July 12, 2010

ቅ/ፓትርያርኩ ለ18ኛ በዓለ ሲመታቸው የ3.4 ሚሊዮን ብር መኪና ተሸለሙ


(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 12/2010)፦ የቅዱስ ፓትርያርኩ 18ኛ ዓመት በዓለ ሲመት ሲከበር ትናንት በቦሌ በተደረገው የሐውልት ምረቃ ዝግጅት ላይ የአዲስ አበባ አድባራት የገዙላቸው ነው የተባለ የ3 ሚሊዮን 332 ሺህ ብር የ2010 አዲስ ቶዮታ መኪና ተሸልመዋል።  የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማዕምራን ፋንታሁን ሙጬ የሀውልቱ ምረቃ በዓል ላይ እንደገለፁት ከሆነ መኪናውን 3.4 ሚሊዮን ብር የገዙት የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት ናቸው። በትክክሉም ብሩ የወጣውን ከነዚህ ገዳማትና አድባራት ነው። ግን እንት ሊያወጡት እንደቻሉ ሊቀ ማዕምራን ፋንታሁን አልነገሩንም። እያንዳንዱ የአዲስ አበባ ቤተ ክርስቲያን እንዳቅሙ ከ45 ሺህ እስከ 65 ሺህ ብር በግድ እንዲያዋጡ መገደዳቸውን አልተናገሩም።
ስለዚሁ ጉዳይ ሊቀ ማዕምራን ፋንታሁን ባለፈው ሳምንት በጠሩት ስብሰባ ላይ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች እና ፀሐፊዎች ተገኝተው ነበር። በወቅቱ እያንዳንዱ ቤተ ክርስቲያን በነፍስ ወከፍ 85 ሺ ብር እንዲያዋጣ የታሰበ ቢሆንም አስተዳዳሪዎቹ እና ፀሐፊዎቹ “ኧረ ሕዝቡ ምን ይለናል? አይቀበለንም” ባሉት የተቃውሞ ሐሳብ መጠኑ ተቀንሶ የሚችሉ 65 ሺህ ብር፣ ገቢያቸው ትንሽ የሆነ ደግሞ 45 ሺህ ብር እንዲያዋጡ ተወስኖባቸዋል። ይህ ሁሉ ብር የቤተ ክርስቲያን ብር እንጂ የአቡነ ጳውሎስም፣ የፋንታሁን ሙጬም አልነበረም።፡ታዲያ እንዲህ እንዲጫወቱበት መብት የሰጣቸው ማነው? ቅ/ሲኖዶሱስ ይህንን እያየ ዝም የሚለው እስከ መቼ ነው? ይህ ወንጀል አይደለምን?

 የነገሮችን አካሄድ ለመመልከት እንደሞከርነው በመኪና ግዢ፣ በጉባዔ እና በሐውልት ምረቃ ስም በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ሰፊ የገንዘብ ምዝበራና የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ጥሰት እየተካሄደ መሆኑን የሚያሳዩ አንዳንድ ፍንጮች አሉ። በዚህ ወንጀል የተባበሩና እየተባበሩ ያሉ ሰዎች አንድ ቀን በሕግ (በፍትሐ ብሔርም ሆነ በወንጀል) ሊጠየቁ ይችላሉ። አሁን ባለው ሁኔታ ግን ሰዎቹ ለመንፈሳዊውም ሕግ፣ ለዓለማዊውም ሕግ የሚገዙ አይደሉም። መንፈሳዊውን ሕግ የያዘው ክፍል ዝም ብሏል፣ የፍትሐ ብሔሩንም የያዘው ዝም ብሏል።  መንፈሳዊው ሕግ አለመፈፀሙ የሚያስጠይቀው ቅዱስ ፓትርያርኩን እና ቅዱስ ሲኖዶሱን ሲሆን ዓለማዊው ሕግ አለመፈፀሙ ደግሞ መንግሥትን ያስጠይቀዋል። ቅዱስነታቸው አሁን እየፈፀሙት ባሉት ድርጊት ቤተ ክርስቲያኒቱን በማዋረዳቸውና ንብረቷን በማስዘረፋቸው (ዘርፈው ለዘራፊ በመክፈታቸው) ራሳቸውም በሕግ ከመጠየቅ ማምለጥ የሚችሉ አይመስሉም። ማምለጥም የለባቸውም። ይህ ድርጊታቸው ከፕትርክናቸውም ሊያስሽራቸው አይገባም? መንግሥት በበኩሉ እነዚህ ወንጀለኞች እንደፈለገ እንዲፈነጩ ዝም በማለቱና ሕግን ባለማስከበሩ፣ የሕዝብን መብት በማስደፈሩ ሊጠየቅ ይገባዋል። መንግሥት የነዚህ ወንጀለኞች ተባባሪ መሆኑን ከቀጠለ መንግሥትን መቃወም ኢትዮጵያዊ ግዴታችን ብቻ ሳይሆን ሃይማኖታዊ ግዴታችንም ይሆናል ማለት ነው።

ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

12 comments:

selamawi said...

በስመ ስላሴ አሃዱ አምላክ አሜን

ያልገባኝ ነገር ለመሆኑ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሃብትና ንብረት መቼ ነው በካህናቱና በምዕመናኑ አዛዥነት የሚተዳደረው ለምን ይቀልዳሉ ፋንታሁን ሙጨ ለምን ትቀልዳለህ የአቡነ ጳውሎስ ጉዳይ አስፈጻሚ እንጅ የቤተክርስቲያናችን አይደለህም ስትሾምም በእሳቸው ፈቃድ እንጅ ካህናቱም ሆነ ምእመናኑ አያውቁህም ከአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ተሸለሙ ብለህ ከምትዋሽ በቁጥጥራቸው ስር ካሉት ቤተክርስቲያናት ብለህ ብታሻሽለው ምን ይመስልሃል? በጋሻው ? ፋንታሁን ? ምናምን የምትባሉ የቤተክርስቲያን ጠላቶች ናችሁ ታሪክ ይፈርድባችኋል የቤተክርስቲያኒቱንም መሪ የማይገባቸውን ክብር ይገባዎታል እያላችሁ ኢንደ ሳጥናኤል ውድቀታቸውን የምታፋጥኑ ሁላችሁም የቤተክርስቲያን አምላክ ጽዋው የሞላ ጊዜ አብራችሁ ትጠፋላችሁ በመጨረሻም በምንኖርባት አሜሪካ ለምትገኙ ጳጳሳት የምለው አለኝ ባለፈው የአቡነ ጳውሎስን ስም የማይጠራ ቤተክርስቲያን ምእመናን እና ካህናት እንዳትገኙ እያላችሁ ስትሰብኩ ሰምቻለሁ አባ ጳውሎስን ትታችሁ ክርስቶስን ስበኩ እሳቸው በኛ ኃጢአትና በደል ምክንያት የበቀሉ እንክርዳድ ናቸው
ይህንን ቃል አስቡ
የሐዋ,ሥ 20፥28 በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።

ምዕመናን ሆይ አትሸበሩ ይህ ይሆን ዘንድ ግድ ስለሆነ ነው በእምነታችሁ ጸንታችሁ ኑሩ ,, ንቁም በበ ህላዌነ እስከ ንረክቦ ለአምላክነ ,, የአምላካችንን ፍርድ እስክናገን በያለንበት እንቁም

ቸር ይግጠመን

kale said...

Is this really important for the church leader.
Do u know how many church are closed due to shortage of money and poor administration.

is aba pawoles deserve this ?

It is really funny and shame what is going on in Ethiopian Orthodox church administration and assigned leader all over the world.

Anonymous said...

ኧረ ተቃጠልን!! በጣም የሚገርመው እስከዛሬ ምንም ተናግሬም ጽፌም አላውቅም ነበር:: "ምን አገባኝ ባይ" ነበርኩኝ ማለት ነው!! .... ኧረ አሁን ግን በቃ ውስጤ ተቃጠለ: ባልናገር ሃሳቤን ባልሰጥ ትዝብት ላይ እወድቃለሁ..ለሕሊናዬ!

እኔ የምለው: በቃ እንዲህ መቀለጃ እንሁን? ሃይ የሚል ይጥፋ? በደላችን እንዲህ የሰማይ የምድር ጉድ "አባ ጳውሎስ እና አጋሮቻቸው"ን አውርዶብን ...ወይ እዳችን!! እኔ ግን በጣም ተናድጃለሁ በጣም:: በቃ መሳለቂያ ሆንን እኮ: አሁንማ ጭራሽ በአደባባይ ብሩን ዘረፉት... እንደው የአባቶቻችን አምላክ እኛ እንደ ፈቃዱ ባንሆንለት: ስሙን አስከብረው ስለሞቱት ብሎ ይታደገን ይሆን? ..እሺ እኛስ ይቅርብን: እውነት በኛ በደል ይህ ሁሉ ከመጣ: ስለቤተክርስቲያን ብሎ ምኅረቱን ያወርድ ይሆን? ኧረ ምን ይውጠን ይሆን? ምን ይበጀናል?.... ኧረ ወላዲተ አምላክ ድረሺልን?!! ልባችን ተሸበረ: ይህ ሁሉ ይሆን ዘንድ እርግጥ ቢሆንም: እኛ ግን አልቻልንም! አምላካችን ሆይ በቃችሁ በለን: ቀኝ እጅህን ስደድልን:: ስለ ቸርነትህ ስለማያልቀው ፍቅርህ ብለህ!! ....አሜን!

Anonymous said...

እኔን የሠሪዎቹም ሆነ ያሰሪዎቹ ነገር አይገርመኝም ምክንያቱን ልቦናቸው በጥቅም ታውሯል፤ በጣም የገረመኝ ግን የቅዱስ ፓትርያርኩ እሺ ብሎ መቀበል!? በጣም የሚያሳዝነኝ ነገር በእውነት ስለ ቤተ ክርስቲያኗ እድገት፤ መስፋፋትና አንድነት የሚደክሙ ከሊቃነ ጳጳሳት እስከ ምህመን ያሉ የተዋህዶ ልጆች ናቸው። እውነተኞቹ ሲደክሙ ሲለፉ ጥቅመኞቹ መሃል ቁጭ ብለው ይንዳሉ። የእግዚአንሔር ቁጣ ሳይገለጽብን ካሁኑ እንመለስ! እግዚአብሔር ሀገራችንንና ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅ። አሜን።

hiwot said...

Aye Fentahun Much Agere asedabe minew balwekih tiru neber.
Those people they do not have any spritual life.He is not even menfesi(asmesai) leave alone to be menfesawi. This is the beginnig so just pray before they have Tsilat in aba paulose name.

Anonymous said...

ye egeziabher fikad yehun belen zem alen !!

Addisu Tesfaye said...

A year before, Archbishop Samuel and other archbishops were in a serious battle with this patriarch. I think the reason is now very clear for everybody.
Was this the reason why he needs to avoid Abuna Samuel from Addis Ababa diocese.

Mesfin said...

By the way he ( Paulos ) ever has preached the word of God or ever has shared any God's word ...... he doesn't deserve it . I think this is the end of his sin before God .God will punish him and his vassals for their shameful violent . God will save our country . Hatiyategnochu bemasut gudguad erasachew yigebalu . here Gud Gud Gud Gud Gud Gud hu hu hu hu hu hu hu hu . Geta hoi bedelachinin yikir bel .

Antehun said...

እኔ የምለው ይህ ሁሉ ነገር ሲፈጠር ብዙ ጊዜ የማነበው ትችትን ነው ነገር ግን ወደ መፍትዬውን ብናስብና ነገሮች ቢስተካከሉ እላለሁ፡፡ እኔ አንድ ሀሳብ አለኝ ከአባቶች፣ ከምእመኑም፣ ከማበረቅዱሳንም፤ ከደጀ ሰላምም፣ እና ከሌሎችም ይህ ነገር ይመለከተኛል ከሚሉ አካላት አንድ ኮሚቴ አቆቁሞ ያለውን ችግር እና ሁኔታ በጥልቀት አጥንቶ፣ ይህንንም ስህተት ከታችት ጀምሮ የሚሰሩትን አካላትና ግለሰቦች ለማነጋገር ጥሮ፣ ከዛ ያገኝውን ችግርና መፍትዬ ይዞ የሚመለከተውን አካል ቢያነጋግር እና ወደ መፍትዬው ቢኬድ እላለሁ፡፡ ይህ የኔ ሀሳብ ነው እናንተ ደግሞ ጨምሩበት መስተካከል ያለበትም አስተካክላቹሁ ወደ መፍትዬው ብንሄድ እላለሁ፡፡

እግዚአብሄር ሀገራችንን ይባርክ!

Anonymous said...

Dear Bros and Sisters, We all Eth Orthdox belivers were, are and will be feel on Abune Paulose and His followers action. A lot of things are hidden, this is the simplest thing that we know....."HODI YIFIJEWE"

Donot warry Alimighty God will pay them one day...

It isnot unique to us....Just let us prey and our God will save our anchiet church

Begashaw, Fentahu....a lot of people are behaind them, they will get the return soon

Anonymous said...

Government recently has asked emergency food aid for more than 5.2 million people. But our patriarch is building monument and buying car which worth more than 3 million.
Hahaha it is so funny in the history of Ethiopia.This money is collected from the contribution of these poor people who beg food assistance .

Unknown said...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን
አረ ሰዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ጧፍ ሻማ እጣን አተው መቀደስ ያልቻሉ ቤተክርስቲያኖች እያሉ እንዲሁም የቤተክርስቲያን ልጅ ሆነው የሚበሉት የሚጠጡት ያጡ እያሉ ምነው ለፓትሪያርኩ አቡነ ጳውሎስ 3.4 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ መኪናመገዛት ለምን መግዛት አስፈለገ አሁን ይሄ የቤተክርስቲያን ስርአት ነው አምባገነንቱ ቢበቃ አይሻልም ስለዚህ መላው የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች በአንድነት ልንታገላቸው ይገባል

ወስበሃት ለእግዚአብሔር
ኤልያስ ቦጋለ ከስዊትዘርላንድ

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)