June 29, 2010

ማስታወቂያ፦በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ዙሪያ የሚያጠነጥን አዲስ ብሎግ እና የጡመራ መድረክ

 http://www.onetewahedo.blogspot.com፦ "በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ስላለችው ቤተ ክርስቲያን አንድነት የምንወያይበት የጡመራ መድርክ።" ውድ የደጀ ሰላም አዘጋጆች እንደምን ከረማችሁ? በደጀ ሰላም በተለያዩ የመወያያ ርዕሰ ሀሳቦች ላይ “አቤል ቀዳማዊ ወይም አቤል ወለቴ” በሚለው ስም የራሴን ሀሳብ ስገልጽ ቆይቻለሁ። ዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው  ውስጥ እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያን እንደሚኖሩ የተለያዩ የሕዝብ መገኛኛ ብዙሃን ይናገራሉ። በዚሁ አካባቢ የተዋሕዶ እምነት ተከታዮች  ምንም እንኳ ትክክለኛ ቁጥር መናገር ቢያዳግትም በርካታ ናቸው። በአካባቢያችን ቤተ ክርስቲያናችንም በተለያየ መልኩ ተከፋፍላ ትርምስ ውስጥ ትገኛለች። ስለዚህ በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው  ያሉት አጥቢያ አቢያተ ክርስቲያናት ልዩነቶቻቸውን አጥብበው እንዴት ወደ አንድነት ሊመጡ ይችላሉ? በሚሉትና በሌሎችም ርዕሰ ሀሳቦች ላይ የምንወያይበት የጡመራ መድረክ ጀምሬያለሁ። ዋሽንግተን ዲሲ በችግሩም ሆነ በመትሄው ለሌሎች አካባቢዎች ተምሳሌት መሆኗ የአደባባይ ምስጥር ነው ። ስለዚህ ውድ የደጀ ሰላም አዘጋጆች እንዲሁም ደጀ ሰላማያን የአካሄድ አስተያየቶች እንድትለግሱኝ አደራ እላለሁ። ይህንንም የመወያያ መድረክ እንድታስተዋውቁልኝ በእግዚአብሔር ስም እጠይቃለሁ። 
ቀዳማዊ አቤል
ጦማሪ

8 comments:

Wongelawi Birhanu said...

Bravo Abel Kedamawi! This is a great start. we all are besides you and insist you use this blog only and only for the benefit of our mother church Hawaryawit, Alemakefawit, One(ahati) and Kidist Orthodox tewahedo church

Abaginbar said...

Fitsamehin Yasamirewu Amen!

Abaginbar negn KeRoma(Italian)

Anonymous said...

abel melkam hasab new egziabher yirdah gin letifat yetazezeche ketema negarit begesem atsema endihon esegalehu dingle maryam kene lijua tirdane amen

desa said...

itis good! go head!

Anonymous said...

ወንድም አቤል፣ ሀሳብ ደስ የሚልና የሚደገፍ ነው። ስለ ቤ/ን ሰላም፤ ስለ ወንጌል አገልግሎት መቅናት፤ መጣር ተገቢ ነው፤ ነገር ግን ሁሉን በማስተዋልና በፀሎት ሲያደርጉት ደግሞ ውጤቱ እጅግ ያማረ ይሆናል። ሰዎችን በመንቀፍ ያይደለ በማክበር፤ አንዱን ደግፎ ሌላውን በማጥላላትም ሳይሆን ሁሉን እንደራስ በማየት መንፈስ፤ አዎ የተሳሳተም ቢኖር ስህተቱን በአደባባይ አውጥቶ በሌላው ማስነቀፍ ባልሆነ መንፈስ ካደረከው፤ ከዚህም ሁሉ ጋር የአባቶቻችን አምላክ ይህ ስራህን የተራርቅን የምንቀራረብበት፤ ሥራዓተ ቤ/ንን መጠበቅም ሆነ ስለ እርሱ መቆርቆር ያቃተን ሰዎች እንድንጠብቅም እንድንቆረቆርም ከፀለይክ እግዚአብሔር ስራህን ይባርክልሃለው እላለው። ይባርክልህም።

ትዝብት said...

በእውነቱ ከሆነ ከላይ ጸሀፊው በጠቆሙወት መንፈስ ውስጥ ሆነው ከሆነ ይሄንን ስራ ለመስራት የተነሱት ይበል የሚያሰኝ መልካም ጅምር ነው። አንድ ነገር ግን ያሰጋኛል እንደተረዳሁዎት ከሆነ ግን እርስዎ የሚሉትንና ከላይ ጸሀፊው የተመኙልወትን ቀና መንፈስ ይዘው የተነሱ አይመስለኝም። ይሄንን እንድል ያደረገኝን ነገር መቸም የሚያጡት አይመስልኝም፤ በእውነቱ ልዩነት ጠቦ አንድነት ሊመጣ የሚችለው እርስዎ በቅርቡ እንዳደረጉት የሰንበት ተማሪዎችን ኢሜል በመስረቅ ወይም በማሰረቅ የቤ/ክ አገልጋዬችን ከመሰሎችወት ጋር በመሆን የኰነኑበትን የተንኰልና የማደናገረያ ብሎም ልዩነትን የሚሰብክ ጽሁፍ መበተን ነው????ችግሩ እኲ ማንኛችሁም ብትሆኑ ራሳችሁን በትክክል አለማወቃችሁ ነው፤ እርስ በእርሳችሁ ስለ አንድነት ባወራችሁ ቁጥር ፍጹም የሰላም ስዎች የሆናችሁ ለዚህም የተጨነቃችሁ መስላችሁ ለእኛ ደግሞ ልዩነትን ትሰብኩልናላችሁ፤ የራሳችሁ ክፉ ጥላቻና አድመኛነታችሁ ላይበቃ የሰ/ተ እህትና ወንድሞቻችን እምነተ ቢስና የተንኰላችሁ ተባባሪ እንዲሆኑ አደረጋችኈቸው ታዲያ እንዲህ አይነት መሰሪ መሆንወትን እያወቅን እንዴት ነው ይሄንን የማስመሰያና የማደናገሪያ ላዪ ማር የተቀባውን ውስጡን ግን;;; የሚባለውን አይነት ሀሳብወትን ልንቀበልወት የምንችለው??? እውነት የሀሳብወትን አይነት ሰው ከሆኑ ሚዛናዊነቱን የጠበቀ እውነት ለማሰብ ብሎም ለመጻፍ ይረዳወት ዘንድ ከኛ ወገን አይደሉም ብለው ሌላም መልክ ሰጥተው የጻፉባቸውን አባቶችንና ወንድሞችን በማነጋገር እውነትን ይረዱ ከዛም ሚዛናዊ የሆነ ጽሁፍ መጻፍ የሚችሉ ይመስለኛል አለያ ግን እርስዎ እየሄዱበት ባለው የጥላቻና የመለያየት መንፈስ ውስጥ ይዘውን እንዳይጠፉ እሰጋለሁ፤ ቢችሉ ግን ተንኲልን ውስጥ ለውስጥ ለየዋሀን መስበክ "በእኔ ይብቃ" ብለው ይሄንን መድረክ ለሌሎች ማለትም መላምትን ሳይሆን እውነትን ከስሩ አጥርተው፤አንድነትንም በማሳደም ሳይሆን በፍቅር፤ መልካቸውንና ስማቸውንም እንደርስዎ ቀይረው ሳይሆን ትክክለኛ እና ሰባኪ የሆነ እነሱነታቸውን ገልጠው እያሳዪ መልካሙንና ትክክለኛውን ሊያሳዪን ለሚችሉ ወንድሞች ቢትውላቸው መልካም አይመስልወትም???? "ወለተ አቤል " እስኪ ይጸልዪበ "መልከ ጥፉን ;;;;;" እንዲሉ ስምዎት ለክፉ ስራዎት መደበቂያ እንዳይሆን ስጋት አለኝ ። እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቅዎት? ይሄንን የውይይት መድረክ ለመክፈት ካሰቡ ስለምንድን ነው ያንን ጽሁፍ ለሰ/ተማሪዎች በድብቅ መላክ ያስፈለገዎት??? ነው ወይስ የውይይቱን መድረክ የከፈቱት ያሰቡትንም ሆነ የፈለጉትን አይነት መልስ እና እንቅስቃሴ ስላላገኙ ማሳደም እንደማይችሉ ያኛው መንገድ ስለአላዋጣወት መቀየስወት ነው??????? በየትም ይምጡ በየትም ለኛ ያው "ቀልቀሎ ስልቻ ስልቻ ቀልቀሎ ነው"። ። ።

Anonymous said...

አይ ወለተ አቤል ይሄንን መድረክ ለመክፈተ ካሰቡ ለምን ይሆን ያንን ጽሁፍ ለሰ/ተዎች የላኩት??? ለመሆኑ ማን ይሆን እምነተ ቢሱ ኢሜላችንን ከኛ ፈቃድና በሰ/ት/ቤቱ የሚመለከተው አካል ሳያውቅ በስርቆት የተባበረዎት??? እንዲያው ጠየኲዎት እንጅ እኛስ "ውስጡን ለቄስ" ብለናል ግን መልክዎትን ቀይረው በዚህ መልክ ሲመጡ ደግሞ ገርሞኝ "ምን ይሆን ፍለጋቸውና አላማቸው???" ብየ እራሴን ጠየኩት መቸስ ጊዜ የማይገልጠው የለምና እህ ጊዜ ይፍታልን ብየ ልለፍ ይሆን????

Anonymous said...

Abel,

Your effort deservest the greatest appreciation and thanks.

Please extend your perspective to cover our beloved church in a wider scale.

Please browse: www.eotcipc.org

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)