July 13, 2010

አንዳንድ ነጥቦች ስለ ሕገ ቤተ ክርስቲያን

የሚከተለው ጽሑፍ የዛሬ ዓመት ጁላይ 2009 ያወጣነው ነበር። እነሆ ዛሬም ከዓመት በኋላ አልቀነሰም። እስቲ ተመልከቱት።
+++
(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 18/2009)
(
አቤል ዘቀዳማዊ እንደጻፈው)
እስቲ ቅዱስ ፓትርያርኩም ሆነ ብዙዎቹ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የማይቀበሉት ሕገ ቤተ ክርስቲያን  ስለ ፓትርያርክ ስልጣንና ተግባር ምን ይላል? ለዚሁ ጥያቄ መልስ ለማግኘት በራሳቸው በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ተቀባይነት ያገኘውን ሕገ ቤተ ክርስቲያን ካነበብኩት ላካፍላችሁ።
1.
ፓትርያርክ ተጠሪነቱ ለቅዱስ ሲኖዶስ ነው (ሕገ ቤተ ክርስቲያን  1991)፣
2.
ፓትርያርክ የቅዱስ ሲኖዶስና የቋሚ ሲኖዶስ ስብሰባዎችን ይመራል፣
3.
በቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ ለብፁዓን ጳጳሳት የሊቀ ጵጵስና መዓረግ ይሰጣል፣
4.
ለታላላቅ ገዳማት አበ ምኔቶችና በሀገረ ስብከቱ ለተመረጡ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች የመዓረግ ስም ይሰጣል፣
5.
ከቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጡና የተላለፉ ሕጎች፤ ደንቦች፤መመሪያዎችና ልዩ ልዩ ውሳኔዎች በተግባር መዋላቸውን ይከታተላል፣
ስለ ቅዱስ ፓትርያርክ ከስልጣን መውረድስ ሕገ ቤተ ክርስቲያን  ምን ይላል?

ፓትርያርኩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ላይ ከተሾመ በኋላ የተቀበለውን ኃላፊነት በመዘንጋት፦
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተ ክርስቲያን ን ትምህርተ ሃይማኖት የሚያፋልስ፤ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የሚያስነቅፍ ተግባር ፈጽሞ ከተገኘ፣
በፍትህ መንፈሳዊ አንቀጽ አምስት ከቁጥር 172 እስከ 208 በተደነገገው መሰረት በደለኛ ሆኖ ከተገኘ፣
በኢ///ቤተ ክርስቲያን  ቅዱስ ሲኖዶስ 1991 በወጣው ሕገ ቤተክርቲያን አንቀጽ 13 ንዑስ አንቀጽ ሰባት መሰረት በተሾመበት ቀን የገባውን ቃለ መሐላ ያልጠበቀ እንደሆነ፣

በአጠቃላይ ታማኝነቱ፤ መንፈሳዊነቱና አባትነቱ በካህናትና በምእመናን ዘንድ ተቀባይነት ያጣ ሆኖ ቤተ ክርስቲያንን የሚያስነቅፍ መሆኑ በትክክል ከተረጋገጠ ከስልጣኑ ይወርዳል። በሱ ምትክም ሌላ ተመርጦ ይሾማል። ፓትርያርክ እስኪሾም ግን ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ይመረጣል። (የኢ///ቤተ ክርስቲያን  ቅዱስ ሲኖዶስ ያወጣው ሕገ ቤተ ክርስቲያን  1996 አንቀጽ 16)

ሕገ ቤተ ክርስቲያን ይህ ሆኖ ሳለ የአሁኑ ቅዱስ ፓትርያርክ ከላይ የተጠቀሱትን ሕጎች ሁሉ እያፈረሱ፤ እኛም እያየናቸው የቅዱስ ሲኖዶሱም አባላት እያዩዋቸው እስካሁን ድረስ በዝምታ ታልፈዋል። ከዚህ በኋላስ መፍትሔው ምንድር ነው? ተስፋ ቆርጦ መተው ወይስ ከጥቂቶቹ ለሕገ ቤተ ክርስቲያን  ተቆርቋሪ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋራ አይዞዋችሁ እኛም ከጎናችሁ ነን በማለት መስራት? መልሱን ለውድ ደጀ ሰላማውያን/ በመተው አንድ ነገር ግን ላሰምርበት እወዳለሁ የኢ///ቤተ ክርስቲያን  “በፓትርያርክ ላይ ፓትርያርክ” የሚል ሕግም ደንብም የላትም።
እግዚአብሔር ተዋሕዶ  ሃይማኖታችን ይጠብቅልን!!! አሜን

8 comments:

Anonymous said...

አዎን ተስፈቆርጦ መተው ይሻላል ፣እኔ በበኩሌ
ከማንም ምንም ስለማልጠብቅ አይናቸውን አያሳኘ
“ከደናዎቹ ጳጳሳት ጋር ሆነን ….”የደጀሰላም አዘጋጅ ሆይ!
ጥሩሰው አልነበርክም ወይ ?ወይስ በገነት ያሉትን ብፁ
አቡነ ጴጥሮስን ማለትህ ነው፤እኔ በበኩሌ በነዚህ ይሁዳዎች
የተነሳ ተዋህዶን አልተውም ጊዚው እስከሚአልፍ ብዩ እቤቴ
ውዳሲ ማርያሜን እየደገምኩኝ ቁጭ ብያለሁ፤
“ተፈጥሮን ተመክሮ አይለውጠውም”
ቸርወሬ ያሰማን “እነዚህ አይሁዶች እያሉ መቺም አንሰማም”

Desa said...

higawi behone melku mekawm!! abatoch wesanie endisetu miemenan gifet madreg.metsly.

Anonymous said...

really our patriaric becomes fade up. it is better for him to be the prsedant of ethiopia, because he cannot lead the EOC as the gosbel and qalawady saied. he is working for him and his families only not for the church of EOC, I donot know for the others????

Anonymous said...

yemtu mejemeria beretabn ...

Anonymous said...

Dear Dejeselam,

Can you please list us the name and the phone number of the Archbishops who are faithful to the Holy Synod.
Mimenan/Mimenat please at least, let us take our part by calling and encouraging our truly fathers to stand up and fight for our church.

Anonymous said...

Hi Everybody
It is a sad thing to know that our church had such a strict Cannon/Dogma but not being followed.
Deje Selam, I disagree with you about a couple of things.
1. We don't have a patriarch for the past 8 years. The "Patriarch" is no more a patriarch starting from Genbot 22, 1994 EC. But you already know that. So, stop talking as if we have a patriarch.

2. The real Synod, the ones loyal to the church, did something worth noting in 1994EC as I mentioned above. That is declare that Abune Paulos is no longer a patriarch.

That is something we all are wishing about right? I don't think you disagree with that cuz this would have taken the headache away.

A couple of Points for all of us out there

WE DON'T HAVE A PATRIARCH. !!! ::
WE DON'T HAVE A PATRIARCH. !!! ::
WE DON'T HAVE A PATRIARCH. !!! ::
WE DON'T HAVE A PATRIARCH. !!! ::

for the past 8 years since 1994 EC.

for those of you Interested to know why and have not seen the post about Synod Decision about Abune Paulos posted here on deje selam and also want a high resolution scan, download the following and compare it to what is written here

http://www.4shared.com/document/kaUl7O9j/EOTC_Synod_Decision_94.html

mester said...

smaet the enbeldem nwe ytbalut betkrstiyanen slgdlu

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)