July 11, 2010

የቦሌ ደ/ሳ/መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባዔ መልቀቂያ አቀረበ


(ደጀ ሰላም፣ ጁላይ 11፤ 2010)፦ “ሰማዕት ዘእንበለ ደም፤ ደም ያልፈሰሳቸው ሰማዕት” በሚል ርዕስ የቅዱስ ፓትርያርኩን 18ኛ ዓመት በዓለ ሲመት ምክንያት በማድረግ በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን” በተዘጋጀው እንዲሁም ለፓትርያርኩ በሚቆመው ሐውልት ምክንያት የደብሩ ሰበካ ጉባዔ አባላት በፈቃዳቸው ሥራቸውን መልቀቃቸውን የሚያሳይ ደብዳቤያቸው ደርሶን ተመልክተነዋል።
ከደብሩ አስተዳዳሪ ከመላከ ሳሌም ቆሞስ አባ ዘርዓ ዳዊት ኃ/ሥላሴ ቀጥሎ ምእመናኑን የሚወክሉት የደብሩ ም/ሰብሳቢ አቶ ትዕዛዙ ኩሪ እንዲሁም የሰበካ ጉባዔው አባላት የሆኑት ወ/ሮ ሙሉ እመቤት ጀምበሬ እና ወ/ሮ እታለም ናደው ሐምሌ 1/2002 ዓ.ም (ጁላይ 8/2010) በጻፉት በዚህ ደብዳቤ ሐውልቱ መሠራቱ፣ “ከሰበካ ጉባዔ አባላት ዕውቅና ውጭ የካቴድራሉ የሥራ ባልደረባ ባልሆኑ ግለሰቦች ትዕዛዝ የሚደረገውን እንቅስቃሴ በፅኑ” እንደሚቃወሙ ገልጸዋል። “ይህ ኃላፊነት ከሕዝብ ተሰጥቶን በሀገረ ስብከቱ ከፀደቀበት ጊዜ ጀምሮ በእግዚአብሔር ፈቃድ ከልብ በሆነ ቅንነት የተጣለብንን ኃላፊነት እየተወጣን ባለንበት ሁኔታ ያላሰብነው ክስተት በመፈጠሩ ከልብ አዝነናል” ሲሉም ድርጊቱ በድንገት የተከሰተ መሆኑን ገልጸዋል።
 
እነዚህ ሦስት ምዕመናን የወሰዱት እርምጃ ትክክል እና በሌሎችም ዘንድ ሊለመድ የሚገባው ነው። የሚሰራውን አስነዋሪ ተግባር ለማስቆም አቅም ባይኖራቸው በተንኮሉ ባለመተባበር ራሳቸውን ነጻ አውጥተዋል። ክፉ ሥራ መሥራት ብቻ ሳይሆን ሲሠራ አለመቃወምም በተዘዋዋሪ ደጋፊ መሆን መሆኑ በርግጥም ገብቷቸዋል። ስለዚህ ትክክለኛ ሃይማኖታዊ ተግባራቸው አንድ ቀን ቤተ ክርስቲያን ታመሰግናቸዋለች።
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

13 comments:

Eleni said...

"ሰማዕት ዘእንበለ ደም" maletis enezihin neber! lebona yisten!

Orthodoxawi said...

Ejig yemimesegenu, ewunetegna ye Betekrtiyan lijoch nachew. Neger gin, betekrstiyanun asalfo lekemagnoch kemestet kewust honewu hizbun astebabrewu bitagelu melkam neber. Ke ene Ejigayehu(Elzabel) gar metagel ejig kebad endehone, ersuam Papasatin enkuan kemasdebdeb endaltemelesech enawukalen.

Yebetekrsiyan Amlak be ewnet yifred.

Long live to Tewahedo.

"Ye Etisa anbesa Teklye tenesa
Mengahin tadegewu ke hatiyat abessa
Tekulawu lemd lebso mekdes gebtoalinaa
Petros hoy zim atibel ende tintu kina
Yohanes zim atibel ende tintu kina
Giorgis zim atibel ende tintu kina::"
...

Anonymous said...

betam yasazenal eytsera yalew neger betkersetyan yemafiya grupe msebesebya mehonwa. sebeka gubaye yseraw yjegenenat sera new.

ksise solomon azagaje new ytbalew ytal tadeya bgubayew laye. semun menegeja new yadrgut. lhulum leb yestew. hulachenenem kemfered yadenen.

amen.

ሲላስ said...

የቦሌ ደ/ሳ/መድኃኔ ኣለም የሰበካ ጉባኤ ኣባላት የወሰዳችሁት አርምጃ ትክክል ነው ።ግን ኣሁንም ከውጭ ሆናችሁ በፅናት መታገል ኣለባችሁ። ለጅቦች ኣስረክባችሁ መሄድ ኣይኖርባችሁም።
አግዚኣብሄር ፅናትን ጥንካሬን ያድላችሁ።

G/Silasie said...

አምልኮ ጣዖትን በጋራ እንከላከል!
የሮማ ካቶሊክ ችግር በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከቀናች የእነ እለ እስክንድሮስ ሐይማኖት ያስወጣቸው የድህነት መንገዳችን የሆነውን ምስጢረ ተዋህዶን እንዲክዱ ያደረጋቸው በቤተ መንግስት ቅርበት የነበራቸው የቤተ ክህነቱ ሰዎች እና የቤተ መንግስት ሰዎች በተለይ ንግስቲቱ ከፍ ከፍ ለማለት እና የመመለክ አባዜ ስላደረባቸው ቀጥተኛ ሐይማኖት የሚከተለውን ዲዮስቆሮስን ፅህሙ እስኪ ነጭ ፥ ጥርሱ እስኪረግፍ በወታደር አስደበደቡት! ዛሬም የመንፈስ ቅዱስ ማረፊያ የሆነች ቤተ ክርስቲያን የባዕድ ምስል አይቁምባት፥ ሕገ ቤተ ክርስቲያን ይከበር ያሉ ወገኖችና አባቶች ቤታቸው እየተደፈረ በሃይል ማንገራገር የተጀመረበት የሮማ ካቶሊክ ባህል በሐይማኖታችን ዘልቆ እንዲገባ ደባ የተሰራበት ጊዜ ነው!
በእውነቱ አባ ጳውሎስ የእነ በጋሻው ጉባኤ የለበጣ ጉባኤ፥ የማታለል ጉባኤ መሆኑን አጥተውት አይደለም! ይልቁንም የማይደፈረውን የቤተ ክርስቲያን ሕግ በ”ደፋሮች” እና በእግዚአብሔር ቸርነት እና በቤተ ክርስቲያን ላይ በሚዘባበቱት በእነ በጋሻው ተጠቅሞ የሮማ ካቶሊክ ባህል ወደ ቤተ ክርስቲያኗ ለማስገባት ነው እንጂ!
እኔ ግን ጥሪዬን ለሕዝቡ ማስተላለፍ እፈልጋለሁ! ማንም በእነዚህ ‘ደፋር” ጦጣዎች ተስፋ ቆርጦ ሐይማኖቱን እንዳይተው፦ በአርዮስ እና ግብራበሮቹ ጊዜ አትናትዮስ እውነትን የሙጥኝ ብሎ፥ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርጐ ስለ እውነት እንደታገለ እናስተውል። በተጨማሪም ጣዖት አምልኮ ወደ ሚከናወንበት ጉባኤ ባለ መሄድ እና ሌሎች እርምጃዎችን በመውሰድ ተቃውሟችንን እንግለፅ።
በማስተዋል እንራመድ! እንዲህ እንዲኩራሩ የሚያደርጉት የአድባራት አስተዳዳሪዎች የካህናቱን ደመወዝ እና የአምልኮ መባውን ለጣዖት ሐውልት ማሰሪያ ማዋላቸውን የየአድባራቱ ሰበካ ጉባኤ በጥብቅ መቆጣጠር እና ከፓትሪያረኩ ጋር ቅርብ ‘ወዳጂነት” ያላቸውን አስተዳዳሪወች የገንዘብ ምንጭ ማድረቅ ያስፈልጋል!

Dereje G. said...

They are right and thanks to them. What is happning is entirly out of our church's Doctrine, Canon and christian tradition.

we never seen a person encarnated as a "MARTYER" while he is alive! we never seen a person ordinated as a "SAINT" while in flesh!

Anonymous said...

ድንጋጤ በድንጋጤ ላይ ይመጣል፥ ወሬም ወሬውን ይከተላል፥ ከነቢዩም ዘንድ ራዕይን ይሻሉ፤ ከካህኑም ዘንድ ትምህርት፥ ከሽማግሌዎችም ዘንድ ምክር ይጠፋል። ንጉሡም ያለቅሳል፥ አለቃም ውርደትን ይለብሳል፥ የምድርም ሕዝብ እጅ ትንቀጠቀጣለች፤ እንደ መንገዳቸውም መጠን አደርግባቸዋለሁ፥ በፍርዳቸውም መጠን እፈርድባቸዋለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
ሕዝ.7:26

Anonymous said...

Abetu degimo min taseman yihon ? Sirachewun yelekekutin abalat bene amelekaket sira alilekekum techemari sira wesdewal yihewum lemiteyikachew hulu orthodoxawi timihirtun benegilets sew hulu endikawemew madreg. Do not forget those organizers will surely send some gangsters to frighten them and retreat from their committed acts. Balebetu yatsinachew

Anonymous said...

ahun qedusu gebremedihn honu. beqa abune ayidelum malet new. meknyatum sayimotu endemutan hawult yeqomelachew, sayitagelu semaet yehonu men ayinet leyu bihonu new. gobez enih sewuye egna alaweqenem enji kemotu koyitewal. leza new hawultum, yesemaetenet seyamewum zare yehonew. egna eko yalu meslon neber leka wodajochachew endemotu yawuku neber, lemutan yemihonewunem benesu gubaeie azegajulachew. yemigermew qedemen balamawoqachin leksoachewunem belten mekretachin new. nefes yimar balen teru neber neger gen edlun alagegnenem. zemedochachew gen hulgizem motachew hazen selehone yatsenachihu enlalen. man atebelugne. nefsachewun gen ene menem alelem.

Ze Dima giorgis said...

ende romaw Kesarina ende Gibtse feron Hawilt amarachew .Wey Kesaru "Abatachin".

selamawi said...

በስመ ስላሴ አሃዱ አምላክ አሜን

በአሁን ሰዓት ቤተክርስቲያን ሃዘን ላይ ነው ያለችው እየደረሰባት ያለው መከራ እና ግፍ k።ግራን መሃመድና ከዮዲት ጉዲት ጊዜ የከፋ ነው ምናልባት ትውልድ ወደፊት በታሪክ መዝገብ ይመዘግበው ይሆናል አይ ካህናት ምን ሆናችሁ? የትንቢት መፈጸሚያ ትሆኑ? ወንጌልን በአግባቡ እንኳን ያልሰበካችሁት ምዕመን ዛሬ ለሃይማኖቱ ሲቆም እናንተ ምን ነካችሁ ?

፤ እናንተ ስሜን የምታቃልሉ ካህናት ሆይ፥ ልጅ አባቱን፥ ባሪያም ጌታውን ያከብራል፤ እኔስ አባት ከሆንሁ ክብሬ ወዴት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ ወዴት አለ? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። ትን ሚል 1፥6

ትን ሚልክ 2፥1፤ አሁንም እናንተ ካህናት ሆይ፥ ይህ ትእዛዝ ለእናንተ ነው።

ለስሜ ክብር ትሰጡ ዘንድ ባትሰሙ፥ በልባችሁም ባታደርጉት፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እርግማን እሰድድባችኋለሁ፥ በረከታችሁንም እረግማታለሁ፤ አሁንም በልባችሁ አላደረጋችሁትምና እኔ ረግሜአታለሁ።

ይህን ስል ታዲያ እውነተኛ አገልጋይ ካህናት የሉም ማለት እንዳልሆn ይታወቅልኝ እኛ የማናውቃቸው እነርሱ በጸሎት የሚያውቁን ብዙ አባቶች አሉን ለማንኛውም በአሁን ሰዓት ቤተክርስቲያን ልጆቿ በተኩላ እየተነጠቁ እያለቀሰች ባለበት ወቅት ሌላ ኃዘን መጨመሩ በጣም ያሳዝናል ቸር ወሬ ያሰማን

መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል ወደ እሳትም ይጣላል። said...

ቤተክርስቲያናችን ከመንግስት ተጽዕኖ ነፃ ለማውጣት ከእግዚአብሄር ጋር እንታገል
ስንት ሰው እምነት አልባ እየሆነ ነው ምክንያቱም በቃ ቤተክርስቲያናችን ተልዕኮዋን መወጣት ባለመቻሏ ነው። ሊቀ ጳጳስ የተባሉት ሰው በእግር ብረት አስረዋታል።
ብዙዎች እሳቸውን የተቃወሙ እየመሰላቸው እምነታቸውን እየተዉ ነው።
እሳቸው አለም የሚወዳቸው አለማዊ ስለሆኑ ነው
ግሎባላይዜሽንን ፤ እምነት አልባነትን እያስፋፉ ነው።

እግዚአሔር በቃ እንዲላቸው እልጸልይ።
ወስብሃት ለእግዚአሔር ።

Anonymous said...

የሰበካ ጉባኤው አባላት ቁርጥ አቋም መውሰዳቸው ጥሩ ነው ነገር ግን ውሳኔውን እና ድርጊቱን መቃወም እና በተቻለ አቅም ተፈጻሚ እንዳይሆን መከላከል ቢቻል የበለጠ ይሆን ነበር እንጂ ለቆ መውጣት መፍትሔ አይመስለኝም፡፡ የመረጣቸው ህዝብ ነው እና ለቀው ከመውጣታቸው በፊት የመረጣቸውን ህዝብ ሰብስበው ሁኔታውን በማስረዳት እስከመጨረሻ መታገል የነበረባቸው ይመስለኛል፡፡ ምናልባት ብዙ ጥረት አድርገው ከአቅማቸው በላይ ሆኖ የለቀቁ ከሆነ ግን ውሳኔያቸው እና አላማቸው ያስቀናል፡፡

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)