July 22, 2010

አባቶችን ወክለው የሚደራደሩት ተደራዳሪዎች ታወቁ

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 21/2010)፦ ከአምስተኛው ፓትርያርክ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሲመት ማግስት ጀምሮ በቤተ ክርስቲያኒቱ የተነሣውን መከፋፈል ለማቆምና በአባቶች መካከልም የተፈጠረውን እስከ መወጋገዝ የሚያደርስ ልዩነት በእርቅ ለመጨረስ በተጀመረው እንቅስቃሴ ቅ/ሲኖዶስ ተወካዮቹን መምረጡ ታወቀ። ከዚህ በፊት መርጧቸው የነበሩትን ሻረ።

ዛሬ ረቡዕ በተካሄደው ስብሰባ ላይ ከዚህ በፊት መርጧቸው የነበሩትንና አሜሪካ ያሉት አባቶች ያልተቀበሏቸውን ልዑካን በመተው አረጋውያን አባቶችን ተክቷል። በዚህም መሠረት ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ፣ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ፣ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል፣  ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስና ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ይሸመግሉ ዘንድ ተመርጠዋል። ከእነርሱም ጋር ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ እና መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስ አብረው ይሄዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካን አባቶችን ወክለው ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ፣ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ እና ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ይደራደራሉ ተብሏል። የቀድሞውን ፓትርያርክም ሆኑ የአሁኑ በድርድሩ ውስጥ እንደማይገቡ ታውቋል።

ከዚህ በፊት በተደረገው ምርጫ ቅዱስ ሲኖዶስ ወክሏቸው የነበሩትን ተደራዳሪዎች እንደማይቀበሏቸው የአሜሪካዎቹ አባቶች በተናገሩት መሠረት እነዚህ አረጋውያን አባቶች ሊመረጡ ችለዋል ተብሏል።
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)