July 19, 2010

“ ለጊዜው ተስማምተናል "

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 18/2010)፦
ክርስቲያን ተብለው የተጠሩ ሁሉ
ኧረ ምን ነካቸው አበዱ ይላሉ
ሞኞች ናቸው ጅሎች ቢዝነስ የማያውቁ
ያልኖረን ቃል ፈጥረው “ተጣሉ ታረቁ
ተወጋግዘው ነበር ዛሬ ግን ተስማሙ“
ብለው የሚያወሩ ሚያቦኩ የሚያሙ።
ድሮም አልተጣላን ክስም አልነበረን
በታክቲክ፡ነው፡እንጂ፡በዓላማ፡አንድ፡ነን::

እርግጥ በተሰለፍንበት ተመሳሳይ ሜዳ
በአጨዋወት ስልታችን አንዱ አንዱን ሲጎዳ
መኖሩን አንክድም ነበረን ተቃርኖ
ደጋፊም ተጣልቷል ሁለት ጎራ ሆኖ፡
አሁን ግን ተግባባን በጋራ ለመብላት
ለሰላም መግለጫም አቁመናል ሐውልት
ዓለም ባደነቀው በgive & take ስልት
እንደተሰጠን ስም - “ቅዱስ“ : “አቶ“ ሆነን
“ለእኔ“ “ለእኔ“ ክብር ልንሰራ ተስማማን
ወዮ ለእናንተ ውጪ ለቆማችሁ
ማልያ ቀይሮ መግባት ላልቻላችሁ
ለራሳችሁ አስቡ አንድ መልክ ላላችሁ
ዓለም ላይ ኖራችሁ “ዓለም“ ላልገባችሁ

5 comments:

Anonymous said...

Really, I love this

Anonymous said...

deje selams we have to do some thing so let we try to do some thing together.i think atleast we can ask abt our money.we have a right it is our property.imebrhan gin minew zim alshin teklye zim alki iwnet i have no word i cant my eyes filled with tear... my heart is broken

Enmar Ketfatachen said...

ብዙኃን እለ ይቤሉ መኑ ያርእየነ ሠናይቶ(መዝ 4-6)
ይድረስ ከላይ ከፓትርያሪኩ እታች እስካለው ምዕመን ድረስ። በዚህ ሰዓት ሁላችንም እንዲህ እያልን ነው በጎውን ማን ያሳየናል? መልሱ ግን መጸሐፍ ቅዱስ ላይ አለ። ከኛ የሚጠበቀው አንብቦ ማስተዋል ነው።
ማቴዎስ 24- ከቊጥር 4-15 ይህን ሊሆን ግድ ነው ብሏል ጌታ ማመን ያለብን የጌታን ቃል ወይስ ሰዎች የሚያደርጉትን። ጌታ ስለቃሉ እንዲህ ብሏል። ሰማይና ምድር ያልፋሉ እንጂ ቃሌ ግን አያልፍም። ታዲያ የዚህን ወንጌል ምዕራፍ ዋና መልእክት ።
ይህ ሊሆን ግድ ነው። ምን ሊሆን ነው ግድ፤የተመረጡት ሊስቱ፣ ጦርን ፣ወሬን፣ ልንሰማ ግድ ነው ግን አትደንግጡ ይህ የምጥ መጀመሪያ ነው። ብዙ አሳቾች ይነሳሉ ፤ከዓመፃ ብዛት የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች እስከ መጨረሻው የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። ይላል ታዲያ በሰው ሳንፈርድ ሰውን ሳናሰናክል ጸንቶ ለመዳን ይህን ቃል እናንብብ ማቴ 24- 15 የጥፋትን ርኵሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ እንባቢው ያስተውል።
አሁን በተቀደሰችው ሥፍራ ጥፋት ርኵሰት ቆሞአል።
የቆሙት ጥፋቶች ሀውልት ብቻ አይደለም
ጥፋት 1- የኖረው ሥርዓት የማዕረግ ስም የሚሰጠው በጳጳስ ነው ታዲያ ዲ/ን በጋሻው ጵጵስና አለው ማለት ነው እኛ ሳናውቅ ??? ለፓትርያሪኩ ሰማዕት ዘእንበለ ደም ብሎ ስም የሰየመላቸው። ምናልባት ፓትርያሪካችን እርሱ ይሆን እንዴ?አሁን እንደ ሆነ ሁሉም ነገር በሲኖዶስ ሳይሆን በግለሰብ ነው የሚጸድቀው ወደ ሲኖዶስ ከቀረበ መንፈስ ቅዱስ አይሆንም ይላል ስለዚህ አጽድቆ ማምጣት እና መግለጫ ማውጣት ብቻ ነው ። መቼም ደጀሰላምን የማያነብ የለም ወደ ቤተክነት ቀረብ ያላችሁ ይህንን ጠይቁና ቁርጡን እንወቅ። ሲያልቅ አያምር እኮ ነው ነገሩ ዘንድሮ። አሊያም ለፓትርያሪኩ ንገሩልን እንዴት በዲ/ን ስም ሲሰየምሎት ይቀበላሉ። ከዚያም በላይ ይህ ስም የወጣሎት ውዳሴ ማርያም ባልደገመ ሰው ነው ውዳሴ ማርያም ተምሮ ቢሆን ሰማዕትነት ያለ ደም እንደ ማይሰጥ ያውቅ ነበር ።
የሀሙስ ውዳሴ ማርያም እንዲህ ፡ይላል ርዕሱ ዳዊት ዘነግሠ ለእስራኤል 6ኛ ተራ ላይ ይገኛል።
ስለ ሰማዕታት ሲናገር ፦ አማን መነኑ ሰማዕታት ጣዕማ ለዛ ዓለም ወከዓው ደሞሙ በእንተ እግዚአብሔር ወተዓገሡ ሞተ መሪረ ይላል፡ ትርጉም ሰማዕታት የዚህን ዓለም ጣዕም ናቁ መራራ ሞትን ታግሠው ደማቸውንም ስለ እግዚአብሔር አፈሰሱ።
በታሪክ ሳይሞቱ ሀውልት የቆመላቸው ብቸኛውና የመጀመሪያው ፓትርያሪክ አቡነ ጳውሎስ ደም ሳያፈሱ ሰማዕትነታቸው በ6ኛው ፓትርያሪካችን ዲያቆኑ ተረጋገጠላቸው። ነገ ደግሞ ቤ/ክን በስማቸው ይታነጽ እንዳትሉን።

Anonymous said...

ሳሙኤል፡ዘአሰቦት፡said...


ትምህርታዊ፡ግጥም፡እንደመሆኑ፡አንዳንድ፡
ስህተቶች፡ቢታረሙ፡በጎ፡ነው።ለምሳሌ፡ ከላይ፡ወደታች፡ስምንተኛው፡ስንኝ፡እንዲህ፡ይላል፦

"በስትራቴጂ እንጂ በዓላማ አንድ ነን።"

የሚለውን፡ስንመለከት፡ስትራተጂ፡የሚለው፡
በአማርኛ፡የቅርብ፡ትርጉሙ፡የወደፊትን፣
የረዥሙን፡መጪውን፡እንደ፡ዓላማ፡የሚያ
መለክት፡ስለሆነ፣ዓላማና፡ስትራተጂ፡ሊቃረ
ኑ፡የማይችሉ፡መሆናቸውን፡እንረዳለን።

ስለዚህም፣የተጠቀሰው፡ስንኝ፡እርስበርሱ፤
የሚቃረንና፣ገጣሚው፡ያሰበውን፡የማያስተላ
ልፍ፡ሆኖ፡እናገኘዋለን።በስትራተጂ፡ተቃር
ኖ፡በዓላማ፡አንድ፡መሆን፡አይቻልምና!

ገጣሚው፡ማለት፡የፈለገውንና፡በርግጥም፡በ
ጣዖት፡ጳውሎስና፡በአገልጋዩ፡በበጋሻው፡መካ
ከል፡ከዚህ፡ቀደም፡እንደቅራኔ፡ይታይ፡የነበረው፡
dylingaልዩነት፡ሁሉ፤

"የታክቲክ፡"

እንደነበረ፡ለመጠቆም፡ነው።የተጠቀሰው፡
ስንኝ፡በሚከተለው፡እርማት፡ተስተካክሎ፡
ቢቀርብ፡ይገጣሚውን፡አስተሳሰብ፡አንባብ
ያንን፡በትክክል፡ሊረዱት፡ይችላሉ።እንደ፡
እርማቱ፡ሲነበብ፡እንዲህ፡ይላል፦

"በታክቲክ፡ነው፡እንጂ፡በዓላማ፡አንድ፡ነን።"


በተረፈ፡እግዚአብሔር፡ተዋሕዶ፡እምነታችንን፡
ከጥፋት፡ርኩሰትና፡አጋሮቹ፡ጥቃት፡ያድንልን።
እመ፡ብርሃንን፡ተደረሰብን፡መዓት፡ታውጣን።
አሜን።


ሳሙኤል፡ዘአሰቦት።

Sirgut said...

Let's pary. And live according to Jesus Christ.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)