July 28, 2010

አባቶችን የማደራደሩ ውይይት ይጀመራል


(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 28/2010)፦ ከአምስተኛው ፓትርያርክ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሲመት ማግስት ጀምሮ በቤተ ክርስቲያኒቱ የተነሣውን መከፋፈል ለማቆምና በአባቶች መካከልም የተፈጠረውን እስከ መወጋገዝ የሚያደርስ ልዩነት በእርቅ ለመጨረስ በተጀመረው እንቅስቃሴ ቅ/ሲኖዶስን ወክለው የሚወያዩት ልዑካን ከዚህ በፊት የዘገብናቸው ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ፣ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ፣ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል፣  ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስና ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ሳይሆኑ ከሐምሌ ስድስቱ የቅ/ሲኖዶስ ጉባዔ ማግስት ስማቸው በየጋዜጣው የተጠቀሰው ብፁዕ አቡነ ገሪማ፣ ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ፣  ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ እና መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስ ናቸው። የአሜሪካን አባቶችን ወክለው ደግሞ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ፣ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ እና ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ይደራደራሉ ተብሏል።

15 comments:

Anonymous said...

minew selam yemiyametu abatoch tefitew new abune gerima yamilakut new weynes kelid new yeteyazew?

Anonymous said...

bune gerima???!!!!Erasn beras matalel
Yikir EnjiAdir bayoch sayhonu Ewnetn yeyazut yideraderu Alezia degmo Biker
HoHoHoY

Anonymous said...

bune gerima???!!!!Erasn beras matalel
Yikir EnjiAdir bayoch sayhonu Ewnetn yeyazut yideraderu Alezia degmo Biker
HoHoHoY

Anonymous said...

I don't think so! No result after this dicus.
Because, Aba Gerima is one of gurd of Aba Paulos and Elyas Abirha is also Tagay/Weyane, Seyfe-Silasie is adirbay and Menafiq, Aba Atnatewos is good father, but, the problem won't solve by one persson interest.
I think it is very chatter and tricky.

Anonymous said...

Wow what a nice fight is gonna be!Am telling U Abune Melketsedek of usa = abune Gerima.I don't think the grouping is the right one to bring peace and unity in the church.Where are those two big names ...Abune Paulos and Merkorios...anyways let's pray for the best

selamawi said...

በስመ ስላሴ አሃዱ አምላክ አሜን

,,የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን ብለን ዝም አልን ,,

ወገኖቼ ከአሁን በኋላ ዝም ብለን ጩኸታችንን ወደ እግዚአብሔር ብናደርግ መልካም ነው ለቤተክርስቲያናችን ሰላም መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ወደ እርሱ እንጩህ እስቲ አስቡት አቡነ ገሪማ እንኩዋን የሲኖዶስ ጉዳይ ይቅርና በግለሰቦች መካከል የተፈጠረን ቅሬታ ያርግቡ ተብለው አለያይተው የሄዱ ሰው ናቸው ብፁእ አባታችን አቡነ አትናቴዎስ በአሁኑ ሰዓት በእርጅና እና በህመም ምክንያት ብዙ መንቀሳቀስ ካቆሙ ቆይተዋል ምንም ማምጣት አይችሉም ብለው ይመስለኛል መጋቤ ቢሉይ ሰይፈስላሴ እና ንቡረእድ ኤልያስ ለዚህ ድርድር መመረጣቸው እራሱ በጣም ነው ግራ የገባኝ ታውቃላችሁ እርቁ እንዲደረግ አቡነ ጳውሎስ በፍጹም አይፈልጉም ለዚያም ነው ይህንን ያደረጉት እነ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ቢመጡ ህዝቡን አንድ አድርገው ለቤተክርስቲያንም መፍትሄ የማምጣት መንፈሳዊ ፀጋ ያላቸው እንደሆኑ ስለሚታወቅ ነው ያስቀሯቸው

አምላክ ሆይ እባክህ ልቦና ስጣቸው

Anonymous said...

ወይ ይሄፈተናመብዛቱ ? አሁንእነዜህናቸው
ሰላም እና እርቅ ፈላጌዎች?ወይስ ያባትቤት ሴዘረፍ
አብረህ ዝረፍ ነው ወይስ ምነው ብቻቸውን………
ብለው አስበውነው.ድሮውም ቤሆን የሃይማኖት ችግር
አላጣላቸውም .እኔ ንእኮን በዚች እድሜ ታላቅ ሰውናቸው
የሜባልላቸው አረጋውያን አውቃለሁ.እንዴት የሜዘገን ነገር
ነው! እስቲዝምብላችሁ አስብት ማንከማን ነው የሜሻለው
እነሱ ምንቸግሮዋቸው ዞሮ ዞሮ የኛው ገንዘብነው የሚባክነው፤
ይዘመን በስላም ያልፍና እናወራው ይሆናል ብቻእግዛብሔር
ይቅር ይበለን የቤተክርስቴያን አምላክ ይቅር ይበለን፤
አሜን.

Dan said...

አማራጭ የሌለው መፍትሄ

አሁን ካሉት ጳጳሳት አምስት ወይም አስር የሚሆኑ
በብቃታቸው:ወንጌላውያን
ለማስተማር የበቁ፥
የማይነቀፉ፥ የማይጨቃጨቁ የማይከራከሩ
ነገር ግን ገር የሆኑ፥፥
ገንዘብን የማይወዱ፥
በጭምትነት ሁሉ እየመከሩ በመልካም ራሳቸውን የሚያስተዳድሩ፤

(ሰው ራሱን መቆጣጠር ማስተዳድር ሳያውቅ፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እንዴት ያስተዳድራል እንዴት ይጠብቃታል?)

በትዕቢት ያልተነፉ (በዲያቢሎስ ፍርድ እንዳይወድቁ)

በዲያቢሎስ ነቀፋና ወጥመድም እንዳይወድቁ፥ በቤተ ክርስቲያን ሰዎች በመልካም የሚመሰከርላቸው ።

እግዚአብሔርንም መምሰል ታላቅነት ያወቁ ፤

በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገውን ክርስቶስን የሚመሰክሩ

ለደሀ ወንጌልን የሚሰብኩ ይለዩልን::

እንደነሱ ብቃት ያላቸውን በመልካም የሚመሰከርላቸው (በአሮጌ እርሾ ያልተበከሉትን ) ከቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ጋር ሆነው እየመረጡ
በየቦታው እየሾሙ ክርስቶስን እንዲመሰክሩ ለደሀ ወንጌልን እንዲሰብኩ ይላኩዋቸው

እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ያለ የበጎች አረኛ እነሱንም በቅድስና የሚመራ ከመካከላቸው በጸሎት ይምረጡ::

የቀሩትን ግን ጠብቁ ተብለው የተሰጣቸውን በጎች ግልገሎች የሚበሉ
ለአውሬ አሳልፈው የሰጡትን ቤተ ክርስቲያን ስብስባ በየገዳማቱ በጸሎት ተወስነው ይቀመጡ::
ጌታ አንድም ነፍስ እንድትጠፋ አይፈልግምና::

Anonymous said...

Wendimoch na Ehitoch erki selam ayiwerdim kemalet minew binitseliy. Yebetekihinet chigir ahun aydelem yetejemerew yebizu gize zemenat chigir new. yihinin chigir degmo bitinat bitagez yebelete tiru yihonal. Lemisale chigirechu lemtikes: Be bizu ageligayoch(Be teley ye betekihinet timihirt bedemb yaltemaru ageligayoch), Le-abatoch , ke Like Diakon jemiro eske papas , yemisetew kibirye kelik yalefena yewushet, yemasmesel kibir new. Le shumet, lesiltan, Le genzeb yemiset kibir new. Bizu ageligayoch le tikim yekomu enji be' ewunet lehayimanotachesw, lebetekiristiyanachew, le miemenachew gid yelachewum. Bedagim mitsiat Bekistos fit le fird yemikerbum aymeslachewum.Yihin zengitewutal chirash. Bizuwochu mi'emenan benezih wushetegnoch ageligayoch bezer be poletika aquam kemeselwuachew yidegifiwauchewal. minim enquan wushet biyaweu binageru, Dibin yale hatiat biserum. Lemisale Ye abune morkerewos ye americaw patryarik binaye dibin yale hatiat new yeseru. Hizbun tito, sema'etnet fertew(Menist endayigedilachew fertew)hizbun le tekula tilew sihedu America metew ene negn patriyarik silwachew amen bilew tekebeliwachew. Eski egziabher yasayachihu ye Ethiopia hizib wede America eyehede new ke patriyariku libarek Ehadeg eskiwedk dires malet new. Endet bilo lihon yichilal weyis le transport yichilutal. Betam, betam tilik sihitet be Ethiopia tarik. Le Kibrachew, Letikimachew silu hizib kefafelu, kezih befit yalinebere sir'at aderegu. Bizu ageligayoch endezih nachew sirachew. Tikimachew esketekeber dires ye miemenan hiwet yibelash ayibelashim minim ayimeslachewum. Biziwoch Mi emenanin kemeqawem yilike bezer be plotitica ketemesaseliwachew amen biew mekebel new. minim enquan andande me'emenainin binoru betikikil yemikawemu bizu sew gin besimet yemigauzinew yalew. Abetu, O Egziabher amlakachi kezih kesimet weten beteregaga menfes yeminasibibet ena yeminastewulibet menfes adilen. Chigiru ke me'emenum ke agelegayochum new. Lehulachin egziabher amlak libona yisten.God bless Ethiopia.

gb22 said...

BE EZIH ZEMEN YEMININOR EGNA BETECHRISTIAN BE MENAFIKAN TEKEBA, BE AHZAB TEWERA EGNA BE BETECHRISTIAN ASTEDADER TETALTEN "EYETEDERADERIN NEW" KIDUSAN EBAKACHIHU EZENULIN ENJI ATIZENUBIN.
KIDUS Kerlos hoy atizenibin.
KIDUS Yohanis Afewerk hoy atinaken.
ABA Heryakos ebakih atatatilen.
ABUNE Tekelehaymanot ayitekizubin.
minim enkua le genzeb adliten be Ayropilan heden Newyork gebiten alekochua nenina "binideraderim" be betechrisian lay binafezim egnan enji betechristian atitawekibin.Gin lehulum ye zare zemen lijochiwo "E Y E T E D E R A D E R N" NEW.

Endiaw lemehonu lijochachin min yilun?be ezih amet be ezih wer Betechristian be menafikan techenka abatochu "E Y E T E D E R A D E R U" neber sibal!!!!

Anonymous said...

ይድረስ ለኢትዮጵያ መንግሥት
መንግሥት ዉክልናዉ የሕዝብን ሰላምና ጸጥታ ለማስከበር መሆኑ የማየሻማ ግልጽ ነዉ። የሕዝብ ሰላም ደግሞ ለመንግሥት የተረጋጋ ሥራ ማከናወኛ ዕድሜ ነዉ ። የሕዝብ ሰላም የሚደፈርሰዉ ደግሞ ሰዉ ባህሉን፣ሃይማኖቱን ከፈጣሪዉ በተቸረዉ ነጻ ፈቃድ መገልገልና ማገልገል ሳይችል ሲቀር መሆኑ ግልጽ ነዉ። መንግሥት ለሀገር ልማትና እድገት ደፋ ቀና ሲል አንዳንድ ግለሰቦች ለግል ዝናና ክብር የመንግሠትን የተረጋጋ ሥራ ለማደፍረስ ደፋ ቀና ሲሉ ማየት ከተራዉ ህዝብ ዘልቆ ወደ ሃይማኖት መሪዎች ማምራቱ የአደባባይ ምስጢር እሆነ መጠቷል። ስለሆነም በአጭር ቋንቋ የጥቂት ግለሰቦችንና የአቡነ ጳዉሎስን የሕዝብን ሰላም የማደፍረስ ዘመቻ መንግስት እንዲፈትሸዉ እላለሁ።ህዝብን ከግለሰብ ነጥሎ የማየት ዓይን ይኑረን። በሃይማኖት ሽፋን የግል ኑሮአቸዉን ለማደላደል በአቡነ ጳዉሎስ ቡራኬ የአመጽ ጦር የሚሰብቁትን ማስታገስ ለሰላሙ ሲል የመንግሥት እርምጃ መሆን አለበት።አስታራቂ እንጂ አናካሽም መሆን የለበትም። ኩሩ ባህልና ሃይማኖት እያለን ስደት ይብቃን። ብዕሩ ነኝ

Anonymous said...

የ አባ መልኬ ጼደቅ ዘአሜሪካ የመጀመሪያ አጀንዳ ማን ይዉደም ይሆን? አባ ጳዉሎስ ወይስ ማህበረ ቅዱሳል?

ቸር ወሬ ያሰማን

Anonymous said...

betam yasazenal abune germa liasetareku new woyese liayayezu kelede new yikere yebelachehu

Anonymous said...

gerima ketelaku wutetune kahunu megemete yechalale belu steleyu germa enkuan ye abune phawelose estnfase nachew jerusalem yemigegnwene church leshetu yeneberu sew nachew

Anonymous said...

THIS IS THE TRUTH:

As long as the current brutal and power-hungry WEYANE regime is in power both the county and its national church (The Ethiopian Orthodox Tewahedo) could by no means be free from the regime's oppressive rule.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)