July 1, 2010

ኤልዛቤል ከታሪክ አንድ ገጽ

(ደጀ ሰላም፤ ጁን 30/2010)፦ የሚከተለውን አጭር መጣጣፍ ያገኘነው ከዲ/ን ዳንኤል ክብረት መጦመሪያ መድረክ ላይ ነው። ደጀ ሰላማውያን ብትመለከቱት መልካም ነው ብለን አሰብን። እንዲህ ይነበባል።
+++
ታሪክ ራሱን ይደግማል ይባላል፡፡ በቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፉ ምሳሌዎች በአንድ ወቅት ብቻ ተፈጽመው የቀሩ ታሪኮች አይደሉም፡፡ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ በየዘመናቱ የሚከሰቱ የቤተ ክርስቲያን ጉዞ አካላት ናቸው፡፡ እነዚህ ለክፉም ሆነ ለበጎ ምሳሌ ሆነው የተጻፉ ታሪኮች፣ ቤተ ክርስቲያንን የመከራ እና የደስታ ዘመናት ተከትለው ይፈጸማሉ፡፡ የዮሐንስ ራእይን ለመተርጎም ከተጻፉ ከግሪክ እና ሶርያ የጥንታውያን መዛግብት ያገኘሁትን ይህንን ትርጓሜ እስኪ ተመልከቱት፡፡


ነገር ግን አንተን የምነቅፍበት ነገር አለኝ፡፡ ሳትሆን ራስዋን ነቢይት ነኝ የምትለውን አገልጋዮቼንም ለጣዖት የተሠዋውን እንዲበሉ እና እንዲሴስኑ የምታስተምረውንና የምታስተውን ያችን ሴት ኤልዛቤልን ዝም ብለሃታልና (ራእይ 2÷20)

ኤልዛቤል ማናት?

1. በብሉይ ኪዳን

በብሉይ ኪዳን የአክአብ ሚስት፣ የሲዶናዊው የኤትበኣል ልጅ ናት (1ኛነገሥ.16-31)፡፡ ባልዋን አክአብን የበኣልን ጣዖት እንዲያመልክና ክፉ ሥራ እነዲሠራ ትገፋፋው የነበረች እርሷ ነች፡፡ በእሥራኤል አምልኮ ባዕድ እንዲስፋፋ ያደረግችና ኤልያስን ያሳደደችው ኤልዛቤል ነበረች፡፡ በቤተ መንግሥቷ አራት መቶ የበኣል፣ አራት መቶ ሃምሳ የአሸራህ ነቢያትን ትመግባቸው ነበር (1ኛ ነገሥ.18-19)፡፡

ባልዋ አክአብ የየዋሑን ሰው የናቡቴን የወይን እርሻ ለመውሰድ አስቦ ናቡቴ ርስቴን አልሸጥም ባለው ጊዜ ተናደደ፡፡ አልዛቤልም ይህንን አይታ ናቡቴን በግፍ አስገደለችው፡፡ እርሻውንም ቀማችው (1ኛ ነገሥ.21÷1-19)፡፡

2. በሐዲስ ኪዳን
በዮሐንስ ራእይ አልዛቤልን የተጠቀሰችውን የትያጥሮኗን ኤልዛቤል በተመለከተ ለቃውንት ልዩ ልዩ ሐተታ አቅርበዋል፡፡
የመጀመርያው ሐተታ ኤልዛቤል የተባለችው የጳጳሱ ሚስት ናት የሚለው የሶርያን እና የግሪክ ጥንታዊ መዛግብት መሠረት ያደረገው ትርጉም ነው፡፡ በእነዚህ መዛግበት «ሚስትህን ኤልዛቤልን» ይላል፡፡ ይህች የጳጳሱ ሚስት የጥንቷን ኤልዛቤል መንገድ ተከትላ አምልኮ ጣዖትን እና ዝሙትን እያስፋፋች ነገር ግን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነግሣ ትኖር ነበር፡፡ በነገራችን ላይ እስከ ሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጨረሻ ድረስ ጳጳሳት ሚስት ያገቡ ነበር፡፡

ይህች የጳጳሱ ሚስት ቤተ ክርስቲያኒቱን ተረከበቻት፡፡ ማንኛውም የቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳይ በእርሷ በኩል ብቻ ነበር የሚያልፈው፡፡ ደግሞም ምግባረ ብልሹ እና ሕይወቷ በዝሙት የተነከረ በመሆኑ ምእመናኑን ለሥነ ምግባር ብልሹነት አጋለጠቻቸው፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያኒቱ የሚመጡ አሕዛብም የርሷን ምግባር በማየት «ክርስትናማ እንዲህ ከሆነ» ማለት ጀመሩ፡፡

ሊቀ ጳጳሱ ይህንን ሁሉ ክፉ ሥራ እያዩ በቸልታ ያልፏት ነበር፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱ መደፈር እና የምእመናኑ ሕይወት አላሳሰባቸውም፡፡ በዚህም ምክንያት «ዝም ብለሃታልና» ተብለው ተገሠጹ፡፡

ቅዱስ ኤጲፋንዮስን የመሳሰሉ ሌሎች መተርጉማን ደግሞ በትያጥሮን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ትኖር የነበረች፣ ክርስቲያን መስላ ጳጳሱን ያታለለችና ብዙ ክርስቲያኖች ከዝሙት ጋር የተቀላቀለውን አምልኮ ባዕድ ችግር የለውም ብለው እንዲቀበሉት ያደረገች ኃይለኛ ሴት ናት ይላሉ፡፡

እንደ ኤጲፋንዮስ ሐተታ ይህች ሴት ሀብታም እና ኃይለኛ፣ በዘመኗም በዘርዋ የምትመካ የልዑላን ቤተሰብ ነበረች፡፡ ክርስቲያን ነኝ ብላ ወደ ቤተ ክርስቲያን ብትጠጋም አምልኮ ባዕዷን እና ዝሙቷን አላቆመችም ነበር፡፡ በዚህ ጠባይዋም ለጳጳሱም ሆነ ለብዙ ምእመናን መሰናከያ ሆነች፡፡

የኤልዛቤል ፍጻሜ

እግዚአብሔር ታጋሽ ነው፡፡ ለሰው የንስሐ ዕድል ሳይሰጥ አይቀጣም፡፡ አሁንም ለዚያች ክፉ ለኤልዛቤል የንስሐ ዕድል ሰጥቷት ነበር፡፡ ነገር ግን አልተጠቀመችበትም፡፡ በመሆኑም የሚመጣባቸውን ቁጣ ነገራቸው፡፡ አስቀድሞ ቅዱስ ጳውሎስ «የእግዚአብሔር ቸርነት ወደ ንስሐ እንዲመራህ ሳታውቅ የቸርነቱንና የመቻሉን፣ የትዕግሥቱንም ባለጠግነት ትንቃለህን? ነገር ግን እንደ ጥንካሬህና ንስሐ እንደማይገባ ልብህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ በሚገለጥበት በቁጣ ቀን ቁጣን በራስህ ላይ ታከማቻለህ፡፡ እርሱ ለእያንዳንዱ እንደ የሥራው ያስረክበዋል፤ በበጎ ሥራ በመጽናት ምስጋናንና ክብርን፣ የማይጠፋንም ሕይወት ለሚፈልጉ የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸዋል፤ ለዐመፃ በሚታዘዙ እንጂ ለእውነት በማይታዘዙትና በአድመኞች ላይ ግን ቁጣና መቅሰፍት ይሆንባቸዋል» በማለት እንዳስተማረ (ሮሜ 2÷4‒8)፡፡

የብሉይ ኪዳኗ ኤልዛቤል ከስሕተቷ ልትመለስ ባለመቻሏ የኢዩ ሠራዊት በክፉ ሞት እንድትሞት፣ ለቀብርም ሬሳዋ እንዳይገኝ አድርጓታል (2ኛ ነገሥ.9÷30‒37)፡፡ ሰባዎቹ የእርሷ እና የአክዓብ ልጆችም በሰይፍ ተገድለዋል (2ኛ ነገሥ.10÷1‒11)፡፡ በዚሁ አንፃርም የሐዲሷ ኤልዛቤልም «እርሷም ትቀጣለች ልጆቿም ይቀጣሉ» ተብሏል፡፡

እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን ከኤልዛቤል ያድናት!!!!
++++

(ደጀ ሰላም፤ ጁን 30/2010)፦ ዛሬስ ቤተ ክርስቲያንን እንዲህ ያስቸገሩ፣ በቤተ ክርስቲያን ሕግ የሚመሩ ሳይሆን በፈቃዳቸው የሚመሩ ብዙዎች  አይደሉምን? አቤት ኤልዛቤሎች ....

13 comments:

Zekios said...

oh Dn Daniel,kale hiwot Yasemalin.Awo lasitewalew bizu Elzabeloch tenestewubatalina enberta.

Anonymous said...

timihirtu tiru new neger gen deacon daniel yemibalew ato daniel bemilew yetekalegn, enena daniel betam keblate maseltegna jemro selementewawek? yared nege

Anonymous said...

Ena mene yetebese anete awekewena

Anonymous said...

what does it mean? that has no meaning and big deal if you know him starting from his childhood instead BELATE

Anonymous said...

To the first Anonymous:

So what? What is the big deal here that u know him since Blatte?
Are you one of the Elzabels?
You know that false accusation is on of the sin of Elzabel.

ewunetu said...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

ዳኒ ስለ አንተ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ ጥሩ አእምሮ ነው የሰጠህ በተለይ በአሁኑ ሰዓት የምታስተላልፋቸው መልእክቶች በአይናችን የምናያቸው በጆሯችን የምንሰማቸው በመሆናቸው ለማመን አንቸገርም

እግዚአብሔርን የማያውቁ የእግዚአብሔር ሰዎች

የሚለውን ስብከትህን ሰምቼ ባንተ ላይ አድሮ እግዚአብሔር የተናገረውን እዉነት በውስጤ አሳደርኩት አምላክ ሆይ ልብ ስጠን ነው እሚባለው? ለአገልግሎት የተጠሩ ሁሉ ይህንን ስብከት እንዲሰሙ እጋብዛቸዋለሁ ከላይ እስከታች ላለነው ማስተዋል ከሰጠን እውነተኛ መልእክት ነው እላለሁ

ዛሬ በቤተክርስቲያናችን ለተንሰራፋው ስርዓተ አልበኝነት ተጠያቂዎቹ አገልጋዮች ካህናት ተብየዎች ነን ምክንያቱም በዘር በጎሳ በዝምድና ምክንያት እግዚአብሔርን ወደ ኋላ ትተን ለስርዓቱ ሳንጨነቅ ስለሆነ የምንጓዘው ይህ ሁሉ መጣብን ቤተክርስቲያናችን ለሁሉም ነገር ስርዓት አላት ዛሬ ልጆቿ በስርዓት መጓዝ ሲያቅታቸው ለቤተክርስቲያን ችግር ሆኑ እስቲ ይብቃንና እንደ ጥንቱ እንደ አባቶቻችን ክህነቱም አገልግሎቱም መስፈርቱ ተጠብቆ እንዲሰጥ ይደረግ ? ወደ ጥንቱ ስርዓታችን ብንመለስ እግዚአብሔርም ወደኛ ይመለሳል እኛ በምናበላሸው ነገር የኛ ህይዎት ይበላሻል እንጅ ቤተክርስቲያኒቱ እንደሆነ አንድ ጊዜ በክርስቶስ ደም የተዋጀች ስለሆነች ቅድስናዋን አንቀንሰውም አምላካችን በቸርነት አይለየን አሜን

Anonymous said...

To first anonynous

Timirtu tiru kehone Why you need to talk about his personal life? No one need to hear his or other personal lives.You should worry about your life.You dont point your finger to others. Use God's words to change your life.Dont complain others.

Anonymous said...

To first anonynous

Timirtu tiru kehone Why you need to talk about his personal life? No one need to hear his or other personal lives.You should worry about your life.You dont point your finger to others. Use God's words to change your life.Dont complain others.

Anonymous said...

May be there are Elzebels being unknowingly; and also there is a difference b/n Elzabel of the old Testament & of the new Testament. The two have the difference in mission & belief; So same is now by more than one Elzabel.

Anonymous said...

ኤልዛቤሎች ሁለት ዓይነት ናቸው፡፡
ከሊቃውንቱ ግልጽ የሃይማኖት ልዩነት ያላትና /የብሉዩዋ/
ከሊቃውንቱ የፍላጎት እንጂ የሃይማኖት ልዩነት የሌላት /የሀዲሱዋ ትመስለኛለች/
አሁንም ቢያንስ ሁለት ኤልዛቤሎች አሉ፡፡ ለዘውገ ሀዲሱዋ ልብ ይስጥልን፡፡

Anonymous said...

ቃለ ህይወት ያሰማልን

Unknown said...

ቃለ ህይወት ያሰማልን

Anonymous said...

dani I greatly appreciate your fearless comments on our life and our church problems.God bless you

Geta yitebikih kene Elzabel

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)