July 3, 2010

“የብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ጅምር ሥራዎች ካልተቋረጡ ብፁዕነታቸው አይሞቱም”


  • የእርሳቸውን አርማ ተቀብሎ ይዞ የሚሄድ ሌላ “አቡነ መልከ ጼዴቅ” ቢሾም
(ደጀ ሰላም፣ ጁላይ 3/2010)፦ ያለፈው ሁለት ሳምንት የብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ዜና እረፍት ለሁላችን ታላቅ መርዶ ነበር። መርዶነቱ ለሥጋ ዘመዶቻቸው እና ለመንፈስ ልጆቻቸው ብቻ ሳይሆን በጠቅላላው ለቤተ ክርስቲያናችን ነበር። ሕልማቸውንና ርእያቸውን፣ ትጋታቸውንና ጥረታቸውን ለሚያውቅ ሰው በሙሉ የእርሳቸው ሞት ትልቅ ጉዳት እንደሆነ ይረዳል። እንደ መንፈስ አባታቸው እንደ አቡነ ጎርጎርዮስ ገና በ50 ዓመታቸው ቢያርፉም በአጭር ዘመናቸው የሠሩት ሥራ ታላቅነታቸውን አይቀንስባቸውም። በዚህ ወቅት ግን ልናነሣው የምንሻው ቁም ነገር የእርሳቸውን እረፍት እያሰብን ለማዘን ሳይሆን ጅምር ተግባራቸው እንዴት ይቀጥል የሚለው ጉዳይ ነው። “የጉራጌ፤ ሐዲያ እና ስልጤ አህጉረ ስብከት” የወደፊት ዕጣ ፈንታ ጉዳይ ሊያሳስበን ይገባል።
ብፁዕነታቸው ባላቸው ትጋት እነዚህን አህጉረ ስብከት አደራጅተዋቸው አልፈዋል። እርሳቸው ያደራጁት እንዳይፈርስ፣ የጀመሩት እንዳይቋረጥ፣ የሰበሰቡት እንዳይበተን ቅዱስ ሲኖዶስ እንደሚጨነቅበትና እንደሚነጋገርበት ብናውቅም ዞሮ ዞሮ ለዚህ ማሰሪያ የሚሆነው ይህንን ተግባር የሚያቀናጅ እና የሚመራ አባት ነውና እንደ ብፁዕነታቸው ያለ አባት በምትካቸው ይተካል ብለን እንጠብቃለን። ወይም ደግሞ በሌሎቹ አሐት አብያተ ክርስቲያናት እንደሚደረገው በብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ምትክ የእርሳቸውን አርማ ተቀብሎ ይዞ የሚሄድ ሌላ “አቡነ መልከ ጼዴቅ” ቢሾም ደግሞ በርግጥም ቅዱስ ሲኖዶስን ያስመሰግነዋል። የብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ጅምር ሥራዎች ካልተቋረጡ ብፁዕነታቸው አይሞቱም፤ ጅምሮቻቸው ከተቋረጡ በርግጥም እርሳቸው ሞተዋል ብለን እናዝናለን።

ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)