁዓን አባቶችን የሚያዋርድ ተግባር ከመፈጸም ወደ ኋላ የማይለው ይኸው ቅጥረኛ ግለሰብም ቀን እንዲሰጠው ጠይቆ ሲያስብበት ይቆያል፡፡ በመጨረሻም ዲያቆን በጋሻው የፓትርያርኩን አፍቃሬ ርእስ(መወድስ) የመኾን ከልክ ያለፈ ፈቲው ተጠቅሞ ‹ከጎጉል ጎልጉዬ አገኘኹት› ያለውን የሐውልት ሥራ ዐይነቶች በመዘርዘር ለአቡነ ጳውሎስ ‹የምስክርነት› ሐውልት እንዲሠራላቸው ሐሳብ እንዲያቀርብ፣ ለአፈጻጸሙም ራሱ ዘሪሁን ከሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ ጋራ፣ ዲያቆን በጋሻው ደግሞ ከወ/ሮ እጅጋየሁ ጋራ ተመካክረው ለማስወሰን ይስማማሉ፡፡

የፓትርያርኩን 18ኛ ዓመት በዓለ ሢመት ‹‹በልዩ ኹኔታ እናከብራለን፤›› በሚል ሽር ጉድ ሲሉ የነበሩት፣ በተለይም ቀደም ብሎ በወንጀል ከሚፈለጉበት የሕግ ተጠያቂነት ተሰውረው የቆዩት ሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒም በሚያስተዳድሯት ቁጥጥር የሌለባት አጥቢያ ቅጽር ውስጥ የአቡነ ጳውሎስን ምስል በ170‚000 ብር (እርሳቸው 400‚000 ብር ነው ያወጣኹት ብለው ሪፖርት ቢያቀርቡም) አሠርተው በማስመረቅ መሥዋዕተ እርያ የማቅረብ ‹ልምድ› ያገኙ በመኾናቸው የፓትርያርኩን ሐውልት እስከ በዓለ ሢመቱ መዳረሻ ቀን ድረስ ሰውረው በድብቅ በማሠራት እና በዋዜማው በመግለጥ ከተጠያቂነት ለመሸሽ ተጠቅመውበታል፡፡

ዲያቆን በጋሻውም በተጋለጠው እውነተኛ ማንነቱ የተነሣ የደረሰበትን ክስረት ለመሸፈን፣ በአበው ጳጳሳት ጉባኤ ፊት ኦርቶዶክሳዊነትን በመፃረር ሲፈጽማቸው ለቆዩት ድርጊቶቹ ገሥጸው፣ ‹መጋቤ ሐዲስ› የተባለበትን ቀድሞም በአቡነ ፋኑኤል አለግባብ የተሰጠውን ማዕርግ ገፍፈው ‹አቶ› አሰኝተው ባስለቀሱት እና ባዋረዱት አቡነ ጳውሎስ ፊት ‹ሞገስ› ለማግኘት፣ ስለ ድካሙ ‹‹ፍሬም›› በበዓለ ሢመታቸው የራት ግብዣ ምሽት በበዓል አከባበር ኮሚቴ መዘጋጀቱ የተገለጸለትን የምስክር ወረቀት ከግብር አበሮቹ ጋራ መቀበሉ ይታወሳል፡፡

በተያያዘ ዜና በርእሰ አድባራት ቁሉቢ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ እየተገኙ በዓሉን የሚያከብሩት ፓትርያሪኩ የዚህን ዓመት የቅዱስ ገብርኤል በዓል ለማክበር ያመሩት ግን ወደ አዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ነበር፡፡ ቅዱስነታቸው በጉዟቸው ሻሸመኔን አልፈው ልዩ ስሙ ጥቁር ውኃ  እየተባለ በሚታወቀው የአዋሳ ከተማ መግቢያ ላይ ሲደርሱ በእነ ሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ፣ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ እና በተለይም የማፊያው ቡድን ተባባሪ በመኾን የሀገረ ስብከቱን የስብከተ ወንጌል እንቅስቃሴ በተሐድሷዊ ስልት ለመቆጣጠር እና የግለሰቦችን ኪስ ለማደለብ በሚሠራው ‹‹ማኅበረ ተስፋ ኪዳነ ምሕረት›› እየተባለ በሚጠራው አካል ተቀስቅሰው የተሰለፉ ወጣቶች ከሌላው ጊዜ በበለጠ በአቡነ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና የተለየ ሥራ መሠራቱን የሚያወሱ መፈክሮችን በማንገብ ተቀብለዋቸዋል፡፡ ሐምሌ አራት ቀን በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በተከናወነው የፓትርያርኩ ‹የምስክርነት ሐውልት› መገለጥ ወቅት ራሱን ‹‹የቅድስት ማርያም ስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ማኅበር›› እያለ የሚጠራው የእነ በጋሻው  ቡድን ባዘጋጀው መድረክ ላይ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ ባቀረቡት የበዓል አከባበር ኮሚቴ ‹ሪፖርት› ተመሳሳይ ሐሳቦችን ያዘሉ የቅስቀሳ ንግግሮችን በማሰማት ፓትርያርኩን ለጉባኤ ወደ አዋሳ መጋበዛቸው ይታወሳል፡፡

በማግሥቱ በገዳሙ በተከናወነው ሥነ በዓል ላይ ‹‹ማኅበረ ተስፋ ኪዳነ ምሕረት›› ለፓትርያርኩ የወላይታን ባህላዊ ቡሉኮ አልብሷል፡፡ ስለ ተደረገላቸው ስጦታ ምስጋና ያቀረቡት አቡነ ጳውሎስ፣ ‹‹እኛ የእንጀራ ልጅ የለንም፤ ሁላችኹም ታስፈልጉናላችኹ፤. . . ሁሉም ማኅበራት ለቤተ ክርስቲያን ይጠቅማሉ፤ የማይጠቅም የለም፡›› በማለት ለአክብሮ በዓል የተሰበሰበውን ምእመን ግራ ያጋባ ንግግር አሰምተዋል፡፡ የፓትርያርኩን አነጋገር የተከታተሉ በርካታ ምእመናን፣ ‹‹እኛ እዚህ የተገኘነው ከመልአኩ በረከት ለመካፈል እንጂ እርሳቸውን እና አጋፋሪዎቻቸውን ብለን አይደለም፤ ለምንድን ነው በዓሉን የተመለከተ ትምህርተ ወንጌል የማይሰጡት?›› በማለት በኀዘን ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ ከዚህ በተፃራሪ በዐውደ ምሕረቱ በፓትርያርኩ ዙሪያ የተኮለኮሉ የ‹‹ማኅበረ ተስፋ ኪዳነ ምሕረት›› ጥቂት ወጣቶች ፓትርያሪኩ በተናገሩ ቁጥጥር በኾነው ባልኾነው ቅጥ ያጣ ጭብጨባ ያሰሙ እንደ ነበር ተመልክቷል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሌላ ዜና የአዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት፣ ሐምሌ 17 ቀን 2002 ዓ.ም፣ ‹‹የሰበካ ጉባኤውን ቃለ ዐዋዲ በመፃረር በጠቅላላ ጉባኤ የተመረጡ የሰንበት ት/ቤቱን አመራሮች ለማገድ እና ሰንበት ት/ቤቱን አላግባብ ለመቆጣጠር በማሰብ የሰንበት ት/ቤቱን ቁልፍ በመሥበር በሌላ ቁልፍ ቀይረዋል፤›› ባላቸው ሦስት ግለሰቦች ላይ ክስ መሠረተ፡፡፡-

1) በኩረ ትጉሃን ዓለምነህ ሽጉጤ - የሲዳማ ሀገረ ስብከት የመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር አስተባባሪ፣ ‹‹ማኅበረ ተስፋ ኪዳነ ምሕረት›› እያለ በሚጠራው ማኅበር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ፣

2) መጋቤ ሐዲስ ፍሥሓ ለማ - የሲዳማ ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች ማ/መ ሐላፊ እንዲሁም በልማት እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ  ኮሚሽን የሀገረ ስብከቱ ፀረ-ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠርያ አስተባባሪ፣

3) ላእከ ወንጌል ያሬድ አደመ - የፓትርያርኩን ሐውልት አወራው ‹‹የቅድስት ማርያም ስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ማኅበር››  አባል ናቸው።

12 comments:

hiwot said...

Egize'o meharene Kirstose.Cher wore aseman Amlake kidusan.

Anonymous said...

Selam Deje selam bloger, would you post thier picture pls.Endinawukachew
ዐሥራ አንድ ብፁዓን አባቶች (ብፁዕ አቡነ ገሪማ፣ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ፣ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም፣ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ፣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ፣ ብፁዕ አቡነ ያሬድ፣ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል፣ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ ብፁዕ አቡነ ስምዖን፣ ብፁዕ አቡነ ኢሳይያስ፣ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል)

ኦርቶዶክስ ዩናይት said...

Every association is working to get grace infornt of the Patriarch not for the truth teaching of the church. Weather Mahibere Mariam or Mahibere Tesfa or Mahibere Kiduan are all the same. They want to get grace infront of Paulos not in front of God.
While mahiber Mariam and the so called Mahibere Tesfa erect the Hawlete to get grace by Paulos Mahibere Kidusan also don’t want to say anything about it because the association doesn’t want to disregarded by the man. This what you call lying infront of God. If we work for God let us tell the truth on time otherwise we are working for existence of our mahiber not for God’s word. Me as member of the church of Christ ashamed of this paul’s act and as Mahibere Kidusan ashamed of my mahiber for keeping silent.
God Bless Ethiopia forever, let God give us Matry like bishop peter who witness the truth

Anonymous said...

YEMENAFIKAN SERA YIALETAL

Anonymous said...

አቤት ይህቺ ቤተክርስቲያን ያለባት ፈተና!!! በተለይ በዚህ ወቅት እኔ የጳውሎስ እኔ የአጵሎስ እያለ የሚከፋፈለው መብዛቱ፡፡ ማን ይሆን ይህንን አስተውሎ ከልቡ ወደፈጣሪ የሚፀልይ; ማን ይሆን ጎራ ለይቶ ከመነቃቀፍ ይልቅ መክሮ ማረም የሚችል; ማን ይሆን ለጥቅም ሲል የምእመኑን መከፋፈል እያየ ዝም የማይል; ማን ይሆን እስካሁን የሰራው ስህተት ተሰምቶት በንስሀ ወደ ትክክለኛው መንገድ የሚመለስ; ማን ይሆን ፀሎቱ ተሰምቶ ይህ ሁሉ አልፎ ነገ ላይ ያለችውን መልካም ቀን ለማየት የሚበቃ; ማን ይሆን ይሆን ለብተክርስቲያን ቁርጥ ቀን ልጅ ሆኖ የሚወጣ; ማን ይሆን…
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በዱር በገደሉ ድንጋይ ተንተርሰው የአራዊቱን እና ጋንንቱን ፈተና ተቁአቁመው ስለዚህች ቤተክርስቲያን እና ስለዚህ ህዝብ ቀን ከሌት ሳታክቱ ስለሚለምኑት አባቶች ብሎ ህንን ዘመናችንን ፈተና በቃችሁ ይበለን፡፡

ሲላስ said...

አነዚህን ጣኦት ኣምላኪዎች ማንም ኣባት ብሎ መስቀላችውን እንዳይሳለም። በተለይ ኣቡነ ፋኑኤል ለበጋሻው መጋቢ ሃዲስ ብለው ሲሾሙ ማእረጉ ኣይደለም ለበጋሻው ለእሳችውም የማይገባ መሆኑን ልቦናችው ያውቀዋል።

አግናጢዎስ ዘጋስጫ said...

የሁለት ዓለም ሰው


አስመስሎ መኖር እራስን ሳያውቁ
እውነትን ዘንግቶ ክብርን ሳይጠብቁ
ህሊናውን ሽጦ መኖር በባርነት
ለእግዚአብሔር ሳይሆን ለገንዘብ መገዛት
ደግሞም ለማጭበርበር ከርስቲያን ለመምሰል
በአውደ ምህረት ቆሞ ራስን መደለል
የሚያዋጣ አይደለም ካልሆነ ለጥፋት
እውነት በአደባባይ የተገለጠች ለት
ታቦትና ጣዖት አንድላይ አይሄዱም
የሁለት ዓለም ሰው መሆን አይቻልም
ስለዚህ መምረጥ ነው ከሁለቱ አንዱን
ወይ ዓለምን መውደድ ወይም እግዚአብሔርን::

selamawi said...

በስመ ስላሴ አሃዱ አምላክ አሜን

እኔን የሚያሰጋኝ የዛሬው አይደለም ነገ በቤተክርስቲያን ላይ እነዚህ ማህበራት የሚያመጡት መከራ ይታየኛል ዛሬ በአቡነ ጳውሎስ መልካም ፈቃድ የተቋቋሙ ማህበራት ነገ እንደነ ሃይማኖተ አበው የቤተክርስቲያንን ልጆች በመናፍቃን ትምህርት እንደሚመርዙ አትጠራጠሩ ምክንያቱም ዛሬ ማህበር ብለው ያቋቋሙት ህዝቡን ለማገልገል ሳይሆን ገንዘብ የማግኛ ዘዴ ስለሆነ የተሻለ የሚከፍል ከተገኘ ለሌላ ድርጅትም መስራታቸው ስለማይቀር ፍሩ በተለይ የአቡነ ጳውሎስ እሩጫ በጣም አደገኛ ነው እንደምታውቁት ዛሬ በጳጳስነት ደረጃ በእሳቸው እጅ የተሾሙት አባቶች ከጥቂቶቹ በስተቀር ህጸጽ ያለባቸው ናቸው እንኳን ለጳጳስነት ይቅርና ለምንኩስና የሚያበቃ መስፈርት የሌላቸውን ሁሉ ሾመዋል አሁንም እየተዘጋጁ ነው በየአብያተክርስቲያናቱ ሊቃውንቱ እየተባረሩ ወታደሮች ቦታውን ይዘውታል ሽጉጥ ይዞ የማይንቀሳቀስ ዲያቆንና ቄስ የለም የቤተክርስቲያን አገልግሎት ጨርሶ ተዳክሟል ካህናቱና ዲያቆናቱ የቤተክህነትን መመሪያ ለማክበር እንጅ እግዚአብሔርን መፍራት የለም አዲስ የሚተኩትም የቤተክርስቲያን ልጆች ይህንን እየተከተሉ ነው እግዚአብሔር አምላክ በትንቢተ ሕዝቅኤል 22፥ 26 ካህናቶችዋም ሕጌን በድለዋል ቅድሳቴንም አርክሰዋል ቅዱስ በሆነና ቅዱስ ባልሆነ መካከልም አልለዩም፥ በንጹሕና በርኩስ መካከል ያለውን ልዩነት አላስታወቁም ዓይናቸውንም ከሰንበታቴ ሰወሩ እኔም በመካከላቸው ረከስሁ።

እንዳለው እግዚአብሔርን ማምለክ ቀርቶ አቡነ ጳውሎስን ማምለክ ተጀምሯል እግዚአብሔርን መፍራት ቀርቶ እሳቸውን ብቻ መፍራት ተጀምሯል የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሳይሆን የሳቸውን ፈቃድ ብቻ ነው የሚፈጽሙት ታዲያ ,, ለአምልኮቴ ቀናተኛ ነኝ ያለው አምላክ በአምልኮቱ ለመጡበት ለአቡነ ጳውሎስ ምን ያመጣ ይሆን ? እድሜ ይስጠን አብረን እናየዋለን

Anonymous said...

አለምነህ ሽጉጤ(በምን ምክንያት በኩረ ትጉሀን አሉት ደሞ እሱን)አዋሳን የምታውቁና ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያንን ለምታውቁ የአጥሩ በርጋር የነበረችው ነዋየ ቅዱሳት መሸጫ ሱቅ ውስጥ ይሸጥ የነበረእና የሰንበት ት/ቤት አባልም ነበር። አለምነህ ሱቋ ውስጥ ሲሰራ ሳያውቀው በነበረው የተዝረከረከ የገንዘብ አያያዝ ሳቢያ ተቆጣጣሪም ስላልነበረው ጭልጥ ወዳለ የቤተክርስቲያን ዘረፋ የገባ ምስኪን ነው አለምነህ የዛሬ 10 አመት ገደማ ደሞዙ 150 ብር ሆናና ብቸኛ ገቢውም ሆና ከቤተክርስቲያን ውጪ እና ፊት ለፊት ሌላ የግሉን መዝሙር ቤት የከፈተ ጀግና ነው። ከዛ በተጨማሪ ጥሩ ያደረገ እየመሰለው እቤቱ የነመለሰ ወጉና ሌሎችም የጴንጤ ሰባክያንን መጻህፍት የሚሰበስብና የሚያነብ ቀስእያለም እየተለማመዳቸው መጥቶ ተው ይቅርብህ ሲባል ይከራከር የነበረ ነው ከሶስት አመት በፊትም የዚህ ጽሁፍ ጸሀፊ ቀድሞ በነበራቸው ጓደኝነት ሳቢያ ከአሜሪካ ደውሎ ሲያዋራው ስለጼንጤዎች በመከራከር እኛም ልክ ነን እነሱም ልክ ናቸው ይል የነበረ የጴንጤ አስተሳሰብ ልክፍተኛ ነው። ያሬድ አደመም ቀደም ብሎ ጀምሮ የገንዘብ ነገር የማይሆንለት አገለገልኩም እያለ ሀይለኛ ፍቅረ ነዋይ ያለበት ልጅ ነው ያሬድ አደመ ዘማርያንን በማሰባሰብ አዋሳ ገብርኤል ሲመረቅ ግቢ ውስጥ አስፋልት ለማንጠፍ በሚል ብር አሰባስቦ አላግባብ እንደተጠቀመም ይታማል እኔ የማዝነው ሐዋርያው ቅዱሱ የወንጌሉ ገበሬ አባታችን መልአከ ምህረት ጳውሎስ ቀፀላ እድሜ ልካቸውን የደከሙበት ቦታ በእንደዚህ አይነት አረሞች ሲታመስ ምን ይሰማቸው ይሆን እያልኩኝ ነው። ለነገሩ የእውነት የተዋሕዶ ዘር የበቀለባቸው ጠንካራ ልጆች ደሞ ስላሉ እጽናናለሁ። ምዕመናን ያሬድና አለምነህ ላእከ ወንጌል እና በኩረ ትጉሃን ተብለው ሲመጡ የቤተክርስቲያን ሰዎች መስለዋችሁ እንዳታስቡ እንደሌላው ምስኪን ወንድሜ ወተው ወርደው በላባቸው ላለመብላት የወሰኑ ባንድ ወቅት ከነበረ የስሜት ሰንበት ተማሪነት ያልዘለቀ እውቀት የሌላቸው መሪ እንጂ ቁጥር ስፍር በሌላቸው ሊቃውንት በተሞላች ቤተክርስቲያን ውስጥ አለቦታቸው እራሳቸውን ስበው ለማስቀመጥ የሚፍጨረጨሩ እበላ ባይ አረሞች ናቸው። የቅድስት ተዋህዶ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስትያናችንን ትንሳኤና ቤተክርስቲያናችንም ዳግም በሊቃውንቶቿ ምትመራበት ዘመን ያሳየን።

Anonymous said...

አለምነህ ሽጉጤ(በምን ምክንያት በኩረ ትጉሀን አሉት ደሞ እሱን)አዋሳን የምታውቁና ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያንን ለምታውቁ የአጥሩ በርጋር የነበረችው ነዋየ ቅዱሳት መሸጫ ሱቅ ውስጥ ይሸጥ የነበረእና የሰንበት ት/ቤት አባልም ነበር። አለምነህ ሱቋ ውስጥ ሲሰራ ሳያውቀው በነበረው የተዝረከረከ የገንዘብ አያያዝ ሳቢያ ተቆጣጣሪም ስላልነበረው ጭልጥ ወዳለ የቤተክርስቲያን ዘረፋ የገባ ምስኪን ነው አለምነህ የዛሬ 10 አመት ገደማ ደሞዙ 150 ብር ሆናና ብቸኛ ገቢውም ሆና ከቤተክርስቲያን ውጪ እና ፊት ለፊት ሌላ የግሉን መዝሙር ቤት የከፈተ ጀግና ነው። ከዛ በተጨማሪ ጥሩ ያደረገ እየመሰለው እቤቱ የነመለሰ ወጉና ሌሎችም የጴንጤ ሰባክያንን መጻህፍት የሚሰበስብና የሚያነብ ቀስእያለም እየተለማመዳቸው መጥቶ ተው ይቅርብህ ሲባል ይከራከር የነበረ ነው ከሶስት አመት በፊትም የዚህ ጽሁፍ ጸሀፊ ቀድሞ በነበራቸው ጓደኝነት ሳቢያ ከአሜሪካ ደውሎ ሲያዋራው ስለጼንጤዎች በመከራከር እኛም ልክ ነን እነሱም ልክ ናቸው ይል የነበረ የጴንጤ አስተሳሰብ ልክፍተኛ ነው።

Anonymous said...

ያሬድ አደመም ቀደም ብሎ ጀምሮ የገንዘብ ነገር የማይሆንለት አገለገልኩም እያለ ሀይለኛ ፍቅረ ነዋይ ያለበት ልጅ ነው ያሬድ አደመ ዘማርያንን በማሰባሰብ አዋሳ ገብርኤል ሲመረቅ ግቢ ውስጥ አስፋልት ለማንጠፍ በሚል ብር አሰባስቦ አላግባብ እንደተጠቀመም ይታማል እኔ የማዝነው ሐዋርያው ቅዱሱ የወንጌሉ ገበሬ አባታችን መልአከ ምህረት ጳውሎስ ቀፀላ እድሜ ልካቸውን የደከሙበት ቦታ በእንደዚህ አይነት አረሞች ሲታመስ ምን ይሰማቸው ይሆን እያልኩኝ ነው። ለነገሩ የእውነት የተዋሕዶ ዘር የበቀለባቸው ጠንካራ ልጆች ደሞ ስላሉ እጽናናለሁ። ምዕመናን ያሬድና አለምነህ ላእከ ወንጌል እና በኩረ ትጉሃን ተብለው ሲመጡ የቤተክርስቲያን ሰዎች መስለዋችሁ እንዳታስቡ እንደሌላው ምስኪን ወንድሜ ወተው ወርደው በላባቸው ላለመብላት የወሰኑ ባንድ ወቅት ከነበረ የስሜት ሰንበት ተማሪነት ያልዘለቀ እውቀት የሌላቸው መሪ እንጂ ቁጥር ስፍር በሌላቸው ሊቃውንት በተሞላች ቤተክርስቲያን ውስጥ አለቦታቸው እራሳቸውን ስበው ለማስቀመጥ የሚፍጨረጨሩ እበላ ባይ አረሞች ናቸው። የቅድስት ተዋህዶ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስትያናችንን ትንሳኤና ቤተክርስቲያናችንም ዳግም በሊቃውንቶቿ ምትመራበት ዘመን ያሳየን።

Anonymous said...

ሳሙኤል፡ዘአሰቦት፡ said…

የእግዚአብሔር፡አገልጋዩ፡አባታችን፡ሊቀ፡
ሊቃውንት፡አለቃ፡አያሌው፡ታምሩ፡በጊዜው፣
እያሱ፡ወልደ፡ነዌ፡አይሁድን፡እንዳስጠነቀቃ
ቸው፣"የምታመልኩትን፡ዛሬ፡ምረጡ።እኔና፡
ቤቴ፡ግን፡እግዚአብሔርን፡እናመልካለን።" በማለት፡ያቀረበልንን፡ጥሪ፡አላደምጥ፡ብለን፡ይ
ኸው፡ክውስጥ፤እስከ፡ዳርና፣ከዳርም፡እስከ፡ውስጥ፡
ከበቡን፣አስከበቡን፤ተከበብን።

እኒህ፡ምድራዊ፡ዓለምን፡የመረጡ፣ለገንዘብ፡ያደ
ርሩ፡ዓማፂያን፣ለዓይኖቻችን፡የከፋና፡ለተዋሕዶ፡
እምነታችን፡ፀር፡የሆነውን፣የምርጫቸውን፣ምል
ክት፣የጣዖታቸውን፡ድንጋይ፣ለውርደታችን፡ምስ
ክርነት፣መድኃኔ፡ዓለም፡ደጃፍ፡የገባ፡ይግባው፡ብ
ለው፡ግልጥ፡አድርገው፡አቆሙ!።

ከዚህ፡ወዲያ፡ነቢያትና፣ሐዋርያት፡ስለ፡ጥፋት፡ር
ኩሰት፡ያስተማሩንን፡በምን፡ቋንቋ፡ቢነገረን፡እንረ
ዳና፣እንደ፡ካሌብ፡ወልደ፡ዮፎኒ፡የእግዚአብሔርን፡
ጠላቶች፡እንቋቋም፡ይሆን?!

የአቡነ፡ተክለ፡ሃይማኖት፡አምላክ፤የደቀ፡መዝሙ
ሩ፡የአያሌው፡ታምሩ፡አምላክ፣እኛንም፡እንደ፡ካሌ
ብ፡አዘጋጅቶን፡ተዋሕዶ-ኢትዮጵያን፡ለመታደግ፡
ያብቃን።አሜን


ሳሙኤል፡ዘአሰቦት

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)